💟 ሳትጸልይ እዳተኛ ሳትጸልይ ምንም አትስራ * ሁልግዜ ጸሎት 🙏
✝ ጸሎት ልምድ አይደለም፡፡ ጸሎት የቃላት ሽምደዳ አይደለም፡፡ ጸሎት ድጋም አይደለም፡፡ ጸሎት የችግር መፍቻ ብቻ አይደለም፡፡ ጸሎት ልመና ብቻ አይደለም፡፡ ጸሎት ከአባት ከእግዚአብሔር ጋር የሚደረግ ኅብረት ነው፡፡ ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ንግግር ነው፡፡ ጸሎት ለምኖ ለመቀበል ይመስለን ይሆናል፤ አይደለም፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ስናደርግ የኅብረቱ ውጤት በረከት ያመጣል፡፡ ኅብረት የምናደርገው ልጆች ስለሆንን ነው እንጂ ለመቀበል አይደለም፡፡ ኅብረት ስናደርግ ግን ብዙ የምንቀበለው ነገር አለ፡፡
✝ ጸሎት የሕይወት አካል ነው፡፡ በስሜት የሚጀመር ፥ በስሜት የሚቆም አይደለም፡፡ መጽሐፉ "በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤"
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6: 18። ዘወትር መጸለይ እንዴት ደስ ይላል፡፡ ሐዋርያው ለተሰሎንቄ አማኞችም "ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።" ብሏል፡፡ 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5: 17-18። ሁልጊዜ እንደምንተነፍሰው ሁልጊዜ መጸለይ አለብን፡፡
ጌታ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን !!! 🙏
--------------------
🔔 ውዳሴ ቤቴል
☦ @widase_betel
🔘 @widase_betel