ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዝበ ሙስሊሙ ለግድቡ ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶች ላበረከተው አስተዋጽኦ አመሰገኑ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ነገ የሚከበረውን የዒድ አል-አድሐ (አረፋ) በዓል አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
የዘንድሮው አረፋ በተለያዩ ምክንያቶች ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ለየት ያለ ትርጉም አለው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ውኃ ሙሌት በተሳካበት ጊዜ የሚከበር መሆኑን በከፍተኛ ሐሴት ውስጥ ሆኖ በዓሉን ለመቀበልና ለማክበር እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡
በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ሙስሊሞች ለተገኘው ዲፕሎማሲያዊ ስኬት ለከፈሉት መስዋዕትነትም አመስግነዋል፡፡
በዓሉ መልካም ሰዎች ለመልካም ዓላማ ሲሉ እጅግ ውድ የሆነ ሀብታቸውን፣ ልጃቸውን የሰጡበት “የመሥዋዕትነት በዓል” ነው ያሉም ሲሆን ከዚህ በተቃራኒው ባላቸው እኩይ ዓላማ በወንድምና እህቶቻቸው ላይ ሳይቀር በትር የሚያነሱ አካላትን ህዝበ ሙስሊሙ “በጥበብ እንዲያስተምራቸው አደራ” ብለዋል፡፡
የዘንድሮው በዓል ዓለም በኮሮና ወረርሽኝ እየተፈተነች ባለችበት ወቅት የሚከበር ነው ያሉት ዐቢይ አህመድ ህዝበ ሙስሊሙ ጥንቃቄ እንዲያከብረውና ወረርሽኙን መከላከልን እንደ አንድ ሃይማኖታዊ ግዴታ አድርጎ ሊወስደው ይገባልም ነው ያሉት፡፡
አቅማቸው ደከም ያሉ ወገኖች እንዲደግፉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
“በቀሪ የግድቡ ሥራዎች ላይ እንድንረባረብና የአረንጓዴ አሻራችንን በስኬት እንድንወጣ ከሁላችንም ይጠበቃል” ሲሉም የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።