* እብድ ነኝ *
የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር)
፡
እብድ ነኝ ጨለሌ አቅሌንም የሳትኩ፣
ከዚ አለም ወጥቼ ብቻዬን የከተምኩ፣
ዘንድሮም ወፍፌ አለሁኝ እንዳበድኩ፣
በሆነው ባልሆነው እንደ ሞኝ እየሳኩ፣
አዎ እኔ እብድ ነኝ እያወኩኝ ያበድኩ፣
፡
እብደቴን ወድጄው አብጄ ኖራለው፣
ጤናዬን ጠልቼ በሩቅ ሸሸዋለው፣
፡
አዎ እኔ እብድ ነኝ፣
ማጣት ያሳበደኝ፣
ፍቅር ያናወዘኝ፣
ጤናዬን ያጣሁኝ፣
፡
ታውቃታለህ ስሉኝ አላውቃትም ብዬ፣
በእብደቴ ልረሳሽ ሞከርኩኝ አንቺዬ፣
፡
ስምሽን ሲጠሩብኝ እንደ ሞኝ ስቄ፣
የውስጤን በውስጤ አፍኜ አምቄ፣
አስመስላለሁኝ እውነቱን ደብቄ፣
አላውቃትም እያልኩ እንደ ጅሉ ስቄ፣
፡
አንቺማ ረስተሽኝ ስሜም ጠፍቶብሻል፣
አረ ከነ አካቴው አላውቅም ብለሻል፣
፡
እኔ ግን በእብደቴ አስታውስሻለው፣
ምስልሽን ከቦዩ ከገንዳ አየዋለው፣
ከሰንደሉ ሽታ ጠረንሽን ስባለው፣
ከቅዳጁ ልብሴ ዘንጠሽ ስላለው፣
ካደፈው ገላዬ ነፅተሽ አይሻለው፣
ካልተገራው ፀጉሬ ዞማሽን ዳሳለው፣
ከገረጣው ፊቴ ፊትሽን ነካለው፣
ካመዳሙ ወዜ ወዝሽን ጠቅሳለው፣
ከህዝቡ ጫጫታ ድምፅሽን ሰርቃለው፣
ከተራማጅ መሀል ኮቴሽን እሻለው፣
ወፍፌ አብጄ መች ረሳሻለው፣
፡
ቁር ካቆረፈደው ቆዳዬ ዘልዬ፣
አስታውስሻለሁ ደግሜ አንቺዬ፣
፡
በጫቱ ገረባ መሬቱን ሞንጭሬ፣
አካልሽን ነድፋለው በእንጨቱ ብዕሬ፣
፡
ካፌ ቢሚወጣው የሲጋራ ጭሰት፣
ውልብ ይላል ፊቴ ያለፈው የኛ ወቅት፣
፡
እንድረሳሽ ነበር አውቄ ማበዴ፣
ግን አልወጣ አለኝ እግርሽ ከመንገዴ፣
፡
አይኔ በቆሻሻ ሊታወር ተቃርቦ፣
ያይሻል በስሱ በዕንባ ተከቦ፣
፡
ነፍሴም ከሞት አፋፍ በር ላይ ቁጭ ብላ፣
ንስሀም አልገባች አለች አንቺን ብላ፣
፡
አንጀቴም ተርቦ በጠኔ ተመቶ፣
አንቺን አንቺን ይላል ከምግብ ተጣልቶ፣
፡
አቅሌም ሌላ አያስብ መች ይታየውና፣
ካንቺ ነው ሚኖረው አካሌ ጎዳና፣
፡
ዝም ብዬ ስቃለሁ ደስታው ሳይታየኝ፣
ባንቺ የተነሳ አዎ እኔ እብድ ነኝ፣
፡
የሚል ስንኝ ከላይ ለካ ሰድሬያለሁ፣
ለማንስ ነው የፃፍኩት እኔኮ አብጃለሁ፡፡
፡
21/12/08...ቅዳሜ....3:30 ጠዋት
@yeneta
#ሼር
@sheelff
የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር)
፡
እብድ ነኝ ጨለሌ አቅሌንም የሳትኩ፣
ከዚ አለም ወጥቼ ብቻዬን የከተምኩ፣
ዘንድሮም ወፍፌ አለሁኝ እንዳበድኩ፣
በሆነው ባልሆነው እንደ ሞኝ እየሳኩ፣
አዎ እኔ እብድ ነኝ እያወኩኝ ያበድኩ፣
፡
እብደቴን ወድጄው አብጄ ኖራለው፣
ጤናዬን ጠልቼ በሩቅ ሸሸዋለው፣
፡
አዎ እኔ እብድ ነኝ፣
ማጣት ያሳበደኝ፣
ፍቅር ያናወዘኝ፣
ጤናዬን ያጣሁኝ፣
፡
ታውቃታለህ ስሉኝ አላውቃትም ብዬ፣
በእብደቴ ልረሳሽ ሞከርኩኝ አንቺዬ፣
፡
ስምሽን ሲጠሩብኝ እንደ ሞኝ ስቄ፣
የውስጤን በውስጤ አፍኜ አምቄ፣
አስመስላለሁኝ እውነቱን ደብቄ፣
አላውቃትም እያልኩ እንደ ጅሉ ስቄ፣
፡
አንቺማ ረስተሽኝ ስሜም ጠፍቶብሻል፣
አረ ከነ አካቴው አላውቅም ብለሻል፣
፡
እኔ ግን በእብደቴ አስታውስሻለው፣
ምስልሽን ከቦዩ ከገንዳ አየዋለው፣
ከሰንደሉ ሽታ ጠረንሽን ስባለው፣
ከቅዳጁ ልብሴ ዘንጠሽ ስላለው፣
ካደፈው ገላዬ ነፅተሽ አይሻለው፣
ካልተገራው ፀጉሬ ዞማሽን ዳሳለው፣
ከገረጣው ፊቴ ፊትሽን ነካለው፣
ካመዳሙ ወዜ ወዝሽን ጠቅሳለው፣
ከህዝቡ ጫጫታ ድምፅሽን ሰርቃለው፣
ከተራማጅ መሀል ኮቴሽን እሻለው፣
ወፍፌ አብጄ መች ረሳሻለው፣
፡
ቁር ካቆረፈደው ቆዳዬ ዘልዬ፣
አስታውስሻለሁ ደግሜ አንቺዬ፣
፡
በጫቱ ገረባ መሬቱን ሞንጭሬ፣
አካልሽን ነድፋለው በእንጨቱ ብዕሬ፣
፡
ካፌ ቢሚወጣው የሲጋራ ጭሰት፣
ውልብ ይላል ፊቴ ያለፈው የኛ ወቅት፣
፡
እንድረሳሽ ነበር አውቄ ማበዴ፣
ግን አልወጣ አለኝ እግርሽ ከመንገዴ፣
፡
አይኔ በቆሻሻ ሊታወር ተቃርቦ፣
ያይሻል በስሱ በዕንባ ተከቦ፣
፡
ነፍሴም ከሞት አፋፍ በር ላይ ቁጭ ብላ፣
ንስሀም አልገባች አለች አንቺን ብላ፣
፡
አንጀቴም ተርቦ በጠኔ ተመቶ፣
አንቺን አንቺን ይላል ከምግብ ተጣልቶ፣
፡
አቅሌም ሌላ አያስብ መች ይታየውና፣
ካንቺ ነው ሚኖረው አካሌ ጎዳና፣
፡
ዝም ብዬ ስቃለሁ ደስታው ሳይታየኝ፣
ባንቺ የተነሳ አዎ እኔ እብድ ነኝ፣
፡
የሚል ስንኝ ከላይ ለካ ሰድሬያለሁ፣
ለማንስ ነው የፃፍኩት እኔኮ አብጃለሁ፡፡
፡
21/12/08...ቅዳሜ....3:30 ጠዋት
@yeneta
#ሼር
@sheelff