የብስለት ልህቀት!
➡️➡️➡️🗣️
እድገትና ብስለት የእድሜ እርከን ተከትለው የሚመጡ ቢሆንም በጊዜያቸው የሚታወቁበት መለያ ባህሪያት አሏቸው። አንደኛው ማደግህንና ብስለትህን የምታውቅበት ሁኔታ ሁሉም ድርጊት ግብረመልስ አለመፈለጉን ስትረዳ ነው። መረዳት ብቻም ሳይሆን የተረዳሀውን በተግባር መግለጥ ስትችል ነው። ሰዎችን መጫን፣ መገፋፋት ታቆማለህ፤ ማስገደዱን ትተዋለህ፤ እስከፈለጉት ነፃ እንዲሆኑ ታደርጋቸዋለህ። ማንም ምንም ቢሆን ግድ አይሰጥህም፤ ለመፍረድ አትቸኩልም፤ በነገሮች ላይ less reactive ትሆናለህ። ነፃ ታደርጋቸዋለህ፤ የእራስህን ነፃነት ግን አሳልፈህ አትሰጥም። ህይወትህ ካላስፈላጊ አታካራ የነፃ ይሆናል። ተግባቢነትህ በመጠን ይሆናል፤ ትኩረትህ ሰዎችን አስገድዶ ወደእራስህ ማምጣት አይሆንም። በመልካምነት መታነፅ ትጀምራለህ፤ ደግን ማድረግ፣ በነፃ መስጠትን እየተለማመድክ ትመጣለህ።
አዎ! ጀግናዬ..! የብስለት ልህቀት በሂደት የሚመጣ ነው። ሁን ብለህ ባትኖረውም በምታልፋቸው የህይወት መንገዶች እያዳበርከው የምትመጣው ነው። ለእልህ ቦታ አይኖርህም፤ በቀል አይታይህም፤ በምትኩ የእራስህ እድገት ላይ፣ የእራስህ ጥንካሬ ላይ ታተኩራለህ። ማንም ምንም ቢያደርግብህ መርጦና ፈልጎ ነውና ምክንያቱን ለማወቅ አትጓጓም። ለዘመናት የነገሰብህ ፍረሃት ቀስበቀስ እየለቀቀህና እየተወህ ሲመጣ ትመለከታለህ። ድሮ የሚያጓጓህ ነገር ዛሬ ላይ ምንህም አይደለም። የተዉህን መተው፣ የረሱህን መርሳት ላንተ ቀላል ነው። የፍቅርን ጥግ ከእራስህ ጋር ታሳልፋለህ፣ ቀዳሚው መልካምነት ሌላውን በማይጎዳ መልኩ ለእራስህ ይሆናል። በትግልና በግዴታ የምታገኘው የሰዎች ትኩረትና ስሜት እንደሌለ ከልብህ ትረዳለህ።
አዎ! የእውቀት ብዛት ብስለትት አይሆንም፤ የእድሜ መግፋት ብስለትን አያመጣም። ከእድሜው በላይ የበሰለ፣ ከእድሜው በታች የወረደም ሰው አለና። ብስለት ጥበብ ነው፤ ብስለት የህይወት ሚስጥር ነው፤ የአኗኗር ዘይቤ ነው። ጥሩ ተማሪ ያድጋል፤ አስተዋይ ሰው ይቀየራል፤ ብለሃትን ይወርሳል፤ ብስለትን ይላበሳል፤ እራሱን ይመራል፤ የአቋም ሰው ይሆናል። ደረጃህን በብስለህ አኳሃን መቃኘቱን እወቅበት፤ የህይወት መርህህን ለይ፤ ክፍተቶችህ ላይ እርምጃ ለመውሰት አትዘግይ። ከእድሜህ የቀደመ፣ ከእውቀት የገዘፈ ብስለት እንዲኖርህ ሁሌም ለእድገት የፈጠንክ፣ ለለውጥ የተጋህ ብልህና ታታሪ ሰው ሁን።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨⭐️
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪