"ይፈውሰኛል ያልከው ሰው ቁስልህ ላይ ጨው ሲነሰንስበት እንደማየት የሚያም ነገር የለም....የቆሰለው ሰውነትህ አቅምህን ከተጫነው በላይ....ከፈሰሰው ደምህ በላይ የሚፈሰው እንባህ ያቃጥልሀል...."....ማውራቷን ቀጥላለች...
"ከዛ በኃላ ሁሉም ነገር ይታክትሀል...ማውራት ብቻ ትልቅ ዳገት ይሆንብሀል....ማውራት...እንዲህ ሆንኩ ማለት ትርፍ የሌለው ነገር ይሆንብሀል....በቃ ዝምም...በራስህ አለም ውስጥ ጭጭጭ....የራስህ ዋሻ ውስጥ ዘግተህ ትቀመጣለህ..."
"እኔ ነኝ አይደል እንደዚህ ያደረግኩት...?"....በሆዴ አይ አንተ አይደለህም እንድትለኝ እየተመኘሁ በአፌ ይቺን ጠየቅኩ....
"አንተ አይደለህም...."....ኡፎፎፎፎፎይ አልኩኝ በሆዴ....ቀጠለች....
"ጊዜ ነው....ጊዜ ነው አንተ ላይ የጣለኝ....ጊዜ ነው እንደ ፌስታል አሳስቶ የሚያንኮሻኩሸኝ....እሱ ነው...".....ያረጋጋሁት ልቤ በቅፅበት በፀፀት ይነድብኝ ጀመር....እንደድሮ አይደለችም...እንደድሮ የሁሉም ሰው ፊት ላይ ሳቅ ለመፍጠር አትጣጣርም....አይኔን በጥልቀት አታይም...አይኗን ምታሳርፍበት አጥታለች...አንዴ ሰማዩን አንዴ መሬቱን ታያለች....
"ከማልሞግተው ጋር ተጣላሁ...ጊዜን ምን ብለህ ትሞግተዋለህ.....እንዲሁ ቶሎ እለፍ እስኪ ትለው ይሆናል እንጂ "....
✍Shewit