ነይ አትምጪ. (ልዑል ሀይሌ)
ይኸው እድሜ ላንቺ ጠላሁት ዓለሙን፤
አላውቅም ነበረ
መንገዴ በሙሉ ባንቺ መረገሙን፤
ብፈልግ አጣሁት
አንቺ የሌለሽበት የመኖር ትርጉሙን፤
.
ከራቅሽኝ በኋላ ፀፀት ልቤን ናጠው፤
ባሕር ዝምታዬን ማዕበል አናወጠው፤
እንዴት የኔን ዓለም
ለወጪ ወራጁ አሳልፌ ሰጠሁ?፤
.
ይኸው እዞራለሁ...
ቅርጫት ሙሉ ፀፀት ቁጭት ተሸክሜ፤
እንዳታወርጂልኝ
ዳግም ብትመጪም አልድንም ታክሜ፤
መዳን አልፈልግም
ያወረድሽብኝን እርግማን ፈርቼ፤
ከዚህ የበለጠ
ዓለሜን አልጠላም ወዳንቺ መጥቼ፤
.
በህይወት መንገድ ላይ
ስቃይ ምታበዢ መስቀል አሸካሚ፤
ከፀፀት እንድድን
አንቺም ተፀፅትሽ በስቃይ ታከሚ፤
.
እንደኔ ምነና
ዓለም እንደጠላሁ ዓለምሽን ጥዪ፤
ራሴን እንዳነፃሁ አንቺም ነፅተሽ ነዪ፤
.
ያኔ እንገናኛለን!
ታህሳስ 26, 1520
@poethaymi
ይኸው እድሜ ላንቺ ጠላሁት ዓለሙን፤
አላውቅም ነበረ
መንገዴ በሙሉ ባንቺ መረገሙን፤
ብፈልግ አጣሁት
አንቺ የሌለሽበት የመኖር ትርጉሙን፤
.
ከራቅሽኝ በኋላ ፀፀት ልቤን ናጠው፤
ባሕር ዝምታዬን ማዕበል አናወጠው፤
እንዴት የኔን ዓለም
ለወጪ ወራጁ አሳልፌ ሰጠሁ?፤
.
ይኸው እዞራለሁ...
ቅርጫት ሙሉ ፀፀት ቁጭት ተሸክሜ፤
እንዳታወርጂልኝ
ዳግም ብትመጪም አልድንም ታክሜ፤
መዳን አልፈልግም
ያወረድሽብኝን እርግማን ፈርቼ፤
ከዚህ የበለጠ
ዓለሜን አልጠላም ወዳንቺ መጥቼ፤
.
በህይወት መንገድ ላይ
ስቃይ ምታበዢ መስቀል አሸካሚ፤
ከፀፀት እንድድን
አንቺም ተፀፅትሽ በስቃይ ታከሚ፤
.
እንደኔ ምነና
ዓለም እንደጠላሁ ዓለምሽን ጥዪ፤
ራሴን እንዳነፃሁ አንቺም ነፅተሽ ነዪ፤
.
ያኔ እንገናኛለን!
ታህሳስ 26, 1520
@poethaymi