Footnotes in blue


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


What I read, what I hear at night, what crosses my mind when I’m not trying to be interesting.
Jazz, philosophy, reflect

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ለይላ ጋር ሄድኩ አንዷን ኬክ አገኘው😊 ስሚ ቆንጅዬ አልኳት ...ትስቃለች ያው ወዬ ማለት ነው ብዬ ቀጠልኩ ፤ መሀመድ ዳርዊሽ ምን እንዳለ ሰምተሻል  !? > አልኳት ፤

< ምን አለ  !? > አለችኝ !

“A donkey doesn’t smoke or drink coffee. And it doesn’t write.” ብሏል አልኳት ፤

በሳቅ እየተንከተከተች ምናለች ...

< አላሃምዱሊላህ አህያ ያላደረገን አምላክ ! >

_

አህዮች😁 ለምን አትፈነዱም ስትፈልጉ ቡና ማጠጡ ሰዎች ገጣባ አህያ ናችሁ😂


ቀን የጠጣሁት ቡና ማታ እያነቃኝ እኮ ነው የተቸገርኩት!

ሰው እንዴት ቡና ይጠማዋል ቆይ!?🤦‍♂️


« O Captain! My Captain!
አስፈሪው ጉዟችን ተጠናቋል
መርከቧ ማዕበሉን ሁሉ አልፋለች »

ግን ...ግን...ግን

የሚያስቀን ሰው እንዴት ያዝናል? የሚለው የዓለም የየዋህነት ጥያቄ ነው ። ማልቀስ ቢፈልጉ እንኳ “አንተ እኮ የሁልጊዜ ሳቃችን ነህ” የሚለው የተመልካች ፍርድ ዕንባ እንዳይወጣ ይገታዋል ።

በጣም የሚገርመውና የሚያሳዝነው ተቃርኖ ፤ የሚያጽናኑን ፥ መከፋታችንን በሳቃቸው ያለዘቡልን ፤ እሲ አንድ እንሞክር ያስባሉን ። ማንም በማይሰማው የውስጥ ጩኸት እና በማያየው ድብርት መከበባቸው ነው ። እኛ በነሱ ፈገግታ ተደንቀን "ምንኛ የታደሉ ናቸው!?" ስንል ፥ እነሱ ግን በሚሊዮኖች ፍቅር መሃል ሆነው በብቸኝነት ይገረፋሉ ።

ለቆሰሉ ልቦች የሚሆን የቃላት ቅባት አያጡም፤ ተስፋ ለቆረጡት የሚሆን የምክር ድልድይ ይዘረጋሉ ፤ ነገር ግን የገዛ ቤታቸው ጣራ በሐዘን ዝናብ ሲደመሰስ የሚጠለሉበት ስፍራ የላቸውም። የራሳቸውን ስብርባሪ እየረገጡ ፥ ለሌላው አበባ የሚዘሩ ...

ዓለም “ሁልጊዜ ደስተኛ ነበር” ብላ ስታደንቀው የነበረው ሰው ፥ በብቸኝነትና በጭልምልም ስሜት ውስጥ ሲጠፋ ይገርማታል ። በስተመጨረሻ ያ የሳቅ ጭምብል ሲሰነጠቅና ጨለማው ሲያሸንፍ ዓለም ትደነግጣለች ።
- የብቻ ጦርነታቸውን መች አይታ ?

ራስን ማጥፋት ለጊዜያዊ ችግር ዘላለማዊ መፍትሄ መፈለግ እንደሆነ የሰበከን ፥ ራሱን ሲገድልስ ?
ሚሊዮኖችን ከጭንቀት ባህር የዋጀ "ካፒቴን" እሱ በገዛ አእምሮው ማዕበል ተመትቶ ሲሰምጥስ ??

"አስፈሪው ጉዟችን ተጠናቋል
መርከቧ ማዕበሉን ሁሉ አልፋለች"

ካፒቴናችን ግን ወደቀ ።

Robin Williams


| ... |

በሸመገለ ልባችን
ወጣት መሃል ተገኝተናል ፤

ሥጋ ለብሰን
ከመለኮት ጉባይ ታድመናል።

አውቀንበታል ምስጢሩን
... ውሉን ፤

መፍቻውን አለይ ብሎ እንጂ [ጌትዬው]
እኛስ ለዬነው ሁሉን።


ለወደድከው ሞተህ ለጠላኸው ካልኖርክ
እንኳን ልትፈጠር ገናም አልተጀመርክ "

(አያ ሙሌ "ሙሉጌታ ተስፋዬ )


ጭልጥ እንደ ውሀ ላጥ እንደ መንገድ
አጠገቤ ሆና ሣላያት ሥትሄድ
አንተ የክራር መንገድ እባክህ መልሣት
ትዝታ ክፋ ነው ያነዳል እንደ እሣት
በጣትዋ ፈላልጋ ባወጣችው መንገድ
ታሣዝነኛለች ተቀምጣ ሥትነጉድ
ባምሥቱ ጣቶችዋ ደርድራ ደርድራ
አጠገቤ እያለች ወጣች ተንደርድራ

ፊርማዬ ዓለሙ


„Der Schlaf ist das unschuldigste Geschöpf, und der schlaflose Mensch der schuldvollste.“

Letter from Franz Kafka to Milena (1920)

My dear Milena,
Sleep is the most innocent creature there is, and a sleepless man the most guilty. That is how it seems to me. When one cannot sleep, it is as if the soul were continually standing before a tribunal. The mind searches for something it has done wrong, or for something it has failed to do. One turns from side to side like a man who cannot find a place in the world.

But sleep—sleep is pure. It comes like a small, quiet animal and lies down beside us. It asks for nothing, it accuses no one. It simply takes us away from ourselves for a while. In sleep, the day’s burdens loosen their hold, and the soul rests from its questioning.

When I lie awake at night, I think of many things, and often of you. Thoughts come and go without order. Sometimes they comfort me, sometimes they disturb me. But they always return to the same point: the strange fact that a person far away can nevertheless become so present in one’s life that every quiet hour seems filled with her presence.

You must not think that I write these things in order to trouble you. On the contrary, it comforts me to write. A letter is like a bridge thrown across distance. Even if the bridge trembles, it still connects two shores.

For now I will try again to sleep. Perhaps sleep will come quietly and forgive the restless mind that has kept it away.
Yours,

Franz




መሄድ መሄድ ብቻ

ሜዳው ጫካው ሁሉ
የብስና ባህሩ
ሩቅ የሚመስለው
ኦና አየር ጠፈሩ
ደቂቅ ትላትሉ
ነፋስ የገለበው
ረቂቅ ዐፈሩ
ሆኖ የተገኘው
ሁሉ ሁላ ሁሉ
መዳረሻ ሳይኖር
መንገድ ተበጅቶለት፣
ውጥኑ አይሰምር
ጉዞው አይበጅለት።

ይኖር እንደው ብለን
ሁሉን የፈጠረ፣
ባገኘው ባስገኘው መንገድ የሚመትር
ይኖር እንደው ብለን
'ከ... እስከ' ማይባል
ስፍር አልባ ቁጥር
ይኖር እንደው ብለን
አንድ እሱን ፍለጋ
ስንለፋ ስንታትር፣
እሱም ሌላ መንገድ
ጫፍ አልባ ቁልቁለት
ሞቱ ለትንሣኤ
ውልደቱ ለስቅለት፤

ሄደን ሄደን ሄደን
ፈልገን ብናጣው
የለም ላለማለት
ሽቶ አለማግኘትን
ፈልጎ ማጣትን
በእውነት ስም ልንዘጋው
"አለመገኘት ነው አምላክነት ጸጋው"
ብለን ተማምለን
በፍጥረት አንደበት 'ምንም' አሰኘነው
ባለመሆን በኩል ፈጣሪን ሸኘነው።


የማንም "የብቻ" ማንንም "የብቻችን" ማድረግ አንችልም!

ግን ብቻችንን የብቻቸው እና ለብቻችን የብቻችን አድርገናቸው  መኖር የህይወት አጋጣሚያችን ወይም የህይወታችን መስመር ሊሆን ይችላል......ምንአልባትም ትልቁ ሞኝነት እና ብቸኝነት በዚህ ቅዠት ውስጥ መሆን ነው።

ያኔ እሷ ካስተማረቺኝ tongue twister መካከል ላካፍላቹ ብዬ ነው😉


ለተቀማጭ እንኳን ሰማይ፤
ምድርም ሺህ ዘመን ይርቃል።

ለራስ የሳሱት ጉልበት፤
በቅመሱልኝ ያልቃል።

ሙከራችን ሁሉ እንደ አህያ ስጋ፤
አልጋ ሲሉት መሬት ይወድቃል።

ከጨለማ ተወዳጅቶ የብርሃን ህልም እንደማለም፣
ያንቺ እና እኔ ታሪክ፣
እንዴ ፀጉራም ውሻ አለ ሲሉት የለም።


«...The Greek word for "return" is nostos. Algos means "suffering." So nostalgia is the suffering caused by an unappeased yearning to return.»

Milan kundera ; Ignorance




To listen to Ephrem's "አካሌ" is to feel that the memory of love is not just personal.

It is temporal architecture . What we remember is not just someone we loved,but the person we were when we loved them and in this way Ephrem is not just artist of feeling but he is artist of the time it self!

This is not just Nostalgia. It is an epistemology of intimacy:a philosophy of how feeling,sensation and time fold into each other!

......."የማብሰልሰል ሚስጥር የሀሳብ ሹክሹክታ
መወያየት ሆኗል ገጥሞ ከትዝታ"

  


-----------

አይገባኝም...
ትኩስ ገላ ውስጥ የልብ ማርጀት
ውበት ነው? መርገምት?

አልረዳውም...
ለአበባ ፣ ለሰው ወድቆ መሸነፍ
መኖር ነው? መክሸፍ?

አይዘልቀኝም
ነፋሱን አምኖ መጎዝ በዱር በሜዳ
ነዋይ ነው? ዕዳ?

የቱን ልመነው?
ማንን ቀርቤ ልስማ
ተቀባዥሮብኛል
እሳት አለ ሆዴ...ውሃ ሚያስጠማ
:
በመገረም
በአፍ መክፈቴ
ወፍ ቢመገብ ከጥርሶቼ መሀል ገብቶ
በህይወት ሚሆነው ቢያንቆራጥጠኝ
በሀዘን ሆዴ ቢወጠር መልስ ማጣት ሽሉን ዘርገቶ
በቃ! አልኖርኩም ከቶ?
:
ውበት እና ትርጉም ማጣት መሀል
እድሜዬ የሽቦ ገመድ መስሎ ተወጣጠረ
በፀሀይ...በዝናብ ፍርርቅ
ያሰጣሁት ልቤ ተፈረፈረ
ለአይኔ ቢያሳሳኝ የሰው መግባት መውጣቱ
እንጀራ ቢሆነኝ የህይወት ኪነቱ
አቅፌ ባፅናናው የኑሮን ባዛናነቱ
ያስብላል ከነቱ?
:
ልጆች ባልወልድ
ርዕዮተ አለም ፅፌ ታሪክ ባልሰራ
ለሀገሬ ባልዘምት በዱር በጋራ
እሱማ ህይወቱን ኖሯል ለመባል
ጀግና እንዲያስብለኝ ስሜ ተጠቅሶ
አይበቃም ነበር?
ለሰው ድካም ግጥም የፃፍኩት
ለከተማዬ ያለቀስኩት ለቅሶ!




Connected beyond blood and bones
We made ourselves in our likeness
A predestined appointment of souls
Bound to end up in the same life line..

To discover the beauty in life
Together
To experience the ecstasy of it
Together
To lough at the gods and their creations
Together...

The primitive part of me is still in awe
With the similarity of our face and essence
Little do i know the arrangement we made
In the realm of spirits.....

We really buried
some fragments of our self
and created others along the way....
And some pieces of us died
with the departure
of close ones who help created them....

And there are some bonds
Beyond breaking or melting
Forged in the realm of the Avatars
A predestined Union of souls
Glad we found our way to each other
Old souls in a little earth....!!

Alas star dust
See u in the next relm
Then in the next life
Yes...!! You heard me right...
I am making this a habit..!!


"Adwa is not only a victory.
It is the moment an imperial system met its limit—and could not explain it away."

ለ ነፃነት ቀን ዋዜማ የምትሆን አንዲት ፅሁፍ ልጋብዛቹ!
“The Counter-Scramble: From Adwa to Fashoda — Series Preface” by Elias Wondimu!

this completely reframes how we think about Ethiopia during the Scramble for Africa.

“This series is not a correction of European history for its own sake… an African state becomes the variable empires cannot fully control.”
ይለናል Elias በሀተታው!

በጣም ያስደመመኝ ነገር ቢኖር how he shows that Ethiopia wasn’t just resisting — it was calculating, negotiating, and strategically shaping its survival.

If you’re interested in African sovereignty, history beyond colonial narratives, and deeper political thinking — this is worth your time.

ከወዲሁ እንኳን አደረሳችሁ እንኳን አደረሰን✌️

ለማንበብ ካሻቹ:- https://open.substack.com/pub/eliaswondimu/p/the-counter-scramble-series-preface?utm_source=share&utm_medium=android&r=7q99uy


"ሕይወት በየቀኑ ያለውና የምትኖረው እንጂ ፖለቲከኞች በአጀንዳቸው ውስጥ የሚዘረዝሩት የተስፋ ማስታወቂያ አይደለም፡፡ አንዲት የምትወዳትን ሴት ማቀፍ ከአንቀጽ አስራ ሶስት ይበልጣል፡፡"

***
📖 የስንብት ቀለማት | አዳም ረታ


Whenever i'm vibing to Aster,its like my internal void finally caught a signal and started broadcasting. I mean it is a strange thing to hear one's own internal geometry translated into sound....የ አስቱ ድምፅ ደግሞ የማታዩትና እስትንፋስን ግን የሚያጥሩ ግድግዳዎች ያሉበት ጠባብ ቤት ውስጥ እንደመታሰር አይነት ስሜት መፍጠር ይችላሉ እና makes my face every ghost i've been ghosting.

as i listen, i feel like a man locked inside a giant cello. ደግሞ ብድግ ብዬ በሩን እንደሚፈልግ ሰው እሆናለሁ...በሩ ግን በየትኛውም የግድግዳ ጥግ አይኖርም። እንኳን በር ሽንቁር አላይም። Even if there were a door,i don't have the keys to unlock myself from this beautiful,melodic trap ልክ አንደ ልብ ትርታ የማያልቅ ናፍቆት...የማይመለስ ትዝታ...የማይፈቱ መስመሮችን ደበላልቃ ወደተለያዩ ስሮች የምትረጭ እመቤት ናትና...በር በሌለው ቤት ውስጥ ተቀምጦ ተመቻችቶ መኖር የተቻለውም በዚህ ህይወት በሆነ ድምፅ ይመስለኛል!
if u asked me  if i feared the quiet my answer would be "No!" But i fear the noise that lives in quiet. And Astu is the high definition of sound of that noise!

I am alone,and her entire song is the only thing that knows my true name.🖤

20 last posts shown.

52

subscribers
Channel statistics