አ.ት.ቅ.ጣ.ኝ
ደካማ ነኝ እና፣
አልችልም ሲወቅሰኝ የራሴ ህሊና፣
ጀርባዬን ሰጥቼህ ክህደትን ስለምድ፣
አትሰረኝ በእምነት አትቅጣኝ በመውደድ፣
በቃ ልኑርበት ክህደቴን ይዤ፣
እንዴት አይንህን ልይ...
ወዳጄ ካልከው ሰው መንታ ልጅ አርግዤ፣
ሰላሜን አትንሳኝ ይብቃህ አትበጥብጠኝ፣
ለኔ አይገባኝም በጥላቻ ፈንታ ፍቅርን አትስጠኝ፣
ደህና ሁን ሄጃለሁ ሳልነግርህ ሳታቀው፣
አንተኮ የዋህ ነህ ክህደቴንም ነው የምትናፍቀው፣
እኔ አልመለስም...
እናትነት ይዞኝ ላሳድግ ስለፋ የክህደት ልጅን፣
አንተን ላለማግኘት...
ስምክን አሸሻለሁ በስመአብ እዳሉት ጅን !!
🫣🫣
✍ኤዶምገነትፃፈችው
@arifgtmbcha@arifgtmbcha