TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
የልጅነት ፍቅር🧚‍♀🌹🥀❤️‍🔥

15 Aug 2025, 16:32

Open in Telegram Share Report

ከወንድሜ ጀርባ 2


አልገባበት ጉድ የለኝ የልጅቷ እጆች መጥበቅ ሲጀምሩ ከሀሳቧ ባነነች በጣም አጥብቃታለች ወጌሻዋ ህመሟን ለማረሳሳት ይመስል ወሬ ጀመረች
"ለምን ከቤተሰብጋ አልመጣሽም ምን ስትሆኚ ነው የወደቅሽው" ምን እንዳናደዳት አይታወቅም የማርያም በንግግራቸው ቅጥል እያለች ድምጿን ከፍ አርጋ
"ሁሉም ሞተዋል ከታናሽ ወንድሜጋ ነው የምኖረው ቤት ሳፀዳ ነው የወደቀውት ኧረ ወየው ገደለቺኝ" ከዚ በፊት ጠንካራ መሆኗን እያሰበች ነበረ ግን ዛሬ ያ ሁሉ ገደል ገባ በአንድ ሰከንድ ነፍሷ የምታመልጣት መሰላት የሴትየዋን ንግግር ሳትሰማ "ኧረ በማርያም ቀስ በይ ኡኡኡ የፈጣሪ ያለህ ወይኔ እናቴ ድረሺ" ሴትየዋ ጥያቄያቸውን ደገሙት "ምን እየሰራሽ ነው የምትኖሪው" ባትሰማ ባታወራ ምኞቷ ነበረ ሴትየዋን እገልሻለሁ አይነት እይታ እያየች "ልብስ አጠባና ፅዳት" ደረታቸውን እየደለቁ ለቤተሰቦቿ መልካም እረፍትን ሲመኙ እሷ ራሷ አብራቸው አለመሞቷን መውቀስ ጀመረች የምታሻት ልጅ ቀና ብላ "ከዚ በፊት ተሰብረሽ ነበር አይደለ"
በግራ መጋባት አይን እያየቻት "ወጌሻ ነሽ ጠንቋይ? እስኪ ቀስ በይ በፈጠረሽ"
"አይዞሽ ጨርሻለሁ ከሁለት ሳምንት ቡሀላ ደና ትሆኛለሽ" እረፍት ተሰማት
"ተመስገን ገድለሽኝ ነበረኮ ስንት ነው ምከፍለው"
ወጌሻዋ "አይ ልጄ ይቅር ስምሽ ማነው"
የማ "የማርያም ነው ኧረ ለምን ስንት ልክፈል"
ወጌሻዋ "በቃ ቢጥር እየመጣች ታይሻለች አሁንም ቁርስ ቀመስ አርጊና በሳይክል ታደርስሻለች"
የማ "አይ ማዘር አያስቡ" እውነት ለመናገር ከሆነ ትህትናቸው ይገዛል እኔም ባልድን ራሱ ሀሳባቸው ይበቃል እንዳሳዘንኳቸው አይናቸው ያዘለው እንባ ይናገራል እድሌ ሆኖ ሰው ያዝንልኛል መቼስ በዚ ኑሮ ውድነት እኔ የሰራሁት ብቻ አያስተዳድረን ነገሩ ላያስችል አይመጥም እናማ ሰዎች ልጅነቴ እያሳሳቸው ይመስለኛል ለምበላው አላጣም እሳቸው ደሞ እናት ስለሆኑ መሰለኝ የበለጠ ስፍስፍ አሉ ተብሰልስላ ሳትጨርስ ቢጥር ጠርታ አነቃቻት መንገዱን እንድትጠቁማት ነበረ ቤታቸው ስትደርስ ቢጥር ራሷ አዝና ነበረ አይኖቿ እንባ እንዳዘሉ እሷ እናቷን ብታጣ ምን እንደምትሆን ማሰብ ጀመረች ሀሳቧ እንዳይታወቅ የለበጣ ፈገግ ብላ የተዝረከረከውን ቤት አስተካከለችላት
ቢጥር "ሊጥ ካለሽ እንጀራ ጋግሬልሽ ልሂድ"
የማ "እኔኮ ጋግሬ አላውቅም ሰው ነው የሚሰጠኝ በተረፈ እገዛለሁ እንጂ እንጀራ መጋገር አልችልም"
ቢጥር "እሺ እኔ ላስለምድሽና ለእማዬ አሳምናታለሁ እኔን አግዢኝ እ በብር ወንድምሽ የት ነው ሚማረው"
"የግል ከፍዬ ነው ማስተምረው"
"በጣም ጥሩ የወንድምሽን ትምሮ ቤትና የቤት ክራይ ልክፈልልሽ ከ9-2 ሰአት ድረስ አግዢኝ ካልሆነ ደሞ እኛ ቤት ኑሪ ከዛ አግዢኝ እባክሽ ከትምሮጋ በጣም ከብዶኛል ደሞ የምንበላውን ትበያለሽ ሌላ ስራ ራሱ አያስፈልግሽም ከስተመር ስለጨመረ አሁን በቀን 300 እንጀራ መጋገር አለብን 150 አንቺ 150 እኔ ምን ይመስልሻል"
"ደስ ይለኛል" የምሬን ነበረ ደስ ብሎኛል ከልቤ አንድ ቦታ ሰርቼ ከተገላገልኩ ምን ፈልጋለሁ
"እኔ ልሂድ ፈጣሪ ይማርሽ" አሁን ጥሩ ሆነልኝ ወንድሜን በዛው ስለማገኘው ፈጣሪን እያመሰገንኩ ወደሱ ሄድኩ እሱ ራሱ በደስታ ሞቷል ስለ ወንድሜ ትንሽ ልንገራችሁ ብዙ መልክ የሌለው ፉንጋ ቢጤ ቢሆንም አቋሙ ግን የትም የለም የቀረውን እየቆያችሁ ታያላችሁ ስሙን ረስቼ ዮናስ ይባላል
ዮናስ "ቢጥርዬ ከየት ተገኘሽ"
ቢጥር "ተጣልቼሀለሁ ለምን ጠፋህ"
"አለው አክስቴ እንዴት ናት"
"ትንሽ ብርድ እያሳላት ነው አዶዬ እንዴት ናት"
"ደና ናት ስሚማ ቢጥርዬ.....

84 0 1 8
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot