true_1
ሳይኮሎጂስቶች የፍቅር ሦስት መአዘን የሚሉት ንድፈ-ሀሳብ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
የእውነተኛ ፍቅር መገለጫዎች…
1. ጥልቅ ስሜት (passion)
ፍቅረኛዬን ሳያት/ሳስባት የምወድላት፣ የማደንቅላት እና የምደነግጥላት ነገር ሊኖር ይገባል፡፡ ያ ነገር ለኔ ልዩ ስሜት የሚሰጠኝ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ወይ ዞማ ፀጉሯን…ወይ ብርሃን ፈገግታዋን…ወይ የጠቆሩ ብሌኖቿን…ወይ ውብ ተክለሰውነቷን…ወይም ሌላ፡፡ ይህ ጥልቅ ስሜት ከባህሪ/ስብዕና ይልቅ ወደ አካላዊ ገፅታ የሚያደላ ይመስላል፡፡ ከታች ያሉት የመሀሙድ አህመድ የዘፈን ስንኞች ይህን ስሜት ጥሩ አድርገው ይገልፁታል…
ቁንጅና ምንድነው፣ ሰዎች ንገሩኝ
እኔ እሷን በማየት ተብረከረኩኝ፡፡
2. ቅርበት/ቁርኝት (intimacy)
ፍቅረኛዬ የቅርብ ጓደኛዬም መሆን አለባት፡፡ በመሀከላችን ምስጢር የሚባል ነገር ከቶ ሊኖር አይገባም፡፡ የቅርበቱ መጠን ልክ እንደ ቅርብ የወንድ/የሴት ጓደኛ አይነት እንዲሆን ይፈለጋል፡፡ ለቅርብ ጓደዬ የምደብቀው፣ ለመንገር የማፍረው ባጠቃላይ ስለራሴ የማልነገረው ነገር የለም፡፡ ለፍቅር ጓድዬም እንዲሁ መሆን አለበት፡፡ ይሄ በሌላ ቋንቋ መጠናናት የምንለው ነገር ነው፡፡
(አንድን ሰው በደንብ ለማወቅ ያ ሰው በተለያየ ጊዜ እና ሁኔታ የሚያሳየውን ባህሪ ማየት ያስፈልጋል፡፡ ምን ያስደስተዋል/ያስደንቀዋል፣ ምን ያሳዝነዋል፣ ምን ያናድደዋል፣ ምን ያስፈራዋል፣ ለተለያዩ ነገሮች ያለው ምልከታ ምን ይመስላል እና የመሳሰሉትን ነገር ለማወቅ ከሰውየው ጋር ዘለግ ያለ ጊዜ መዝለቅ ያስፈልጋል፡፡)
3. ቁርጠኝነት/ዘላቂ ስሜት (commitment)
ከፍቅረኛዬ ጋር ለረጅም ጊዜ (የሕይወት ዘመኔን) አብሬአት ልቆይ እፈልጋለሁ ወይ? ለዚህ ጥያቄ እውነቱ ሁልጊዜም እውስጣችን አለ፡፡ ለውስጣችን ጆሮ ከሰጠነው መልሱ ሩቅ አይደለም፡፡
ጥልቅ ስሜትና ቅርበት ሳይኖርበት አብሮ የመኖር ቁርጠኝነት ብቻ ያለውን ፍቅር ባዶ ፍቅር ብለው የስነ-ልቦና ሰዎች ይጠሩታ አንብባቹ ከተመቻቹ
Share @hayunamahi