" ተዋት!!! "
ደስተኛ ትምሰል
ትሁን ከሰው እኩል፣
የትናንቱን እንባ
ትደብቀው በኩል፣
ዝንጥንጥ ትበል
እንዲለብሱት ለብሳ፣
ትደብቅ ትናንቷን
የአካሏን ጠባሳ፣
ምስቅልቅል ብስቁልቁል
ብትል ብትጎዳ፣
አይገኝም አፅናኝ....
እልፍ ሀዘኑን ትቶ
እርሷን የሚረዳ፣
ደስተኛ ትምሰል....
በሰዎች መካከል
ይመርባት በቀን፣
ትደርስበታለች ስትሆን ለብቻዋ....
የአምሮዋን ጩኸት
የውስጧ ሰቀቀን፣
ተ
ዋ
ት።
✍ኤዶምገነት ፃፈችው
@arifgtmbcha
@arifgtmbcha
ደስተኛ ትምሰል
ትሁን ከሰው እኩል፣
የትናንቱን እንባ
ትደብቀው በኩል፣
ዝንጥንጥ ትበል
እንዲለብሱት ለብሳ፣
ትደብቅ ትናንቷን
የአካሏን ጠባሳ፣
ምስቅልቅል ብስቁልቁል
ብትል ብትጎዳ፣
አይገኝም አፅናኝ....
እልፍ ሀዘኑን ትቶ
እርሷን የሚረዳ፣
ደስተኛ ትምሰል....
በሰዎች መካከል
ይመርባት በቀን፣
ትደርስበታለች ስትሆን ለብቻዋ....
የአምሮዋን ጩኸት
የውስጧ ሰቀቀን፣
ተ
ዋ
ት።
✍ኤዶምገነት ፃፈችው
@arifgtmbcha
@arifgtmbcha