ቴዎድሮስ ካሳሁን
የሳባን ዘመን ሚስጥር የያዘው
አክሱምም መጣ የተገረዘው
መች ተገርዘናል እኛስ ሁላችን
ፍቅር ማጣት ነው ሸለፈታችን፤
በአክሱም አለቶች ሳባን አሻግሮ
የቃል ኪዳኑን ምስጢር መርምሮ
በእምነት የእኩል ቤት በፍቅር መክሮ
በሃያላን ላይ ዙሪያውን አጥሮ
ስራን ቢሰራ ወገኔ ነቅቶ
ይነሳ ነበር እንዳይቀር ሞቶ
እንዳይሰማ ግን ትእቢት ተሞልቶ
ተረትን ናቀው፤ ታሪኩን ናቀው፤
የራሱን ናቀው; መፅሃፍ በልቶ
በሰው መፅሃፍ ያበደ አዋቂ
ለጥፋት ሁሉ ነው ተጠያቂ
የራሱን ሳይጥል የሰው ቢሰማ
ይረዳን ነበር እንድንስማማ
የራሱን ጥሎ የሰው ከሰማ
በቃ ሆነናል እንዳንስማማ
ሁሉም ሲመጣ ነው ተናጋሪ
መመሪያው ላይ ግን የለም ፈጣሪ
በሌሎች መንገድ ለማንድን እኛ
ስሙን ይሉናል ጆሮ አለን እኛ?
ጆሮስ ቢሰማ አፍስ ቢናገር
እውነት ካልሆነ የሚነጋገር
ምጣድ ነው እንጂ የታል ሚጋገር
አንዳቸው ጋግረው እኛ እንዳንበላ
ዱቄቱ የኛ እርሾው የሌላ
ይልቅ ይልቅስ
ፍሰሃ እንዲሆን፤ ደስታ እንዲሆን እንዲቆም ሙሾ
ከሽማግሎች እንዋስ እርሾ
የነሱ እርሾ የነፋው ቡኮ
ከእኛ አልፎ ለሰው ይተርፋል እኮ
ግን ምን ያደርጋል አትሰሙም እኮ
አረ ባካችሁ አቃተን እኮ፤ ደከመን እኮ
ይህ ሁሉ ሲሆን ያገሬ ሰዎች ያሳዝኑኛል
ይህንንም ስል፤ ከመስማት ይልቅ ማነህ ይሉኛል፤
ትንሽ ልጅ ተናግሮ ትልቅ ሰው ሲሰማ
እውቀት ነው ብሎ ሰው አይስማማ፤
ይህንን እውነት ያሳጣው አቻ
እኔ አይደለሁም ፈጣሪ ብቻ
ለቀረን ጉዞ ማስተዋል ጠፍቶ ቀና መንገድ
አደራ እላለሁ፤ ለገዥው ፓርቲም
ለተቃዋሚም ደም እንዳይፈስ
የኋላ ኋላ ጠፍቶ የሚሰማ በዝቶ የሚናገር
ከእነ ልጆቿ እንዳትሞት ሃገር
ከየራሱ ጋር ሰው ይነጋገር ።
ቴዲ አፍሮ
Teddy Afro ❤🙏
T.me/s37fe
የሳባን ዘመን ሚስጥር የያዘው
አክሱምም መጣ የተገረዘው
መች ተገርዘናል እኛስ ሁላችን
ፍቅር ማጣት ነው ሸለፈታችን፤
በአክሱም አለቶች ሳባን አሻግሮ
የቃል ኪዳኑን ምስጢር መርምሮ
በእምነት የእኩል ቤት በፍቅር መክሮ
በሃያላን ላይ ዙሪያውን አጥሮ
ስራን ቢሰራ ወገኔ ነቅቶ
ይነሳ ነበር እንዳይቀር ሞቶ
እንዳይሰማ ግን ትእቢት ተሞልቶ
ተረትን ናቀው፤ ታሪኩን ናቀው፤
የራሱን ናቀው; መፅሃፍ በልቶ
በሰው መፅሃፍ ያበደ አዋቂ
ለጥፋት ሁሉ ነው ተጠያቂ
የራሱን ሳይጥል የሰው ቢሰማ
ይረዳን ነበር እንድንስማማ
የራሱን ጥሎ የሰው ከሰማ
በቃ ሆነናል እንዳንስማማ
ሁሉም ሲመጣ ነው ተናጋሪ
መመሪያው ላይ ግን የለም ፈጣሪ
በሌሎች መንገድ ለማንድን እኛ
ስሙን ይሉናል ጆሮ አለን እኛ?
ጆሮስ ቢሰማ አፍስ ቢናገር
እውነት ካልሆነ የሚነጋገር
ምጣድ ነው እንጂ የታል ሚጋገር
አንዳቸው ጋግረው እኛ እንዳንበላ
ዱቄቱ የኛ እርሾው የሌላ
ይልቅ ይልቅስ
ፍሰሃ እንዲሆን፤ ደስታ እንዲሆን እንዲቆም ሙሾ
ከሽማግሎች እንዋስ እርሾ
የነሱ እርሾ የነፋው ቡኮ
ከእኛ አልፎ ለሰው ይተርፋል እኮ
ግን ምን ያደርጋል አትሰሙም እኮ
አረ ባካችሁ አቃተን እኮ፤ ደከመን እኮ
ይህ ሁሉ ሲሆን ያገሬ ሰዎች ያሳዝኑኛል
ይህንንም ስል፤ ከመስማት ይልቅ ማነህ ይሉኛል፤
ትንሽ ልጅ ተናግሮ ትልቅ ሰው ሲሰማ
እውቀት ነው ብሎ ሰው አይስማማ፤
ይህንን እውነት ያሳጣው አቻ
እኔ አይደለሁም ፈጣሪ ብቻ
ለቀረን ጉዞ ማስተዋል ጠፍቶ ቀና መንገድ
አደራ እላለሁ፤ ለገዥው ፓርቲም
ለተቃዋሚም ደም እንዳይፈስ
የኋላ ኋላ ጠፍቶ የሚሰማ በዝቶ የሚናገር
ከእነ ልጆቿ እንዳትሞት ሃገር
ከየራሱ ጋር ሰው ይነጋገር ።
ቴዲ አፍሮ
Teddy Afro ❤🙏
T.me/s37fe