Big ቅሌት ማለት 🙊🙊
ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ, የአከራዬ ልጅ ልደት ነበር እና Program-u ትልቅ ስለነበር ከዝግጅቱ አንድ ቀን ቀደም ብላ አከራዬ እንግዶቹን በማስተናገድ እንድረዳት ትጠይቀኛለች፤ እኔም ያለ ምንም ማቅማማት ደስተኛ እንደሆንኩኝ እና ልረዳትም ዝግጁ እንደሆንኩ ነገርኩዋት።
የማይደርስ የለም ቀኑ ደርሶ ዝግጅቱም ተጀመረ፣ እንግዶቹም መግባት ጀመሩ እኔም ቃሌን አክብሬ ማስተናገዱን ተያያዝኩት፣ አከራዬ ሀብታም ቢጤ ስለሆኑ program-u ሰርግ እንጂ ልደት እይመስልም ነበር፤ ዲኮሩ፣ መጠጡ🍾፣ Especially ደግሞ ምግቡ 😋😋
ታድያ ከእንግዶቹ መሀል አንዲት ቆንጂት ትኩረቴን ለመሳብ መሞከር ጀመረች፤ ያው እኔም ትንሽ ኩራት ቢጤ ስላለችብኝ ምንም እንዳልገባው እና እያየኹዋት እንዳላየሁ ማስመሰል ጀመር፣ ግን እሷ ድርጊቷን አላቆመችም ባለፍኩ ቁጥር እጇን እያውለበለበች ልትጠራኝ ትሞክራለች እኔም እንዳላየዃት act ማድረጉን ተያያዝኩት
🤔🤔 በውስጤ ይሄ ሁሉ ሰው መሀል እኔን ለመማረክ እንደዚህ እምትሆነው ምን አይነት ፈጣጣ ብትሆን ነው እያልኩ እያሰብኩ አስተናጋጅ የሚጠራበትን አይነት የጭብጨባ ድምፅ ሰማው እና ዞር ስል አጅሪት ናት ኧረ መናናቅ ብዬ በዛውም እንደፈለገችኝ እና እንደኮራውባት በቦታው ለነበሩ ሰዎች ለማሳየት ......
ወደ ተቀመጠችበት ቦታ በመሄድ ትንሽ ድምፄን ከፍ አድርጌ የኔ እህት ትኩረቴን ለመሳብ እየሞከርሽ እንደሆነ እና ልታናግሪኝ እንደምትፈልጊ አውቃለሁ ግን ይቅርታ Girlfriend አለኝ ስላት በProgramu ላይ የነበሩት ሰዎች እንዳለ ወደ እኛ ዞሩ
አጅሪት ምንም ሳይመስላት ድምጿን ከፍ አድርጋ፣ የኔ ወንድም እንዳንተ አይነቱን ጣውላ እራስ እንኳን እኔ ሙታንም አይፈልግ የጠራውህ በኪስህ የደበከው የአሳ ስጋ እንደሚታይ ልነግርህ ነበር ስትለኝ😳😳😳
you can't imagine ምን ያህል እንደተሸማቀኩ 🙊🙊😔😔😔 By z way ሌላ ቤትም ፈልግ ተብያለው
መልዕክት፦ እቃ ስትደብቁ በደንብ እንደማይታይ እርግጠኛ ሁኑ 🤣🤣🤣
@poethaymi