የልጅነት ፍቅር🧚‍♀🌹🥀❤️‍🔥


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified



Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ከወንድሜ ጀርባ 3

"ደና ናት ስሚማ ቢጥርዬ ከአዶዬጋ ልንሄድ ነው እና ሳምንቱን አናወራም እሺ"
"ናበይ"(ወዴት)
"ወደ ደብረሊባኖስ"
"ንምንታይ"(ለምን)
"አንቺ ደሞ ልጠመቅ ነዋ ፀበል"
"እህህ እንቢየው እናወራለን እንዴ ትናፍቀኛለህ እኮ"
"ፍትውተይ(የኔ ውድ) ሕንቅቅተይ(የኔ ቀበጥ) አዶዬን እያወቅሻት"
"ናይ ብሀቂ ዲኻ"(ከምርህ ነው እንዴ)
"ዱጋ"(እውነት) ውስጤ ተረብሿል ግን ግድ ነው መሰለኝ አክስቴ ደሞ ቢጥርን ከአጠገቧ ማራቅ አትፈልግም እኔ ምን ላርግ ብቻ ፈጣሪ ብቻ እንዳትነጫነጭ እርዳኝ
"እሺ በቃ እማዬ እንዳትቆጣ ወደቤት ልሂድ"
"ቻው ጥኡም ተይ"(የኔ ጣፋጭ)
ዞራ ሳታየው ሄዳ መብሰልሰል ጀመረች እውነት ለመናገር ከሆነ ኣነ ደብሮኛል ያው አንዳንዴ ትግርኛ እደባልቃለሁ አውቃለሁ መሄዱኮ ፅቡቕ እዩ ማለቴ ጥሩ ነው ግን ደሞ በጣም ስለለመድኩት መሰለኝ ቶሎ ቶሎ ነው የሚናፍቀኝ በነገሬ ላይ ለምን ትግርኛ እንደምደባልቅ ልንገራችሁ ያው እኔ ሸገር ከመምጣቴ በፊት ወለጋ ነበረ የምኖረው የአፍ መፍቻዬ ኦሮምኛ ነበረ መቼስ ይሄ ጦርነት ያልከፈተው ደጅ ያላሰቃየው ሰው ያላፈሰሰው ደም የለም እናማ በረብሻ ምክንያት ወደ መዲናችን አዲስ አበባ መጣን ዮናስም ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ መጣ እሱ ሙሉ ትግርኛ እኔ ደሞ ሙሉ ኦሮምኛ ብቻ ነበረ የምናውቀው መግባባት አቃተን ከዛ እኔም እሱን ለማናገር በስርአቱ ትግርኛ አጠናሁ እሱም ለኔ ሲል ኦሮምኛ አጠና ከዛ ከአፍ መፍቻችን በላይ ለመድነው እንገርማለን አደለ ያው በመሀል እዚ አማርኛ ስለሚበዛ በውዥንብር አማርኛ ለመድን ባይገርማችሁ አሁን ከልክ በላይ ከማጥናቴ የተነሳ ትግርኛ ቶሎ አፌ ላይ ይመጣል እሱም ሳት እያለው ኦሮምኛ የሚያወራው ለዛ ነው አንዳንድ ጊዜ መዋደድ ሁሉንም ያስችላል በቃ እኔ ወንድሜን ሳየው የሞተው የናቴ ልጅ ትዝ ይለኛል በጣም ያማል ስቆ ያልጠገበው ጥርሱ አፈር ሲለብስ ቦርቀው ያልጠገቡት እግሮቹ ሲታሰሩ ለማሰብ ይጨንቃል አይደለ እኛ ግን ኖረነዋል እናቴ የቀረዋት እኔን ለማዳን ሽሽት መረጠች ይቅርታ ብሶት አበዛሁ መሰለኝ እና ዮኒን ሳገኝ እንባዬ ስለታበሰ ነው የምሳሳለት ሳይታወቃት ቤት ደረሰች ጉንጮቿን ያራሰውን እንባ እናትየው ስትመለከት ከተኛችበት ተነሳች ብፅአት ባላለች ወጌሻና ጋጋሪ ናት ልጇን ጥሩ አሰልጥናታለች
"የኔ ልጅ ማል ታቴ ማለቴ ምን ሆነሽ ነው"
"እማ ወንድሜ"
"ልጄ ምን ላርግሽ ምን ልሁን እኔስ ልጄ አይናፍቀኝም መኖር ስላለብኝ እንዴ" እሷም በማንባት አገዘቻት
"ግን ለምን"
"በቃ አታልቅሺ ልጄ በቃ" ተቃቅፈው ቆዩ
ቀን ቀንን ሲተካ የማርያም እየተሻላት መጣ ደስታዋን ለመግለፅ ወደነ ቢጥር ብትሄድም ብፅአትን እንጂ ቢጥርን ማግኘት አልቻለም የትምህርት መውጫ እስከሚደርስ የማርያም ከብፅአትጋ ማውጋት ጀመረች ቢጥር ስትገባ ፍልቅልቅ ብላ ነበረ
"ሀዳኮ ላሊ"(እናቴ እይ)
ብፅአት "ምን ልይ ልጄ"
ቢጥር "የፈተና ውጤቴን ጎበዝ ነኛ የማ እንዴት ነሽ"
ብፅአት "ጎበዝ የኔ ልጅ እደጊልኝ"
የማርያም "ደና ነኝ በእውነት ላመሰግንሽ ነበረ እግሬ እየተሻለኝ ነው"
ቢጥር "ስራዬ ነውኮ አደዋይ ይቅርታ የአፍ ወለምታ ነው እናትዬ ለማለት ነው"
የማርያም "ምነኛ ነው"
ብፅአት "እኔ ልሂድ እናንተ አውሩ"
ቢጥር "ትግርኛ ነው"
የማርያም "ውይ መጀመሪያ ያወራሽው ስትገቢ ኦሮምኛ ነዋ"
ቢጥር "አዎ መአረይ"
የማርያም "አስለምጂኝ"
ቢጥር "እኔ ወንድሜን ሳየው ነው በደንብ ትዝ የሚለኝ እንጂ እሱ ከሌለ አማርኛ ነው ማወራው ፅፌ እሰጥሻለሁ"
የማርያም "ወንድምሽ የት አለ"
"እሱ ከአዶዬጋ ነው ሚኖረው ዛሬ ከደብረ ሊባኖስ ስለተመለሰ ስለተገናኘን ነው"
"አይ ጥሩ ነው ግን ስምሽን አልነገርሽኝም"
"ሀሴት እባላለሁ"
"ምን..." ፊቷ በአንድ ጊዜ ቀላ "ሀሴት ነው ያልሽው..."


እናቴ የነገረቺኝ አንድ የስርቆት ታሪክ ልንገራችሁ ያው ነገሩ ያለው አባባጋ ነው ማለቴ ሀያቴ ላይ የተፈፀመ ታሪክ ነው ልላችሁ ነው

አንዳንዴ ስራችን በምን እንደሚከፍለን አናውቅም ብቻ ምራቱ ናት ስለምትሰስት የራሷ እንዳያልቅ ከእታታ(ሴት ሀያቴ ናት) የመውሰድ ልማድ አላት ደሞ እያየቻት ወይም አስፈቅዳ አይደለም ተደብቃ ነው አባባ ይሄን አይቶ አንዴ መክሯት ነበረ የምትሰማ አይነት አይደለችም ከፈገግታ ያለፈ ክፉ አይናገርም "እንግዲህ ስመክርሽ ካልሰማሽ ጊዜ ይፈታዋል" ብቻ ነበረ ያላት በአንድ ወቅት መሬታቸውን ከተልባ ውጪ ሌላ ምርት እያበላሸ ሲያስቸግር ሙሉ ተልባ ዘርተውት ብዙ ስለወጣው ወደመሬት ቆፍረው ያስቀምጡታል ገጠርም አይደለ እቃ ብዙ አይታወቅም ምራት ሆዬ አገኘሁ ብላ ተልባውን ለመውሰድ ስትገባ አጅሬ ተልባ ሸርተት ማለት እሷም ዞር ለማለት መንቀሳቀስ እስከተቆፈረበት መጨረሻ አንሸራትቶ አስገባት ሚስቱ የጠፋችበት አጎቴ ተስፋ መቁረጥ ከመጀመሩ የአካባቢው ጠረን ሲቀየር አይጥ ሞታ ይሆናል በሚል ተልባው ወደተቀመጠበት ይሄዳሉ አንሸራታች ስለሆነ እንዳይውጣቸው ወደ ጉድጓዱ ሳይጠጉ ዳር ቆመው ለመገላለጥ ሲሞክሩ ምራትየው እዛው ሞታለች እንግዲህ የክፋት መጨረሻው ይሄ ነው ስርቆትም ሆነ ሌላ ወንጀል ከህግ በላይ በሆነ ጊዜ ሲዳኝ ፍርዱ የከፋ ነው ለማለት ያህል ነው መልካም ውሎ

@loves2512


Forward from: ዝምተኛው የግጥም ቤተ-መጽሐፍ
ልረሳሽ ነው መሰል

ባፈቀርሁሽ መጠን
ልረሳሽ ነው መሰል ልቤ ጠረጠረ
እኔም መሳቅ ጀመርሁ
አለምም ካንች ውጭ ይታየኝ ጀመረ

ልረሳሽ ነው መሰል
ይኧው ቃልሽን
አትጠጣ ያልሽኝን
ጠላ ከአረቄ ጋር ቀላቅየ ጠጣሁ
እርሷ የት ነች ሲሉኝ
አለች ማለት ትቼ
ነበረች የሚል ቃልካፌ ላይ አወጣሁ

ልረሳሽ ነው መሰል
ካንች መለየቱን ችየ ተቀበልሁት
ተሰባብሮም ቢሆን
ስትሄጅ ያጣሁትን ልቤን አገኘሁት

ልረሳሽ ነው መሰል
ያኔ የማለ ልብ ሊረሳሽ አስቧል
ያረግሁት ቀለበት ከጣቴ ላይ ጠቧል

ልረሳሽ ነው መሰል ከልቤ ልትወጭ
ጥርሴ ስቆ ታየ ይኧው ካንች ውጭ


✍ ዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI


Forward from: ቅዳጅ ገፆች📜
.
.
.
"ሀሴት የምር እየሳቅሽ ነው?"

"አይ አብርሽ፤ ምን እንድል ጠብቅህ ነበር? 'አትተወኝ የኔ ፍቅር ይበቃናል' ወይስ 'ካላንተ መኖር አልችልም፤እሞታለሁ' እንድልህ?"

"ምንም ባይበዛ ይሄን አልጠበኩም።ልብሽ ሚሰበር መስሎኝ ነበር ለረጅም ጊዜ ይዤው የነበረው።አንቺ ግን..."

"ሰውነታችን በተለይም ነጩ የደም ህዋሳችን(WBC) አዲስ የpathogen invasion ሲያጋጥመው ይደነግጣል።በቶሎ ማገገም ይከብደዋል።ምንነቱን ለማያውቀው በሽታም በለው ምን ለመከላከል ጊዜ ይወስድበታል።ተጎድቶም ቢሆን ግን ያገግማል።ከጊዜያት በኋላ ግን ያን pathogen በድጋሚ መጥቶ detect ሲያረገው እንደ መጀመሪያው አይሆንም። Already ያንን ነገር experience ስላረገው አዲስ አይሆንበትም።so ራሱን ለመከላከል ዝግጁ አድርጎ ይጠብቃል። ደማችን ውስጥ ስላሉት antibodies ማሰብም ትችላለህ።እና ምን ልልህ ነው ከብርሀኑ ጎን ጨለማ መኖሩን ረስቼው አላቅም።ከፍቅር አንድ ቀን አለመፈቀር ይኖራል።ከዚ በፊት ብዙ ያፈቀርኳቸውን ነገሮች አጥቻለሁ።ከማንም በላይ ታውቃለህ ያን።ከመፈቀር አጠገብ መ:ሰልቸት፤ስሜት ማጣት አለ።እኔም ልክ እንደ white blood cell ራሴን ብዙ ጊዜ ለተጎዳሁበት ነገር ዝግጁ አድርጌ ነበር።ስሜትህን ካንተ በፊት ነው የተረዳሁት።እንድትሰማው እድል ሰጥቼህ ነው።"

"ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም።ግን አንቺ እንድትጎጂ አልፈልግም ነበር ማንም እንዲጎዳሽም አልፈልግም።"

"አብርሽ ቀለል አርገው።አትጨናነቅ።እኔ አልጎዳም በማፍቀሬ አልፀፀትም።በአንተ ውስጥ የሌለን ስሜት ልጭንብህም አልሻም።ፍቅር ከአንድ ወገን አይሆንም።ካልሆነ ልክ እንደ አጋም እና ቅንጭብ አንዱ ወጊ አንዱ ደሚ የሆነ ግኑኝነት ይፈጠራል።ስለዚህ ልክ ነህ።መቋጫ እናበጅለት።"

"አ...አዎ።"

"ብቻ አደራ እንደ ክፉ ex እንዳንተያይ።አንዳንዶች ስንት ነገር አብረው ያሳለፉትን ሰው እንደ አባታቸው ገዳይ አድርገው ሲተላላፉ ይቀፈኛል።ብቻ አንተም እንዲያ እንዳታረግ ካልሆነ ለእቴቴ ነግሬ ነው ማስመዘልግህ።ሃሃሃ..."

"እብድ ነሽ።እንዴት እንደዛ አረጋለሁ ምንም ቢሆን ትዝታ አለን የምንጋራው ደሞ እወድሻ..."
"አብርሽ እንደ ማይተዋወቅ ሰው እንዳንሆን ነው ያልኩት።ከዚህ በኋላ መመለስ የለም።መንገዳችን ተገንጥሏል።ትዝታችንም በየጓዳው ይቀመጣል።'የበፊት' ብለን የጣልነው ታሪክ አለ።ከንፁህ ጓደኝነታችን እና አሁን ከቆምንበት አፅናፍ መሀል ላይ የነበረውን ቆርጠን እንጥለዋለን።እንዲያ ማትችል ከመሰለህ ሁሉም ይቁም እና ሙሉ ታሪኩ ይሰረዝ።አቋምህን ግልፅ አርግልኝ።"

"እኔንጃ...ሀሱ መቻሌን አላውቅም።"

"ጥሩ። መልካም ቀን አብርሀም።መልካም ህይወት።"

ቆማ ጨብጣው ሄደች።ተመልሳ መጥታ ከእቅፉ እንደምትገባ ነበር ያሰበው።አልዞረችም።በተቃና እርምጃዋ እንደ ሁሌውም ቀና ብላ በፍጥነት ራመድ እያለች ከአይኑ ተሰወረች።እጎዳት ይሆን ብሎ የከፈተው መንገድ ተመዞ ተመዞ እሷን ሸኝቶ መለሰው።ጠብ! አንዲት እንባ አመለጠችው።

✍️🏼ቃል

https://t.me/Piece_of_pages
https://t.me/Piece_of_pages


አልተመቻችሁም እንዴ like የለምኮ


አንተን ማየት የተውኩበት
በእንባ ውሎ ያደርኩበት
እመነኝ አይኔን አሞኛል
ሳቅህን ማየት እርቦኛል
ድምፅህን መስማት ያቆመው
ጆሮዬን ቆየ ካመመው
ናፍቆትህ ያሳሰረብኝ
ስማኛ ችግር አለብኝ
መውደድህ የዘለቀበት
ይህ ልቤ ህመም አለበት
ከገባህ ና ና ሻርበት

✍hani

@loves2512


Forward from: @chelpbot
"አንድ መጥፎ ምዕራፍ
ሙሉ ታሪክህን አይገልጽም!

One bad chapter
doesn't define your whole story! 🤍✨
●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●● 
✨join us:- for great thought ✨
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇


በደንብ ሪአክት ካደረጋችሁ ማታ ክፍል 3 እፅፋለሁ


ከወንድሜ ጀርባ 2


አልገባበት ጉድ የለኝ የልጅቷ እጆች መጥበቅ ሲጀምሩ ከሀሳቧ ባነነች በጣም አጥብቃታለች ወጌሻዋ ህመሟን ለማረሳሳት ይመስል ወሬ ጀመረች
"ለምን ከቤተሰብጋ አልመጣሽም ምን ስትሆኚ ነው የወደቅሽው" ምን እንዳናደዳት አይታወቅም የማርያም በንግግራቸው ቅጥል እያለች ድምጿን ከፍ አርጋ
"ሁሉም ሞተዋል ከታናሽ ወንድሜጋ ነው የምኖረው ቤት ሳፀዳ ነው የወደቀውት ኧረ ወየው ገደለቺኝ" ከዚ በፊት ጠንካራ መሆኗን እያሰበች ነበረ ግን ዛሬ ያ ሁሉ ገደል ገባ በአንድ ሰከንድ ነፍሷ የምታመልጣት መሰላት የሴትየዋን ንግግር ሳትሰማ "ኧረ በማርያም ቀስ በይ ኡኡኡ የፈጣሪ ያለህ ወይኔ እናቴ ድረሺ" ሴትየዋ ጥያቄያቸውን ደገሙት "ምን እየሰራሽ ነው የምትኖሪው" ባትሰማ ባታወራ ምኞቷ ነበረ ሴትየዋን እገልሻለሁ አይነት እይታ እያየች "ልብስ አጠባና ፅዳት" ደረታቸውን እየደለቁ ለቤተሰቦቿ መልካም እረፍትን ሲመኙ እሷ ራሷ አብራቸው አለመሞቷን መውቀስ ጀመረች የምታሻት ልጅ ቀና ብላ "ከዚ በፊት ተሰብረሽ ነበር አይደለ"
በግራ መጋባት አይን እያየቻት "ወጌሻ ነሽ ጠንቋይ? እስኪ ቀስ በይ በፈጠረሽ"
"አይዞሽ ጨርሻለሁ ከሁለት ሳምንት ቡሀላ ደና ትሆኛለሽ" እረፍት ተሰማት
"ተመስገን ገድለሽኝ ነበረኮ ስንት ነው ምከፍለው"
ወጌሻዋ "አይ ልጄ ይቅር ስምሽ ማነው"
የማ "የማርያም ነው ኧረ ለምን ስንት ልክፈል"
ወጌሻዋ "በቃ ቢጥር እየመጣች ታይሻለች አሁንም ቁርስ ቀመስ አርጊና በሳይክል ታደርስሻለች"
የማ "አይ ማዘር አያስቡ" እውነት ለመናገር ከሆነ ትህትናቸው ይገዛል እኔም ባልድን ራሱ ሀሳባቸው ይበቃል እንዳሳዘንኳቸው አይናቸው ያዘለው እንባ ይናገራል እድሌ ሆኖ ሰው ያዝንልኛል መቼስ በዚ ኑሮ ውድነት እኔ የሰራሁት ብቻ አያስተዳድረን ነገሩ ላያስችል አይመጥም እናማ ሰዎች ልጅነቴ እያሳሳቸው ይመስለኛል ለምበላው አላጣም እሳቸው ደሞ እናት ስለሆኑ መሰለኝ የበለጠ ስፍስፍ አሉ ተብሰልስላ ሳትጨርስ ቢጥር ጠርታ አነቃቻት መንገዱን እንድትጠቁማት ነበረ ቤታቸው ስትደርስ ቢጥር ራሷ አዝና ነበረ አይኖቿ እንባ እንዳዘሉ እሷ እናቷን ብታጣ ምን እንደምትሆን ማሰብ ጀመረች ሀሳቧ እንዳይታወቅ የለበጣ ፈገግ ብላ የተዝረከረከውን ቤት አስተካከለችላት
ቢጥር "ሊጥ ካለሽ እንጀራ ጋግሬልሽ ልሂድ"
የማ "እኔኮ ጋግሬ አላውቅም ሰው ነው የሚሰጠኝ በተረፈ እገዛለሁ እንጂ እንጀራ መጋገር አልችልም"
ቢጥር "እሺ እኔ ላስለምድሽና ለእማዬ አሳምናታለሁ እኔን አግዢኝ እ በብር ወንድምሽ የት ነው ሚማረው"
"የግል ከፍዬ ነው ማስተምረው"
"በጣም ጥሩ የወንድምሽን ትምሮ ቤትና የቤት ክራይ ልክፈልልሽ ከ9-2 ሰአት ድረስ አግዢኝ ካልሆነ ደሞ እኛ ቤት ኑሪ ከዛ አግዢኝ እባክሽ ከትምሮጋ በጣም ከብዶኛል ደሞ የምንበላውን ትበያለሽ ሌላ ስራ ራሱ አያስፈልግሽም ከስተመር ስለጨመረ አሁን በቀን 300 እንጀራ መጋገር አለብን 150 አንቺ 150 እኔ ምን ይመስልሻል"
"ደስ ይለኛል" የምሬን ነበረ ደስ ብሎኛል ከልቤ አንድ ቦታ ሰርቼ ከተገላገልኩ ምን ፈልጋለሁ
"እኔ ልሂድ ፈጣሪ ይማርሽ" አሁን ጥሩ ሆነልኝ ወንድሜን በዛው ስለማገኘው ፈጣሪን እያመሰገንኩ ወደሱ ሄድኩ እሱ ራሱ በደስታ ሞቷል ስለ ወንድሜ ትንሽ ልንገራችሁ ብዙ መልክ የሌለው ፉንጋ ቢጤ ቢሆንም አቋሙ ግን የትም የለም የቀረውን እየቆያችሁ ታያላችሁ ስሙን ረስቼ ዮናስ ይባላል
ዮናስ "ቢጥርዬ ከየት ተገኘሽ"
ቢጥር "ተጣልቼሀለሁ ለምን ጠፋህ"
"አለው አክስቴ እንዴት ናት"
"ትንሽ ብርድ እያሳላት ነው አዶዬ እንዴት ናት"
"ደና ናት ስሚማ ቢጥርዬ.....


ሪአክት አርጉ አደራ


ለመቆያ ያህል አንድ ግጥም ልላክላችሁ የኔ ግን አይደለም የእህቴ ነው ስሙ ሪአክት አርጉ በግጥሙ ዙሪያ ፈልጌው ነው እሺ አስተያየት ካላችሁ ደሞ ኮመንት ላይ ፃፉልኝ አደራ ስላስፈለገኝ ነው


አልተመቻችሁም እንዴ ሪአክት የለምኮ


ከወንድሜ ጀርባ 1


ፀሀዩዋ ወደ ምእራብ ካዘቀዘቀች ቆየት ብላለች የፈጠረችው ብርቱካንማ ቀለም ለአይን ይማርካል ዙፋኗን ለጨረቃ ላለመልቀቅ እየታገለች ቢሆንም መሬት ጀርባዋን ስትሰጣት አማራጭ አጥታ ተራዋን እየለቀቀች ነው የማሪያም መራመድ ያቃተው እግሯን እየጎተተች ወደ ቤቷ ታቀናለች ጠየም ያለች አይኗ የባቄላ አበባ የመሰለ የደስ ደስ ያላት ልጅ ናት ፈገግ ስትል የሚወጡት ስርጉዶች የበለጠ ቆንጆ አርገዋታል ከበሯ ስትደርስ መምጣቷን ጥበቃ ቆሞ የነበረው ናሆም እንደሷ የሚያሳሳ ፈገግታውን አሳይቷት ደግፏት ገባ እሱ የቀይ ዳማ ቢሆንም መልካቸው ግን በደንብ ይመሳሰላል ውበት የበዛበት ይመስላል ሲናገር እያዜመ ይመስላል አይንቀለቀልም ጎርነን ያለ አስደሳች ድምፅ አለው
"የማ ይሄ እግርሽ ግን እየባሰብሽ ነው ወይ ሌላ ቦታ ብትታሺውስ"
"እሺ ናሆሜ አስቤያለሁ ነገ እሄዳለሁ አንድ ጎበዝ ሴትዮ አሉ ብለውኛል እዛ እሄዳለሁ"
"ራት ላቅርብ እርቦኛል" መልስ ሳይጠብቅ አቀራርቦ ትንሽ ከበላ ቡሀላ ወሬውን ቀጠለ
"እህቴ ስለ አዲሷ ቺክ አልነገርኩሽም ለካ"
"የኛ ሮሚዮ እስኪ ንገረኝ"
"ቀለል ያለች ልጅ ናት አይኖቿ ከሁሉም ነገሯ በላይ ያምራሉ እንዲያውም እሷ ከመወለዷ በፊት ፀሀይ ራሱ ብርሃን አልነበራትም ለፀሀዩዋ ብርሃን የሆናት ሳቋ ነው መሬትማ ሀሴት ረገጠቺኝ ብላ አንዳንዴ ከወገቧ ሸብረክ ብላ እጅ ትነሳለች"
"አቤቱ ጌታ ሆይ የሚያወራውን አያውቅምና በስራህ ገብቶ ስለዘላበደ ይቅር በለው አንተ ድንቢጥ ምን ትዘባርቃለህ"
"ከምሬ ነውኮ እህቴ አታሹፊ"
"ደልቶሀል አንተ እኔ ልተኛ ነው"
"እንዴ ግን አልጨረስኩም እኮ"
"ምን እንደሚገርመኝ ታውቃለህ ሴት በቀየርክ ቁጥር እነሱን የምታሞግስበት ቃል ከየት እንደምታመጣ ነው ዝም ብለህ ድርሰት ጀምርና እኔንም ከሰው ቤት አውጣኝ"
"እህቴ ደሞ ደረስኩልሻ አሁን ትንሽ ጊዜ ነው የቀረኝኮ"
"ስቀልድ ነው ደና እደር ይልቅ ነገ ትምህርት ስላለ ጠዋት አንተን የመጎተት አቅም የለኝም በጊዜ ተኛ"
ጨረቃ እንደ ፀሀይ አደለችም ዛሬ ከስልጣን ስስቷ የተነሳ በጠዋቱ ራሱ ወደ ቤቷ አልገባችም ናሆም ጨረቃዋ ካልገባች አልነሳም የሚመስል ድብን ያለ እንቅልፍ ላይ ነው የማሪያም የአላርሙን ድምፅ በሀይል ከፍታ ጆሮው ስር አስቀምጣው ወጣች አላርሙ ሲያንባርቅ ናሆም ባነነ በእንቅልፍ ልቡ ለባብሶ ሲወጣ ፀሀይ ደና አደርክ ስትለው እንቅልፉ ከሱ ሸሸ እንደለመደው ተሽቀርቅሮ ወጣ

በሌላ ትእይንት

የማሪያም አስሬ እያረፈች የተባለችው ወጌሻ ቤት ደረሰች ስትገባ ራሷን ነው የጠላችው ሴትየዋ ሳል እየተናነቃቸው ነው አንዲት ልጅ ጥላሸት እንደተቀባባች ከሴትየዋጋ ታወራለች የማሪያም እስከምትገባ ሳትጠብቅ ወደ ጓዳ ሄደች የማሪያም ስትገባ ቤቱ እንደጠበቀችው አይደለም አነስ ቢልም እቃው በስርአቱ ተቀምጦ ውበት ሰጥቶታል ሶፋው ላይ ጋደም ያሉት ሴትዮ ጠየም ያሉ ቀጫጫ ባልቴት ናቸው
ወጌሻ"ምን ነበረ ልጄ ኡሁ ኡሁ"
የማሪያም "እግሬ ተሰብሮ እማዬ ታሽቼም አልዳነም"
ወጌሻዋ ድምፃቸውን ከፍ አርገው "ቢጥር"
"ወዬ እማዬ" ከጓዳ የተሰነዘረ መልስ ነው
"ነይ ልጄ የሚታሽ ሰው አለ እኔ አቅም የለኝም ነይ እስኪ አንቺ እሻት"
ንግግሯ አናዷት በቅጡ ሳትለብስ ፎጣ ጠቅልላ ወጣች "እማ ትምህርት ይረፍዳልኮ"
"ልጄ እኔ ብመርቅሽ አይበልጥም ለብሰሽ ነይና ዳበስ ዳበስ አርጊያት" መልስ ሳትሰጥ ወደ ጓዳ ገብታ ሺቲዋን ለብሳ ተመለሰች ብዙ ሳታሳምም ነካ ነካ አርጋ ወደ ወጌሻዋ ዞረች አሳዛኝ አይኖች ስላሏት ተቁለጨለጨች ወጌሻዋ ስለገባት ከሶፋዋ ተነስታ ፋሻ ይዛ መጣች
"ከዚ ይብሳል" ፋሻውን ወደ ልጅቷ እየሰነዘረች ጠየቅ
"ይሞከርና ተመልሳ ትምጣ"
ወጌሻዋ "ልጄ ማን ነበረ ያሸሽ ልክ አላሹሽም ትንሽ አዛብተውሻል"
ግራ እየገባት ነበረ ድምፅ ሳታወጣ ተብሰለሰለች ሆሆሆ የነዚ ደሞ ከፋ ልጅቷ ለነካችኝ እናትየው ምን አውቀው ነው ሚዘረዝሩት ወይ ፈጣሪ አልገባበት ጉድ የለኝ....


እንግዲህ እውነተኛ ታሪክ ነው የሰፈራችን አዛውንት ናቸው ያጫወቱኝ

ድካም ስለተጫናቸው ተደግፈውኝ ወደ በር ወጥተው ቆሙና አንድ ሱቅ አይተው ለስለስ ያለ ፈገግታ ፈገግ አሉ ባይገባኝም አብሬያቸው ፈገግ አልኩ እውነት ለመናገር እርጅናቸው ብዙ አያስታውቅም ጠየም ቢሉም ከዛ አልፎ የሚታይ ውበት አላቸው እግራቸው ላይ ባለው ቁስል ምክንያት እንጂ እንደ ጥንካሬያቸው እንኳን በ86 በ96 አመታቸው ራሱ የሚያረጁ አይመስሉም የሚያናግራቸው ሰው ስለሚናፍቁ አልያም ስሜቱ ስላልወጣላቸው አላቅም ብቻ ለመጣ ለሄደው ነው ታሪካቸውን የሚናገሩት "የዛሬን አያርገውና" የሚል የቁጭት ቃላቸውን አስከትለው ትረካቸውን ጀመሩ
"ያውልሽ ልጄ የዛሬን አያርገውና እንዴት ያለው ጥጋበኛ ነበርኩ መሰለሽ አይ ጊዜ ደጉ አይ ጊዜ ክፉው ስንቱን አሳየኝ ብቻልሽ ጥጋቤ የበረደበትንና የመላጣነቴን ታሪክ ልንገርሽ" አነጋገራቸው ፈገግ ሲያስብለኝ አብረውኝ ፈግገው ንግግራቸውን ቀጠሉ
"እንደው ሀረር ውስጥ የማላወጣት ሴት አልነበረችም ደሞ የባጃጅ ሹፌር ነበርኩ አንድ ጓደኛዬ እንደኔ ነው እሱም አንዷ ቺክ እንቢ ትለዋለች ብትደረግ ብትሰራ ወንድ አንድ ቀን ነክቷት አያቅም አልቻለም ስለሷ እያወራን ይዣት ከወጣው 20 ብር እንደሚሰጡኝ ተስማማን ብሩን ተቀብዬ የምትሰራበትን ስጠይቅ ቀበሌ 11 ነው አሉኝ ቀጥ ብዬ ወደሷ ቀለል ያለች ናት አቤት ብታይ ውበቷ አጃኢብ ነው ቀስ ብዬ ተግባባዋት እንደ ፉከራዬ ይዣት ወጣሁ ችግሩ ግን ከወዲያ ነበረ አፍቅሬያት እርፍ አልኳ ከዛ አገባዋት" ትንፋሽ ሲሰበስቡ እኔ ቀደም ብዬ "ደስ ይላል የምር አባባ ግን እግሮትን ምን ሆነው ነው"
"ወግጅ እስኪ አስጨርሽኝ ዳሩ ግን ማተራመሴን ስታውቅ ቅናት ጀመራት ኧረ በሞትኩት እኔማ ራሴን ፈራሁ አንድ ነገር አይቀራት ውሎዬን ስትተርክ በቃ ለምን ሴት ከጎንህ ተቀመጠች ስትል እሱን ትቼ ውትድርና ለመግባት እያሰብኩ ባለሁለት ላማክራት ስገባ እሷ ሆዬ እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ ጠበቀችኝ አይ ጉድ ለማረጋጋት ላቅፋት ስጠጋ እንደው የጣደችውን አንስታ አናቴ ላይ ስታራግፈው ፀጥ ያልኩ መሰለኝ እኔም ብን ብዬ ወታደር ሆንኩ አናቴም ተቃጠለ ፀጉር ደግሞ ላያበቅል እግሬንም እዛው ወታደር ሆኜ ነው የተመታሁት እንደው ስወዳትኮ ብታይ አሁንስ መች ፍቅሯ ወጣልኝ አላስቀርብ አለችኝ እንጂ አይ ቅናቷ ባትኖር እንዴት ያለች ዘመናይ ዝምንምን መሰለችሽ"
"ብርድ እየመጣ ነው እንግባ አባባ"
"በይ እሺ ልጄ ደግፊኝ..."


share ማድረግ አይረሳ
👉 @loves2512


በጣም ጥሩ አጠር ያለ ታሪክ ይሻላል ወይስ ግጥም
ታሪክ 👍
ግጥም ❤️


እንቅልፍ እንቢ አለኝ ምን ይሻላል ላድርቃችሁ ያልተኛ አለ እስኪ ሪአክት እያረጋችሁ

የቅኔው መልስ
ህብረ ቃል ከመሶቡ አይጡ
ሰም አይቸገሩ
ወርቅ አይጥ መሶብ ውስጥ አለ


🙎ምን ልታረጊ ነው ብትሸሺ ከጎኔ
ማንም አይፈልግሽ ልንገርሽ ያለኔ

👰‍♀ታውቀኛለህ መቼስ ውሸት ምን ሊሰራ
ወንድ የማሰልፈው በተራ በተራ
ተው ከኔ ለመድረስ ብዙ አትንጠራራ


🙎አታስቂኝ እማ ማነው ያለው እንዲ
አንተዋወቅም አንች መጥፎ ከሀዲ
ሞክሪ እድልሽን በይ ከእንግዲህ ወዲ


👰‍♀እንዲያውም ልንገርህ እኔ አልፈልግህም
ሰው ካገር ቢጠፋ ከሰው አልቆጥርህም
ሳቅ ላያጎልብህ ጥቂት ከማጀቱ
ወንድነት ያስንቃል ሲበዛ ኩራቱ


🙎ሄይ ትሰሚኛለሽ
ተለቅልቀሽ ብትውይ በኩልሽ ላትወዢ
ሞኛሞኝ ህልምሽን ብትውይ ስትቃዢ
ምታገኚ መስሎሽ ልቤን ብትጓጊ
ዞሬም አላይሽም ሞኝሽን ፈልጊ


👰‍♀ አመድ ቡናኝህን ቅባት ላያወዛ
ብትለፈልፍ እንኳን ምላስ ብታበዛ
ያ ስንጥር አቋምህ ምግብ ባያቃናው
ሆረር መሳይ አይንህ የበዛ ምርቃናው
ምን ልሁን ብዬ ነው ባንተ የምቀናው


🙎 ጢኒዝዛ መልክሽን ሜካፕ ላያቀላ
ኩሪንቻቻ ፀጉርሽ በእጆቼ ላይሞላ
ኩርንችት አቋምሽ ሂል የማያቃናው
ምን ልሁን ብዬ ነው ባንቺ የምቀናው


👰‍♀ ቅናት ቢሆን እንጂ የሚያንጨረጭርህ
ድሮስ አልነበረም ምላሳም ምግባርህ


🙎አው ብንጨረጨርስ ብቀና ለፍቅሬ
ለዚ ጅል ፍቅርሽ ነው የኖርኩት ዳክሬ


👰አሁን አማረብህ አው ገባኝ ስለዚ
ቅናት ነበር ለካ ያረገህ እንደዚ

🙎እወድሻለሁ
👰‍♀እወድሃለሁ


ከተመቻችሁ ለጓደኞቻችሁ share ማድረግ አይረሳ ሪአክት ደሞ ያበረታታኛል እሺ
👉 @loves2512




የዳንኩ መስሎኝ ከህመሜ
የሞላ መስሎኝ አለሜ
የራቀ መስሎኝ ትላንቴ
ስላንቺ ነፍሴን መስጠቴ
በነፍሰ አለም ተይዤ
ጎኔ ከሌለሽ ተክዤ
ከደመናጋ ሳወራ
በሌለሽበት ስጣራ
ከፀሐይ እንካ ሰላምታ
ምድር ልትውጠኝ ተከፍታ
ናፍቆትሽ ነፍሴን ሲይዛት
መኖርሽ ሳቄን ሲቀርፃት
አንቺን ቢመስለኝ ተፈጥሮ
ከዝናቡጋ ቀጠሮ
መስማት ከቻለ እሮሮ
ከሀይቅ ጋራ ጨዋታ
ምናልባት ህልሜ ቢፈታ
ከዛፍ ብጫወት ኩኩሉ
ልቤ ይሄ ነው እድሉ
ከግኡዝ ወሬ
በእንባ ሰክሬ
እብደት ካባዬ
ሀዘን ጎጆዬ
ሆኖ የቀረው
ባንቺ ሰበብ ነው

✍hani

share ማድረግ አይረሳ
👉@loves2512


"በላነው ጠጣነው ከእንጀራ ከወጡ
እግዚአብሔር ይስጥልኝ ከመሶቡ አይጡ"
መልስ እየፃፋችሁ


የዛኛ ጥያቄ መልስ
ህብረ ቃል ዳኛ አይደለን
ሰም ከኛ ፍትህ አታገኝም
ወርቅ እኛም ታመናል አልዳንንም

@loves2512

20 last posts shown.

333

subscribers
Channel statistics