መሄድ መሄድ ብቻ
ሜዳው ጫካው ሁሉ
የብስና ባህሩ
ሩቅ የሚመስለው
ኦና አየር ጠፈሩ
ደቂቅ ትላትሉ
ነፋስ የገለበው
ረቂቅ ዐፈሩ
ሆኖ የተገኘው
ሁሉ ሁላ ሁሉ
መዳረሻ ሳይኖር
መንገድ ተበጅቶለት፣
ውጥኑ አይሰምር
ጉዞው አይበጅለት።
ይኖር እንደው ብለን
ሁሉን የፈጠረ፣
ባገኘው ባስገኘው መንገድ የሚመትር
ይኖር እንደው ብለን
'ከ... እስከ' ማይባል
ስፍር አልባ ቁጥር
ይኖር እንደው ብለን
አንድ እሱን ፍለጋ
ስንለፋ ስንታትር፣
እሱም ሌላ መንገድ
ጫፍ አልባ ቁልቁለት
ሞቱ ለትንሣኤ
ውልደቱ ለስቅለት፤
ሄደን ሄደን ሄደን
ፈልገን ብናጣው
የለም ላለማለት
ሽቶ አለማግኘትን
ፈልጎ ማጣትን
በእውነት ስም ልንዘጋው
"አለመገኘት ነው አምላክነት ጸጋው"
ብለን ተማምለን
በፍጥረት አንደበት 'ምንም' አሰኘነው
ባለመሆን በኩል ፈጣሪን ሸኘነው።
ሜዳው ጫካው ሁሉ
የብስና ባህሩ
ሩቅ የሚመስለው
ኦና አየር ጠፈሩ
ደቂቅ ትላትሉ
ነፋስ የገለበው
ረቂቅ ዐፈሩ
ሆኖ የተገኘው
ሁሉ ሁላ ሁሉ
መዳረሻ ሳይኖር
መንገድ ተበጅቶለት፣
ውጥኑ አይሰምር
ጉዞው አይበጅለት።
ይኖር እንደው ብለን
ሁሉን የፈጠረ፣
ባገኘው ባስገኘው መንገድ የሚመትር
ይኖር እንደው ብለን
'ከ... እስከ' ማይባል
ስፍር አልባ ቁጥር
ይኖር እንደው ብለን
አንድ እሱን ፍለጋ
ስንለፋ ስንታትር፣
እሱም ሌላ መንገድ
ጫፍ አልባ ቁልቁለት
ሞቱ ለትንሣኤ
ውልደቱ ለስቅለት፤
ሄደን ሄደን ሄደን
ፈልገን ብናጣው
የለም ላለማለት
ሽቶ አለማግኘትን
ፈልጎ ማጣትን
በእውነት ስም ልንዘጋው
"አለመገኘት ነው አምላክነት ጸጋው"
ብለን ተማምለን
በፍጥረት አንደበት 'ምንም' አሰኘነው
ባለመሆን በኩል ፈጣሪን ሸኘነው።