TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
የልጅነት ፍቅር🧚‍♀🌹🥀❤️‍🔥

14 Aug 2025, 11:28

Open in Telegram Share Report

ከወንድሜ ጀርባ 1


ፀሀዩዋ ወደ ምእራብ ካዘቀዘቀች ቆየት ብላለች የፈጠረችው ብርቱካንማ ቀለም ለአይን ይማርካል ዙፋኗን ለጨረቃ ላለመልቀቅ እየታገለች ቢሆንም መሬት ጀርባዋን ስትሰጣት አማራጭ አጥታ ተራዋን እየለቀቀች ነው የማሪያም መራመድ ያቃተው እግሯን እየጎተተች ወደ ቤቷ ታቀናለች ጠየም ያለች አይኗ የባቄላ አበባ የመሰለ የደስ ደስ ያላት ልጅ ናት ፈገግ ስትል የሚወጡት ስርጉዶች የበለጠ ቆንጆ አርገዋታል ከበሯ ስትደርስ መምጣቷን ጥበቃ ቆሞ የነበረው ናሆም እንደሷ የሚያሳሳ ፈገግታውን አሳይቷት ደግፏት ገባ እሱ የቀይ ዳማ ቢሆንም መልካቸው ግን በደንብ ይመሳሰላል ውበት የበዛበት ይመስላል ሲናገር እያዜመ ይመስላል አይንቀለቀልም ጎርነን ያለ አስደሳች ድምፅ አለው
"የማ ይሄ እግርሽ ግን እየባሰብሽ ነው ወይ ሌላ ቦታ ብትታሺውስ"
"እሺ ናሆሜ አስቤያለሁ ነገ እሄዳለሁ አንድ ጎበዝ ሴትዮ አሉ ብለውኛል እዛ እሄዳለሁ"
"ራት ላቅርብ እርቦኛል" መልስ ሳይጠብቅ አቀራርቦ ትንሽ ከበላ ቡሀላ ወሬውን ቀጠለ
"እህቴ ስለ አዲሷ ቺክ አልነገርኩሽም ለካ"
"የኛ ሮሚዮ እስኪ ንገረኝ"
"ቀለል ያለች ልጅ ናት አይኖቿ ከሁሉም ነገሯ በላይ ያምራሉ እንዲያውም እሷ ከመወለዷ በፊት ፀሀይ ራሱ ብርሃን አልነበራትም ለፀሀዩዋ ብርሃን የሆናት ሳቋ ነው መሬትማ ሀሴት ረገጠቺኝ ብላ አንዳንዴ ከወገቧ ሸብረክ ብላ እጅ ትነሳለች"
"አቤቱ ጌታ ሆይ የሚያወራውን አያውቅምና በስራህ ገብቶ ስለዘላበደ ይቅር በለው አንተ ድንቢጥ ምን ትዘባርቃለህ"
"ከምሬ ነውኮ እህቴ አታሹፊ"
"ደልቶሀል አንተ እኔ ልተኛ ነው"
"እንዴ ግን አልጨረስኩም እኮ"
"ምን እንደሚገርመኝ ታውቃለህ ሴት በቀየርክ ቁጥር እነሱን የምታሞግስበት ቃል ከየት እንደምታመጣ ነው ዝም ብለህ ድርሰት ጀምርና እኔንም ከሰው ቤት አውጣኝ"
"እህቴ ደሞ ደረስኩልሻ አሁን ትንሽ ጊዜ ነው የቀረኝኮ"
"ስቀልድ ነው ደና እደር ይልቅ ነገ ትምህርት ስላለ ጠዋት አንተን የመጎተት አቅም የለኝም በጊዜ ተኛ"
ጨረቃ እንደ ፀሀይ አደለችም ዛሬ ከስልጣን ስስቷ የተነሳ በጠዋቱ ራሱ ወደ ቤቷ አልገባችም ናሆም ጨረቃዋ ካልገባች አልነሳም የሚመስል ድብን ያለ እንቅልፍ ላይ ነው የማሪያም የአላርሙን ድምፅ በሀይል ከፍታ ጆሮው ስር አስቀምጣው ወጣች አላርሙ ሲያንባርቅ ናሆም ባነነ በእንቅልፍ ልቡ ለባብሶ ሲወጣ ፀሀይ ደና አደርክ ስትለው እንቅልፉ ከሱ ሸሸ እንደለመደው ተሽቀርቅሮ ወጣ

በሌላ ትእይንት

የማሪያም አስሬ እያረፈች የተባለችው ወጌሻ ቤት ደረሰች ስትገባ ራሷን ነው የጠላችው ሴትየዋ ሳል እየተናነቃቸው ነው አንዲት ልጅ ጥላሸት እንደተቀባባች ከሴትየዋጋ ታወራለች የማሪያም እስከምትገባ ሳትጠብቅ ወደ ጓዳ ሄደች የማሪያም ስትገባ ቤቱ እንደጠበቀችው አይደለም አነስ ቢልም እቃው በስርአቱ ተቀምጦ ውበት ሰጥቶታል ሶፋው ላይ ጋደም ያሉት ሴትዮ ጠየም ያሉ ቀጫጫ ባልቴት ናቸው
ወጌሻ"ምን ነበረ ልጄ ኡሁ ኡሁ"
የማሪያም "እግሬ ተሰብሮ እማዬ ታሽቼም አልዳነም"
ወጌሻዋ ድምፃቸውን ከፍ አርገው "ቢጥር"
"ወዬ እማዬ" ከጓዳ የተሰነዘረ መልስ ነው
"ነይ ልጄ የሚታሽ ሰው አለ እኔ አቅም የለኝም ነይ እስኪ አንቺ እሻት"
ንግግሯ አናዷት በቅጡ ሳትለብስ ፎጣ ጠቅልላ ወጣች "እማ ትምህርት ይረፍዳልኮ"
"ልጄ እኔ ብመርቅሽ አይበልጥም ለብሰሽ ነይና ዳበስ ዳበስ አርጊያት" መልስ ሳትሰጥ ወደ ጓዳ ገብታ ሺቲዋን ለብሳ ተመለሰች ብዙ ሳታሳምም ነካ ነካ አርጋ ወደ ወጌሻዋ ዞረች አሳዛኝ አይኖች ስላሏት ተቁለጨለጨች ወጌሻዋ ስለገባት ከሶፋዋ ተነስታ ፋሻ ይዛ መጣች
"ከዚ ይብሳል" ፋሻውን ወደ ልጅቷ እየሰነዘረች ጠየቅ
"ይሞከርና ተመልሳ ትምጣ"
ወጌሻዋ "ልጄ ማን ነበረ ያሸሽ ልክ አላሹሽም ትንሽ አዛብተውሻል"
ግራ እየገባት ነበረ ድምፅ ሳታወጣ ተብሰለሰለች ሆሆሆ የነዚ ደሞ ከፋ ልጅቷ ለነካችኝ እናትየው ምን አውቀው ነው ሚዘረዝሩት ወይ ፈጣሪ አልገባበት ጉድ የለኝ....

145 0 3 16
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot