መሸ አይደል!
"ደህና ነህ"? የሚል ባይጠፋ
ድንኳኔን በአዛኝ ብትሞላው፤
"አለሁኝ" የሚል ቢከበኝ
ብቸኝነቴን ባ'ጀብ ብትከላው
ከመሸ ሽልብ አድርገህ
ብትችል ዳግም አታንቃኝ፤
/ተመስገን/
ይህችን ታህል ከኖርሁኝ በቃኝ፡፡
/መሸ አይደል/..!?
አኑረኽኛል እስከዛሬ
'ኑር' ባልከኝ ስርፋ ባልኖርብህም፤
ሁሉን ኖርኹት እንደመሻቴ
ያልኖርኹትንም አልቆጥርብህም፤
ከሁሉም አቅጣጫ ቢያዩት
አንድ ነው የህይወት ጭንጫው፤
ተኖረና_ተኖረ ተብሎ
መሞት ነው ኩሉ መቋጫው፤
/ብቻ ግን/
ሰው መሆን ትርጉመን ሳስስ
በንግልል መጪውን ስቃኝ፤
ለመሞት ምን አደከመኝ
የኖርኹት ከእንዲህ በቃኝ፡፡
/መሸ አደል እግዚአብሔርዬ/
አንተም በኔ ከመድከም ዕረፍ
በንኩርፍ ሽልብ አድርገኝ፤
ምን አለኝ ከኖርኹት ወጪ
ነግቶልኝ በአዲስ ቀን ብገኝ!
By: Astawseng Regasa
@poethaymi
"ደህና ነህ"? የሚል ባይጠፋ
ድንኳኔን በአዛኝ ብትሞላው፤
"አለሁኝ" የሚል ቢከበኝ
ብቸኝነቴን ባ'ጀብ ብትከላው
ከመሸ ሽልብ አድርገህ
ብትችል ዳግም አታንቃኝ፤
/ተመስገን/
ይህችን ታህል ከኖርሁኝ በቃኝ፡፡
/መሸ አይደል/..!?
አኑረኽኛል እስከዛሬ
'ኑር' ባልከኝ ስርፋ ባልኖርብህም፤
ሁሉን ኖርኹት እንደመሻቴ
ያልኖርኹትንም አልቆጥርብህም፤
ከሁሉም አቅጣጫ ቢያዩት
አንድ ነው የህይወት ጭንጫው፤
ተኖረና_ተኖረ ተብሎ
መሞት ነው ኩሉ መቋጫው፤
/ብቻ ግን/
ሰው መሆን ትርጉመን ሳስስ
በንግልል መጪውን ስቃኝ፤
ለመሞት ምን አደከመኝ
የኖርኹት ከእንዲህ በቃኝ፡፡
/መሸ አደል እግዚአብሔርዬ/
አንተም በኔ ከመድከም ዕረፍ
በንኩርፍ ሽልብ አድርገኝ፤
ምን አለኝ ከኖርኹት ወጪ
ነግቶልኝ በአዲስ ቀን ብገኝ!
By: Astawseng Regasa
@poethaymi