Forward from: Thoughts
"ቡና አይጠጡማ ምን ላድርግ" አልኳት።
እናቴ ደነገጠች "ማለት? ለምንድነው የማይጠጡት?" "ስለማይወዱ ነዋ" አልኳት "ቡና የማይወድም ሰው አለ ማለት ነው" ገረማት
"እና በቃ ቡና ስለማይጠጡ ነው እንደጎረቤት የማትጠያየቁት?" አለቺኝ ተገርማ "ታድያ እሺ ምን ብዬ ልጥራቸው"
" ድሮ እኔ የማውቀው ጎረቤት ቡና ተጠራርቶ ሲተዋወቅ ሲግባባ ነው። የታመመ እንኳን መኖሩ እንኳን የምናውቀው ቡና ስንጠራራ አንዷ ስትቀር አይደለ? የሞተ ሰው ካለ የተቸገረ ካለ የሚሰማው በቡና ሰበብ ስንሰበሰብ ነበረ" አለቺኝ
"ውይ እማ ደሞ ስታካብጂ ነው እንጂ ቡና ከሀሜት የዘለለ ምን ጥቅም ነበረው ብለሽ ነው?" አልኳት "ሀሜቱስ ቢሆን?! ሀሜት ጥሩ ነው እያልኩሽ አይደለም ግን ሰው አፍ ውስጥ ላለመግባት የሚደረገው መሟሟት ትዝ ይልሻል? ፀብ እንኳን ቢኖር ቶሎ ታርቀው ወሬው እንዳይዛመት ነው እኮ የሚደረገው፤ አሁን ግን ታረቅሽ ተጣላሽ እንኳን ሊወራ ዞር ብሎ የሚያይሽም የለ።
ፀቡን ተይው በክብር ሳትዳር የወጣች ልጅ ካለች ሰዉ ዝም አይልም አንድ ሳምንት ቡና መጠጫ ትሆናለች ቤተሰቦቿ ሰው እንኳን ቀና ብለው ለማየት ያፍራሉ።"
" ታዲያ ይሄ ጥሩ ነው??" አልኳት አካሄዷ ስላልገባኝ "በደፈናው ካየሽው ጥሩ ላይሆን ይችላል ውስጠ ወይራው ግን ከዛ በኋላ ሰፈር ውስጥ ያሉ እናቶች በሙሉ ልጆቻቸውን ጠበቅ ማድረግ ይጀምራሉ።" አለቺኝ
"አይገርምም እንደ ዘበት የሚደረግ ቡና መጠራራት እንዴት ማህበረሰቡን እንደሚያንፅ እና እንደሚያስተሳስር" አልኳት ገርሞኝ
"አሁን ልቤን አታውልቂው ሂጂና ጥሪያቸው ቡናው ቢቀር ተጫውተው ይመለሳሉ።"