ተረተሃልና እመን!
፨፨፨/////////፨፨፨
እርሱ ሳያውቅህ አንተ ካወከው፣ እርሱ በግል ስላንተ ሳያወራ አንተ ደጋግመህ ስለእርሱ ካወራህ፣ እርሱ ስለመኖርህ እንኳን መረጃ ሳይኖረው አንተ የቀን ውሎውን ሁሉ የምታውቅ ከሆነ፣ እርሱ ሰዎች አፍ ውስጥ ገብቶ እርሱን እየተጋፈጠ አንተ ግን በዙሪያህ ካሉ ሰዎች በቀር ስላንተ የሚያወራ ሰው ከሌለ አንድ እውነት መቀበል ይኖርብሃል። He is doing something especial. ምንም ሊሆን ይችላል ነገር ግን ካንተ ደረጃ ከፍ የሚያደርገው፣ በመሃከላችሁ ሰፊ ርቀትን የሚፈጥር፣ ልዩነታችሁን በብዙ የሚያሰፋ አንድ የተለየ ክንውን በመሃከላችሁ እንዳለ አስተውል። ያንተ አስተያየት ተፅዕኖ መፍጠር ካልቻለ፣ ንግግርህ ብዙዎች ጋር ካልደረሰ፣ የት እንዳለህ check የሚያደርግህ ሰው በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ሆነህ አንተ ተኝተህ እርሱ ሲሰራ የነበረን ሰው የመስደብ፣ የመተቸትና የመናቅ መብቱ አይደለም ሞራሊተው አይኖርህም።
አዎ! ጀግናዬ...! ተረተሃልና እመን፤ መሬት ላይ ባለ በሚታይ ውጤት ተሸንፈሃልና ተቀበለው፤ ምንም ሌላ ትንተናና ሃተታ ሳያስፈልግህ እውነታው ከፊትህ ተቀምጧልና አይተህ እንዳላየ አትሁን፤ ዋጋውንም አታሳንስ። የሰው ትልቁ ውበቱ ፍቅሩ ነው፤ እርስ በእርሱ መደጋገፉ፣ እርስ በእርስ መተሳሰቡና አብሮ ማደጉ ነው። ቅናት እጅግ ክፉ ነች። የአመፃም የበኩር ልጅ ነች። በወንድምህ ስኬት አይንህ ከቀላ፣ በእድገቱ ከተበሳጨህ፣ በመቀየሩ ከተናደድክ አንተ እራስህ እራስህን ካልረዳህ ማንም ሰው ሊረዳህ እንደማይችል እወቅ። ህመማችን ከውጪ ከመጣብን እራሳችንን በመመልከት የመታከሙ ድርሻ የእራሳችን ነው። ማንኛውም ሰው የሚያምንበት የህይወት መርህ አለው፤ ከልቡ የሚቀበለውና የሚመራበት ፅኑ ህግ አለው። የሁላችንም የህይወት መርህ፣ የምንጓዝበት አቅጣጫና የምንቀበለው አመክንዮ አንድ መሆን አይጠበቅበትም።
አዎ! አንተ ካልወደድከው ስህተት፣ አንተ ከወደድከው ደግሞ እውነት የሚሆን አስተምህሮ የለም። እውነታ ባንተ ሳይሆን በእግዚአብሔር ህግ የሚታወቅ ነው። አልችልም ማለትህን ለእራስህ እንደ እውነት ልትቀበለው ትችላለህ፤ በሌላው ዘንድ ግን አለመቻል እውነታ ሊሆን አይችልም። ከሁሉ ከሁሉ የወንድምህ እንቅፋት ከመሆን፣ በቅናት ከመታወር፣ በጭፍን ጥላቻም ከመታሰር እራስህን ጠብቅ። አንዳንድ ነገሮች ስንሰማቸው ላይመቹን ይችላሉ ነገር ግን እውነት መሆናቸውን ልንቀይረው አንችልም። በተቻለህ መጠን አስተሳሰብህን ከጥላቻ የፀዳ፣ ከቅናት የራቀና አሉታዊነትን አብዝቶ የሚጠየፍ አድርገው። በፍቅር፣ በአዎንታዊነትና በደስታ ህይወትህን ሙሉና አጓጉዊ አድርጋት።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪