TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
Footnotes in blue

15 Mar, 10:43

Open in Telegram Share Report

Prev Next
« O Captain! My Captain!
አስፈሪው ጉዟችን ተጠናቋል
መርከቧ ማዕበሉን ሁሉ አልፋለች »

ግን ...ግን...ግን

የሚያስቀን ሰው እንዴት ያዝናል? የሚለው የዓለም የየዋህነት ጥያቄ ነው ። ማልቀስ ቢፈልጉ እንኳ “አንተ እኮ የሁልጊዜ ሳቃችን ነህ” የሚለው የተመልካች ፍርድ ዕንባ እንዳይወጣ ይገታዋል ።

በጣም የሚገርመውና የሚያሳዝነው ተቃርኖ ፤ የሚያጽናኑን ፥ መከፋታችንን በሳቃቸው ያለዘቡልን ፤ እሲ አንድ እንሞክር ያስባሉን ። ማንም በማይሰማው የውስጥ ጩኸት እና በማያየው ድብርት መከበባቸው ነው ። እኛ በነሱ ፈገግታ ተደንቀን "ምንኛ የታደሉ ናቸው!?" ስንል ፥ እነሱ ግን በሚሊዮኖች ፍቅር መሃል ሆነው በብቸኝነት ይገረፋሉ ።

ለቆሰሉ ልቦች የሚሆን የቃላት ቅባት አያጡም፤ ተስፋ ለቆረጡት የሚሆን የምክር ድልድይ ይዘረጋሉ ፤ ነገር ግን የገዛ ቤታቸው ጣራ በሐዘን ዝናብ ሲደመሰስ የሚጠለሉበት ስፍራ የላቸውም። የራሳቸውን ስብርባሪ እየረገጡ ፥ ለሌላው አበባ የሚዘሩ ...

ዓለም “ሁልጊዜ ደስተኛ ነበር” ብላ ስታደንቀው የነበረው ሰው ፥ በብቸኝነትና በጭልምልም ስሜት ውስጥ ሲጠፋ ይገርማታል ። በስተመጨረሻ ያ የሳቅ ጭምብል ሲሰነጠቅና ጨለማው ሲያሸንፍ ዓለም ትደነግጣለች ።
- የብቻ ጦርነታቸውን መች አይታ ?

ራስን ማጥፋት ለጊዜያዊ ችግር ዘላለማዊ መፍትሄ መፈለግ እንደሆነ የሰበከን ፥ ራሱን ሲገድልስ ?
ሚሊዮኖችን ከጭንቀት ባህር የዋጀ "ካፒቴን" እሱ በገዛ አእምሮው ማዕበል ተመትቶ ሲሰምጥስ ??

"አስፈሪው ጉዟችን ተጠናቋል
መርከቧ ማዕበሉን ሁሉ አልፋለች"

ካፒቴናችን ግን ወደቀ ።

Robin Williams

22 0 0 2
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot