🔗የሱና ወገኖች ሆይ ታገሱ //የአላዋቂዎች ወይም የአስመሳይ አዋቂዎች ጩኸትና ውይታ አይረብሻችሁ!!
`````````````````
◾️የሱና ወንድምና እህቶች ሆይ፥ ጽኑ ታገሱ እርሰ-በርሳችሁም ተዛዘኑ!!
🔻መሰረታዊ ባልሆኑና ኺላፍ ሊከሰትባቸው የሚችሉ ነገሮች ላይ የሚፈጠሩ ልዩነቶችን በመመካከርና በጥሩ በመተርጎም አሳልፏቸው
እነሆ እናንተ ቁጥራችሁ አናሳ ነው የውጭና የውስጥ ጠላታችሁም ብዙ ናቸው
🔹በትዕግስት ☞ካሰቡት መድረስ ይቻላል ለጃሂሉ ህዝብም ሐቁና ትምህርቱ ይደርሳል የጠላትንም ሴራ መመከትና ማዳከምም ይቻላል
🔻ነቢያችንም صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ብለዋል
"ከበስተኋላችሁ የትዕግስት ዘመን አለ በዛ ጊዜ ዲኑን አሳምሮ ለያዘና እዛ ላይም ለጸና ሰው ከናንተ-ከሰሓባዎች- ውስጥ የ50 ሸሂድ ምንዳ አለው!"
📚ሰሂሁል ጃሚዕ 2234
🗂ወደ ባጢል ተጣሪዎች መብዛታቸውና ያላዋቂዎች ወከባ አይሸንግላችሁ
ለዚህም ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሰዒድ ረስላንም እንድህ ይላሉ " እያደር ወደፊት ነገ ሐቁ ይወጣል፣አቧራው ሲወገድ እየጋለቡበት የነበረው ፈረስ ይሁን አህያም ይታወቃል "
🔺ግፈኞችና ለሆዳቸው አዳሪዎችም ይቆጫሉ በጭፍን ተከታዮችም የሚይዙትን ያጣሉ የግልንም ጉዳይ ወደ መንሃጅ በማስገባት የመንሃጅ ያስመሰሉ አስመሳዮችም ዋይ ምነው ባላደረኩት የሚሉበት ቀን ቅርብ ይሆናል ቢርቅ በአንድ ሰው እድሜ ነው!
▪️ታገሱ ብቸኝነት አይሰማችሁ ወገን ዘመድ መክዳቱና ማግለሉም አይክበዳችሁ
▫️የሐቅና የሱናን ጣዕም የቀመሰ ሰው ያድናቂና የአጃቢ መብዛት ምንም አይጨምርለትም
የነቃፊ መብዛትና የተከታይ ማነስም ምንም አይጎዳውም
🔺ታገሱ አላዋቂዎችና በአላህና በአኼራ ትክክለኛውን ኢማን ያላመኑ ሰዎች ተግባር ወዳልሆነ አቅጣጫ እንድታመሩ አያድርጋችሁ፣
በውስጥና በውጭ ጠላቶች ስማችሁ መጥፋቱም ብዙ አይክበዳችሁ፣ የረዳቶች ማነስም አይበግራችሁ
🔺ነቢያችን ከመካ ተባረዋል እብድና ድግምተኛም ተብለዋል
ኢብራሂም እሳት ላይ ተጥለዋል
▪️ዩኑስ ምድር ጠባቸው ባህር ውስጥ በአሳ ነባሪ ተውጠዋል
ኑሕ እብድ ሲባሉ፣
🔺ሁድም ጅል ተብለዋል ስለዚህ የድንበር አላፊዎች ስድብና ወከባ ምንም አይግረማችሁ
🔺የነቢያትን ፈለግ የተከተሉ ምዕምናንም በየዘመኑና በየሀገሩ ተመሳሳይ በደሎችን አስተናግደዋል
🔺ሐቁ ላይ ከጸናችሁ ሽልማታችሁ "ጡባ" የሚባል ጀነት ነው
ዱኒያና በርሷ ላይ ያሉ ብልጭልጮችና አላዋቂዎች አኼራቸውን የሚያበላሹለት ነገር ሁሉ ጠፊ ነው
▫️ክብርና የመጨረሻ ማማርም ለአህለል-ሐቅ ነው! " ያሳፈራቸውና ሊያወርዳቸው የሞከረ በሙሉ አይሳካለትም"
ብለዋልና ነቢያችን ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም !
✅ የፖለቲካ ፖርቲ ይመስል እንትናም ከእኛ በው አይነት አካሄድም እንዳይሸነግልህ ስለዚህ ወንድሜ አስተውል
" በመደናነቅና በቲፎዞ የተገነባ መንሃጅ
በመናናቅና በመነቋቆር ይፈርሳል " ኢንሻ አላሁ ረቡል ዓለሚን
አላህ መቸም በዳዮችንና ወሰን አላፊዎችን እረድቶ አያውቅም!
🔸ሐቁን ለማጠልሸት ባለቤቱቹንም ለማሰናከል መጣራቸው ግን አይቀርም
⚠️ስለዚህም በርቱ በዓላማችሁ ላይ ....
ማሳሰቢያ
በማንኛውም ፊርቃ ላይ ይሁን ወለው ከሃድ ላይም ቢሆን ሲያጠፋ በጥፋቱ መጠን እንጅ በሱ ላይ ተዋሽቶ እና ድንበር ታልፎ ያላለውን ብሏል ተብሎ ተቀጣጥፎ ተጨምሮ መልስ እንደማይሰጥ ላስተማረንና ይሄን ጥርት ያለ መንሃጅ ለወፈቀን አረህማን ከፍጥራኖቹ በገዘፋ ምስጋና ይገባው
ወንድሜ አስተውል በአህባሽም ሆነ በኢኽዋን ላይ ሲዋሽና ድንበር ሲያልፍ ያየኸው በሱና ወንድምህ ላይ ሲዋሽና ድንበር ሲየልፍ በጣም እንደሚዘገንንህና እንደሚከብድህ ይገባኛል ቢሆንም ታገስ ይሄም ያልፋል ገለባው ይሄዳል ምርቱ ይቀራል ወንድሜ የገለባው መብዛት የእህሉን ፍሬ አማነት አያሳይም ስለዚህ
በቀን እያየኸው የዋሸህ በጨለማ ሳታየው ላለመዋሸቱ ምን ዋስትና አለህ? ?
ለዚህም አንዳንድ ኦለሞች
" የምታውቀውን እውነታ በማታውቀው የሃሰት ግርግር ልትቀይር አይገባህም ያሉህ " ስለዚህ ወንድሜዋ አሁንም አደራህን በትዕግስት ላይ! !
ያ ኢላሂ እነዚህ ሰዎች እውነትም ሃቁ ተሰዉሮባቸው ከሆነ ያ አረህማን አንተ ሁሉንም በማድረግ ላይ ቻይ ነህና ሃቁን አሳያቸው!
ያ አረህማን ! ሃቁን እያወቁት ሆን ብለው ባላቸው እውቀት ተከታይ ለማብዛትና እውቅናን ለማግኘት ከሆነ አንተ ሁሉንም የውጩንም የሩቁንም አዋቂ ነህና ወገባቸውን ስበርልን! !
ከሃርቡው ወንድማችን ላይ የተወሰነ ማስተካከያ የተደረገበት
@JemalEndro https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/11107