ከወንድሜ ጀርባ 3
"ደና ናት ስሚማ ቢጥርዬ ከአዶዬጋ ልንሄድ ነው እና ሳምንቱን አናወራም እሺ"
"ናበይ"(ወዴት)
"ወደ ደብረሊባኖስ"
"ንምንታይ"(ለምን)
"አንቺ ደሞ ልጠመቅ ነዋ ፀበል"
"እህህ እንቢየው እናወራለን እንዴ ትናፍቀኛለህ እኮ"
"ፍትውተይ(የኔ ውድ) ሕንቅቅተይ(የኔ ቀበጥ) አዶዬን እያወቅሻት"
"ናይ ብሀቂ ዲኻ"(ከምርህ ነው እንዴ)
"ዱጋ"(እውነት) ውስጤ ተረብሿል ግን ግድ ነው መሰለኝ አክስቴ ደሞ ቢጥርን ከአጠገቧ ማራቅ አትፈልግም እኔ ምን ላርግ ብቻ ፈጣሪ ብቻ እንዳትነጫነጭ እርዳኝ
"እሺ በቃ እማዬ እንዳትቆጣ ወደቤት ልሂድ"
"ቻው ጥኡም ተይ"(የኔ ጣፋጭ)
ዞራ ሳታየው ሄዳ መብሰልሰል ጀመረች እውነት ለመናገር ከሆነ ኣነ ደብሮኛል ያው አንዳንዴ ትግርኛ እደባልቃለሁ አውቃለሁ መሄዱኮ ፅቡቕ እዩ ማለቴ ጥሩ ነው ግን ደሞ በጣም ስለለመድኩት መሰለኝ ቶሎ ቶሎ ነው የሚናፍቀኝ በነገሬ ላይ ለምን ትግርኛ እንደምደባልቅ ልንገራችሁ ያው እኔ ሸገር ከመምጣቴ በፊት ወለጋ ነበረ የምኖረው የአፍ መፍቻዬ ኦሮምኛ ነበረ መቼስ ይሄ ጦርነት ያልከፈተው ደጅ ያላሰቃየው ሰው ያላፈሰሰው ደም የለም እናማ በረብሻ ምክንያት ወደ መዲናችን አዲስ አበባ መጣን ዮናስም ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ መጣ እሱ ሙሉ ትግርኛ እኔ ደሞ ሙሉ ኦሮምኛ ብቻ ነበረ የምናውቀው መግባባት አቃተን ከዛ እኔም እሱን ለማናገር በስርአቱ ትግርኛ አጠናሁ እሱም ለኔ ሲል ኦሮምኛ አጠና ከዛ ከአፍ መፍቻችን በላይ ለመድነው እንገርማለን አደለ ያው በመሀል እዚ አማርኛ ስለሚበዛ በውዥንብር አማርኛ ለመድን ባይገርማችሁ አሁን ከልክ በላይ ከማጥናቴ የተነሳ ትግርኛ ቶሎ አፌ ላይ ይመጣል እሱም ሳት እያለው ኦሮምኛ የሚያወራው ለዛ ነው አንዳንድ ጊዜ መዋደድ ሁሉንም ያስችላል በቃ እኔ ወንድሜን ሳየው የሞተው የናቴ ልጅ ትዝ ይለኛል በጣም ያማል ስቆ ያልጠገበው ጥርሱ አፈር ሲለብስ ቦርቀው ያልጠገቡት እግሮቹ ሲታሰሩ ለማሰብ ይጨንቃል አይደለ እኛ ግን ኖረነዋል እናቴ የቀረዋት እኔን ለማዳን ሽሽት መረጠች ይቅርታ ብሶት አበዛሁ መሰለኝ እና ዮኒን ሳገኝ እንባዬ ስለታበሰ ነው የምሳሳለት ሳይታወቃት ቤት ደረሰች ጉንጮቿን ያራሰውን እንባ እናትየው ስትመለከት ከተኛችበት ተነሳች ብፅአት ባላለች ወጌሻና ጋጋሪ ናት ልጇን ጥሩ አሰልጥናታለች
"የኔ ልጅ ማል ታቴ ማለቴ ምን ሆነሽ ነው"
"እማ ወንድሜ"
"ልጄ ምን ላርግሽ ምን ልሁን እኔስ ልጄ አይናፍቀኝም መኖር ስላለብኝ እንዴ" እሷም በማንባት አገዘቻት
"ግን ለምን"
"በቃ አታልቅሺ ልጄ በቃ" ተቃቅፈው ቆዩ
ቀን ቀንን ሲተካ የማርያም እየተሻላት መጣ ደስታዋን ለመግለፅ ወደነ ቢጥር ብትሄድም ብፅአትን እንጂ ቢጥርን ማግኘት አልቻለም የትምህርት መውጫ እስከሚደርስ የማርያም ከብፅአትጋ ማውጋት ጀመረች ቢጥር ስትገባ ፍልቅልቅ ብላ ነበረ
"ሀዳኮ ላሊ"(እናቴ እይ)
ብፅአት "ምን ልይ ልጄ"
ቢጥር "የፈተና ውጤቴን ጎበዝ ነኛ የማ እንዴት ነሽ"
ብፅአት "ጎበዝ የኔ ልጅ እደጊልኝ"
የማርያም "ደና ነኝ በእውነት ላመሰግንሽ ነበረ እግሬ እየተሻለኝ ነው"
ቢጥር "ስራዬ ነውኮ አደዋይ ይቅርታ የአፍ ወለምታ ነው እናትዬ ለማለት ነው"
የማርያም "ምነኛ ነው"
ብፅአት "እኔ ልሂድ እናንተ አውሩ"
ቢጥር "ትግርኛ ነው"
የማርያም "ውይ መጀመሪያ ያወራሽው ስትገቢ ኦሮምኛ ነዋ"
ቢጥር "አዎ መአረይ"
የማርያም "አስለምጂኝ"
ቢጥር "እኔ ወንድሜን ሳየው ነው በደንብ ትዝ የሚለኝ እንጂ እሱ ከሌለ አማርኛ ነው ማወራው ፅፌ እሰጥሻለሁ"
የማርያም "ወንድምሽ የት አለ"
"እሱ ከአዶዬጋ ነው ሚኖረው ዛሬ ከደብረ ሊባኖስ ስለተመለሰ ስለተገናኘን ነው"
"አይ ጥሩ ነው ግን ስምሽን አልነገርሽኝም"
"ሀሴት እባላለሁ"
"ምን..." ፊቷ በአንድ ጊዜ ቀላ "ሀሴት ነው ያልሽው..."