ውዳሴ ቤቴል - Widase Betel


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


🌼 በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ።
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ።🙏
#ውዳሴ_ቤቴል(@widase_betel)

🌻 ሰላም በዚህ መንፈሳዊ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን አስተምህሮ የጠበቁ  :-
➻ ስብከቶችን ፣ ትረካዎችን ፣
➻ ዝማሬዎችን ከነ ግጥማቸው ፣
➻ ጥያቄዎችን ከተብራራ መልስ ጋር ፣ እንዲሁም የተለያዩ ስነ - ፅሁፎችን ያገኛሉ።
💌 @widase_bot

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


❤ °°° ምስጋናው ይቀጥል °°°

© #ውዳሴ ቤቴል ዝማሬ ™


ምስጋናው ይቀጥል ዝማሬው ይቀጥል ፣
እግዚአብሔር ስላለ ከያዘ የማይጥል ፣
በምናየው ነገር በምንሰማው ወሬ ፣
እንዳይቆም ምስጋናህ እንዳይቆም ዝማሬ ፣

🌻 አዝማች
የሰማዕታቱ ደም የፈሰሰው በምድር ፣
አይተናል ሲያስቀጥል የክርስትናን ዘር ፣
እንድናምን ብቻ መች ተጠራንና ፣
በእሳቱም መካከል ቅኔ አለን ምስጋና ፣

🌻 አዝማች
መች ማጥፋት ይቻላል እሳትን በእሳት ፣
አይቆምም ማኅሌት ቅዳሴ ሰአታት ፣
ከሰማዩም በላይ ከሰማዩም በታች ፣
ቤተ ክርስቲያን ዛሬም ነገም አለች።

🌻 አዝማች
የዓለም ጨው ሆነን በዓለም የበዛነው ፣
እየተደበደብን እየተገፋን ነው ፣
በገደሉን ጊዜ ቁጥራችን ይበዛል ፣
ከሞትም በኋላ ሕይወት ይቀጥላል።
 
🌻 አዝማች
የተስፋይቱን ምድር ተነሱ እንወርሳለን ፣
በመዝሙር በእልልታ ቅጥሩን እያፈረስን ፣
የሰላዮቹን ቃል ሰምታችሁ አትፍሩ ፣
በሃይማኖት ፅኑ በእምነታችሁ ኑሩ።


-----------------
#ዘማሪ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
___

🟩🟨🟥

🔔 ውዳሴ ቤቴል

@widase_betel
🔘 @widase_betel
@widase_betel


#የምህላ_አዋጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ #በጳጉሜ_ወር ለሀገር ሰላም እና አንድነት በመላው ዓለም በምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፀሎት እና ምህላ ወስኗል።

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ፣ ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፥ ቋሚ ሲኖዶሱ 5ቱን የጳጉሜ ቀናት በፀሎትና ምህላ እንዲታሰብ መወሰኑን ገልፀዋል።
#ብፁዕ_አቡነ_ዮሴፍ ፥ 2013 ዓ.ም ብዙ ችግሮችን ያሳየ መሆኑን ያነሱ ሲሆን "በፈተናው ውስጥም ቢሆን ግን ብዙ በረከቶችን ያሳየን ነገሮች አሉ" ብለዋል። እንደሀገር ፤ እንደዓለምም የተከሰቱ ችግሮች ወደቀጣይ ዓመት አብረው እንዳይተላለፉ እግዚአብሔርን በፀሎት መጠየቅ ስላለብን ይህ ውሳኔ ተላልፏል ሲሉ አስረድተዋል።

አክለውም፥ "ቤተክርስቲያን በሀገራችን ውስጥ ያለው ጦርነቱ ፣ ረሃቡ ፣ ስደቱ ፣ መፈናቀሉ ፣ ከቦታ ቦታ ያለው ህዝባችን በስጋት እንዳይኖር ይሄን ሁሉ ጉዳዬ ነው ብላ ወደእግዚአብሔር ማቅረብ አለብን በሚል ቀናቱን በፀሎት እና በምህላ በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እንዲታሰብ ወስናለች" ብለዋል።

"#ወደሰዎች_ሳይሆን_ወደእግዚአብሔር_በመፀለይ ለውጥ ይመጣል ፤ ያጣነው ሰላማችን ይመለሳል ፤ ወደእግዚአብሔር መፀለይ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለው ብሩህ ተስፋ፤ ጨለማ ውስጥ ነን ብሎ ለሚያስብ ህዝብ ብርሃን የሆነ ህይወት እንዲኖረው የሀገራችንም ከፍታ እንዲኖር ያደርጋል" ብለዋል።

"በዚህች ሰዓት ይሄ ፀሎት ወሳኝ በመሆኑ ትንሹም ትልቁም #በሀገር_ውስጥም_በውጭም_ያለው_ቢፆም_ቢፀልይ_መፍትሄ_ይመጣል ፤ አምስቱን ቀን በፀሎት እና በምህላ ማሳለፍ ይገባል" ሲሉ አክለዋል።
-------------
🔔 ውዳሴ ቤቴል

@widase_betel
🔘 @widase_betel
@widase_betel


⭕️ ጥበብ ከማር ትጣፍጣለች ከስኳርም ትመረጣለች ፤ ከሷ የቀመሰ ጨምሩልኝ ጨምሩልኝ ይላል እንጂ በቃኝ ጠገብኩ አይልም ፡፡

☦ እድሜውን ሙሉ ሲመገባት ቢኖር እንኳን አይሰለቻትም ።


✝ #ጥበብ ማለት እግዚአብሄርን መፍራት ነው ። ✝

----
🔔 ውዳሴ ቤቴል

@widase_betel
🔘 @widase_betel
@widase_betel


ዛሬ "ሆያ ሆዬ" ጭፈራ ላይ ያሉ ስንኞች ትርጓሜን ቀንጨብ አድርገን ብንመልከትስ፦

"ሆያ ሆዬ ሆ"፦ ማለት ጌታዬ ሆዬ ፥ እሜቴ ሆዬ ማለት ነው፡፡

"እዚያ ማዶ ጢስ ይጤሳል"፦ የተባለበት ምክንያት እስራኤላውያን በበረሃ ለአርባ ዓመታት ሲጓዙ ደመና እየጋረደ (እየጤሰ) ስለመራቸው ነው፡፡

"አጋፋሪ ይደግሳል"፦ የተባለው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፤

፩. ቅዱስ ሚካኤል እስራኤላውያንን "በዕደ መልአኩ ይዕቀበነ፥ ሰላመ ዚአሁ የኀበነ" እንዲል፤ በአምላክ ትዕዛዝ ቅዱስ ሚካኤል መናን ከደመና፥ ውኃን ከጭንጫ ዓለት እያፈለቀ (እየደገሰ) መርቷቸዋልና ነው፡፡

፪. የአብነት (የቆሎ) ተማሪዎች በክረምት ሲለምኑ የቆዩትን አጠራቅመው፤ የደብረ ታቦር ዕለት ብርሃነ መለኮቱን የገለጠ ጌታ ለእኛም እንዲገልጥልን በማለት ደግሰው ለሕዝብ ስለሚያበሉና ስለሚያጠጡ ነው፡፡

"ያችን ድግስ ውጬ ውጬ"፦ የተባለውና በድግስ የተመሰለው መና ሲሆን፤ በደጋሹ ቅዱስ ሚካኤል አማካኝነት እስራኤላውያን ለአርባ ዓመታት መመገባቸውን (መና መዋጣቸውን) ለማስታወስ ነው፡፡

"ከድንክ አልጋ ተገልብጬ"፦ ድንክ አልጋ የምትመች እንደሆነች ሁሉ፥ በድንክ የምትመሰለውንና የምትመቻቸውን የተስፋይቱ ምድር ኢየሩሳሌምን መውረሳቸውን ለመናገር ነው፡፡

"ያቺ ድንክ አልጋ አመለኛ፥
ያለአንድ ሰው አታስተኛ"፦ መባሉ እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር ሲወጡ 600,000 ቢሆኑም አብዛኞቹ በምድረ በዳ አልቀው ኢየሩሳሌምን የወረሷት ሴትና ሕፃናት ሳይቆጠሩ፤ አንድ ኢያሱና ካሌብ በመሆናቸው ነው።

በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ይህን መሰል ትርጓሜ የሚሰጠው የ"ሆያ ሆዬ" ጭፈራ በተለይ ከእኛ ትውልድ ጀምሮ ዓለማዊ መልክ እየያዘ ከመምጣቱ በተጨማሪ ግጥሞቹ እየተሰረዙና እየተደለዙ በሌላ ስንኝ ተቀይረዋል፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግጥሙ ተበርዞ ስሰማ ይከፋኝ ጀመር። ዝርዝሩን ለመመልከት በጣም ሰፊ ጥራዝ ስለሚያስፈልገኝ ለዛሬ በዚሁ ይብቃኝ።

.........................................

🔔 ውዳሴ ቤቴል

@widase_betel
🔘 @widase_betel
@widase_betel


🎚 " ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያእቆብን ወንድሙንም ዮሀንስን ይዞ ወደ ረዥም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው ። በፊታቸውም ተለወጠ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ ፤ ልብሱም እንደ ብርሀን ነጭ ሆነ ። እንሆም ሙሴና ኤልያስ ከርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩዋቸው ። "

ማቴ 17 ÷ 1-4

-------
🔔 ውዳሴ ቤቴል

@widase_betel
🔘 @widase_betel
@widase_betel


ክ 3
👉 ኑሮ ምንድነው?
👉 ሕይወትስ ምንድን ነው?
👉 ኑሮና ሕይወት ምን ያለያያቸዋል?
ተራኪ - ሠረቀ ብርሃን

#ሼር

#ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን !🙏
-------
🔔 ውዳሴ ቤቴል

@widase_betel
🔘 @widase_betel
@widase_betel


ክ 2
👉 ኑሮ ምንድነው?
👉 ሕይወትስ ምንድን ነው?
👉 ኑሮና ሕይወት ምን ያለያያቸዋል?
ተራኪ - ሠረቀ ብርሃን

#ሼር

#ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን !🙏
-------
🔔 ውዳሴ ቤቴል

@widase_betel
🔘 @widase_betel
@widase_betel


ክ 1
👉 ኑሮ ምንድነው?
👉 ሕይወትስ ምንድን ነው?
👉 ኑሮና ሕይወት ምን ያለያያቸዋል?
ተራኪ - ሠረቀ ብርሃን

#ሼር

#ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን !🙏
-------
🔔 ውዳሴ ቤቴል

@widase_betel
🔘 @widase_betel
@widase_betel


🤔 ​ #ሲኦል ምን ትመስላለች ?

⁺ አንድ ተማሪ ወጣት እድሜ ጠገብ ወደ ሆኑ አረጋዊ ቀርቦ "አባቴ ሆይ ሲኦል ምን ትመስላለች?" ሲል ጠየቃቸው፣

አረጋዊውም ሲመልሱ :- ልጄ ስለዚህ ነገር የሰማሁትን አንድ ታሪክ ላጫውትህ :-

በአንድ ወቅት እግዚአብሔርን ገነት እና ሲኦል ምን እንደሚመስሉ ያሳየው ዘንድ አጥብቆ የሚለምነው አንድ የዋህ ሰው ነበር፡፡ ከእለታት በአንደኛውም ምሽት ይህ ሰው ‹ሲኦል ምን እንደምትመስል ና ላሳይህ› የሚል ድምፅን ይሰማል፡፡ ወዲያውም ምግብ የተሞላበት ማሰሮ በጠረጴዛው ላይ ካለበት እና ብዙ ሰዎች በገበታው ዙሪያ ተሰብስበው ከተቀመጡበት ክፍል ውስጥ ራሱን አገኘ፡፡ እያንዳንዳቸውም ሰዎች ዘንጋቸው የረዛዘሙ ማንኪያዎች ይዘዋል፡፡ ነገር ግን ምግቡን ምንም ከማሰሮው ውስጥ ማውጣት ቢችሉም ምግቡን የተሸከመውን የማንኪያውን ጫፍ ግን ወደ አፋቸው ማድረስ አልተቻላቸውም፡፡ በዚህም ምክንያት አንዳንዶቹ ያጉረመርሙ፣ አንዳንዶቹም ይጮሁ፣ ሌሎቹ ደግሞ ያለቅሱ ነበር፡፡

በመቀጠልም ያ የዋህ ሰው ‹ገነትም ምን እንደምትመስል አሳይህ ዘንድ አሁኑኑ ና› የሚል ተመሳሳይ ድምፅን ሰማ፡፡
አሁንም እንደ ቀድሞው ብዙ ሰዎች በጠረጴዛ ላይ ባለ ማዕድ ዙሪያ ከተሰበሰቡበት ሌላ ክፍል ራሱን በድንገት አገኘ፡፡ እነዚያም ሰዎች እንዲሁ ከቀድሞው ጋር ተመሳሳይ ርዝመት ያላቸውን ማንኪያዎች በእጃቸው ይዘዋል፡፡ ነገር ግን ሁሉም ሰዎች ጠግበው እና ደስተኛ ሆነው ይታዩ ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ አንዱ ሰው ማንኪያውን ወደ ማሰሮው በማጥለቅ ለእርሱ የቀረበውን ሰው በመመገብ እርስ በእርስ ይመጋገቡ ስለ ነበር ነው፡፡

-በዚህ ዓለም እያለህ እንዴት ራስህን በገነት የምትኖር ያህል እንዲሰማህ ማድረግ እንደምትችል አሁን ተረዳህን? መልካምን የሚያደርግ ማንም ቢኖር ደስታ ይኖረዋል፡፡ ምክንያቱም አምላካዊ መጽናኛን ይሸለማልና፡፡ መልካም ያልሆነውን የሚያደርግ ደግሞ ስቃይ ያገኘዋል። እንደ ገነት የነበረውንም ምድር ወደ ሲኦል ይቀይረዋል፡፡

ፍቅር፣ መልካምነት በውስጥህ አሉን? እንዲህ ከሆነ አንተ ምድራዊ መልአክ ነህ፡፡ በምትሄድባቸውና በምትቆምባቸው ቦታዎች ሁሉ ከአንተ ጋር ገነትን ተሸክመሃታል፡፡

ጥልቅ የሆነ የንዴትና የብስጭትስ ስሜት ይሰማሃልን? ሁል ጊዜ በሆነው ባልሆነው ትቆጣለህ? እንዲህ ከሆነስ በአንተ ውስጥ ክፉ ዲያብሎስ አለ፡፡ በምትሄድባቸውና በምትቆምባቸው ቦታዎች ሁሉ ከአንተ ጋር ሲኦልን ተሸክመሃታል፡፡

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
--------------


🔔 ውዳሴ ቤቴል

@widase_betel
🔘 @widase_betel
@widase_betel




◈ መዝሙረ ዳዊት ◈

ለመዘምራን አለቃ፤ ወደ ቤርሳቤህ ከገባ በኋላ ነቢዩ ናታን ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ፤ የዳዊት መዝሙር።


1 አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።

2 ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ፤

3 እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።

4 አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ፥ በነገርህም ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ።

5 እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ።

6 እነሆ፥ እውነትን ወደድህ፤ የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ።

7 በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ፤ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ።

8 ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፥ የሰበርሃቸውም አጥንቶቼ ደስ ይላቸዋል።

9 ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ፥ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ።

10 አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።

11 ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ።

12 የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ።

13 ለሕግ ተላላፎች መንገድህን አስተምራለሁ፥ ኃጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ።

14 የመድኃኒቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከደም አድነኝ፥ አንደበቴም በአንተ ጽድቅ ትደሰታለች።

15 አቤቱ፥ ከንፈሮቼን ክፈት፥ አፌም ምስጋናህን ያወራል።

16 መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር፤ የሚቃጠለውም መሥዋዕት ደስ አያሰኝህም።

17 የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም።

18 አቤቱ፥ በውዴታህ ጽዮንን አሰማምራት፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጽሮች ሥራ።

19 የጽድቁን መሥዋዕት መባውንም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በወደድህ ጊዜ፥ ያን ጊዜ በመሠዊያህ ላይ ፍሪዳዎችን ይሠዋሉ።


...............

📜 መዝሙር ፶ \ 51

🟩⬜️🟨⬜️🟥

@widase_betel




🙏 #ሰላም የውዳሴ ቤቴል አባላት በሙሉ !

👉 ውዳሴ ቤቴል ቻናል ላይ አስተዳዳሪ ሆኖ ማገልገል ለሚፈልጉ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች ክፍት ነው 🙏

👉 በዚህ ያሳውቁን @widase_bot


❤ °°° ያለሽ ልዩ ፀጋ °°°

© #ውዳሴ ቤቴል ዝማሬ ™


ያለሽ ልዩ ፀጋ ያለሽ ልዪ ክብር
የሁሉ እመቤት በሰማይ በምድር
አኩራሪተ መዐልት ምራገ ፀሎት
ሲነግሩሽ ሰሚነሽ ኪዳነምህረት

#አዝማች
መከራ ላለው ሁኝለት መፅናኛ
ዕንባውን አብሺው አይዘን ዳግመኛ
ጉድለቱን ሙይለት በፈረሰው ቆመሽ
ስለምታስምሪ በልዩ ኪዳንሽ

ከኪዳንም በላይ ኪዳንሽ ልዩ ነው
እናቴ የሚልሽ አምላክሽ ልጅሽ ነው


#አዝማች
ተበጠሰ ከእጁ የወይኑ ሰንሰለት
የሞቱ ደብዳቤ ይቀየር በህይወት
አዲስ ተስፋ ሞልተሽ አዲስ ሰው አድርጊው
መቅበዝበዙ ይጥፋ ድንግል አረጋጊው
ከኪዳንም በላይ•••••••••••••


#አዝማች
በዕንባ የመጣ ይመለስ በደስታ
መጠማቱ ይቅር ይሞላ በእርካታ
ስለቱ ሰምሮለት ጀመረ ምስጋና
የአብራኩን ክፋይ አሳቅፊውና
ከኪዳንም በላይ••••••••••••


#አዝማች
ተኝቶ ለሚኖር በአልጋ ቁራኛ
አንቺ ሁኝ እመቤቴ የዴውም ዳኛ
ሚነግሩት ላንቺ ነው መማፀን ወዳንቺ
ተስፋን ለምትቀጥይ ህልምን ለምትፈቺ

ከኪዳንም በላይ••••••••


--------------
#ዘማሪ - ሊቀ-መዘምራን ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ
--------------


🔔 ውዳሴ ቤቴል

@widase_betel
🔘 @widase_betel
@widase_betel


🕯🕯🕯

ሁለተኛው ሻማህ ካልጠፋ ሌሎቹ ይበራሉ

(አባት ልጃቸውን ሲመክሩ)
ጥንት ነው አሉ አንድ ሰው ከሰማይ ወደዚህ ና ! ተመልከትም የሚል እንደ ውሃ የሚፈስ ድምጽ ሰማ፡፡ ሄደ! አየም እነሆ በአንድ እጅግ ጠባብ በሆነ መንገድ ላይ ሶስት ሻማዎች ይበሩ ነበር፡፡ የሚገርመው የመጀመሪያው ሻማ እምነት ሁለተኛው ተስፋ ሶስተኛውም ፍቅር የሚባሉ ስሞች ነበሯቸው፡፡

ድንገት ግን ታላቅ ነፋስ ከምዕራብ ነፍሶ እምነትና ፍቅር የተባሉትን ሻማዎች አጠፋቸው፡፡ ሁለተኛው ተስፋ የተባለው ሻማ ግን በብዙ ትግል ከመጥፋት ሲተርፍ ተመለከተ በዚህን ጊዜም በታላቅ ድምጽ ጮኸ ፡፡ እምነትና ፍቅር የተባሉት ሻማዎች ጠፍተዋል ወድቆ አለቀሰ፡፡ ወዲያውም ከምስራቅ በነጭ ደመና የተቀመጠ በዘመናት የሸመገለ ሰው መጥቶ ልጄ ሆይ አይዞህ አትዘን የእምነትና ፍቅር ሻማዎች ቢጠፉም የተስፋ ሻማ ስላለ እንደገና ሁለቱን ሻማዎች ማብራት ይቻላል አለው፡፡ ተስፋ የተባለውም ሻማ አንስቶ እምነትና ፍቅር የተባሉትን ሻማዎች ለኮሰና አበራቸው፡፡ ፍጹም ብርሃንም ሆነ ልቡም ተጽናንቷልና እንባውም ታብሷልና ደስ አለው አመሰገነም፡፡
ልጄ ሆይ ሁል ጊዜም እግዚአብሔርን ተስፋ አድርገው እምነትህ ቢደክም ፍቅር ሲቀዘቅዝ ብታይስንኳ ተስፋ ቆርጠህ ወደ ኋላ አትመለስ፡፡ ነገ መለመጥን ተስፋ አድርግ እንጂ ክርስትና ከሥጋና ደም ጋር የምትታገልበት ሕይወት ሳይሆን ትግሉ ከጨለማ ገዥዎች ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር መሆኑን አትዘንጋ፡፡ በሕይወትህ ውስጥ ጠላት ለማጥፋት የሚፈልገው ታላቅ የልብ ሻማ ተስፋ ነው፡፡ የልብህን ተስፋ አጥብቀህ ጠብቅ ተስፋ ካለ ሁሉን መልሰህ ማግኘት ትችላለህ፡፡ ተስፋ ከሌለህ ግን ልታምንም ልታፈቅርም ይከብዳል፡፡ ተስፋ የማታደርግ ከሆነ እንዴት ታምናለህ? ታፈቅራለህስ?
ስለዚህ ልጄ ሆይ ዛሬን ብትወድቅ ተስፋ አትቁረጥ ተነስ እንጂ ዛሬ እንደ ቃሉ በፍቅር መኖር ቢያቅትህ መፍትሔው ተስፋ መቁረጥ አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ እንጂ ዛሬ በአገልግሎትህ ብትደክም ተስፋ ቆርጠህ ከቤቱ ከቶ አትውጣ፡፡ ከሐዋርያት ጋር ሆነህ ጌታ ሆይ ወደ ማን እሄዳለሁ? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ በለው፡፡ ዮሐ 6፡68 ከዳዊት ጋርም ሆነህ አሁንስ ተስፋዬ ማነው አንተ እግዚአብሔር አይደለህምን በለው መዝ 38፡7 ፍሬ ለማፍራትም በእርሱ ተስፋ አድርግ፡፡ በተስፋ ለምትጠባበቀው ለምትሻውም ነፍስ ጌታ ቸር የሚራራም ነውና፡፡ ልጄ ሆይ አዳም ከገነት ቢሰደድ ይዞ የወጣው ሌላ አይደለም ተስፋን ነው፡፡ በጌታ ቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ እድሜ ልኩን በክፉ ስራ ቢኖርም ተስፋን ግን አልጣለም በመጨረሻ ትንፋሽ ላይ ሳለ ወደ ሕይወት ያደረሰችው ይህች ተስፋ አለመቁረጥ ናት፡፡ በግራ ያለውማ ተስፋ በመቁረጡ የእምነትና የፍቅር ሻማዎቹ ሊበሩለት አልቻሉም፡፡ እንግዲህ ልጄ ሆይ በጊዜውም ያለጊዜውም እርሱን ተስፋ አድርገህ ኑር፡፡ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ ቸር ያሰንብትህ፡፡
‹‹እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን እነርሱ ምድርን ይወርሳሉ›› መዝ 36፡9
ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን ለእርሱ ክብርና ኃይል ይሁን፡፡
አሜን 🙏


---------------

🔔 ውዳሴ ቤቴል

@widase_betel
🔘 @widase_betel
@widase_betel


❤°°° ለስንቱ እንጀራ ሆንክ °°°

© #ውዳሴ ቤቴል ዝማሬ ™


ለስንቱ እንጀራ ሆንክ ለስንቱ መጠጥ *2
ኢየሱስ ስምህ ሲጣፍጥ


#አዝማች
የበላነው በለስ ገድሎን ሰለነበር
የሕይወት እንጀራን ስንናፍቅ ነበር
ከሰማያት ወርደህ ታርደህ የበላንህ
ኢየሱስ ክርስቶስ ይጣፍጣል ስምህ


#አዝማች
የሕይወት ውሃ ምንጭ ከሆድህ ይፈልቃል
ሰማርያ ወርዶ ውሃ ማን ይቀዳል
በልብ እየፈሰስክ ነፍስ የምታረካ
ቅዳልን ኢየሱስ ጓዳችንን እንካ


#አዝማች
ከያዕቆብ ጉድጔድ ለዘመናት ጠጣን
አመታት አለፉ እጅግ እየጠማን
አይደለም ለእንስራ ለልብ የምትደርስ
የወይኑ ዘለላ በነፍሳችን ፍሰስ


#አዝማች
በሲና የነበርክ የጉዟችን አለት
በረሃው ቀዝቅዞ ረክተን አለፍንበት
ከጥልቅ እንደሚፈልቅ ከአለቱ ላይ ጠጣን
ስምህ እርካታ ነው ከእንግዲህ ላይጠማን


#አዝማች
ሳምሪት ታመኝበት መቅጃ አትጠይቂው
ጉድጔዱም ጥልቅ ነው ብለሽ አትንገሪው
የሕይወትሽ ውሃ መፍሰሻ ነው እርሱ
ለልብ የሚቀዳ እርሱ ነው ንጉሱ

---------------
#ዘማሪ ሊቀ-መዘምራን ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ

------------------

🔔 ውዳሴ ቤቴል

@widase_betel
🔘 @widase_betel
@widase_betel


💟 ሳትጸልይ እዳተኛ ሳትጸልይ ምንም አትስራ * ሁልግዜ ጸሎት 🙏

✝ ጸሎት ልምድ አይደለም፡፡ ጸሎት የቃላት ሽምደዳ አይደለም፡፡ ጸሎት ድጋም አይደለም፡፡ ጸሎት የችግር መፍቻ ብቻ አይደለም፡፡ ጸሎት ልመና ብቻ አይደለም፡፡ ጸሎት ከአባት ከእግዚአብሔር ጋር የሚደረግ ኅብረት ነው፡፡ ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ንግግር ነው፡፡ ጸሎት ለምኖ ለመቀበል ይመስለን ይሆናል፤ አይደለም፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ስናደርግ የኅብረቱ ውጤት በረከት ያመጣል፡፡ ኅብረት የምናደርገው ልጆች ስለሆንን ነው እንጂ ለመቀበል አይደለም፡፡ ኅብረት ስናደርግ ግን ብዙ የምንቀበለው ነገር አለ፡፡


✝ ጸሎት የሕይወት አካል ነው፡፡ በስሜት የሚጀመር ፥ በስሜት የሚቆም አይደለም፡፡ መጽሐፉ "በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤"
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6: 18። ዘወትር መጸለይ እንዴት ደስ ይላል፡፡ ሐዋርያው ለተሰሎንቄ አማኞችም "ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።" ብሏል፡፡ 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5: 17-18። ሁልጊዜ እንደምንተነፍሰው ሁልጊዜ መጸለይ አለብን፡፡

ጌታ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን !!! 🙏

--------------------

🔔 ውዳሴ ቤቴል

@widase_betel
🔘 @widase_betel
@widase_betel


❤ °°° የትንሣኤው ጌታ °°°

© #ውዳሴ ቤቴል ዝማሬ ™


የትንሣኤው ጌታ ሊያነሳን ተነሳ *2
ሙስና መቃብርን በኃይሉ ድል ነሳ *2

#አዝማች
ነብሱን በስልጣኑ ከስጋው የለየው
ዳግመኛም በኃይሉ ምት ድል አረገው
ሙታንን ያድን ዘንድ በፍቃዱ የሞተው
ከሙታን ተነስቷል እነሳለው ያለው


#አዝማች
እንደኃያሉ ሰው እንደ ተወው ስካር
ተነሳ ክርስቶስ ድል አርጎ መቃብር
እሱም ጠላቶቹን ከኋላ መታቸው
የዘላለም አሳር እነሆ ሰጣቸው


#አዝማች
እንደተናገረው በአፈ ነቢያት
ከሙታን ተነሳ አምላከ አማልክት
ወዶን ከሰማያት እንደ ወረደልን
የሙታን በኩር ሆኖ ጌታ ተነሳልን



#አዝማች
እንደተናገረው ተነስቷል ክርስቶስ
ሞትን አሰናብቶ ችንካሩን ሰበረው
ከሙታን ተነስቶ በሶስተኛው ቀን
እስራችን ተፈታ ሰላም ሆነልን


#አዝማች
በእምነት ገሰገሰች ማልዳ ከመቃብሩ
እውነታው ቢከብዳት ባያስተኛት ፍቅሩ
የአምላኮን መነሳት ሰምታ ከመላእክት
አየች ትንሳኤውን ማርያምመቅደላዊት


#አዝማች
በእውነት አምነናል መቃብሩን አይተን
ነጭ የለበሱትን መላእክቱን ሰምተን
እግዚአብሔር ሲነሳ ጠላት ተበትኗል
በጌታ ትንሳኤ ትንሳኤያችን ሆኗል

--------------------
#ኢየሱስ_ክርስቶስ በኃይሉ በሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጐ ÷ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ተነሥቷል ፡፡ እርሱ የትንሣኤና የሕይወት ባለቤት ነውና፡፡

ዮሐ ፲፩ ÷ ፳፭ | 11 ÷ 25
-------------------------
#አዲስ_የትንሳኤ_መዝሙር

#ዘማርያን ሊቀመዘምራን ቴድሮስ ዮሴፍ እና ሊቀዲያቆን ተመስገን ይባቤ

-------------------------

🔔 ውዳሴ ቤቴል

@widase_betel
🔘 @widase_betel
@widase_betel


#ድንግል_ሆይ 🙏

ከልጅሽ ሌላ ባለመድኃኒት አልሻም፡፡ ከጸሎትሽም ረዳትነት በቀር ደግሞ ኃጢአቴን የሚያስተሠርይልኝ አልፈልግም፡፡ ንጽሕት ሆይ ከርኩሰቴም ከዕዳ በደሌም ሁሉ ንጹሕ አድርጊኝ፡፡ ከሥጋና ከነፍስ ቁስሌም ፈውሽኝ፡፡
ለደዌ መድኃኒት ይሹለታል፤ ለቁስልም አቃቂር መልካሙን ቅመም ይፈልጉለታል፤ የኃጢአት ቁስል ግን ያለ ልጅሽ ፈቃድ አይጠግም፡፡

በዕብራይስጥ ማሪያም የተባልሽ የተመረጥሽ ደንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ! የደናግል መመኪያ የቅዱሳንም ሁሉ የመመረጣቸው አክሊል ኃጢአቴን እንደ ነጭ ሐር ግምጃ ንጹሕ አድርጊው ዕዳ በደሌንም እንደ በረድ ነጭ አድርጊው፡፡
ጸሎቴም ወደ ልጅሽ ፊት ትግባ፡፡ በልጅሽም በወዳጅሽም ጆሮ የተሰማች እርሱም የተቀበላት ትሆን ዘንድ ባንቺ ፊት እማለላለሁ፡፡ ከልጅሽም ዘንድ ለኃጢአቴ ሥርየት እሻለሁ፡፡
በየሰዓቱም በየጊዜውም ለማኅፀንሽ ፍሬ ይቅርታ መምጣት ደጅ እጠናለሁ፡፡ ልጅሽም እንደ በደሌ ቢበቀለኝ እንደ ሥራዬም ቢከፍለኝ አንዲት ሰዓት ለመቆም የተገባሁ ባልሆንኩም ነበር፡፡
ነገር ግን የጸሎትሽ ረዳትነት የልጅሽም ይቅርታው በየዕለቱ በየዘመኑ ሁሉ ይከራከርልኛል፡፡ ስለዚህ አልፈራም ምንም ምድር ብትናወጽ ተራሮችም በምድር ላይ ቢናወፁ ባንቺ ምልጃ እድናለሁና አልፈራም።

-------------------------

🔔 ውዳሴ ቤቴል

@widase_betel
🔘 @widase_betel
@widase_betel


❤️ °°° ፍቅርህ ማረከኝ °°°

© #ውዳሴ ቤቴል ዝማሬ™


ፍቅርህ ማረከኝ በህይወቴ በዘመኔ/፪/
እግዚአብሔር ለኔ መድኃኒቴ
ፍቅርህ ማረከኝ በህይወ ቴ በዘመኔ


#አዝማች
ተገዝቻለው በወርቅ ደምህ
አለምን ትቼ ላገለግልህ
ሞትህ ህይወቴ ለኔ ሆኖኛል
ባንተ መከራ ሸክሜ ርቋል
በክብር ቆሜ እዘምራለሁ
እንደ አቅሜ አገንሀለሁ


#አዝማች
ምድርና ሰማይ እልል ይበሉ
ምስጋና ላንተ ይድረስ እያሉ
መሳይ የለህም ለቅድስና
አቀርባለሁኝ ላንተ ምስጋና
ጣቴ በገናን ይደረድራል
በቀን በሌሊት ያመሰግናል


#አዝማች
ክብርህን አይተው ጠላቶች ፈሩ
በጌትነትህ ወድቀው ተገዙ
እንዲህ ነህ አምላክ እንዲህ ነህ ጌታ
ሁሉን በፍቅር የምትረታ
በአንተ ተመካነን በፈጣሪያችን
አዳኝ በሆንከው በንጉሳችን

#ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
---------------------

🔔 ውዳሴ ቤቴል

@widase_betel
🔘 @widase_betel
@widase_betel

20 last posts shown.

350

subscribers
Channel statistics