የሚጠፋውና የማይጠፋው!
ጊዜያዊውና ዘላለማዊው!
በቤተሰብ ዙሪያ ባለው ተጽእኖ አሳዳሪ አገልግሎቱ የሚታወቀው ጄምስ (James Dobson) አንድ ጊዜ እንዲህ ሲል ተናገረ፡-
“አንድ ጊዜ ድሮ high school የተማርኩበትን ትምህርት ቤት ለመጎብኘት ስሄድ ቴኒስ ስጫወት አሸንፈ የተሸለምኳቸውን ዋንጫዎች በቆሻሻ ማጠራቀሚያ እቃዎች ውስጥ ተጥለው አየኋቸው፡፡
ይህንን ያደረጉት ሌሎች ተማሪዎች ለሚሸለሟቸው አዳዲስ ዋንጫዎች ስፍራ ለማዘጋጀት ሲባል ነበር፡፡
በዚህ ምድር ላይ የሰው ልጆች አከናወንኳቸው የሚሏቸው ነገሮች ሁሉ የጊዜን ፈተና ማለፍ የማይችሉና የኋላ ኋላ ቦታ እንደሚያጣብብ ቆሻሻ የሚቆጠሩ እንደሆነ እንዳስታውስ አደረገኝ፡፡
ዛሬ ተጨብጭቦለት ነገ የሚጣለው ምድራዊ ስኬት ላይ ብቻ ከማተኮር ይልቅ የሰዎችን ሕይወት በመለወጥ ላይ ማተኮር ምን ያህል ዋጋ ያለውና ዘላቂ እንደሆነ እንዳስብም አደረገኝ፡፡
ከምድራዊው የስኬት ሩጫ መለስ እያልን የሰዎች ሕይወት የሚለወጥበትን ስራም ለመስራት መመረጥ እጅግ መታደል ነው፡፡
እንቀጥልበት!
ይህንን ታሪክ ሳነብ ወደ ልቤ የመጣውና ከፍቼ ያነበብኩት ክፍል ይህ ነው፡- “ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ እግዚአብሔር አብ የማረጋገጫ ማኅተም ስለ አተመው የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ፥ የዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው ምግብ ሥሩ” - ዮሐ. 6፡27
እናንተስ ይህንን ታሪክ ስታነቡ የትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ትዝ አላችሁ ?
Dr. Eyob
@worlds_light