Samaritan club"


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


"Therefore to him that knoweth to do good, and doeth(it) not, to him it is sin" james 4:17
"እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሰራዉ ኃጢአት ነው" የያዕቆብ መልክት ፬:፲፯
for any comment @abuttysda and @edbornagain @SAMAAritanclub_bot

We are here to create a compassion..join us

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ሰላም ቤተሰቦቼ እንደት ናችሁልኝ??

ዛሬ አንድ አስተማሪ መዝሙር ልጋብዛችሁ።

title: እሰኪ አስተምረን
singers:ቀበና ክዳነ-ምህረት
size:4.6mb
Duration:4:58


ተባረኩበት🙏


፩.እስኪ አስተምረን ጌታ መሸካከም፣
አንዳችን ለአንዳችን እንቻል መተሳሰብ፣
አቅሙ የበረታ ይሁን ለደካማው፣
መረዳዳት ይንገስ ይህ ጸሎታችን ነው።

አ አስተምረን ልገሳ }
ዝ አስተምረን ፍቅር }፪×
ማ ለመድራችን ተስፋዋ }
ች ሁን ሕልውናዋ። }

፪.አንዱ እየቆዘመ በሃዘን በችግር ፣
ሌላው ተደላድሎ ይኖራል በክብር
ሰው ምንድነው ነው ትርፉ እንደዚህ መኖሩ
እንደት ያዛልቀው እራሱን ማፍቀሩ?፣

፫.ፍጹም አዛኝ መስሎ ከንቱ እንባ ማንባት፣
ምድራችን ሽንገላ ኤሬ ይሄ አይረባትም፣ #በፍቅር_እንበርታ_በእውነት_እንዋደድ_እግዚአብሔር_ባርኮቱን_በእጥፍ_እንዲያወርድ ።


ተባረኩልኝ🙏


መልካም ግዜ

ከቀበና መድሀንዓለም ሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ።


#ባልንጀራህን_እንደራስህ_ውደድ


" ከእግዚአብሔር ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።"

👨‍👩‍👧‍👦ሁላችንም ፣ ቤተሰባችንን፣ ዘመዶቻችንን ፣ እህት ወንድሞቻችንን፣ ጓደኞቻችንን እንደምንወድ ፤ ለሎችንም እንደነሱ ከልባችን ብንወድድ ፤ ምን አይነት አከባቢ እንደሚፈጠር አስቡ።

🙍እናቶች፦
🔅ሁሉንም እፃናትን እንደልጃቸው አድርገው ቢወድዱ።
👴🏿አባቶችም ፦
🔅ሁሉንም ያልወለዱትን ልጆት እንደወለዱአቸው ቢወድዱ።

👦🏾ልጆችም(እኛ) ፦
💑እህት ወንድሞቻችንን እንደምንወደው ሌሎችንም በስጋ አህት ወንድሞቻችን ያልሆኑትን ከልባችን ብንወዳቸው።

🚫ያለ አንዳች አድሎና ክፍፍል ሁሉንም ሰበአዊ ፍጡርን ብንወድ ምን አይነት አከባቢ (Environment )እንደሚፈጠር መገመት አይከብድም፦

👱🏽‍♀እናት ከሆንሽ
➡️ልጆችሽ ሲራቡ ፣ሲጠሙ ፣ እርቃናቸው ስታዩ ፣የሚያይ አንጀት ስለ ለለሽ ካለሽ እንደምንም ትሰጪአለሽ።

⚜ ስለዚህ በምግብና በልብስ እጦት የሚሰቃይ እፃን አይኖርም።

👴🏿አባትም ብትሆን፣
➡️የወለድካቸው ልጆች ፣ በጎዳና ላይ ወድቀው፣ ብርድ፣ዝናብና ውርጭ ሲፈራረቅበት የሚታይበት አይን የሉህም ። ምክንያቱም አባት ለልጆቹ ፦ ጋሻ ፣ መከታ፣ ጠባቂ ነው።
⚜ ስለዚህም ጎዳና የሚወድቅ አይኖርም ማለት ነው።

👨🏻ወንድሜ አንተስ ብትሆን።
👱🏿👦🏾በብቸኝነት፣ ሰውን በማጣት ተስፋ ለቆረጠው ወንድምህ ሔደህ አለሁልህ ብትል፣ ተስፋው አይዘራም ?? ሚኖርለት አለማ አላገኘም ??

⚜ስለዚህ ማንም በብቸኝነቱ ተስፋ አይቆርጥም ማለት ነው።

🤔እናስብ ሁላችንም እርስ በርሳችን ከልባችን ያላንዳች ክፋት፣ መከፋፈል፣ አድሎ፣ ተንኮል ብንፋቀር ምድራችን የሰላም፣ የደስታ፣ የመተሳሰብ፣ ለመኖር የምታጓጓ፣ ትሆናለች።


👆አንተስ አንቺስ በንደዚህ አይነት አከባቢ(environment ) ውስጥ መኖር ከፈለክ፦
=>ከአሁኑ ጀምርህ ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ።



" እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።
"
(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:21)


#መልካምነትን_እንኑር

መልካም ቀን

ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ በቅንነት share ያድርጉ።

ለአስታየት @abuttysda ላይ ያድርሱኝ።

💚💚 @samaritanclub 💚💚
💚💚@samaritanclub 💚💚


Complete book of intelligence tests.pdf
1.3Mb
ሰላም ዉድ ቤተሰቦች

እስኪ ዛሬ ደግሞ ለየት ባለው መልኩ አንድ አስፈላጊ መጽሐፍ ላስተዋውቃችሁ።
መጽሐፉ በEnglish ነው የተጻፈው እናም በጣም ቀለል ባሉ ቃላቶች ነው፤ ስለዘለህ አውርዳችሁ እንድታነቡት የልቤ ምኞት ነው።
አዕምሮአችን ምን ያህል እንደ ተጠቀምበት የምነግረን ነው።


@samaritanclub


ደራሲ :Philip Carter
size:1.3mb
Type:pdf
Title:complete book of #intelligence tests


>

(ማቴ 25:31_46)

" ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ይሁን።"

መሪ ሪዕስ :- በጎች 🐏 🆚 ፍየሎች🐐

የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤"

፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥

" አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥"

፤ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።"

⬆️ ከላይ ያለው ትንብት መሳይ የ ግዜአት ኩነቶች ጌታችን ዳግም ስመጣ ያለውን የፍርድ ትእይንት ለደቀመዛሙርቱ አሳያቸው።

የፍድር ውሳኔም በአንድ ነገር ላይ እንደሚያተኩርም ነገራቸው ።
ሕዝቦች በፊቱ በተሰበሰቡ ግዜ #በሁለት እንደሚመደቡና #የዘላለም እጣፈንታቸው የሚወሰነውም:------

⚖ለእርሱ ሲሉ ለድኾችና ባደረጉት በጎ አድራጎት ወይም
⚖ባሳዩት #ቸልተኝነትና እራስወዳድነት፤ መሆኑን ገለጸላቸው!!።

እስኪ በየወገኖቻቸው እንመልከት።


በጎቹ 🐑

ፍየሎቹ🐐

🐑በቀኙ ይሆናሉ
___________
🐐በግራው ይሆናሉ
____________
🐑ወራሾች ናቸው
___________________
🐐የሚጠፉ ወይም ወደ ዘላለም ውርደት የሚሄዱ ናቸው
________________
🐑ተርቦ አብለተውታል
_________________
🐐ተርቦ አላበሉትም፤ ቸል ብለውታል
_________________
🐑እንግዳ በሆነ ግዜ ተቀብለውታል
___________________
🐐በእንግድነቱ ግዜ አልተቀበሉትም፣ ከቤታቸው አባረውታል
_________________
🐑በታረዘ አልብሰውታል
__________________
🐐አላለበሱትም፦ ግን ድሪቶ ለበሰ ብለው ስቀውበታል።
___________________
🐑በታመመ ግዜ ጠይቀውታል
__________________
🐐በታመመ ግዜ ቸል ብለው አልፈውታል
____________________
🐑በተጠማ ግዜ አጥጠውታል
____________________
🐐በተጠማ ግዜ አላጠጡትም
____________________
🐑 በታሰረበት ግዜ ጎብኝተውታል
____________________
🐐በታሰረበት ግዜ አልጎበኙትም
___________________

ልዩነቶቹ በግልጽ ይታያሉ እንግዲህ አነዚህ #ጥቃቅን መመዘኛዎች የመጨረሻውን መዳረሻችንን ይወስናሉ።

❇️እናስተውል ፣ እነዚህ መመዘኛዎች በክርስትና ሕይወታችን ካልተጨመሩ ያም ማለት (የበጎቹ ድርግቶች) ፣ አሁን ባለው ምልልሳችን ማሳየት አለብን ያ ካል ሆነ ግን መጨረሻችን በፈረየሎቹ ግራ መሆኑ ነው!!!

🔱ለማታውቀው ወንድምህ ያደረከው ነገር ልክ ለምታመልከው፣ እወደዋለሁ ለምትለው አምላክህ እንዳደረክ እወቅ!!

⚜እንዲህ ስታደርግ ለወንድምህ ብቻ ሳይ ሆን ለራስህም ጭምር በጎ ነገር እያደረክ እንደሆነ አስብ።

" ያን ጊዜ። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል።
(የማቴዎስ ወንጌል 25:45)


ሁላችንም በበጎቹ ተርታ እንሁን ዘንድ ዛሬውኑ ፤ አቅማችን በፈቀደ መጠን
🍔ለተራቡ ወገኖቻችን
🍼ለተጠሙ እህት ወንድሞቻችን
🥋ለታረዙ ሚስኪኖች
🤕ብቸኝነት፣ ሰው ማጣት ተስፋ ያስቆረጣቸው ወገኖቻችን
👫ወላጆቻቸውን ላጡ ዕጻናት

እንድረስላቸው‼️‼️‼️

" እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።
"
(የማቴዎስ ወንጌል 25:46)

ወደ ዘላለም ሕይወት እንጂ ፣ ወደ ዘላለም ቅጣት የማይሆኑ ያድርገን❗️❗️

🙏 አሜን
ለአሳብ አስታየት @abuttysda

#መልካምነትን_አረንኑር
መልካም ግዜ

በቅንነት share ያድርጉ

💚💚 @samaritanclub💚💚
💚💚 @samaritanclub 💚💚


ሰላም ሰላም ቤተሰቦቼ እንደት ቆያቹልኝ??

የእስካሁኑ መልክታችን አሪፍና ቁምነገርን ያስጨብጣል ወይስ ማማሸያዎች ይደረግባቸው?

👌ወደነዋል ✍በዛ ይዘቱ ይቀነስ።

በጌታ ፍቅር vote አድርጉና ደግፉን 🙏


ሰላም የተወደዳችሁ የ @samaritanclub ቤተሰቦች እንዴት ናችሁልኝ??

የሚለጠፈው አሳብ ላይ እስከ ዞሬ ምን አስታየት እንዳላችሁ ማወቅ ስለሚያፈልገን የchannel bot አዘጋጅተናል።
አስታየታችሁን በነጻነት አድርሱን ፤ በጌታ ፍቅር ምንጠይቃችሁ ነገር ከጎናችን እንድትሆኑ እንድውም አሳባችሁን እንድትታካፍሉን ነው።

እባኮትን ይህን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም አስታየቶን ያስቀምጡ።

@SAMAAritanclub_bot

ተባረኩ🙏
#መልካምነትን_እንኑር
መልካም ግዜ


#ከተረፋቸው_ሳይሆን_ካላቸው_የሚሰጡ_እጆች ።

🙋‍♂ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ይሁንላችሁ ።

ዛሬ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በመስጠት ምሳሌ የምትሆነን ስለ አንዲት ባልተት( እናት)እንመለከታለን።

" እርስዋም። አምላክህ ሕያው እግዚአብሔርን! በማድጋ ካለው ከእፍኝ ዱቄት፥ በማሰሮም ካለው ከጥቂት ዘይት በቀር እንጀራ የለኝም፤ እነሆም፥ ገብቼ ለእኔና ለልጄ እጋግረው ዘንድ በልተነውም እንሞት ዘንድ ጥቂት እንጨት እሰበስባለሁ አለች።"
(መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 17:12)

👆ከላይ እንደተመለከትነው ይህች እናት ምንም እንደሌላት ለ ነብዩ ኤልያስ ፥ተስፋ በመቁረጥ ትናገራለች።

ያላት ነገር ለልጇና ለርሷ እንኳን ከአንድ ግዜ ያለፈ ምንም እንደማይተረፋት ስታስብ ፣ ሆዷን ባር ባር ይላታል፣ ገና ወደፍት ምበሉትን አተው እሷና ልጇ በረሃብ ተጎድተው ፤ አጥንታቸው ብቻ ስቀር ይታያታል። ምክንያቱም ለምቀጥሉት ሶስት (3) አመታት ዝናብ እንደማይዘንብ ፣ ድርቅም ስለሚሆን ነው።


👳‍♀ነገር ግን ድንገት ያልተጠበቀ እንግዳ ማጣባት፣ እውነተኛ የእግዚአብሔር ነብይ ተርቦ ፣ ተጠምቶ ፣እርዳታዋን ጠየቀ።

ምን ታድርግ ያላት ነገር በጣም ጥቅት ነው ፣ እውነቱን ነገረችው እንጂ፤ በማይረባ ቸልተኝነት
"እግዚአብሔር ይስጥህ"
ብላ አላለፈችውም!!

❗️❗️ወንድም እህቶቼ ሆይ እናንተስ ዛሬ ፥ ካላችሁ ነው ወይስ ከተረፋችሁ ነው የምትሰጡት???

‼️‼️ወይስ የለኝም ብለችሁ ታስባላችሁ??
👩‍💻ተማሪ ለትሆን ትችላለህ ፤ ገንዘብም የለህም 💪💪ግን አቅም አለክ።

👩🏾እናም ሕድና እናንተ ሰፈር ያሉትን አቅመ ደካማዋ አክስትህ ቤታቸውን መጥርግ፣ ማጽዳት ያልቻሉትን፤ ልብሳቸውን ማጠብ ያቃታቸውን አክስትህን (ዘመድህ ባይሆኑም)እርዳቸው ።

👴🏿እናንተ ሰፈር ያሉትን ደካማውን አጎትህ፣ ልብሳቸው ቆሾባቸዋል፣ ጽማቸው አድጎ የሚያስተካክልላቸው አተው ፣ ጸጉራቸው እንዲው ተንጨባሩዋል፣ እና ዛሬውኑ ሂድና አግዛቸዋ።

👏ስለምታደርገው ጌታ ይባረከሃል።

ታሪኩም ሲያልቅ
👉 ያች ያህዋ ባልተት ለነብዩ ምግቡን መጠጡንም ከተረፋት ሳይሆን ካላት ያውም ከጥቅቱ ሰጠችው። ለርሷም ጌታ በእጥፍ መለሰላት👇

"" ኤልያስም አላት። አትፍሪ፤ ይልቅስ ሄደሽ እንዳልሺው አድርጊ፤ አስቀድመሽ ግን ከዱቄቱ ለእኔ ታናሽ እንጎቻ አድርገሽ አምጭልኝ፥ ከዚያም በኋላ ለአንቺና ለልጅሽ አድርጊ፤"

" የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። በምድር ላይ እግዚአብሔር ዝናብ እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ፥ ዱቄቱ ከማድጋ አይጨረስም፥ ዘይቱም ከማሰሮው አይጎድልም።"
" እርስዋም ሄዳ እንደ ኤልያሳ ቃል አደረገች፤ እርስዋና እርሱ ቤትዋም ብዙ ቀን በሉ።"
" በኤልያስም እጅ እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ዱቄቱ ከማድጋው አልተጨረሰም፥ ዘይቱም ከማሰሮው አልጎደለም። "
(መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 17:13-16)

ዛረም ከተረፈው ሳይሆን ካለው የሰጠ ሰው መሆን አለብን።

👍" ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፥ ገንዘብህንም የሚወስድ እንዲመልስ አትጠይቀው።"
(የሉቃስ ወንጌል 6:30)

📢#መልካምነትን.እንኑር
መልካም ምሽት ውዶቼ:;
🙏ከተረፈን.ሳይሆን.ካለን.እንስጥ።

ተ🀄️ላ🀄️ሉን
share በማድረግ ቅንነትን ያስተምሩ።

@abuttysda ላይ አሳብ ይስጡኝ።


💆💆 @samaritanclub 💆💆
💆💆 @samaritanclub 💆💆


ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ይሁንላችሁ ።

ሰላም ውድ የ@samaritanclub ቤተሰቦች ።
እኔ ወንድማችሁ Naol ነኝ፣ የchannel creator:: ቻነላችን ለምን #samaritan እንደተባለ ትንሽ ልንገራችሁ።

#samaritan ማለት 'ሳምሪያዊ' ማለት ስሆን፣ ይህም ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ አራት (4) ግዜ እናገኘዋለን ።

1⃣የመጀመሪያው በሉቃስ 10:33 ላይ እናገኛለን ።
33" አንድ #ሳምራዊ ግን ስሄድ ወደ እርሱ መጣ አይቶትም አዘነለት"።

2⃣ቀጣዩ እዛው በሉቃስ 17:16 ላይ እናገኘዋለን ።

📝"እያመሰገነውም በእግሩ ፍት በግንባሩ ወደቀ፤ እርሱም #ሳምራዊ ነበር"

3⃣ በዮሐንስ 4:9* ላይ #ሳምራዊት የሚል ቃል እናገኛለን ።
📜"ስለዚህም ሳምራዊቲቱ። አንተ የአይሁድ ሰው ስትሆን፣ #ሳምራዊት ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንደት ትለምነኛለህ? አለችው፤ አይሁድ ሳምሪያውያን ጋር አይተባበሩም ነበር።"

4⃣በዮሐንስ 8:48 ላይ እናገኛለን ።
📜"አይሁድ መልሰው። ሳምራዊ እንደ ሆንህ ጋኔን እንዳለብህ በማለታችን እኛ መልካም እንል የለም? አሉት።

⬆️እንግዲህ ከላይ ከተጠቀሱት ክፍሎች ውስጥ ስለ ሳምራዊያን መልካምነት፣ ገርነት፣ አመስጋኝነትና ሪሁሩነት እንመለከታለን።

የእኔም አሳብ ይህ ነው፥ ከመጠን በላይ እራስ-ወዳድነት ፣ክፋት፣አመጸኝነትና ምስጋና-ቢስነት በነገሰባት አለም ፤ እንደ ሳምራዊው ሰው ገር ፣ቅንና እሩሩህ እንድንሆን @samaritan ያልኩት ።

በሉቃስ 10:33-35 ያለውን ክፍል እንድታነቡት አደራ እላችኋለሁ ። የስብስባችንም አሳብ በዚህ ክፍል ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ።

" #የቅኖች_መንገድ_ከክፋት _መራቅ_ነው_መንገዱን_የሚጠብቅ_ነፍሱን_ይጠብቃታል ።
" ምሳሌ 16:17

#_ለቅኖች_ብርሃን_በጨለማ_ወጣ ...።
መዝ 112:4
#_ጠማማ_ሁሉ_በእግዚአብሔር_ፍት_ርኩስ_ነው_ወዳጅነቱ_ግን_ከቅኖች_ጋር_ነው_።_
ምሳሌ 3:32

📢 መልካምነትን.እንኑር

📢 ቅንነትን.እናስብ

መልካም ግዜ🙏

በቅንነት share እናድርግ።

ለአሳብ አስታየት @SAMAAritanclub_bot ን ይጠቀሙ።

💚💚 @samaritanclub 💚💚
💚💚 @samaritanclub💚💚


Forward from: àßütty Tata
ሰላም ውድ ቤተሰቦች ::
በተከታታይ እየተላለፈ ያለው ትህምርት እንደት አያችሁት??

ካለፈው ትምረታችን ትንሽም ቢሆን አንዳች ቁም ነገር እንደጨበጣችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
አሳባችሁ አስታየታችሁ በጣም ስለምደግፈን @SAMAAritanclub_bot አዘጋጅተናል። አሳባችሁን በ ግልጸኝነት አድርሱን።

መልካም ግዜ


#ገንዘብ_ላላቸው_ወደ_እግዚአብሔር_መንግስት_መግባት_እንዴት_ጭንቅ_ይሆናል ?
(ሉቃ 18:24)

ከአባታችን.ከእግዚአብሔር ከጌታችንም.ከእየሱስ ክርስቶስ.ጸጋና ሰላም.ይሁንላችሁ ።

አንድ ባለጸጋ ሰው ወደ ጌታችን ይመጣና
"ቸር መምህር ፣ የዘላለም ሕይወት እወርስ ዘንድ ምን ማድርግ አለብኝ?"

ኢየሱስ መልሶ
".....ትዕዛዛቱን ታውቃለህ አታመንዝር፣አትግደል ፣አትስረቅ ፣በሐሰት አትመስክር ፣አባትህንና እናትህን አክብር አለው።"

ባለጸጋውም
"እሱን ከሕጻንናቴ ጀምሬ ጠብቅአለሁ አለ።"

ኢየሱስም
"...አንዲት ቀርተሃለች፤ #ያለህን_ሁሉ_ሽጠህ_ለድሆች_ስጥ። "

ባለጸጋውም ይህንን ስሰማ በጣም አዘነ ምክንያቱም በጣም ባለጸጋ ነበርና። እናም ተመልሶ ሔደ።

እናም ክርስቶስ በጣም አዝኖበት፥ ገንዘብ ምንያህል ከፈጣሪ እንደምበልጥባቸው፣የክፋት ሁሉ ምንጭ እንደሆነና (እንደ አጠቃቀም )የዘላለም ሕይወትን እንደሚያሳጣም ተናገረ ።

🤔አስብ አንድ ወንድምህ፡ በመንገድ ላይ እየሄድክ እርቃኑን ብታየው እና በውድ ብር የገዛከውን jacket ለብሰህ ብታገኘሁ ትሰጠዋለህ?

ከዚህ በፊትስ አልፈኃው አታቅም??🤔🤔


😡ያንን ወንድምህን ካለፍከው ፥ ምትወደውን ጌታህን እንዳለፍከው እወቅ !!

እናም ዛሬ አንተም ወንድምህን አትለፈው።

"ወዳጆች ሆይ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን ፥እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባል"
(1ዮሐንስ 4:11)


📢መልካምነትን እንዘምር

መልካም ግዜ


ከወደዳችሁት share በማድረግ ይደግፉን።

ለማንኛውም አሳብ @abuttysda ላይ ያድርሱኝ🙏

@samaritanclub
@samaritanclub


#የሚበሉትን_እናንተ_ስጡአቸው ።
(ማቴ 14:13-21)
ከአባታችን.ከእግዚአብሔር.ከጌታችንም.ከኢየሱስ.ክርስቶስ.ጸጋና.ሰላም.ይሁንላችሁ ።

#ፍላጎትን_ማገልገል።

ጌታችን.ምድር.ላይ.የወንጌሉን.ስራ.በሚሰራበት.ግዜ.ለሰዋች.በቅድሚያ.ፍላጎታቸውን.ያገለግላቸው.ነበር ።

💆‍♂💆አካላዊ.ህመም.ላለባቸው.በቅድሚያ.ከስቃያቸው.እረፍትን.ይሰጣቸዋል.ከህመማቸውም.ያሳርፋቸዋል ።
"በዚህም ግዜያት አንድ ለምጻም ሰው ወደ ኢየሱስ መጣ፤ በግንባሩም ተደፍቶ "ጌታ ሆይ! ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ!" አለ።
ኢየሱስም አጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና "ፈቅጃለሁ ፥ ንጻ!" አለው። ለምጻሙም ወዲያውኑ ከለምጹ ነጻ።
(ማቴ 8:2-3)
🍔 ለተራቡትና.ለተጠሙ.ወገኖች.በነፃ.ይመግባቸዋል ።
"....አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ አንስቶ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና የምስጋና ጸሎት አደረገ፤ እንጀራውንም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ አቀረቡ። ሁሉም በልተው.ጠገቡ ።
(ማቴ 14:19-20)

"እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፥ "የተጠማችሁ ሁሉ ወደ ውሃ ኑ ፤ የምትገዙበት ገንዘብ የሌላችሁ ኑ ፤ ያለ ገንዘብና ያለ ዋጋ እህል ወስዳችሁ ብሉ፤ የወይን ጠጅና ወተትም በነፃ.ጠጡ ።
(ኢሳ 55:1)

🔗⛓ ለታሰሩትና.ተስፋቸው.ለጨለመባቸው.ወገኖች.ነጻነትንና.መጽናናትን.ያበስራቸው.ነበር ።
"ፍርድን ድል ለመንሳት እስኪያወጣ ፥ የተቀጠቀጠን ሸንቦቆ አይሰብርም የሚጤስም የጠዋፍ ክርም አያጠፋም።
"አሕዛብም በስሙ ተስፋ ያደርጋሉ።"
(ማቴ 19:20-21)

👕👗 ለታረዙትና.መጠለያ.ላጡም.መሸሸግያቸው.ነው።
"እግዚአብሔርም ለድሆች መጠጊያ ሆናቸው ፥ እረሱም በመከራቸው ግዜ ረዳታቸው ነው።"
(መዝ 9:9)

ከብዙው.በጥቅቱ.ለመጥቀስ.ያኽል.ነው።👆

እናም.ዛሬ.ራሃብ.እያንገበገበው.ጉሮሮው.ደርቆ.እያሌ
📜ስለ.መንግስቴ.ሰማያት ብትሰብከው
🗞ሰለ.ፍረድ.ሺህ.ግዜ.ብትነዘንዘው
📖ስለ.ጽድቅ.ደጋግመህ.ብትዘምርለት

ሊሰማህ.አይችልም.ምክንያቱም.ከሱ.በፍት.የሚያስፈልገው.ነገር.ስላለ.ነው ።

ወንገልን ለሕዝብ ሁሉ ማዳረስ የሁላችንም ኢላማ ነው፥ ነገር ግን ቅድመ ሁኔታዎችን አላሟላንም!!

ወንድምህን አፍንጫው ላይ እያሳከከው ፥ ወገቡን ብታክለት ይጠቅመዋልን ???



በመጀመሪያ ለወዳጆቻችን ፍላጎታቸውን ካገለገልን፥ ሌላው አይከብደንም !!!

" ከእናንተ እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም ይሸከም እንዲሁም የክርስቶስን.ሕግ.ፈጽሙ።"
(ገላ 2:6)

📢መልካምነትን እንዘምር
📣ሰናይ ምሽት

ለወዳጅ ዘመዶ share በማድረግ ይጋብዟቸው!

@samaritanclub
@samaritanclub


Forward from: àßütty Tata
እንደምን ውላችኋል የአባቴ ልጆች። 🌕🌕🌕🌕
እስኪ ትንሽ ሀሳብ ልበላችው....

🤔🤔🤔🤔🤔


ራስንህን ካልካድ መኖር አትችልም(ማር 8:34 )
ሊከተለዉ የሚወድ ካለ እራሱን መካድ እንዳለበት ይናገራል...

ራሱን መካድ የሚችል ሰው መንፈስ ቅዱስ ያለው ሰው ብቻ ነው።
፨ የተፈጥሯዊ ሰው የሚሰራው በራስ ወዳድነት ላይ የተመሰረተ ነው።
፨ የምንሰራው ፣ የምንለብሰው፣ የምናደርገው ለራሳችን ነው።
፨ ስሜታችን ቢጎዳ ፣ ብንቆጣ ራሳችንን ከመውደዳችን የተነሳ ነው።
፨ ሰው በተፈጥሮው ራስ ወዳድ በመሆኑ ነው አለም ሀጢያት እና መከራ የበዛባት።
፨ ሰዉም ከእግዚአብሔር ተለይቶ የቀረው በራስ ወዳድነቱ ነው።
፨ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር የመጣው እኛን ከራስ ወዳድነት ሊለየንና ከእግዚአብሔር ጋር ሊያስታርቀን ነው ( 2ቆሮ 5:15) በክርስቶስ መንፈስ ዳግመኛ የተወለደ ሰው ለራሱ አይኖርም።
፨ የሚኖረው ለክርስቶስ ነው እንዲህ አይነት ሰው በደስታ መስጠት የማይገባውን የውጪውን ኮቱን አውልቆ ይሰጣል፣ መስጠት ባህሪው እንጂ ሀሳብ አይሆንበትም፣ ለኔ የሚለው ነገር አይኖረውም፣ አንዘንጋ ያለን ገንዘብ፣ ንብረት ሆነ እኛም የኛ አይደለንም ባለቤቱ ጌታ ነው።
👉 በመጋቢነት እንድናስተዳድር ተቀመጥንበት እንጂ የኔ ልብስ፣ ቤት፣ ምግብ... ማለት አንችልም " #ነገር_ግን_የዚህ_አለም_ገንዘብ_ያለው_ወንድሙም_የሚያስፈልገው_ሲያጣ_አይቶ_ያልራራለት_ማንም_ቢሆን_የእግዚአብሔር_ፍቅር_በርሱ_እንደት_ይኖራል?
(1ኛ ዮሐንስ 3:17) እናም ውዶች እራሳችንን እንይ በክርስቶስ ትምህርት ምንያህል እየኖርንበት ነው???

ባልንጀሮቻችንን እንደራሳችን እንውደድ።


መልካም ምሽት👋👋👋👋

📢መልካምነትን እንዘምር

ለወዳጅ ዘመዶ share እንድታድርጉት በጌታ ፍቅር እንጋብዞታለን።

@samaritanclub
@samaritanclub


#የሚጎድለኝ_ምንድንነው ??
(ማቴ 19፡16-30)


ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን ።

በነፃ ተቀበላችሁ፥ በነፃ ስጡ።
(በከንቱ ተቀበላችሁ፥ በከንቱ ስጡ።) (ማቴ 10፡8)

➡️ሁላችንም ጌታን(ፈጣሪን) የመከተል ፍላጎት አለን ፣ እንፈልገዋለንም። ነገር ግን በሙላት ጌታን ተከትለን ወደ ተፈለገው ግብ ደርሰናል ሆይ???
➡️ጌታን አየተከተልን ነው ብለን አናስብ??


ከ እጻንነታችን ጀምሮ ክርስትናን ትከታትለን ይሆናል ፣

🔸ወላጆቻችንን እናከብራለን!።
▪️አንሰርቅም!
◽️አንዋሸም!
🔻ገዳይ አይደለንም !
🔺አናመነዝርም!

ብቻ ሁሉንም ፲ቱ ትዕዛዛትንና የቤተክርስቲያንን ወግና ደንብ እንጠብቃለን። ግን በቅ አይደለም‼️

🤔እና ምን ጎደለኝ❓ ???


ግን ይህ ሁሉ ክርስቶስን ለመከተላችን በቂ አይደለም!!

👉ወንድማችን እና እህቶቻችን ቁራሽ ዳቦ አታው ፆማቸውን ስያድሩ እኛ ከየአይነቱ እየመረጥን በልተን የምናድር ከሆነ ።!❗️
👉እኛ fashion ልብስና ጫማ እየመረጥን እየለበስን ባልንጀራችን ድሪቶ ሚለብስ ከሆነ ፣
👉እኛ በጣም ውድ የሆነ ቤት 🏘ወስጥ፥ የቅንጦት እቃዋችን(ኮንትሮል ቢፌ) ሰብስበን እየኖርን ባልንጀራችን መጠለያ አጥቶ በብርድና በውርጭ እየተሰቃየ የሚኖር ከሆነ።
👉ከዚህ ሁሉ አብት ንብረታችን ድንገት አንድ የቸገርው ባልንጀራችን ሲመጣ፥ ትራፊ፣ ፍርፋሪ ፍለጋ ቤት ውስጥ መዞር፥ ሰውየው ቤት ውስጥ እንዳይገባ መጠንቀቁ፣ ፍርፋሪውን በቆሻሻ እቃ(ለራሳችን ማንጠቀመውን) መስጠቱ።

👉 ይህን ሁሉ ጉድ ተሸክመን ወደ ቤተክርስቲያን ስንሄድ እኛ ሱፋችንንና በውድ የተገዛ ጫማችንን አድርገን ፤ ሌላው ደግሞ ባዶ እግሩ ፣ቡቱቶ ለብሶ ፤ በአንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማምለክ፣ እዛው ውስጥም ለራሳችንና ለድሆች ቦታ መለየታችን!!


☝️እናም ይህን ሁሉ እያደረግን፣
🎤🎸መዝሙራችን እንደት ይማርካል ??
🎤ስብከታችንስ እንደት ይለውጥ???
🤦‍♂ፈጣሪስ በአምልኮአችን እንደት ይደሰት???

ስለዚህ
"...... ፋጹም ልትሆን ብትወድ ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆችና ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ።"
(ማቴ 19:21)

ዛሬውኑ ማድረግ የምንችለውን እናድርግ!!

📣መልካምነትን እንዘምር
📢መልካም ቀን

ከወደዳችሁት ለወዳጅ ዘመዶ ሼር ያድርጉና ይደግፉን🙏

ለአስታየቶ @abuttysda ይጠቀሙ።

@samaritanclub
@samaritanclub


#የአገልጋዮች_አገልጋይ

(ሉቃ 22:7_18፤ 24፤ ዮሐ 13:1-17)

ከእግዚአብሔር አብና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

ዛሬም እንደተለመደው ከመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ክፍል በሥዕላዊ ጽሑፍ እንመለከታለን።



አንድ በዝምታና በትንሽ ብርሃን የተሞላ አደራሽ አስራ ሁለቱን ደቀመዛሙርትንና አለቃቸውን በውስጡ ይዟል ። ክፍሉ ውስጥ ሁለት ከመሬት ትንሽ ከፍ ብሎው የተቀመጡ ሁለት አግዳሚዎች ከፍት ለፊት ይታያሉ፣ አሥራ ሁለቱ ደቀመዛሙርትም ከግራና ቀኝ ሆነው በአግዳሚው ላይ ተሰይመዋል፣ መሃል ላይ የተዘረጋው ሼልፍ ላይ ተለቅ ተደርጎ የተጋገረ እንጀራ (ሕብስት ) ይዟል፣ በአጠገቡም ጽዋ ይታያል። በቤቱ ውስጥ ዝምታው ደስ የምል የተረጋጋ መንፈስን ይዘራል ፣ ግርጌ ላይ የተንጠለጠለው ጦዓፍ (ችቦ) ከውጭ የሚመጣው ጨለማ ቤቱ ውስጥ እንዳይነግሥ ከልክሏል ። ቤቱ ደስ በሚል ብርቱካናማ ብርሃን ተውቧል። ከጠዋፉም አጠገብ የእግር ማስታጠቢያና የእግር ማድረቂያ መሃረብ ይታያሉ፣ በአጠቃላይ በዚያ ቤት ውስጥ "ግብዣ" እንዳለ ያስታውቃል ።

ግብዣውም ተጀምሮ ከጨረሱ በኋላ እግራቸውን መታጠብ ነበረባቸው ። የሁሉም ሐዋሪያት አሳብ "ማነው ከሁሉም አስቀድሞ እግራችንን የሚያስታጥበን?? ማነው ታናሹ? ማነው የአገልጋዮች አገልጋይ?? ብሎ ሁሉም ይጠባበቅ ነበር።

እናም
👴🏻ጴጥሮስ በልቡ አንዲሀ ይል ነበር
🤔"መቼም ቢሆን እኔን እየጠበቁኝ አይሆንም። በእድሜና በእውቀት እበልጣቸዋለሁ። አድስ ነገር ማመጣው ራሱ እኔ ነኝ። አይ አይ እኔ እንኳ ከፉክክሩ ውጭ ነኝ።"" ብሎ ይጠባበቃል።
ሁሉም በዝምታ ተውጦአል፣ አይኖችም ሁሉ👀 ወደ ማስታጠቢያው ያያሉ😳።

ይሁዳም በአሳቡ
👳🏽🤔"ምን እነዚህ ፣ይሄኔኮ ብር መጠየቅ ብሆን ኖሮ ፣ እንደምናምን ከበውኛል። ሆዳም ብቻ።"

👱🏻👨🏻 ዮሐንስና ያዕቆብ ደግሞ የዛን ሰሞን የሚንስተሪነት ማመልከቻ በእናታቸው በኩል ለመምህሩ አስገብተው ነበሪና ፣እንዲህ ይባባላሉ።
ዮሐንስ "ስማ ያዕቆብ ፣ተነስተህ እንዳታስጀምር።"
ያዕቆብ "እሺ ወንድሜ ።ከተነሳውማ ያንን ማመልከቻ ውሃ በላው። ጭራሹንም እንደ ታናሽ አድርገው ነው ሚቆጥሩን አታስብ አልነሳም።"
ዮሐንስ "ጎሽ ጎበዝ፣ ገብቶሃል ማለት ነው።" ብለው ያንሾካሽኩ ነበረ። ሁሉም እራሱን ከማስታጠብ አግልሏል ።

ኢየሱስ የሁላቸውንም አሳብ ያውቅ ነበርና ፣በውስጡ ይገረማል ።
እራሱንም
"በሰማይ ዙፋን ላይ ፣ ከፍ ካሉ ሁሉ ከፍ ብሎ ባለው ዙፋን ላይ ሆኖ፣ በማይገመት ብርሀን ውስጥ አንዳች የመለኮት ጉድለት ሳይኖርበት ከአብ እኩል በዙፋኑ ላይ ሆኖ እራሱን ያይ ነበር።

6 "እርሱ የመለኮት ባሕርይ አለዉ፤ ይሁን እንጂ ፥ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የሚያደርውን የመለኮት ባሕርይ እንደ ያዘ መቅረት አልፈለገም።
7"ይልቁንም ያለውን #ክብር በገዛ ፈቃዱ ትቶ አገልጋይ መሆንን መረጠ።
8"እንደ ሰው ሆኖም በትሕትና ራሱን ዝቅ አደረገ፤ እስከ ሞት ድረስ ፥ ያውም #በመስቀል ላይ ተሰቅሎ እስከ መሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ።
( ወደ ፈልጵስዩስ ሰዋች 2:6-8)

ይህንን ሁሉ አሰበና ፥ለራሱ ዝምታውን ያይረብሽ ብድግ ብሎ ተነስቶ ፣የለበሰውን ልብስ አውልቆ። ያ ያደፈውን የአገልጋዮች አገልጋይ የሚለብሰውን ለብሶ ፣
4"......ልብሱን አስቀመጠ፤ ፎጣም አንስቶ በወገቡ ታጠቀ። 5 ከዚህ በኋላ በመታጠቢያ ሳሕን ውሃ አድርጎ የደቀመዛሙርቱን #እግር ማጠብ ጀመረ፤ በታጠቀውም ፎጣ እግራቸውን አበሰ።
( የዮሐንስ ወንጌል 13:4-5)

ወገኖቼ እዚህጋ ቆም ብለን እናስብ፥
🌊ኢየሱስን ፈጣሪ ነዉ። የሁሉም ነገር ፈጣሪ።
የከዋክብት🌟
የሰው ልጆች 👨‍👩‍👧‍👦
የእጽዋት 🌿☘🍂🍃
የእንስሳት🐑🐏🦍🐘
ሰማይና ምድርን 🌊
ባህርና የውሃ ምንጮችን💨🌩

እና ሰማይን በዘረጋ እጁ፣ከዋክብትን በሰሩት እጆቹ፣ እኔ፣አንተና አንቺን የጥበብ መደምደሚያ አድርጎ በሰሩት ጣቶቹ እግር ሊያጥብ፣🙈

❓ እኛስ ዛሬ ትንሽዬ ስልጣን ወይም ውድ ልብስም ለብሰን እነኳን ጎንበስ ማለት ምነኛ ይከብደናል?!
❓መንገድ ላይ የወደቁ ወገኖቻችን እንዳያቆሹን ምን ያህን እንጸየፋቸዋለን?!
❓እግር ማጠብ ይቅርና ትንሽ #ደሃ፣ #ችግርተኛ፣ #አሮጌ ልብስ የለበሰውን ወገናችንን #ሰላም ማለት አልከበደንም??

❗️እናም በእነዚያ ሙታንን ያስነሱ ፣ ድንቅና ታአምራትን ባደረጉ እጆቹ፤ የእነዚያን ሰዋች እግር ሊያጥብ ጎንበስ አለ።


‼️‼️አይገርምም‼️⁉️

ሁሉም ተደነቁ ፣ ገርማቸው ፣ ማመን አቃታቸው ። ጴጥሮስ እንቢ አለ።

እኔም እደነቃለሁ ‼️
ምክኒያቱም

ያታላቅ አምላክ
ከሰማይ ሰማያት ዙፋኑ
⬇️
ወደዚች አስጠልታ ምድር
⬇️
ያውም ስጋን ለብሶ
⬇️
ሕፃን ሆኖ በሰው(ሴት) ማህፀን ውስጥ አድሮ
⬇️
በበረት ተወልዶ
⬇️
የአገልጋዮቹን እግር አጥቦ
⬇️
ተገርፎልኝ ፣ቆስሎልኝ
⬇️
ሙቶልኝ
⬇️
ያውም የመስቀል✝ ላይ ሞት።

ሰለዚህ በጣም ብገረም አይገርምም🤷‍♂።

አጠበላቸው፣ በአውአራ የተበላሸውን እግራቸውን አጥቦ አደረቀላቸው።።

🔹ወገኖቼ እኛስ ዛሬ ማንን ነው መርዳት ያለብን???
🔸እራሳችንን ብቻ ምንወድድ ከሆነ ማጥፊያችን እራሳችን ይሆናል

፲፫'እናንተ 'መምህርና ጌታ ' ትሉኛላችሁ ፤ እኔ መምህርና ጌታ ስለሆንሁ ያላችሁት ትክክል ነው።
፲፬'እንግዲህ እኔ ጌታችሁና መምህራችሁ ስሆን እግራችሁን ካጠብኩ፥ እናንተም እርስ በርሳችሁ እግራችሁን መተጣጠብ ይገባችኋል ።
(የዮሐንስ ወንጌል ፲፫:፲፫_፲፬)



በትዕግስት ስላነበበችሁ ጌታ ይባርካችሁ ።🙏

"እንግዲህ ከመካከላችሁ የበላይ ሊሆን የሚፈልግ የሁሉም አገልጋይ ይሁን።"
(የማርቆስ ወንጌል 10:44)


መልካም ግዜ

ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ share ያድርጉና ይደግፉን🙏

share

Join

@samaritanclub
@samaritanclub


የቀጠለ
በእውነተኛ ደግነት እንጂ በሥርዓቱ ፣ በሚከተለው ቀኖናና የስግደት ዓይነት አይደለም ።


በሉቃስ ወንጌል 10:25-37

አንድ የሕግ ምሑር ኢየሱስን እንድህ ብሎ ይጠይቅ ነበር "መምህር ሆይ !የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ ይገባኛል?" ክርስቶስም "በሙሴ ሕግ ምን ተጽፎአል ? አንብበህስ እንደት ትረዳዋለህ?" ብሎ በመጠየቅ ጠያቂውን መልስ እንድሰጥ ጋበዘው።
"ሕጉማ እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ ፣ በፍጹም ነፍስህ በፍጹም ኃይልህ፣ በፍጹም አሳብህ ውደድ ፣ እንዲሁም #ባልንጀራህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ አለው።"
ኢየሱስም "በትክከል መልሰሃል፣ እንግዲህ አንተም ይህን አድርግ የዘላለም ሕይወትም ታገኛለህ" አለው።


ትልቁ ጥያቄ አሁን ነው " ለመሆኑ ባልንጀራዬ ማን ነው???"

ዛሬስ ወዳጄ ባልንጀራህ ማን ነው??
👴🏿በዘርና በክልል ውስጥ ያሉ ናቸዉ ?
✝☪በ ሃይማኖትህ ውስጥ ብቻ የምገኙ ናቸው?
💰💸በ economy ከንተ ጋር የምስተካከሉና ካንተ የምበልጡ ናቸው?

እስኪ ዛሬ እራሳችንን እንጠይቅ! በዘር፣በቋንቋ ፣በቀለም፣እና በሃይማኖት የሰውን ልጅ ለይተን አናቅም??

እንግዲህ የሕግ ምሁሩ ለጠየቀው ጥያቄ ፥ ጌታችን መልስ ሲሰጠው እንዲህ አለ።
"አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ሲወርድ በመንገድ ላይ ሳለ፣ የቀኑ ተረኛ ወንበደዎች አግንተውት ልብሱን ገፈፉት እስኪ በቃው ድረስ ከደበደቡት በኋላ ሊሞት ሲያጣጥር ጥለውት ሄዱ። ከእያሪኮ ወደ ኢየሩሳሌም የምወስደው መንገድ በመሃሉ ሸለቆአማ ነው ብዙ ወንበዴዎች እዛ ይገኛሉ ። እስከ ዛሬ ይህ ቦታ የደም ጎዳና በመባል ይታወቃል።
እንዳጋጣሚ አንድ #ካህን በዘመኑ አጠራር (pastor) በዚያ መንገድ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ነበር ፥ ያው ወደ አምልኮ ይሆናል፨ እናም በመንገድ ዳር የሚያቃስት ድምፅ ይሰማና ትንሽ ተጠግቶ ያየዋል! እናም በልቡ "🤔 አሁን ይህን ሰውዬ ቢነካካው ድንገት በእጄ ላይ ልሞት ይችላል፥ የሞተ ሰውን የነካ ደግሞ ሙሉ ቀን እርኩስ ይሆናል። ስለዝህ መሄድ አለብኝ" ብሎ ምንም ሳያደርግለት በሌላ በኩል አልፎ ሄደ። አንተስ ዛሬ ምታስታውሰው/ሽው አጋጣሚዎች የሉም? ቤተከርስቲያን እየሄድክ/ሽ ያለፍካቸው/ሽአቸው እርዳታን የምፈልጉ ወገኖችን??
እንዲሁም ከካህናት ወገን የሆነ አንድ ሌዋዊ በዘመኑ አጠራር (ዲያቆን) በዚያ መንገድ ይሄድ ነበር። እሱም ድምፁን ሰምቶ ተጠግቶ አየውና እሱም ሰዓቱን መልከት አድርጎ ⌚️" ሆሆሆ እኔ ለ choir ምሳሌ መሆን አየተገባኝ ፤ እዝህ መርፈድ የለብኝም" ብሎ በሌላ መንገድ አልፎ ሄደ።

እነዚህ ሁለት ሰዋች የተቀደሰ ሥራ የነበራቸውና የቅዱሳት መጻሕፍት አስተማሪዎች ነን ባዮች ነበሩ። እንዲሁም "ደንቆሮዎችንና ስሕተተኞችን በርኅራኄ "የመመልከት ግደታ አለበት። ዕብራውያን 5፡2

" የጠላትህ ላም ወይም አህያ ጠፍቶ ብታገኝ መልስለት። አህያውም ከጭነቱ ክብደት የተነሳ ወድቆ ብታገኝ ፤ አህያውን ከወደቀበት ለመነሳት እንዲችል እረዳው እንጂ አልፈኸው አትሂድ ።" ዘጸ 23፡4፣5።
አነዚያ ፈሪሳውያን እንዲህ ይሉ ነበር፥ "ከሰማርያ ወገን ከሆነች እርጉዝ ሴት እያመጠች እርዳታህን ብትፈልግም አትርዳት ይሉ ነበር።


አንድ ሳምራዊ ሰው በጉዞ ላይ እንዳለ በመሰቃየት ላይ ወደነበረው ሰው ደርሶ ባየው ግዜ ራራለት። ያ አደጋ የደረሰበት ሰው አይሁድ ወይም አረማዊ መሆኑን አልጠየቀም። ሳምራዊዩ መንገደኛ አደጋ የደረሰበት እርሱ ቢሆንና ያኛው አይሁድ ቢሆን በፈቱ ላይ ምራቁን ተፍቶበት እንደሚሔድ ያውቅ ነበር። ነገር ግን ስለዚህ ጉዳይ ቂም አልያዘም አላመናታም ። በዚያ ቦታ ላይ በመቆየት አደጋ ይደርስብኛል ብሎ አልተጨነቀም ነበር። የሚያስፈልገውና በመሰቃየት ላይ ያለ ሰብአዊ ፍጡር ከዚያ መኖሩ ብቻ ነበር ያሳሰበው።
👕የራሱን ልብስ አውልቆ አለበሰው።
💆‍♂በሽተኛውን ተሸክሞ በአህያው ላይ ካስቀመጠው በኋላ በእንቅስቃሴ ምክንያት ሕመሙ እንዳይሰማው በማሰብ በጥንቃቄ እያዘገመ ይዞት ሔደ ።
👨‍⚕ሌሊቱን እየተንከባከበው አደረና ጠዋት በሽተኛው የተሻለው መሆኑን ካየ በዋላ ጉዞውን ለመቀጠል ተነሳ ።
💸የሚያስፈልገውን ሁሉ ለእንግዳ ማረፊያ ጠባቂ ከክፍለ በዋላ ፣ይህ ስላላረከው ስለሚደረግለት ተጨማሪ እርዳታ "ይህን ሰው በጥንቃቄ አስታምልኝ፣ ተጨማሪ ወጪ ብታደርግም በምመለስበት ጊዜ እከፍልሃለሁ" የሚል ቃል ገባ።

ኢየሱስ ቀጠለ"ባለንጀራህ ማነው?" ብሎ ጠየቀው
የሕግ መምህሩም "ያ የራራለት የረዳው ነዋ።" አለ


👬እንግዲህ ባልንጀራነት የሚባል ነገር አንድ ሰው አባል በሆነበት ቤተከርስቲያን ወይም በሚከተለው እምነት ክልል የተወሰነ አለመሆኑን አስረዳ ። ባልነጀራነት በጎሳ፣ በቀለምና በማሕበረሰብ ክፍል አይወሰንም።

👭እርዳታችን የሚያስፈልግው ሰው ሁሉ ባልንጀራችን ነው።

👫የ እግዚአብሔር ፍጡር የሆነ ሰብአዊ ዘር ሁሉ ባልንጀራችን ነው።

"እግዚአብሔርን እወዳለሁ አያለ ወንድሙን የሚጠላ ሐሰተኛ ነው፣ ያየውን ወንድሙን የማይወድድ ከሆነ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወድድ አይችልም"
👨‍❤️‍👨እኛ እርስ በርሳችን ብንፋቀር እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል፣ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል"
1ዮሐንስ 4:20፣21


📣📣መልካምነትን እንዘምር
📢📢መልካም ቀን።

Join
@samaritanclub
@samaritanclub


#ርህሩህ_ሳምራዊ እና #እወነተኛ_ሃይማኖት።
ሉቃ.10:25-37
እውነተኛ ሃይማኖት ምንድነው? እንዴትስ ትገልጸዋለህ/ሽ ?

ክርስቶስ የርህሩህን ሳምራዊ ታሪክ በመናገር የእውነተኛ ሃይማኖትን ምንነት ገለጻ ። እውነተኛ ሃይማኖት የሚታወቀው #በፍቅር ላይ ተመሠረተ ድረግት፣ሌሎችን በሚጠቅም በጎ አድራጎት ነው።


" #ነገር _ግን _የዚህ_አለም_ገንዘብ_ያለው_ወንድሙም _የምያስፈልገው _ሲያጣ_አይቶ_ያልራራለት_ማንም_ቢሆን_የእግዚአብሔር _ፍቅር_በእርሱ_እንዴት_ይኖራል ?" 1ዮሐንስ 3;17

✝ሁላችንም ትልቁ አላማችን የዚህን አለም ጣጣ ጨርሰን ወደ አባታችንና አምላካችን ወዳዘጋጀው ስፍራ መሄድ ነው! ይህ ታላቁ ተስፍችን ነው። ሆኖም ግን እኛ ሰዎች ያውም አማኞች ሆነን ሳለ ከሰማይ ቤት የምአስቀሩን ብዙ ነገሮች ይኖራሉ ። ወገኖቼ ሰማይ የምንገባው:-

⚫️ ቸርች ⛪️በመሄድ ፣
🔴 ትዕዛዛትን በመጠበቅ
⚪️የቤተክርስቲያንን ህግ በመከተል
🔵ለራሳችን ብቻ በመጸለይ እና የተለመደ አይነት አምልኮ ብቻ በማድረግ አይደለም።

እስቲ ዛሬ ቆም ብለህ/ሽ አስብ/ቢ
🤔ባለፈው ሕይወትህ/ሽ ስንት ቀን ወንድምህን/ሽን እህትህን/ሽን ሰለምያስፈልገው ነገር አስበህ/ሽ ታቃለህ/ሽ?
🤔በምትኖርበት/ሪበት አከባቢስ ስንት ሰው ካንተ/ች እርዳታን እንደምሻ ታቃለህ/ሽ?
🤔 ሁሉም ነገር ሰላማዊ በነበረበት ግዜ ቤተከርስቲያን ስትሄድ/ጂ በመንገድ ዳር ሆነው እያሉ እየተጣደፍክ/ሽ ስንት ግዜ አልፈሃል/ሻል?

እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች መልስ ይፈልጋሉ!

ታዲያ ያንተን ያንቺን የእርዳታ እጆችን የሚጠባበቁ ወገኖች ብዙ ናቸውና ዛሬውኑ ድረስላቸው/ሽላቸው!!

18፣ልጆች ሆይ በሥራና በእውነት እንዋደድ እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ። 1ዮሐንስ 3:18


መልካም ግዜ


Join

@samaritanclub
@samaritanclub


ሰላም የተወደዳችሁ የ "ሰማሪታን ክለብ "( #samaritan_club ) ቤተሰቦች! ይህን channel ለማዘጋጀት ያነሳሳኝ ነገር ፣እኛ ሰዋች በወንገል ስራ ውስጥ ትልቅና የተለየ ቦታ ባለው በመረዳዳት ረገድ የራሳችንን አስታዋዕፆ አንድናደርግ ነው።

የዚህም ስብስብ ዋና አላማዎች :-
1. እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነብያትም ይህ ነውና። (ማቴዎስ ወንጌል ፯፣፲፪)

2.
34፣ ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ብሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ግዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግስት ውረሱ።

35፣ተሪቤ አብላታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና።

36፣ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኁልና። (የማቴዎስ ወንጌልን 25: 34-36

3.ከላይ እንደተጠቀሰው የሰማይን ወራሾች እንሆን ዘንድ ።መረዳዳት አለብን ፣ የወደቁ ወዳጆቻችንን ማንሳት :-
ሀ.ትልቁ አላማ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ስሆን ይህም በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ ይሆናል።
ለ.የተቸገሩና ድጋፍ ላጡ ወዳጆች የስነልቦና ምክርና ፀሎት ማድረግ።
ሐ.አስፈላግ የሆኑ ነገሮችን ካሟላን በዋላ ፣የመንግስትን ወንጌለ መስበክ ይሆናል።




Join

@Samaritanclub

20 last posts shown.

133

subscribers
Channel statistics