Only islam


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


Join now. and share to all!
ሊንኩ ይኸው
https://t.me/joinchat/AAAAAE90idLYrtXA9FQl4g

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


"ሰላም"
የሚለውን ቃል ሙስሊሞች በቀን
ስንት ግዜ ይጠሩታል?!
እርስ በርስ ሲገናኙ
ሰላት ውስጥ
ዱዓቸው/ፀሎታቸው ውስጥ…

አሸባሪ የሚለው ታፔላ ቅጥፈት
ነው።
ግን ሙስሊሞች
በዳይንና ግፈኛን የሚያሸብሩ ናቸው።እውነተኞች ስለሆኑ።
መቼም…እኛ በዳዬችን ማስፈራታችንና ማሸበራችን ስህተት አይደለም።😳
@only_islam1


🤷‍♂
@only_islam1


ክርስቲያን ወገኖች ሁሌ ሚተቹት ትችት ነው።
ታሪክ አለማወቅ እንዲህ ነው መዘዙ።
ለውይይትና ለክርክር ሲፈሩ…
የሚያነሱት የጅል ቅጥፈት ነው።
እኛ እኮ በዛን ዘመን የተወለድን ዕድሜ ጠገብ አረብ አይደለንም።
😃
ስለ ስደቱ ከተነሳ…
እስልምና ከነብያችን በፊት ነበር።
ስለዚህም ሉቅማነል ሃኪም
ጥበበኛው ሉቅማን👉 ሙስሊም
ነበረ።ሃበሻ ላይ የሚኖር የአላህ ባርያ ነበር።
ሱረቱል ሉቅማን በሱ ስም ነው የተሰየመው።
ክርስትና ወደ ኢትዮጲያ ከመግባቱ
ቀድሞ የኖረ ጥበበኛ ሙስሊም ነበር።ማለትም ከክርስትና በፊት እስልምና ኢትዮጲያ ውስጥ ነበረ።

እንደውም መጤው ሃይማኖት ክርስትና ነው።
ክርስትና በኢትዮጲያ የገባው በ9
የሃይማኖት አባቶች ሲሆን…
የሶሪያ ስደተኞች ነበሩ።
ፍሪምናጦስ(አባ ሰላማ፣
ከሳቴ ብርሃን) ወደ አክሱም አስገብቶ ነበረ።
«ዘጠኙ ቅዱሳን» በመባል ይታወቃሉ።👇

አባ አፍጼ
አባ አሌፍ
አባ ገሪማ
አባ ጉባ
አባ ሊቃኖስ
አባ ጴንጤሌዎን
አባ ጻሕማ
አባ የማታ እና
አባ ዘሚካኤል ዓረጋዊ ናቸው።
📚The Dictionary Of Ethiopian Biography, Vol.1,
From Early times to the End of the Zagwe Dynasty C.1270 AD, Institute of Ethiopian studies Addis Ababa University, 1975, Pp.
209-210

አብዛኛው የኢትዮጲያ ክርስቲያኖች
ክርስትና ወደ ኢ/ያ ሲገባ ከአንዳንድ ሰዉ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ መስሎ ይታያቸዋል።
ግን በሚያስገርማችሁ መልኩ
ከመቶ አመታት ጦርነት በኃላ ነው
ራሱን ችሎ መቆም የቻለው።
በዚህ መሃል ሙስሊሞች እስላማዊ እስቴት አቋቁመው ነበር
@only_islam1


ክርስትና አንድን ነገር ሲከለክል
በሚገባ አይከለክልም።
"ይህን ተግባር ራቁት" ብሎ መከልከል ይቅርና "አትስሩ" ለማለት እንኳ ያጥረዋል።


አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ
አለምን ብቻውን አስገኚ ነው።
ስለዚህ እሱን ብቻ ልናመልክ ይገባል።

ሁለትና ከዛ በላይ አምላክ ቢኖር ኖሮ
ዩኒቨርሱ በተበላሸ ነበር።


በክርስትና እምነት የውስጥ እንጂ
የውጭ ንፅህና ሚባል ነገር የለም
የውስጥ ንፅህናቸው ትክክል ነው እያልኩ አይደለም።

በእስልምና ንፅህና የኢማን/እምነት
ግማሽ ነው የሚል አስተምህሮ ነው ያለው።

የውጭ ሳይፀዳ አምላክ ዘንድ መቅረብ ተገቢ አይደለም


አጭር መልስ>
ቢላል ረዲየላሁ ዓንሁ ካዕባ ላይ ቆሞ ነበር ወደ ሰላት የሚጠራው
/አዛን የሚል የነበረው።

ታድያ ካዕባን🕋 ብናመልክ ኖሮ
ጣዖት ይባላል።ከዛስ አምላካችን ይሆናል።

አምላካችን ላይ ወጥተን
አዛን ልናደርግ ማለት ነው?
አስታጝፊሩላህ።
አላህ ይምራችሁ።
Join now. and share to all!

ሊንኩ ይኸው
https://t.me/joinchat/AAAAAE90idLYrtXA9FQl4g


በሚገርም ሁኔታ በእስልምና ብቻ ነው የጋብቻ ገደብ የተቀመጠው
Surah An-Nisa’ (النّساء), verses: 3

…فَٱنكِحُوا۟ مَا طَابَ لَكُم مِّنَ ٱلنِّسَآءِ مَثْنَىٰ وَثُلَٰثَ وَرُبَٰعَ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا۟ فَوَٰحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُكُمْ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰٓ أَلَّا تَعُولُوا۟

«…ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ #አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡

በሌላው ሃይማኖት ገደብ የለም 20
30 🤷‍♂
በሰፊው የተፃፈ ቴክስት ሳገኝ እልክላቹኃለሁ።


اسلام عليكم ورحمت الله وبركاته.
بــــــــسم الله الرحمان الرحيم.
እባኮትን ይቺን ፅሁፍ በእርጋታ፣ በሰከነ መንፈስ፣ከልባችሁ አንብቡ።
#መለየት_ከፍቅራቸው!

የኢሻ ሰላት ከሰገዱ በኃላ ወሬና ጨዋታ አይወዱም።የተከበረ አካላቸውን በሰሌን ላይ ያሳርፉታል።አይናቸው እንጂ ልባቸው አይተኛም።የሌሊቱ መጀመርያ ሰአት ላይ ይነቃሉ። ለሊቱን በዱኣ ያሳልፉታል። በጣም ረዥም ሰአት በሰላት ውስጥ ይቆማሉ።እግራቸው እስኪያብጥ ድረስ።ለህዝቦቻቸው ሲሉ ያለቅሳሉ ፂማቸው እስኪርስ ።ሆዳቸው የሲቃ ድምፅ እያወጣ።በዚህ መልኩ የሱብሂ አዛን(የለሊቱ ማለቂያ ሰአት ላይ የሚሰገድ ሰላት)ደርሶ አዛን ይላል።ሱናቸውን ሰግደው በቀኛቸው ጋደም ይላሉ። አይናቸው እንጂ ቀልባቸው/ልባቸው አይተኛም።ከደቂቃዎች በኃላ ኢቃም(የሰላት ማስጀመርያ ጥሪ)ሲሰሙ ይነቃሉ።አማኞችን ያሰግዳሉ።ከዛ በኃላ አይተኙም።
ጠዋት የሚቀመስ ነገር ካለ ለቤተሰባቸው ይጠይቃሉ። ካላገኙ በዛው ለመፆም ነይተው ፆማቸውን ይውላሉ።ካገኙ ብቻቸውን መመገብ አይወዱምና ከሰው ጋር በአንድ ይበላሉ። ቀኑን ሰዎችን በማስተማርና በመጣራት ያሳልፋሉ ።ከመስጊድ ሲመለሱ ቤተሰቦቻቸውን በስራ ያግዛሉ። ፆማቸውን በአንድ ቴምር አንዳንዴም በውሃ ብቻ ለማፍጠር ይገደዳሉ።ሁሉንም ሚስቶቻቸው ይዘይራሉ፤ጥቂት ግዜ ያሳልፉና ተራዋ የደረሰችዋ ቤት በፍቅር ያሳልፋሉ።
የኛ ነብይ በጨረፍታው እንዲህ ናቸው።ሰሃቦቻቸው ከኚህ ውድ
ነብይ ጋር መለየት ፍፁም አይችሉም ነበር።
🖌እስቲ ይቺን ሃዲስ ያንብቧት።👇
📚ሰሂህ ሙስሊም ኪታብ ቁጥር 4 ሀዲስ ቁጥር 903
ኢብን መስዑድ እንዲህ ይላል፡- “በአንድ ምሽት የአላህ መልዕክተኛን አጅበን ነበር ሆኖም ግን ጠፉብን። በሸለቆውና
በተራራው ሁሉ ፈለግናቸው ( በጂኖች) ተወስደዋል ወይም በምስጢር ተገድለዋል አልን፤ #ሰዎች_አሳልፈውት_የማያውቁት #አስከፊ_የሆነ_ሌሊትንም_አሳለፍን፤ በነጋ ጊዜም ከወደ ሒሪ አቅጣጫ ሲመጡ አየናቸው፤ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!
ጠፍተውብን ፈለግነዎት ግና ልናገኝዎት አልቻልንም በመሆኑም ሰዎች አሳልፈውት የማያውቁት #አስከፊ የሆነ ሌሊትንም
አሳለፍን አልናቸው።
🖌ሰሃቦች ፍቅራቸው/ነብዩ ለአፍታ ሲለዩዋቸው እንዴት እንደሚጨነቁ አያችሁ!
🖌አንድ ሰሃባ ከረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ጋር ሁሌ ይቀማመጣል።ወደ ቤቱ ሲመለስ ግን ሱብሃነላህ ለአፍታ ከሳቸው ተለይቶ መቆየት ከብዶት ይመለሳል።"ከርሶ ለአፍታ #መለየት_አልቻልኩም።በመጭው አለምም ላላገኞት እችላለው"። አላቸው።"ከወደድከው ጋር ነክ" ብለው አፅናኑት ነብዬ።
ሰሃባው ለሰአት እንኳ መለየት የከበደው አመታትን በምን ይሆን የሚያሳልፈው።😢

የበኒ ነዲርኒ ሴት የነበረች አንዲት ሰሃባ በኡሁድ ጦርነት ላይ ባሏ መሞቱ ተነገራት፤ነብዩ እንዴት ናቸው ብላ መለሰች።ወንድሟ መሞቱንም ነገሯት የረሱልን ሰላም መሆን ጠየቀች ውድ አባቷ መሰዋቱን አረዷት።ነብዩን አሳዩኝ ብላ መለሰች።ስትመለከታቸው #እርሶ #ደህና_ከሆኑ ሌላው መከራዎች #ኢምንት ናቸው አለች።
🖌ተደግፈው የሚያስተምሩበት አንድ የዛፍ ግንድ ነበረ።ሌላ መደገፊያ ተሰርቶላቸው ይህን ግንድ ለመጨረሻ ግዜ ተለዩት። ጀርባቸው፣እጃቸው ከዚህ በኃላ ላይነኩት ሆነ።አስቡት ግንድ ነው አፍ አውጥቶ አይራቁኝ አይል፤ እርሳቸውን ላለማጣት ሮጦ አይሄድ ፤ፍቅሩ ጠንቶበት በናፍቆት ሊጠወል ነው።ጀርባቸው #ሲለየው ግን #ፍቅሩ_አንሰቅስቆ #አስለቀሰው። ውዴ በተከበረው እጃቸው አቅፈው አባበሉት።

#መለይት_ከፍቅራቸው
አይቀሬው ሞት መጣ…
ወቅቱ ረሱላችን ሊሞቱ አንድ ቀን ብቻ የቀራቸው ግዜ ነበረ። ሙስሊሞችን የሱብሂ ሰላት አቡበከር አስ ሲዲቅ ረዲየላሁ ዓንሁ ተተክቶ ማሰገድ ጀመረ። ረሱላችን በዓኢሻህ ረዲየላሁ ዓንሃ ጓዳ ጋደም ብለው ነበረ።ነብያችን ግርዶውን ገርበብ አድርገው ሲሰግዱመለከቷቸው። ለኡማቸው ቅን መንገድን ይጓጉ የነበሩት ነብይ በረድፍ እየሰገዱ መሆኑን ሲያውቁ ፈገግ አሉ።አቡበክር ረሱላችን ለማሰገድ ሊመጡ ስለመሰለው ወደኃላ አፈገፈገ። ሰሃቦች ስሜቱን ተጋርተው በደስታ ሰላታቸውን ሊያቋርጡ ደረሱ። ረሱል እንዲቀጥሉ ምልክት ሰጧቸውና ግርዶውን መለሱ።
የረሱል ለደቂቃ ጤናማ መሆን ሰሃቦችን ምን ያህል ያስደስታቸዋል
ከፍቅራቸው መለየትስ እንዴት ያስችላቸው ይሆን።ለኡማው የመጨረሻ ትልቅ ኑዛዜ አስተላለፉ « #ሶላታችሁን በተገቢው ሁኔታ ስገዱ። አገልጋዩቻችሁንም #በመልካም አያያዝ ያዙ።» ደጋግመው አስተላለፉ።
መልካም ሆነው ኖረው ወደ አላህ መልካም ሆነው ለመጨረሻ ግዜ ተለዩዋቸው።በረቢዑል አወል 12 ኛው ቀን ላይ በሰኞ እለት ወደ አላህ ተመለሱ።ዑመር መሞታቸውን ሲሰማ ራሱን መቆጣጠር አቃተው ማመን እስኪያቅተው ድረስ።ኢብን አባስም ተዝለፍልፎ ወደቀ።
በረሱል ሞት መዲና በሃዘን ተሸፈነች።አነስ ረዲየላሁ ዓንሁ እንዲህ ብሏል:–«የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም #ወደ_መዲና_ከገቡበት ቀን የበለጠ #አስደሳችና_ብሩህ ቀን አይቼ አላውቅም።እርሳቸው #ከሞቱበት ቀን የበለጠም #አስከፊና_ፀለምተኛ ቀን አይቼ አላውቅም»።

የእዝነቱ ነብይ፣የጥሩ ስነ ምግባር ሟሟያ፣የአላህ ወዳጅ፣የአላህ ውድ ፣የአላህን ሃቅ ጠባቂ አስጠባቂ፣ ለሱ የሆኑለት ለሳቸው የሆነላቸው፣ ለጠላቶቻቸው የበቃቸው፣ ሌት ከቀን ለህዝቦቻቸው መመራት ያለቀሱ፣ ቻይ፣ ታጋሽ፣ አዛኝ፣ተናናሽ፣ ውብ፣ጀግና፣ይቅር ባይ ምስጉን፣ አመስጋኝ፣ ለነፍሳቸው ብለው የማይበቀሉ፣ ድሃ ወዳጅ፣ ምስኪን ጠባቂ፣ ሰላም ወዳድ ሁሉን አክባሪ፣ጥበበኛ፣አዋቂ፣እኛን የናፈቁ፣ቸር ሆነው ኖረው ታላቅ ሆነው አላህን የተገናኙት የሰው ልጆች አይነታና አለቃ…
#ውዳችን_ሃቢቡና_ሙሀመድ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም
ዑማውን/ህዝባቸውን የተለዩበት ቀን ምን ያህል ከባድ ነው!ሳናያቸው አምነንባቸዋለን ሳናያቸው ፍቅራቸው ያንገበግበናል!
ዛሬም የማያምኑባቸው የሚሰድቧቸው ያልሰሩትን የሚቀጥፉባቸው አሉ። እነዚህን ሰዎች ወዳጅ አድርገን መያዝ እፍረት ነው።
#ፊዳከ_ሃያቲ_ያረሱሊ😔
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
" #ጙረባእ_እንሁን!"
ጆይን ሼር
@Only_islamy


اسلام عليكم ورحمت الله وبركاته
بــــــــسم الله الرحمان الرحيم.
#ምግብን_የሚበሉ_ነበሩ።

የተከበረው ቁርአን ሁሉም አንቀፆቹ ተአምር ናቸው።ይቺ አንቀፅ ደግሞ ላስተነተናት ወላሂ አስገራሚ ናት።👇👇👇👇👇👇
5:75

مَّا ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ ٱلرُّسُلُ وَأُمُّهُۥ صِدِّيقَةٌ كَانَا يَأْكُلَانِ ٱلطَّعَامَ ٱنظُرْ كَيْفَ نُبَيِّنُ لَهُمُ ٱلْءَايَٰتِ ثُمَّ ٱنظُرْ أَنَّىٰ يُؤْفَكُونَ

የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ እናቱም በጣም እውነተኛ ናት፡፡ (ሁለቱም) #ምግብን_የሚበሉ ነበሩ፤ አንቀጾችን ለነርሱ (ለከሓዲዎች) እንዴት #እንደምናብራራ ተመልከት ከዚያም (ከእውነት) እንዴት #እንደሚመለሱ ተመልከት፡፡

1⃣«የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም።»
👉ነብያቶች በሙሉ የሰው ልጆች ናቸው።ዒሳም(ኢየሱስም) እንደነሱው ነብያና ፍጡር እንጂ ፈጣሪ አይደለም።

2⃣«እናቱም በጣም እውነተኛ ናት፡፡ (ሁለቱም) ምግብን የሚበሉ ነበሩ፤»
👉የአእምሮህን ሞተር አስነሳው!
ምግብን የሚበሉ ነበሩ ይላል።
ምግብ የሚበሉት
👉ስለሚርባቸው
👉ስለሚደክማቸው
👉ካልበሉ ስለሚሞቱ
ምግብን የበላ ግለሰብ ከሰአታት በኃላ የት ነው?ሽንት ቤት!
ገቢቶ?
አገላለፁ አላስደመማቹም?

3⃣«አንቀጾችን ለነርሱ (ለከሓዲዎች)እንዴት እንደምናብራራ ተመልከት»
👉አየነው። ምንኛ ያማረ ማብራርያ።ግን ከሃድያኖች ልባቸውን ደነደኑ ይቺን ታላቅ አንቀፅ መቀበል አሻፈራቸው።

4⃣«ከዚያም (ከእውነት) እንዴት እንደሚመለሱ ተመልከት፡፡»
👉አላሁ አክበር!! ተመለከትን ያ አላህ።
አንተው ምራቸው።
" #ጙረባእ_እንሁን!"
ጆይን ሼር በሉ።⬇️
@Only_islamy


اسلام عليكم ورحمت الله وبركاته
بــــــــسم الله الرحمان الرحيم.
#ባይብል_አልተበረዘምን?
ክፍል 8
#BONUS
የአሁኑ ባይብል ላለመበረዙ አንድም ዋስትና የለውም። ምናልባት ይህ አንቀፅ ሊነሳ ይችላል።ራእይ 22:18–19
18፤ በዚህ #መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል ለሚሰማ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፤ ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል፤
19፤ ማንምም በዚህ #በትንቢት መጽሐፍ ከተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል፥ በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት #ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ዕድሉን ያጎድልበታል።
እነዚህ አንቀፆች በፍፁም ስለ መፅሃፍ "ቅዱስ" አያወሩም።
1⃣ኛ, «በዚህ_መፅሃፍ…»ሲል የራሱን የራዕይ መፅሃፍ እንጂ ስለ ሌሎቹ በፍፁም አያወራም።
2⃣ኛ, ባይብል ሙሉ ለሙሉ ተዋቅሮ የተዘጋጀው ቆይቶ ነው።
3⃣ኛ,ለባይብል ነው ብንል እንኳ አንቀፁ "ቅጣትና እርግማን ይወርድበታል" አለ እንጂ ፈጣሪ ከመብበረዝ ይጠብቀዋል አላለም።ዋስትና አልገባለትም
🖌ባይብል ያለ ዋስትና ከቀጠለ…
አላህ አያድርገውና…፤ነብዩ ሙሃመድን ሰላም ይስፈንባቸው
በአሉታዊ መልኩ አንቀፅ መጨመሩ አይቀርም።
🖌በአሁን ሰአት ከመቶ አይነት በላይ የሚቆጠሩ የባይብል ቅጂዎች ይገኛሉ።
2ቱን በመውሰድ አነፃፅረን እንመልከት 👇
ኪንግ ጀምስ ቨርዥን KJV(የ1611) ይህ እትም የቅርብ ግዜ ፅሁፎችን ተመስርቶ የተፃፈ ነው።Based on later manuscripts
ሪቪያዝድ ስታንዳርድ ቨርዥን RSV(1952).ይሄ ደግሞ #በጣም ከቆዩ ፅሁፎች ተመስርቶ የተፃፈ ቅጂ ነው።(Based on #most_ancient_manuscripts)
ይህንን ከተረዳን ወዲህ አንድ ምሳሌ ወስደን እናነፃፅራቸው።
1ኛ ዩሃንስ 5:6–8
የ(KJV)ው እንዲህ ይላል።
6: This is he that came by water and blood, even Jesus Christ; not by water only, but by water and blood. And it is the Spirit that beareth witness, because the Spirit is truth.
7: For there are three that bear record in heaven, the Father, the Word, and the Holy Ghost: and these three are one.
8: And there are three that bear witness #in_earth, the Spirit, and the water, and the blood: and these three agree #in_one.
👉ትርጉሙ
6፤ በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በውኃውና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም።መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው።
7፤በሰማይም የሚመዘግቡት አባት ቃል እና መንፈስ ቅዱስ ሶስት ናቸውና ሶስቱም አንድ ናቸው።
8፣ #በምድርም የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም #በአንድ ይስማማሉ።
የሪቫይዝዱ እንዲህ ይነበባል።
6: This is he who came by water & blood, JesusChrist; not with the water only, but with the water & the blood.
👇እዚህ ጋር አንቀፅ7 ይጀምራል።
👉 and the Spirit is the witness, because the Spirit is the truth.
8,and there are 3 witness, the spirit,the water and the blood and these 3 agree.
👉ትርጉሙ
6፤ በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በውኃውና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም።
👇እዚህ ጋር አንቀፅ 7 ይጀምራል
👉መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው።
8፤ የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም ይስማማሉ።
❗️አስተውሉ የሪቫይዝዱ ቅጂ በጣም የድሮ ቅጂን ተመስርቶ ነው የተፃፈው።የKJV ግን ቀረብ ባሉ ነው የተፃፈው።
❗️የ KJVው ቅጂ 7ኛ አንቀፅ የ በባይብል ላይ የተሰነቀረ የፈጠራ ውጤት መሆኑን የደረሱበት የክርስቲያን ሊቃውንት አንቀፁን ከማካተት ተቶጥበዋል።
በኬጄቪ ቅጂ በ8 ኛው አንቀፅ ላይ ደግሞ #በምድርም እና #በአንድ የሚሉ አዲስ ቃላት ተጨምሯል።
❗️ሪቫይዝዱ እነዚህን ከመጨመር ታቅቧል።የአምላክን «አንድም ሶስትምነት» የሚገልፀው ይኽው የ ኬጄቪ ቅጂ 7ኛ አንቀፅ በሌሎችን ቅጂዎች ውስጥ አይገኝ ም።በ The New International Version 1984,The New American Bible 1986,The Living Bible 1971,The New Jerusalem Bible 1985,The New English Bible 1972, The American Standard Version 1901,The New American Standard Bible 1977,The Good News Bible (TEV) 1971

🖌ማርቆስ 16፣15«እንዲህም አላቸው፡— ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፡ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።
ይህ አንቀጽ አዲስ የተጨመረ እንጂ በድሮ ባይብል ውስጥ ሰፍሮ አናገኝም፡፡ቀለል ባለ አማርኛ የ1980 እትም መጽሃፍ "ቅዱስ" ከህዳጉ/ከግርጌ/ ማስታወሻ ላይ የተጻፈውን ይመልከቱ፡፡ እንዲህም ይነበባል፡-
«አንዳንድ ቅጂዎችና የጥንት ትርጉሞች ከቁጥር 9-20 ያለውን ክፍል አይጨምሩም፡፡»ይላል።
🖌NRV ቅጂ ላይ ማቴ 17:21
ማቴ 18:11 ማቴ 23:14 ዩሀ 5:4
ተሰርዟል።
🖌KJV ቅጂ ላይ ዩሀ3:16
John 3 (KJV) - ዮሐንስ
16: For God so loved the world, that he gave his only #begotten Son,ሌሎች ቅጂዎች" #begotten"የሚልቃል ከመጨመር አሁንም ታቅበዋል።
ቃሉ በጣም አሳፋሪ ነው። ቢጋትን የሚለው ቃል በግብረ ስጋ ግንኙነት ለተገኘ ነገር ለመጠቆም የሚያገለግል ቃል ነው።
📌መደምደሚያ
🖌የአንድ እምነት ምሰሶ…እምነቱን የሚመራበት መፅሃፍ ነው። መፅሃፉ ከሰው እጁ ተጠብቆ ይቆይ ዘንድ ከፈጣሪ ዋስትና ያስፈልገዋል።ለመጠበቁ ዋስትና ከሌለው እምነቱን ያፈራርሰዋል።
የመጨረሻው የአምላክ ኪዳን
ቁርአን ብቻ ነው።
በአላህ ፍቃድ ተጠናቀቀ።

👉REMEBER,THE LAST TESTMENT IS QURAN❗️👈
Join and share to all.👇
@only_islam1


اسلام عليكم ورحمت الله وبركاته
بــــــــسم الله الرحمان الرحيم
#ባይብል_አልተበረዘምን?
ክፍል 7
#እስላማዊ_እይታው
#ባይብል_በሰሃባዎች
የ2 ተኛው ኸሊፋ የዑመር ኢብኑል ኸጣብ ገጠመኝ ለኦሪት መበረዝ ማስረጃ ይሆናል።
Sa'eed ibn Al Museeb narrated that it happened that a Muslim and a Jew had a dispute so they went to Umar bin Al-Khattab to judge between them. Umar bin Al-khattab ruled infavor for the Jew,which upon the Jew said: "I swear by Allah, you have judged with the Truth".Umar bin Al-khattab hit the man with a stick that has a small ball on the top of it when he heard him saying that.Then Umar bin Al-khattab asked the Jew, "How do you know that I judged with the truth?" The Jew replied, "We find in the #Torah that whoever judges according to the truth two angels from his right and leftsides assist him to find the truth.Yet, if he went astray from the truth, they will leave him.
ማለትም በተውራት/ኦሪት ላይ
«ማንም በእውነት ለሚፈርድ ሰው፤ እውነትን ያገኝ ዘንድ ሁለት መላእክት ከቀኝና ከግራ ሆነው ይረዱታል።ሆኖም ከትክክለኛው እውነት መውጣትን ቢሻ ይሸሹታል።»
📚(አል ሙንዚር አተርጊብ ወተርሂብ በተሰኘው መጽሀፋቸው ጥራዝ 3 ገጽ 188 ታሪኩን ሰሂህ በሆነ ዘገባ።
በዚህ ዘገባ ውስጥ የምንመ ለከተው የወጣቱ ንግግር በአሁኑ ኦሪት ውስጥ አናገኘውም ይህም በተመሳሳይ ሁኔታ ኦሪትያሳለፈውን የመበረዝና የመለወጥ ሂደት የሚጠቁም ነው፡፡
📌የ3ኛው ኸሊፋ ዐስማን ኢብን አፋን ረዲየላሁ ዓንሑ እይታ 👇ኢብን ከሲር ኡስማን ኢብን አፋን እንዲህ ማለቱን ዘግበዋል
"Because they (the Jews) #distorted the #Torah.They #added to it what they #liked and #erased from it what they #hated and they erased the name of #Muhammad peace be upon him from the Torah and for that Allah became angry" (ኢብኑ ከሲር ለ2፡79 የሰጡት ማብራሪያ እንግሊዝኛው ቅጅ)።ይህ የኡስማን ንግግር በግልጽ አይሁዶች ከመጽሀፉ ውስጥ #ያሻቸውን_ ይሰርዙና_ያ ሻቸውን_ጨምሩ እንደነበር ይገልጻሉ፡፡
ሌላው የታላቁ ሰሃባ የኢብን አባስ ረዲየላሁ ዓንሁ እይታ/ንግግር ነው።በተለያዩ ሀዲሶች ነብያችን ሰላም ይስፈንባቸውና እውቀቱን የመሰከሩለት ድንቅ ሰሀባ ነበር፡፡ ለአብነትም በሰሂህ አልቡኻሪ ጥራዝ 1መጽሀፍ 4 ቁጥር 145 ኢብኑ አባስን አላህ ጥልቅ ኢስላማዊ እውቀት ይሰጠው ዘንድ ዱዓ (ጸሎት) ሲያደርጉለት እንመለከታለን፡፡ቡኻሪጥራዝ 5 መጽሀፍ 57 ቁጥር 100፣ እንዲሁም በሰሂህ ሙስሊም 6055 ተመሳሳይ ዱዓ እንዳ ደረጉለት ተዘገቧል፡፡ስለ እሱ ለመግቢያ ይህንን ካልን ኢብን አባስ ከመምህሩ (ከነብዩ) በተማረው መሰረት ምን እንደሚለን እድሉን እንስጠው በሰሂህ አለቡኻሪ ጥራዝ 9 መጽሀፍ 93 ሀዲስ ቁጥር 613&614 ላይ በግልጽ ቀደምት መለኮታዊ መጽሀፍት እንደተበረዙ ይነግረናል ለአብነት 614ን እንመልከት እንግሊዝኛው ትርጉም እንዲህ ይላል፡- 'Abdullah bin'Abbaas said, "O the group of Musl ims How can you ask the people of theScriptures about anything while your Book which Allah has revealed to your Prophet contains the most recent news from Allah &is pure and not distorted Allah has told you that the people of the Scriptures have changed some of Allah's #Books& #distorted it and wrote something with their #own_hands and said,'This is from Allah,so as to have a minor gain for it. Won't the knowledge that has come to you stop you from asking them? No, by Allah, we have never seen a man from them asking you about that(the Qur'an) which has been revealed to you.>>
በዚህ ሀዲስ ግልጽ በሆነ መልኩ ኢብን አባስ የመጽሀፉ ሰዎች👉
ክርስቲያኖችና አይሁዶች መጽሀፎቻቸውን ይበርዙ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ኢብን ሀዝም ይህን ሀዲስ መሰረት አድርገው ሲናገሩ ‹‹ይህ የኢብን አባስ ዘገባ የሁላችንም እይታ ነው፤በዚህ ጉዳይ ላይ በነብዩ (ሰዐወ) ባልደረቦች መካከል ልዩነት አልነበረም፡፡››
📚ኢብን ሀዝም አል ፈስል ፊል ሚላል ጥራዝ 2 ገጽ 3 በተጨማሪም👇
📚(ተንዊር አል መቅባሰ ሚን ተፍሲር ኢብን አባስ ለ2፡79 የተሰጠ ማብራሪያ-የእንግሊዝኛው ቅጅ)በተመሳሳይ የአል ማዋሪዲ አኑኸቱ ወል ዒዩን ለ2፡79 የተሰጠውን ማብራሪያ ስንመለከት ይህን የኢብን አባስን አቋም አስቀምጦ ይተነትናል፡፡ኢብን ጀሪር አጦበሪ ጃሚዑል በያን ፊ ተዕዊ ሊል ቁርዓን ለ2፡42 የተሰጠ ማብራሪያ ነሳኢ 5305 (ሸይኽ ነስሩዲን አልባኒ በ5400 የነሳኢ ሀዲስ ይህም ሀዲስ #ሰሂህ መሆኑን ገልጸዋል)።
📌የሌላም ሰሃባ ንግግርን እንመልከት።
ዐጣእ ኢብኑ የሳር (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላል፡- "ዐብዱላህ ኢብኑ ዐምር ኢብኑል-ዓስን (ረዲየላሁ ዐንሁማ) አገኘሁትና፡- ስለ አላህ መልክተኛ ባሕሪ በተውራት/ኦሪት ውስጥ ያለውን ንገረኝ አልኩት፡፡እሱም፡- እሺ! ወላሂ እሳቸው በተውራት ውስጥ ከፊል ባሕሪያቸው በቁርኣን ውስጥ፡- "አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ መስካሪ አብሳሪና አስፈራሪም አድርገን ላክንህ።" ተብሎ እንደተገለጸው ተጠቅሶአል፡፡ (የተውራቱ ቃል ይቀጥልና እንዲህ ይላል) መሀይማኖችን ጠባቂ አድርጌ ልኬሀለሁ፡፡ መጥፎን ቃል ተናጋሪ ወይም ልበ ደረቅ አይደለህም፡፡ በገበያ ማእከሎችም ድምጽህን ከፍ በማድረግ የምትጮህ አይደለህም፡፡ መጥፎ ቢሰራብህ በመጥፎ የምትክስ ሳትሆን፡ ነገር ግን ይቅር ባይ እና መሐሪ ነህ፡፡ አላህ ባንተ ሰበብ የጠመሙ ጎዳናዎችን ቀጥእስኪያደርጋቸውና ሰዎች "ላ ኢላሀ ኢልለሏህ"እስኪሉ ድረስ በፍጹም አይገድልህም፡፡
/ማለትም (እስልምናን እስኪ ቀበሉ። )ባንተው ሰበብ የታወሩ አይኖች ሐቅን ለመመልከት ፣የደነቆሩ ጆሮዎች ሐቅን ለመስማት፣ የተዘጉ ልቦች ሐቅን ለመቀበል ይከፈታሉ" (ሰሂህ ቡኻሪይ 2018)፡፡
ማጠቃለያና ያልተጨመሩ ሃሳቦች ይቀጥላሉ።አላህ ካለ።
Join now. and share to all!
@only_islam1
https://t.me/joinchat/AAAAAE90idLYrtXA9FQl4g




اسلام عليكم ورحمت الله وبركاته.
بــــــــسم الله الرحمان الرحيم.

#ባይብል_አልተበረዘምን?
ክፍል 6

#እስላማዊ_እይታው

#ባይብል_በሃዲስ

ተቺዎች እስልምናን ለማጠልሸት ሃዲሶችን ይጠቀማሉ።በራሳቸው ይተረጉሙና እስልምናን ለማጠልሸት ይሞክራሉ።ይሄ ሃዲስ ደኢፍ/ደካማ(ተኣማኒነት የሌለው) ነው ሲባሉ ይተዉታል።ሰሂህ ከሆነ ግን…«መቼም ሃዲሱ ሰሂህ ነው፣ ውሸት ነው አትሉም»ይላሉ የሚያቀርቡት ትችት ከእውነት የራቀና በራሳቸው የተሮገሙት ያብራሩት ሆኖ ሳለ።

እንደዛ ካላችሁን እስቲ እነዚህም ሰሂህ ሀዲሶች ናቸው እንኩልኝ!👇
Abu Abdullah Muhammad Ibn Abdullah As-Saffar told us: Ahmad Ibn Mahdi Ibn
Rustum Al-Asfahani told us: Mu'azh Ibn Hisham Ad-Distwani told us: my father told me:Al-Qasim Ibn 'Awf Ash-Shaybani told me: Mu'azh Ibn Jabal - radiya Allahu 'anhu - told us that he went to Sham and saw the Christians prostrate to their Bishops and priests and saw the Jews prostrate to their Rabbis and scholars. He said, "Why do you do this?"they
answered, "This is the greeting of Prophets (peace be upon him)". I said, "We better do this to our Prophet". Allah's Prophet - salla Allahu 'alaihi wa sallam - said, "#They_lied about their
Prophets just as they #distorted_their_Book.

በአንድ ወቅት ሙዓዝ ኢብን
ጀበል ወደ ሻም ባቀናበት ወቅት ክርስቲያኖችና አይሁዶች ለቀሳውስቶቻቸው ሲሰግዱ በማየቱ ስለ ጉዳዩ ሲጠይቃቸው ‹‹ይህ የነብያት ሰላምታ ነው›› ብለው እንደመለሱለትና የአላህ መልእክተኛ ሀሳቡን ሲሰሙ እንዲህ ማለታቸውን ይገልጻል፡፡
‹‹ በነብያቶቻቸው ላይ ዋሹ.! ልክ
#መጽሃፍቶቻቸውን _እንደበረዙት››

📚(ሙስነድ አህመድ ጥራዝ 4 ገጽ 381 በተጨማሪም አጦበራኒ
አልሙዓጀም አልከቢር ጥራዝ 8 ገጽ 31 በተመሳሳይ ይህ ሀዲስ በኢብን ሀጀር አል ሀይተሚ ‹‹መጅመዓ ዛዋዲ›› ጥራዝ 4 ገጽ 312 ሰሂህ ተብሏል፡፡
በዚህ ሀዲስ በግልጽ
እንደምንመለከተው አይሁዶችና ክርስቲያኖች መፃህፍቱን ከመበረዝ አልፈው መለኮታዊ ትእዛዝ ያላገኙትን መጤ መመሪያ ሳይቀር እየቀጠፉ ያስተምሩ እንደ ነበረ ነው።
ይህንን ሀዲስ ይበልጥ የአላህ መልዕክተኛ በሌላ ቦታ እንዲህ ያብራሩልናል።⬇️
‹‹በኒ ኢስራኢሎች የራሳቸውን መጽሀፍ ጽፈው #እሱን መከተል ጀመሩ #ተውራትንም_ተውት››
📚(ሀዲሱ በአልጦበራኒ አል ሙዓጀም አል አውሰጥ የተዘገበ ሲሆን ሸይኽ ነስሩዲን አልባኒ በሲልሲላ አልሀዲስ አሰሂህ ሀዲስ ቁጥር 2832 ሀዲሱን #ሰሂህ_ብለውታል፡፡
በሌላ ቦታም የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ይላሉ
‹‹በኒ እራኤሎች በጊዜያት ሂደት ልቦቻቸው ደረቁ #ከራሳቸውም_መጽሀፍትን
መፈጣጠር ጀመሩ››

📚በይሀቂ ሹዑቡል ኢማን ጥራዝ 2 ቁጥር 439 ይህንን ሀዲስ ሸይኽ ነስሩዲን አልባኒ በሲልሲላ
አልሀዲስ አሰሂህ ሀዲስ ቁጥር 2694 ላይ ሀዲሱን #ሰሂህ ብለውታል፡፡
ከላይ የተገለፁት ንግግሮች የሼኽ አሊያም ደግሞ የተራ ሰው ንግግር አይደሉም። #የነብያችን_እንጂ!

አይሁዳውያን ዝሙት የፈጸሙ ወንድና ሴትን ፍርድ ይሰጧቸው ዘንድ ወደ ረሱል (ሰዐወ) ዘንድ
መጡ፡፡ እሳቸውም ከነሱ ውስጥ ጥልቅ የኦሪት እውቀት ያለውን ሰው እንዲያመጡላቸው አዘዙ
ሰዎችም በተባለው መሰረት ይዘው መጡ የአላህ መልዕክተኛም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ዝሙት የፈጸመ ሰው በእነሱ ህግ ቅጣቱ ምን እንደሆነ ጠየቋቸው እነሱም #አራት ክስተቱ ሲፈጸም #ያስተዋሉ ሰዎች ቀርበው ከመሰከሩ ዝሙተኞቹ ይወገራሉ አሉ፡፡ እሳቸውም ታዲያ ይህንን ህግ ከመተግበር ምን
እንዳቆማቸው ሲጠይቋቸው ንግስናቸው እንደተገፈፈና በተጨማሪም ግድያን እንደሚጠሉ ተናገሩ፡፡
📚ሙሉ ሀዲሱ ሱነን አቢ ዳወድ ሀዲስ ቁጥር 3862 ላይ ይገኛል ሸይኽ አልባኒ በሱነን አቡዳውድ 4452 ላይ ያለውን ተመሳሳይ ሀዲስ መሰረት አድረገው ሀዲሱ #ሰሂህ ነው ብለዋል፡፡

ይህ ህግ በኦሪት ዘሌ 20:10 ላይ ይገኛል፡፡
ነገር ግን አንቀጹ ዝሙተኞቹ መወገር እንዳለባቸው ይገልጻል እንጅ #ስለዓይን_ምስክሮች
አያወራም፡፡ ስለዚህም የአሁኑ ኦሪት የመበረዝ እክል አጋጥሞታል ማለት ነው።

በተጨማሪም

Do you bear witness that I am the Messenger of Allah? He said: No. The
Prophet peace be upon him said: Do you read the Torah?/ተውራት(ለሙሴ የወረደለት ኦሪት?) He replied back: Yes.Then the Prophet peace be upon him asked: and the Gospel?ኢንጂል(የእየሱስ ወንጌል?) The man replied:Yes. The Prophet peace be upon him then
asked: The Qur'an? The man replied back:No. The Prophet peace be upon him replied back: By He Whose Hand my soul
lies, if I willed I would read it. Then the Prophet peace be upon him pulled the
man and asked: Don't you find me in the Torah and Gospel? The man replied back and said: We #find someone who is similar to you and your Ummah (community) and from the place where you were brought up and we were hoping that you would be from amongst us.When you rose up (as a Prophet) we were afraid that it would be you.However, we looked and saw that it
wasn't you. The Prophet peace be upon him replied back asking: Why is that? The man said: From him will be 70,000 of his
followers from his community who will have no judgment passed on them nor punishment but you have a simple number of men following you. The
Prophet peace be upon him replied back:By He Whose Hand my soul lies it is me and it is referring to my Ummah (community). And they are more than 70
,70 thousand, 70 thousand

ሃዲሱ በአጭሩ…በወንጌልና በኦሪት ውስጥ 70000 ተከታይ ገነትን/ጀነትን ያለምንም ምርመራና ቅጣት ስለሚገቡ የነብይ ተከታይ ባልደረቦች ነው የሚያወራው።እስቲ ይህንን ማን ነው ከአሁኑ ባይብል የሚያሳይ?
ከሌለ ተበርዟል ማለት ነው።
📚(ሀዲሱ ሸይኽ አልባኒ በሰሂህ አል ሙዋሪድ ሀዲስ ቁጥር 1765 #ሰሂህ ብለውታል)፡፡

አላህ ካለ ይቀጥላል።👇
#በነብዩ_ባልደረባዎች/ሰሃ


اسلام عليكم ورحمت الله وبركاته
بــــــــسم الله الرحمان الرحيم

#ባይብል_አልተበረዘምን?
ክፍል 5

#እስላማዊ_እይታው

#ባይብል_በቁርአን

2:79 ‹‹ለነዚያም መጽሐፉን #በእጆቻቸው_ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ
እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት (ኃጢኣት)ወዮላቸው፡፡››

2:146
«እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ወንዶች ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ (ሙሐመድን) ያውቁታል፡፡ ከነሱም የተለዩ ክፍሎች እነርሱ #የሚያወቁ ሲኾኑ #እውነቱን በእርግጥ #ይደብቃሉ፡፡
2:159
እነዚያ ከአንቀጾችና ከቅን መምሪያ #ያወረድነውን ለሰዎች በመጽሐፉ ከገለጽነው በኋላ የሚደብቁ፤ እነዚያ አላህ ይረግማቸዋል፤ ረጋሚዎችም ሁሉ ይረግሟቸዋል።

2:174
«እነዚያ አላህ ከመጽሐፍ ያወረደውን #የሚደብቁ በርሱም (በመደበቃቸው) ጥቂትን ዋጋ የሚገዙ እነዚያ በሆዶቻቸው ውስጥ እሳትን እንጂ አይበሉም…»

📌አንዳንድ ክርስቲያኖች ይህ አንቀጽ ሲቀርብላቸው አንቀጹ ሁሉንም አይሁዶች የሚመለከት ሳይሆን #ጥቂት አይሁዶችን ብቻ ግብ ያደረገ መልዕክት እንደሆነ ቁርዓን አጣቅሰው ለመሞገት ይሞክራሉ፡፡የሚያቀርቧቸው የቁርዓን አንቀጾችም👇
3:113 እና

3:199‹‹ከመጽሐፉም ባለቤቶች ለአላህ ፈሪዎች በአላህ አንቀጾችም ጥቂትን ዋጋ የማይለወጡ ሲኾኑ በአላህና በዚያ ወደ እናንተ በተወረደው በዚያም ወደእነርሱ በተወረደው የሚያምኑ ሰዎች አልሉ፡፡ እነዚያ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ አላህ ምርመራው ፈጣን ነው፡፡››

3:113 የሚያወራው በነብዩ
ሙሀመድ ሰላም ይስፈንባቸውና ስላመኑ አይሁዳውያን ሲሆን
እነዚህ አይሁዳውያን በቁርዓን አምነው ሌሊት የሚያነቡ ህዝቦች ናቸው (ተፍሲር ኢብን ከሲር ለአንቀጹ የሰጡት ማብራሪያ)
ሁለተኛው የቁርዓን አንቀጽ የሚያወራው ደግሞ በነብዩ ሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ነብይነት ስላመኑ አይሁዳውያን ሲሆን እነዚህ አይሁዳውያን በመጽሀፋቸው ውስጥ ስለ
ነብዩ ሙሃመድ ነብይነት የተገለጹ እውነታዎችን ለቁሳዊ ጥቅም ብለው የሚደብቁ ያልሆኑእውነተኛ አማኞች ናቸው (ተፍሲር ኢብን ከሲር እንዲሁም ተፍሲር ጀላለይን ለአንቀጹ የሰጡት ማብራሪያ)
🖌
ሁሉም የአለማችን አይሁድና ክርስቲያን ተሰባስቦ ፈጽሞታል ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ለዚህ ሀላፍትና የወሰዱ ሰዎች (ሊቃውንት) ተግባሩን ከፈጸሙትና
መጽሀፉን ካዛቡት አማኙም በጭፍን እየተከተለ ነውና በእጃቸው ያለው መጽሀፍ እንደተበረዘ ይህንን እራሳቸው እንደፈጸሙት በጥቅሉ ይገልፃል።
2:146 «…ከነሱም #የተለዩ_ክፍሎች…» የሚለውን ማስተዋል ያስፈልጋል።

📌አንዳንድ ሰዎች አይሁዳውያኑ መጽሀፍ በእጆቻቸው እየጻፉ ይህ ከአምላክ ነው የሚሉት መጽሀፍ "ቅዱስን" ሳይሆን ታልሙዳቸውን ነው ሲሉ ይከራከራሉ ይህ ግን የሚያስኬድ አይደለም። ምክንያቱም አይሁዳውያን በየትኛውምጊዜያት
#ታልሙድ_የአምላክ_ቃል_ነው ብለው አያውቁም፡፡ ይህንን አስመልክቶ እውቁ የታልሙድ ምሁር ራችሜል ፈሬይድላንድ እንዲህ ይላል👇
‹‹ እኛ (አይሁዶች) ታልሙድ በሩዋች ሀ ኮዳሽ (መንፈስ ቅዱስ) መሪነት የተጻፈ ነው ብለን
አናምንም፡፡ ታልሙድም እራሱ የአምላክ ቃል ነኝ #አይልም ከዛ ይልቅ ታለሙድ የቶራህ (ኦሪት)
#ማብራሪያና _ትርጓሜ ነው፡፡››
http://therefinersfire.org/talmud_proves_m
essiah.htm+jews+claim+the+talmud+is+fro
m+god&hl=en&ct=clnk&cd=10&gl=ae)

4:157«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ፡፡እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ (መገደል)በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን
ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም፡፡»

ስቅለትን አስመልክቶ ክርስቲያኖች የያዙት አቋም የተዛባና በጥርጣሬ የታጀበ ነው፡፡ ክርስቲያኖች ደግሞ
ለዚህ እሳቤያቸው መረጃየሆኗቸው የወንጌል አናቅጾች ናቸው፡፡ እነዚህ ደግሞ ፍጹም ስህተትና የተበረዘ አመለካከት እንደሆነ ቁርኣን ግልጽ በሆነ መንገድ አስቀመጠ፡፡
ክርስቲያኖች ስቅለትንአስመልክቶ
ማስረጃቸው በእጃቸው ያሉ ወንጌሎች ሲሆኑ እነዚህ አመለካከቶች ስህተት እንደሆኑ ቁርዓን ይገልፃል ይህም ለስቅለት የሚቀርቡ የወንጌል አንጾች የተበረዙና ትክክል አለመሆናቸው ነው፡፡
48:29
مُّحَمَّدٌ رَّسُولُ ٱللَّهِ…
የአላህ መልክተኛ ሙሐመድ እነዚያም ከእርሱ ጋር ያሉት (ወዳጆቹ) በከሓዲዎቹ ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው፡፡ አጎንባሾች፣ ሰጋጆች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ ከአላህ ችሮታንና ውዴታን ይፈልጋሉ፡፡ ምልክታቸው ከስግደታቸው ፈለግ ስትኾን በፊቶቻቸው ላይ ናት፡፡ ይህ በተውራት (የተነገረው) ጠባያቸው ነው፡፡ በኢንጂልም ውስጥ ምሳሌያቸው ቀንዘሉን አንደአወጣ አዝመራና፣ (ቀንዘሉ) እንዳበረታው፣ እንደወፈረምና፣ ገበሬዎቹን የሚያስደንቅ ኾኖ በአገዳዎቹ ላይ ተስተካክሎ እንደ ቆመ (አዝመራ) ነው፡፡ (ያበረታቸውና ያበዛቸው) ከሓዲዎችን በእነርሱ ሊያስቆጭ ነው፡፡ አላህም እነዚያን ያመኑትንና ከእነርሱ በጎዎችን የሠሩትን ምሕረትንና ታላቅ ምንዳን ተስፋ አድርጎላቸዋል፡፡

የነብዩ ሰሃቦችን ባህሪ በኦሪትና በወንጌል የሚያሳይ ሰው አለ?🙄😳የለም!።
አያቹ #ተበርዟል ማለት ነው።
📌በመጨረሻም የምንረዳው የአሁኑ ወንጌልና ኦሪት ከትክክለኛው የኢንጂልና ተውራት ትምህርት የተቃረኑ አመለካከቶችን እንደያዙና እነዚህ ትምህርቶች ደግሞ መጤ የብረዛ ውጤቶች መሆናቸውን ነው።

አላህ ካለ
ይቀጥላል። 👉#በሃዲስ_ እይታ

Join now. and share to all!

ሊንኩ ይኸው
https://t.me/joinchat/AAAAAE90idLYrtXA9FQl4g
اسلام عليكم ورحمت الله وبركاته.


#ባይብል_አልተበረዘምን?
ክፍል 4

#እስላማዉ_እይታው👇

#ባይብል_በቁርአን

ክርስቲያኖች ‹‹ቁርዓን መጽሀፍ
"ቅዱስ"ን እውነተኛ ይለዋል›› የሚል ሃሳብ ያቀርባሉ ተያይዞ ደግሞ የሚቀርበው ‹‹መጽሀፍ "ቅዱስ" ስለ መበረዙ ቁርዓንም ሆነ ሀዲስ እንዲሁም ኢስላማዊ
ምንጮች የሚሰጡት ፍንጭ የለም›› የሚለው ነው፡፡

የመጀመሪያውን አስመልክቶ ባይብል ትክክለኛ ለመሆኑ ኢስላም ይናገራል የሚለው
(በርግጥ የትኛው መጽሀፍ "ቅዱስ" ለማለት እንደፈለጉ አይታወቅም። የኦርቶዶክስ 80 አሀዱ አልያም የካቶሊኮች 73
ወይንም የፕሮቴስታንቶች
66 መጽሀፍ የትኛውን እንደሆነ አይታወቅም ይህ ግን የሚወሰነው እንደምትወያዩት ሰው ማንነት ነው) የተሳሳተ ምልከታ ነው፡፡ ክርስቲያኖች በአንድ ወቅት ‹‹መጽሀፍ "ቅዱስ"›› የተባለ ጥራዝ እንደነበርና ከጊዜያት በኋላ እንደተበረዘ ፣እንደምናምን ያስባሉ ይህ ግን የተሳሳተ አረዳድ ነው፡፡ ቁርዓን ከጅማሮው ‹‹መጽሀፍ "ቅዱስ"››ስለሚባለው ጥራዝ አያወራም፡፡የቆሮንቶስ፤ የማቴዎስ
የሮሜ ወዘተ የሚባሉ ኦሪጅናል መለኮታዊ መጽሀፍት ኖረው ኋላ ተበረዙ የሚል እምነት የለንም፤ መጀመሪያውኑ እነዚህ መጽሀፍት #የግለሰብ_ድርሳናት እንጅ #መለኮታዊ_አልነበሩም፤
ተያይዞ የሚነሳው ‹‹ታዲያ በየትኞቹ ነው የምታምኑት›› የሚለው ነው፡፡
👇
እኛ ሙስሊሞች ለሙሳ በወረደለት ተውራት (ኦሪት) ፤
ለዳውድ በወረደለት ዘቡር (መዝሙር)
እንዲሁም ለኢሳ በተወረደለት ኢንጅል (ወንጌል) እናምናለን፡፡

እነዚህ መለኮታዊ መጽሀፍት አሁን ክርስቲያኖች ‹‹መጽሀፍ ቅዱስ›› ብለው በሰየሙት መጽሀፍ ውስጥ የሚፈልጉትን መርጠው ያካተቷቸው ቢሆንም
ኦሪጅናልነታቸውን አጥተው የሰው እጅ ገብቶባቸዋል፡፡ ጥቂት ከብረዛ የተረፉ መለኮታዊ ቅሪቶች ቢኖሩም በይዘት ደረጃ ግን ጥቅል በሚባል አገላለጽ የተበረዙ ናቸው፡፡
ኦሪጅናሉን ከተበረዘው ለይተን የምናውቅበትን መፅሃፍ ከሺ አመታት በፊት ወርዶልናል።
አዎ ቁርአን በባህሪው ያለፉትን መለኮታዊ መፅሃፍት የያዙትን እውነት የሚገልፅ የተበረዘውን ከእውነቱ የሚለይ አረጋጋጭና ተጠባባቂ መፅሃፍ ነው።

ያለፉት መለኮታዊ መፅሃፍቶች ጊዜያቸውን ጨርሰው በቁርአን ኪዳን ዘግተውታል።
ልክ…
«ፀሃዮዋ ወጥታለች ኩራዝህን አጥፋ»እንደተባለው።
Quran
👉 #The_last_testment👈
በአጠቃላይ ቁርአን ላይ ኢንጂል ፣ዘቡር፣ተውራት ብሎ ሲያወራ አንድናአንድ የሚያመለክተው ከላይ የወረዱትን ነው።
- «…ለዳውድም ዘቡርን #ሰጠነው፡፡»4፡163
«…ተውራትና እንጂልንም #አውርዷል»3:3
📌ለነማቴዎስ ሉቃስ… ወዘተ ከላይ #አልወረደላቸውም_ከታች በራሳቸው ነው የፃፉት።

"ተህሪፍ"
2- የአረብኛ ‹‹ተህሪፍ›› አገላለጽ
ይህ ተህሪፍ የሚለው ቃል ቁርዓን ውስጥ በይበልጥ አይሁዶችና ክርስቲያኖች መጽሀፋቸውን
እንደበረዙ በሚያትቱ ቦታዎች ውስጥ አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ ‹‹ተህሪፍ›› የሚለው ቃል ‹‹ብዕርን
በመጠቀም አንድን ቃል ወደ ሆነ አቅጣጫ #ማዘመም_(መቀየር)›› እንዲሁም ‹‹#ለራስ_ስሜት
በሚመች መልኩ ቃላትን #መጠምዘዝ›› የሚሉ
ፍችዎች አሉት፡፡
(አርረጊብ አለኢስፈሃኒ፣
አልሙፋራዳት ፊ ገሪቢል ቁርዓን ጥራዝ 1 ገጽ 122)

በተመሳሳይ አሸህራሳታኒ ስለተህሪፍ ምንነት
ሲገልጹ ‹‹የተጻፈን ቃል #የተዛባ_ትርጉም ይሰጥ
ዘንድ መቀየር›› በሚል ያስቀምጡታል፡፡ ይህን
አገላለጽ ሸይሁል ኢስላም ኢብን ተይሚያ እቅቲዳአ ሲራጠል ሙስተቂም ሙኻለፈት
አስሀበል ጃሂም ገጽ 8 ላይ በመግለፅ ይጋሩታል፡፡⬇️

‹‹በቋንቋ ደረጃ - መለወጥ ወይንም #ማዛባት የሚል
ፍቺ ሲኖረው ቴክኒካል ፍችው ደግሞ ጹሁፍን በቃልም ይሁን በትርጉም ደረጃ #መቀየር የሚል
ነው››
📚 (Shaikh ul-Islaam Ibn Taymiyyah,
Creed of Hamawiyyah - Chapter 3: The
Way of Ahl us-Sunnah Concerning
Allaah's Attributes
ስለዚህም በዚህ ተህሪፍ በሚለው አገላለጽ ቁርዓን በግልጽ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ቅዱሳን
መጽሀፍትን በጹሁፍ ደረጃ ሳይቀር
መልእክታቸውን ያዛቡ እንደነበር ጠቁሞናል፡፡
ይህን አስመልክቶ የኢማሙ ማሊክን ሙወጣዕ
በተነተነበት ድርሳኑ አልባጂ እንዲህ ያብራራዋል፡፡
‹‹ እነሱ (አይሁዶች) ቃላትን አላህ ካስቀመጠበት ቦታ ውጭ #ይለውጡ ነበር በዚህም አሰላሙ አለይኩም (ሰላም በናንተ ላይ ይሁን) ማለት ሲገባቸው/ ሲኖርባቸው አሳሙ አለይኩም (ሞት በናንተ ላይ ይሁን) ይሉ ነበር››
📚 አል ሙንተቃ ሸርህ ሙወጣዕ
ማሊክ፣ ኪታብ አል ጃሚዕ ባብ ማጃዐ ፊ አሰላም አለል የሁዲ ወነስራኒ ለሀዲስ ቁጥር 1514
የተሠጠው ማብራሪያ
አል ባጂ በዚህ ማብራሪያቸው እንደሚገልጹት
አይሁዶች ‹‹አሰላሙ አለይኩም›› በሚለው ፈንታ
‹‹አሳሙ አለይኩም›› የሚለውን ቃል በመጠቀም ትርጉሙን ብቻ ሳይሆን ቃሉንም ይቀይሩ እንደነበር ነው፡፡ ከዚህም እንደምንረዳው ይቀይሩ የነበሩት ትርጓሜ ብቻ ሳይሆን ቃልንም ጭምር እንደሆነ ነው፡፡
ይጥላል።
Join now. and share to all!

ሊንኩ ይኸው
https://t.me/joinchat/AAAAAE90idLYrtXA9FQl4g


#ባይብል_አልተበረዘምን?
ክፍል 3

ኦሪ, ዘፍ 11፡10-26
የ 1954 እትም ላይ የሴም ትውልድ ይህ ነው ብሎ ይዘረዝራል።
ሴም―አርፋክስድ―ቃየን―ሳላን―
ዔቦር―ፋሌቅን―ራግው―ሴሮሕ―
ናኮር―ታራ―አብራም―ናኮር―
ሓራን
በ1980 እትም ላይ ደግሞ
ሴም―አርፋክስድ―ሼላሕ―ዔቦር―ፌሌግ―ረኡን―ሰሩግ―ናኮር―ታራ―አብራም―ናኮር―ሐራን።

በ1954 እትም ላይ
ታራ ሲወለድ ናኮር እድሜው 109 አመት ነበር
#Vs
በ1980 እትም ግን 29 ይላል።
በ54 ቱ እትም
ታራ ከተወለደ በኃላ ናኮር የኖረው 129 አመት ነበር።
#Vs
በ80 ው እትም ግን 119ነው የሚለው።
በ54 ቱ እትም ናኮር የሞተው 109+129=በ238 አመት ነበር
#Vs
በ80 እትም 29+119=148 አመት ነበር
በ54 ቱ እትም ታራ #ከ100 አመት በኃላ አብራምን ናኮርንና ሃራን ወለደ።
#Vs
በ80 ው እትም ታራ #ከ70 አመት በኃላ አብራምን ናኮርንና ሐራንን ወለደ።

ኦሪት ዘፍ 5:1–23
በ1954እትም ላይ
1⃣አዳም ሴት የሚባል ወንድ ልጅ ሲወልድ እድሜው #230 ነበረ።
2⃣ሴትን ከወለደ በኃላ #700 አመት ኖረ።
3⃣ሴት ሄኖስ ሲወለደ #205 አመቱ ነበር።
4⃣ከሄኖስ ከተወለደ በኃላ ሴት #707 አመት ኖረ።
5⃣ሄኖስ ቃይናን ሲወልድ #190 አመቱ ነበረ።
6⃣ቃይናን ከተወለደ በኃላ ሄኖስ #715 አመት ኖረ።
7⃣ቃይናን መላልኤል ሲወለድ #170 አመቱ ነበረ።
8⃣መላልኤል ከተወለደ በኃላ ቃይናን #740 አመት ነበር የኖረው።
9⃣መላልኤል ያሬድ ሲወለድ እድሜው #165 አመት ነበር፡፡
🔟ያሬድ ከተወለደ በኃላ
መላልኤል የኖረው #730 አመት ነበር፡፡
1⃣1⃣ማቱሳላ ሲወለድ ሄኖክ እድሜው #165 አመት ነበር፡፡
1⃣2⃣ማቱሳላ ከተወለደ በኃላ ሄኖክ የኖረው #200 አመት ነበር፡፡
ይላል።
በትልቁ VS እንልና የ1980ውን እትም ገልፀን ስንመለከተው ከድንጋጤ የተነሳ እንደ ቶምኤንድ ጄሪ አይን ፍ…ጥ…ጥ👀…
በሃቀኝነት ቁጥራቸው ሲቀመጥ ይህን ይመስላል⬇️
1⃣ኛው ላይ #130
2⃣ኛው ላይ #800
3⃣ኛው ላይ #105
4⃣ኛው ላይ #807
5⃣ኛው ላይ #90
6⃣ኛው ላይ #815
7⃣ኛው ላይ #70
8⃣ኛው ላይ #840
9⃣ኛው ላይ #65
🔟ኛው ላይ #830
1⃣1⃣ኛው ላይ #65
1⃣2⃣ኛው ላይ #300
በሚል አስቀምጦታል።

እንዲሁም ባይብልብ በየጊዚው እንደ አስፈላጊነቱና አመቺነቱ እንደሚቀይሩት እንመልከት፡-
«ንቁ» “awake” በመባል የሚታወቀው ወርሃዊ የይሕዋ ምስክሮች መጽሔት ላይ «ተወዳጅነትን
ያገኘ መጽሃፌ "ቅዱስ"?» በሚል ርእስ ስር የሚከተለውን አስፍሯል፡-
«ምእመናን ስለ ሦስተኛው አለም የእዳ ጫና፤ ስለ ፍትሃዊ ንግድና ስለ መሳሰለት ጉዳዮች እንዲያስቡ ለማድረግ ሲባል ከመጽሃፍ "ቅዱስ" የተውጣጡ ጸሎቶችንና መዝሙራት በሚገኙበት የእንግሊዛ ቤተ ክርስቲያን የጸሎት መፅሃፍ ላይ ብዙ ለውጥ ተደርጓል ሲል ሮይተርስ የተባለው የዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡ የ ፖኬት ፕሬይስ ፎር ፒስ ኤንድ ጀስቲስ
የተባለው መጽሃፍ በጌታ ጸሎት ላይ የሚገኘውን «የእለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን» የሚለውን
የኢየሱስ ቃል
«መሬታችንን መልሰን ስናገኝ ወይም የተሻለ ደመወዛ ማግኘት ስንችል የእለት እንጀራችንን ሰጠኸን ማለት ነው» በሚል
ቃል ለውጦታል። በተመሳሳይ «በሞት ሸለቆ ጥላ ውስጥ፤ ብንሄዴ እንኳ» የሚለውን የመዛሙር 23 ቃል እንዲወጣ ተደርጎ «ድብልቅልቅ ያለ ጠብና ብጥብጥ ቢነሳ እንኳን አንፈራም» በሚል ቃል ተተክቷል፡፡»

🖌 /ምንጭ፡- «ንቁ» ሰኔ 2005
የይሖዋ ምስክሮች ወርሃዊ መጽሔት/

ይቀጥላል።

Join now.and share to all!

ሊንኩ ይኸው
https://t.me/joinchat/AAAAAE90idLYrtXA9FQl4g


#ባይብል_አልተበረዘምን?
ክፍል 2

ሌላው ትተን እንኳ የ 1954 እና የ1980 ዓ.ም መጽሃፍ ቅዱስ እትሞች ውስጥ ካሉ ልዩነቶችን የተወሰኑትን እናንሳና እንመልከት
☞ኦሪት ዘዳግም 18፡18 የ 1954
እትም “ #ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነብይ
አስነሳላቸዋለሁ፡፡”
#Vs
☞ኦሪት ዘዳግም 18፡18 የ 1980
እትም ደግሞ“ ስለዚህ እንደ አንተ ያለ ነብይ #ከህዝቦቻቸው መካከል
አስነሳላቸዋለሁ፡፡”

☞“ #ከህዝቦቻቸው_መካከል” ወደሚለው መቀየር ያስፈለገው አንድና አንድ ይህን አንቀፅ ሙስሊሞች ለነብዩ የተነገረ ትንቢት ነው እያሉ ብዙዎችን ሲመሩ ስላዩ ነው።

የዮሀንስ ወንጌል 8፡40
የ 1954 እትም የሚለው“ እውነት የነገርኳችሁን #ሰው
ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ?”
#VS
የዮሀንስ ወንጌል 8፡40 የ 1980
እትም ላይ ደግሞ የሚለው“ እውነት ነገርኳችሁ እናንተ ግን ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ?”
“ #ሰው” የሚለው ቃል የኋላኋላ
ለምን እንዲወጣ ተደረገ ?
እየሱስ ራሱን ሰው ብሏል እንዳይባል❗️

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች1 ፥ 3 በግሪክኛ፡ “Εὐλογητὸς ὁ θεὸς καὶ πατὴρ τοῦ κυρίου ἡμῶν Ἰησοῦ Χριστοῦ ὁ πατὴρ τῶνοἰκτιρμῶν
καὶ θεὸς πάσης παρακλήσεως”
ቀጥተኛ (ቃል-በቃል) ትርጉም፡ ☞”ይባረክ ያ አምላክ እና አባት፤
የጌታ የኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ያ አባት የ ርህራሄ እና አምላክ የሁሉ መጽናናት”
1879፡ እትም”
#VS
እግዚአብሔር ይመስገን የጌታችን የየሱስ ክርስቶስ አባት የምህረት አባት የመጽናናትም አምላክ።”
1954፡ እትም”
#VS
የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ
ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።”
(1980፡እትም “)
#Vs
የምህረት አባትና የመጽናናት ሁሉ አምላክ ለሁነውና እንዲሁም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ለሆነው አምላክ ምስጋና ይሁን” –
የግርጌ ማስታወሻ ”

አዲስ ኪዳን በተጻፈበት በግሪክኛው ቋንቋ ‘የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይመስገን’ ይላል” ይላል።
(አ.መ.ት፡እትም)
“የርኅራኄ አባት፣ የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።”
(1984፡ እትም)
#Vs
“የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ
ክርስቶስ አባት ይባረክ።” –
(የግርጌ ማስታወሻ ላይ”)
በግሪኩ ‘የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት’ ይላል”

ግሪክኛውን በትክክል ያስቀመጠው የቱ ነው? በግልጽ ማየት እንደሚቻለው 1954ቱ እና አ.መ.ት በትክክል አስቀምጠውታል።
የ1879ኙ ፣ የ1980ው እና 1984ቱ ግን በግሪኩ ውስጥ የተጠቀሱ ሁለትአምላክ የሚሉ ቃላት ቢኖሩም አንዱን #አጥፍተውታል፤ በዚህም ለቃሉ
ታማኝ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
(ተመሳሳይ የሆኑትን ጥቅሶች
ኤፌሶን 1፡3፣ እና 1 ጴጥሮስ 1፡3 ተመልከቱ)

ሌላም ጥቅስ እንቀጥል
ራዕይ 14፡1 ላይ “የበጉ ሥምና የአባቱ ሥም ” የሚለውን ሁሉም የአማርኛ
መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ግሪክኛው በሚያስቀምጠው መልክ ሲያስቀምጡ የ1984ቱ ግን “የመንፈስ ቅዱስም ሥም” የሚል ሃረግ
ጨምሯል። ለምን?
#VS
የ1879ኙ ደግሞ በተቃራኒው “የበጉ ሥምና” የሚለውን ሃረግ አውጥቶ ጥሏል።

ኤፌሶን 1፡3፣ 17 ላይ “የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ…” የሚሉ ቃላትን
ግሪክኛው ቢጠቀምም
#VS
የ1879ኙ “አምላክ” የሚለውን “አባት ” በሚል ያለምንም ማብራሪያ አልፎታል። ለምን?
#VS
የ1980 ው “አምላክ” የሚለውን “አባት ” በሚል ተክቶ በግርጌ
ማስታወሻው “አምላክ” መባል እንዳለበት ጠቅሶ አልፏል።

የዮሀንስ ወንጌል 3፡18 የ 1954
እትም “ #አሁን ተፈርዶበታል”
#Vs
… የዮሀንስ ወንጌል 3፡18
የ 1980 እትም ደግሞ “ ገና #ድሮ ተፈርዶበታል”።

«አሁንን»እና «ድሮን» ማን አንድ አደረጋቸው?

የሐዋርያት ስራ 2፡22 የ 1954
እትም “ ከእግዚአብሄር ዘንድ
ለእናንተ የተገለጠ #ሰው ነበር” ይላል።
#VS
የሐዋርያት ስራ 2፡22 የ 1980
እትም ደግሞ “ ከእግዚአብሄር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠው #መለኮታዊ_ስልጣን ያለው ነው፡፡
አሁንም የኋለኛው እትም ላይ
ፍጥጥ ያለ ብረዛ😳

ይቀጥላል።
ጆይን ሼር👇

https://t.me/joinchat/AAAAAE90idLYrtXA9FQl4g


#ባይብል_አልተበረዘምን?
ክፍል 1

የኢትዮጲያ መፅሀፍ ቅዱስ ኢትዮጵያ ውስጥ ስንት ጊዜ
እንደተሻሻለ እና የሌለውን ጥቅስ በራሳቸው እንደጨመሩ ራሳቸው ይናገራሉ።👇

መቅድሙ ባይብል እንዴት እንደተዘጋጀ ሲናገር፡-
«በ1966 "ዓ.ም" መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያ መፅሃፍ "ቅዱስ" ማሕበር በአንድነት ሰብስቧቸው የነበሩ የአብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች ስለአማርኛ መፅሃፍ "ቅዱስ" አዲስ ትርጉም አስፈላጊነት ባስረዳበት ጊዚ ሁከት አማራጭ አሳቦች ቀርበው ነበር፤ አንደኛው አሳብ
በ1954 ዒ.ም የታተመው የአማርኛ መፅሃፍ "ቅዱስ"
#እንዲታረምና_እንዲሻሻል
ይደረግ የሚል ሲሆን ሁለተኛው አሳብ የተሻሻለው ማንንም ሊያስደስት ስለማይችል አዲስ ትርጉም ቢዘጋጅ ይሻላል የሚሌ ነበር፡፡»
/ቀለል ባለ አማርኛ 1980 እትም መቅድም የተወሰደ/
የሚታረመውና የሚሻሻለው የማን ቃል ነው? የአማልክታቹ?😳

ባይብል እራሱ እንደሚበረዝ እንደሚከለስ ይናገራል።
☞«እናንተስ። ጥበበኞች ነን የእግዚአብሔርም ሕግ ከእኛ ጋር ነው እንዴትትላላችሁ ?እነሆ፥ የጸሐፊ ብርዕ ሐሰተኛ ነው በሐሰትም አድርጎአል ።»
( ትንቢተ ኤርምያስ 8:8 )
☞ «ከሞትሁ በኋላ ፈጽማችሁ እንድትረክሱ፥ ካዘዝኋችሁም መንገድ ፈቀቅእንድትሉ አውቃለሁና። በእጃችሁም ሥራ ታስቈጡት ዘንድበእግዚአብሔር ፊት ክፉ ስላደረጋችሁ በኋለኛው ዘመን ክፉ ነገርያገኛችኋል።፣»
(ዘዳግም 31:29)

ኦሪት ዘዳግም 4: 2 እግዛብሄር እንዲህ ይላል
2፤ እኔ ያዘዝኋችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ
ትጠብቃላችሁ እንጂ ባዘዝኋችሁ ቃል ላይ አትጨምሩም፥ ከእርሱም
አታጎድሉም።
☞የሠራዊትን ጌታ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ”የሕያውንአምላክ
ቃል ለውጣችኋልና”
(ኤርምያስ 23፥36 )

በቅዱስ፣ቁርአን 2:77-79 ላይ ደግሞ እንዲህ ይላል ፦ “ለእነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉናከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት ይህ ከአላህ ዘንድ ነው ለሚሉ ወዮላቸው፤…. “ ይለናል።
(ቁርአን 2:77-79)
እኛም ለዚሁ ነው መፅሐፍ ቅዱስ ተበርዟል፣ ተከልሷል ፣ የምንለው
እንዲሁ በደመነፍስ አይደለም።

ይቀጥላል።
ጆይን ሼር👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE90idLYrtXA9FQl4g


እንድንወዳቸው የሚፈልጉ ግን የሚጠሉን ካፊሮች ያነሱት ክስ👇
በአጭር በአጭር መልስ።
🖌ሳሂህ አል ቡኻሪ ቅ6 መ 60 ሀዲስ 402 የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ በጀነት ስልሳ ( 60 ) ማይል ያህል ያለው ሰፊ ክፍት የሆነ ከዙል የተሰራ ዳስ አለ በእያንዳንዱ መአዘን ላይ ሚስቶች የሚኖሩ ሲሆን እንዚህም ሴቶች በሌላኛ መዓዘን ላይ ያሉትን ሊያዩ የማይችሉ ናቸው ሙስሊሞችም ይጎበኟቸዋል ይደስቱባቸዋል።

🖌እዚህ ላይ እንደምንረዳው ሴቶች ባላቸውን ፍለጋ በየጥጋጥጉ ቆመው አብሯቸው "ወሲ*" የሚፈፅም ወንድ ለማግኘት በጥግ በማዓዘን ላይ ቆማ ትጠብቃለች ማለት ነው።
👉መልስ
#በየማእዘኑ የሚለውን በየጥጋጥጉ ብሎ መተርጎም ችግር ያመጣል።
#ቆመው የሚል የለም። እንዲያውም በጣም ውብ በሆነ ምንጣፍ ቁጭ ነው የሚሉት።
ከዚያም የጀነት ወንዶች ከነሱ ጋር ግዜ ያሳልፋሉ።ግንኙነት ማድረግ የፈለገ ያደርጋል።

🖌ለምንድን ነው ወንድ ፍለጋ ጥጋጥግ ላይ መቆምና መፈለግ ያስፈለጋት?????
👉መልስ
አልቆሙም ቁጭ ብለዋል።
በሴቶቹና በወንዶቹ መካከል አላህ መፋቀርን አድርጓል።

🖌ሙስሊሞችም ይጎበኟቸዋል ይደሰቱባቸዋል ይህ ነገር እንዴት ነው ሴቶችስ ሙስሊሞች አይደሉምን?
👉መልስ
ሴቶች ሙስሊም ናቸው።እንደውም በሃዲስ ላይ ነብያችን ከሁሉ ቀድማ ጀነት የገባችን ሴት አይተው ስለሷ ሲጠይቁ አባት አልባ ልጆችን በማሳደጓ ምክንያት ይህን ታላቅ እድል ማግኘቷ ተነግሯቸዋል።
ምናልባት ለምን ለሴቶች ወንድ አልተዘጋጀም ከሆነ…
ጀነት ውስጥ ነፍስ ያሻችው እንደሚሰጣት በቁርአንም በሃዲስም ተገልፇል።
Surah Qaf (ق), verses: 35
لَهُم مَّا يَشَآءُونَ فِيهَا وَلَدَيْنَا مَزِيدٌ
ለነርሱ በውስጧ ሲኾኑ #የሚሹት ሁሉ አልላቸው፡፡ እኛም ዘንድ ጭማሪ አልለ፡፡

ካስፈለጋት ይሰጣታል እናንተ የሴት ጠበቆች😏ድንቄም ጠበቃ!

🖌እስልምና የወንዶች ሃይማኖት ነው ማለት ነው?
👉መልስ
እራሳቹ ታውቁታላችሁ።
የሴቶችም የወንዶችም ነው።

20 last posts shown.

31

subscribers
Channel statistics