አለሁ😊
ተደግፌ የሾኽ አጥር፣
ልነሳሳ ልጓዝ ስጥር፣
ስጋ ደሜን እየነጨኝ፣
ቀጥ እዳልል....
ከራስ ጠጉሬ እየላጨኝ፣
እንደምትደርቅ እንደ አበባ አቀርቅሬ፣
እንደ ሀውልት እንደ ድንጋ ተገትሬ፣
ወደፊቴን የነገን ቀን አስባለሁ፣
አልተራመድኩ በሾኽ ሀረግ ታስሬአለሁ፣
ግን.... አለሁኝ....!!
አኗኗሬ ምንም ባይጥም፣
ለበጎ ነው....
እስካልሞትኩኝ ተስፋ አልቆርጥም።
✍ኤዶምገነት ፃፈችው
@arifgtm
bcha
@arifgtmbch
a