መኖር ቀላል ነው አይደል.....
አዎ ቀላል ነው...ላንተ በጣም ቀላል ነው...ልክ ከመደርደሪያ ላይ ልብስ እንደመመዥረጥ...ልክ ፀጉር እንደመስተካከል....የህይወት መአዛ ላንተ የናርዶስ ሽቱን ያሀል ጣፋጭ ነው። ፈተናም ላንተ ቀላል ነው..."ፈጣሪ የሚወደውን ይፈትናል" ብሎ ማባበልም እንደዛው...
ግድ የለም የኔን መወደድ ውሰድልኝ እና ያንተን መጠላት አውሰኝ...ልብ በል መወደዴን ላትመልስ ወስደህ መጠላትህን ለአፍታ እንድታውሰኝ እየጠየኩህ ነው....ምነው ደነገጥክ...?እድለኛ ነሽ ትለኝ አልነበር......ወዶሽ ይፈትንሻል ብለህ ቃላት አሽሞንሙነህ ከመቀመርህ በፊት ይሄን አላሰብክም ነበር...?
የእኔ ፈተና ከውዴታ የተሰጠኝ ከሆነ ያንተ ድሎት ደግሞ ከጥላቻ ይሆናል ብዬ ነው።ስለተወደድሽ እግርሽን አጣሽ ስትፈቀሪ እጅሽ ተጨመረ ለሚለው ዲስኩርህ ከዚ የተሻለ መልስ አላገኘሁም።
ፈጣሪ ይጥላኝና ላንድ ቀን በእግሬ ልራመድ..አይንሽ ላፈር ብሎኝ ላንዴ እንኳን በእጄ ልመገብ...የፍቅር ጥጉ መቀማት ከሆነ...የመውደድ ልኩ መከልከል ከሆነ ተወው ይቅርብኝ...ከልብህ ከሆነ የኔን ፋንታ ተወደድልኝ።
✍Shewit
https://t.me/shewitdorka