የትኛው ላይ ነህ?
➡️➡️➡️🗣️
ከሶስቱ የትኛው ላይ ነህ? ስቃይ ላይ? ትምህርት ላይ ወይስ ለውጥ ላይ? ከሶስቱም ውጪ ከሆንክ ግን ህይወትም ብዙም ላንተ እያዳላች አይደለም። ካወቁበት ዛሬ ስቃይ ላይ ያሉ ሰዎች መዳረሻቸው በምንም የማይቀለበስ ለውጥ ነው፤ ከገባቸው አሁን ከስቃያቸው በሚገባ የተማሩ ሰዎች በቅርቡ የለውጥን ጉዞ ይቀላቀላሉ፤ አሁን በለውጥ መንገድ ላይ የሆኑ ሰዎች ደግሞ በሚያስገርም ሁኔታ ከዚህ ቀደም የማያውቁትን የተለየ ማንነትን እየገነቡ ነው። የእይታ ለውጥ የህይወት ለውጥ ነው። ከራስህ ጋር ሰላም ብትሆን፣ ውስጥህን ብታረጋጋ፣ ህይወትን ከልብህ ብታጣጥም ዋናው ቁልፍ የሆነብህ ነገር ሳይሆን ለሆነብህ ነገር የሰጠሀው ምላሽ ነው። እንዲሁ በተቃራኒው ከራስህ ጋር ሰላም መፍጠር ቢሳንህ፣ መረጋጋት ቢያቅትህ፣ ህይወት ፊቷን ብታዞርብህ የዚህ ሁሉ ዋና መሰረት የሆነብህ መጥፎ ነገር ሳይሆን ስለሆነብህ መጥፎ ነገር የሰጠሀው ግብረ መልስ ነው። ሁን ብለው ስቃይን የመረጡ፣ አውቀው ውጣውረድ ውስጥ የገቡ፣ ከዛሬው ህመማቸው ጀርባ ያለውን ድል አስበው ዛሬ በፍቃደኝነት የሚሰታመሙ ሰዎች ያለምንም ሌላ መመዘኛ በምርጫቸው ብቻ ታላቅ ሰዎች ናቸው።
አዎ! ጀግናዬ...! የትኛው ላይ ነህ? ወደህም ይሁን ተገደህ፣ መርጠህም ይሁን ተመርጦልህ፣ ፈልገህም ይሁን ሳትፈልግ አንተ የትኛው ላይ ነህ? የትኛው ወቅት ውስጥ ነህ? የስቃይ፣ የትምህርት ወይስ የለውጥ? የህመም፣ የአስተውሎት ወይስ የሽግግር ጊዜ ላይ ነህ? ከውጪ ሆኖ የሚያይህ ሰው የቱ ጋር እንደሆንክ ላያውቅ ይችላል አንተ ግን በሚገባ ጠንቅቀህ ታውቃለህ። የመማር ፍላጎት ካለህ ከህይወት በላይ የሚያስተምርህ ነገር አይኖርም፣ መነቃቃት ከፈለክ አሁን ካለህበት ከባድ ችግር በላይ ሊያነቃህ ቤትህ ድረስ የሚመጣ አካል የለም። ማጣት፣ ድህነት፣ ልመና፣ ሰው ፊት መቆም፣ በትንሽ ጠብታን በምታህን የወር ገቢ መኖር፣ የቤተሰብ ችግር፣ የሀገር የፈተና፣ የግል ግንኙነት አለመግባባት ይህ ሁሉ ለለውጥህ ቀይ መብራት ነው። ለምንም ነገር ምክንያት ከፈለክ ምክንያቱ እዛው አጠገብህ ነው። ጨለማ ላይ ማፍጠጥ ያለሰዓቱ ምረሃንን አያመጣም፣ ብረሃን ላይ መጣበቅም ዘላለም በብረሃን ውስጥ እንድትመላለስ አያደርግህም።
አዎ! መማር ካለብህ ነገር ተማር፣ መልቀቅ ያለብህን ነገር ልቀቅ። በቀላሉ የምትሸበር፣ እላፊ ልፍስፍስ የምትሆን የሚታዘንልህ ሰው አትሁን። ሰው አዝኖልህ የሆነ ነገር እንዲያደርግልህ ከምትጠብቅ አንተ ለራስህ ብታዝን ብዙ ማስተካከል የምትችለው ነገር ይኖራል። አንተ ሙሉ እንደሆነች ማሰብ ካልቻልክ ህይወት መቼም ሙሉ ልትሆን አትችልም፣ አንተ ውስጥህ ያለውን ሙሉ አቅም አውጥተህ መጠቀም ካልቻልክ መቼም ህይወትህ ሊቀየር አይችልም። ሁሌም የለውጥና የእድገት በርህ ክፍት ነው፣ ሁሌም ቢሆን ላንተ የሚገባህ የተሻለ ነገር ከፊትህ አለ። አሁን ነገሮች ሁሉ ባሰብከው መንገድ አልሔዱም ማለት እድለኛ አይደለህም ወይም ህይወት ፊቷን አዙራብሃለች ማለት አይደለም። የሆነው ይሁን፣ ለምን እንደሆነ፣ እንዴት እንደሆነ ለማወቅ ሞክር፣ አውቀህም አትቅር በእውቀትህ መሪነትም ቀና ብለህ በድፍረት የማይቀለበሰውን የለውጥና የእድገትን ጉዞ ተቀላቀል።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪