#ልማር_ወይስ_ልቅጣ
የሩቅ ጉዞ አድክሞኝ
ብመስል የዋዛ፣
ሊይዘኝ የሚጥር
አንዣባቢ በዛ፣
እግሬ ተሳስሮብኝ
ቢያዩኝ ስወላገድ፣
መድረሻ አልባ አረጉት
የያዝኩትን መንገድ፣
ሊይዙኝ ተመኙ
ሊያስገቡኝ በጃቸው፣
ሳቃስት ሳዘግም
ድኩም መሰልኳቸው፣
አሰቡ ቀመሩ
ወጥመድ አነጠፉ፣
ቀስት ቀሰቱልኝ
ወንጭፍ ወነጨፉ፣
እዱለኛ እግሮቼ
በትአምር አለፉ፣
'ሮጡ ገሰገሱ
አሳደዱኝ በጣም፣
እራሴን ለማዳን
ቅንጣት ሀይል አላጣም፣
ብዬ ስነሳሳ፣
እንደ አቦሸማኔ
ወይም እንደሰሳ፣
ሲያበሩኝ በወጀብ
ሲያዳፉኝ በጠጠር፣
ስሮጥ ስፈናጠር
ልድን በደመነብስ፣
በፍጥነት ደረስኩኝ
አላማዬ ድረስ፣
ታየኛ ቦታዬ!
መድረሻዬ ደምቆ፣
ሊረዳኝ ነው ለካ....
ምክንያተኛው ጌታ
መዘግየቴን አውቆ፣
ከንግዲህ ጥላቴም
ምንም አያመጣ
ፍርዱ በጄላይ ነው
ልማር ወይስ ልቅጣ?🤔
✍ኤዶምገነት ፃፈችው
@arifgtmbcha
@arifgtmbcha
@arifgtmbcha
የሩቅ ጉዞ አድክሞኝ
ብመስል የዋዛ፣
ሊይዘኝ የሚጥር
አንዣባቢ በዛ፣
እግሬ ተሳስሮብኝ
ቢያዩኝ ስወላገድ፣
መድረሻ አልባ አረጉት
የያዝኩትን መንገድ፣
ሊይዙኝ ተመኙ
ሊያስገቡኝ በጃቸው፣
ሳቃስት ሳዘግም
ድኩም መሰልኳቸው፣
አሰቡ ቀመሩ
ወጥመድ አነጠፉ፣
ቀስት ቀሰቱልኝ
ወንጭፍ ወነጨፉ፣
እዱለኛ እግሮቼ
በትአምር አለፉ፣
'ሮጡ ገሰገሱ
አሳደዱኝ በጣም፣
እራሴን ለማዳን
ቅንጣት ሀይል አላጣም፣
ብዬ ስነሳሳ፣
እንደ አቦሸማኔ
ወይም እንደሰሳ፣
ሲያበሩኝ በወጀብ
ሲያዳፉኝ በጠጠር፣
ስሮጥ ስፈናጠር
ልድን በደመነብስ፣
በፍጥነት ደረስኩኝ
አላማዬ ድረስ፣
ታየኛ ቦታዬ!
መድረሻዬ ደምቆ፣
ሊረዳኝ ነው ለካ....
ምክንያተኛው ጌታ
መዘግየቴን አውቆ፣
ከንግዲህ ጥላቴም
ምንም አያመጣ
ፍርዱ በጄላይ ነው
ልማር ወይስ ልቅጣ?🤔
✍ኤዶምገነት ፃፈችው
@arifgtmbcha
@arifgtmbcha
@arifgtmbcha