**ጓደኛዬ*
ጓደኝነት ውስጤ ሲስል፣
ድቅን ይላል የርሱ ምስል፣
ይገርመኛል....
ደስ ሲለኝ እደሁሉም ይደሰታል፣
በሀዘኔ ድንገት መቶ ካጠገቤ ይከሰታል፣
ቢጨላልም ፀሀይ ብትሸሽ ምድርን ለቃ፣
አይተወኝም ለብቻዬ አይረሳኝም ለደቂቃ፣
ያፅናናኛል የሀዘኔ ምንጭ እስኪጠፋ፣
ያሳየኛል አዲስ ብርሀን አዲስ ተስፋ፣
ይሰጠኛል ቃሉን አስሮ በዕምነት ማተብ፣
ይሆነኛል የቅርብ አካል በልቤ ላይ የሚታተም፣
የማይሽረው ያልቀዬረው ጊዜና ወቅት፣
በወደዱኝ በሚያደንቁኝ የሚደሰት፣
አይበገር ለጠላቴ ሰይፍ ሰዳጅ፣
እርሱነቱን የሚመክት ጋሻ ነበር የኔ ዎዳጅ፣
የሰው ጋሻ እኔን ነቅቶ የሚጠብቅ፣
ቅር የሚለኝ ችላ ብዬ ከርሱ ስርቅ፣
የኔን ያክል ምኞት ህልሜን የሚጋራ፣
ሳቃልለው ሳጣጥለው ይቅር የሚል የሚራራ፣
ስንፍናዬን ለመሸፈን የሚጀግን፣
የርሱስ ጠና....
ጓደኝነት እዲህ ነው ግን ??
ያሳዝናል....
እኔ እንደርሱ ሳልሆንለት፣
ሞት ቀደመኝ....
ዘመን ገፋው የኔና 'ዕርሱን ጓደኝነት።
✍ኤዶምገነት ፃፈችው
@arifgtmbcha
@arifgtmbcha
@arifgtmbcha
ጓደኝነት ውስጤ ሲስል፣
ድቅን ይላል የርሱ ምስል፣
ይገርመኛል....
ደስ ሲለኝ እደሁሉም ይደሰታል፣
በሀዘኔ ድንገት መቶ ካጠገቤ ይከሰታል፣
ቢጨላልም ፀሀይ ብትሸሽ ምድርን ለቃ፣
አይተወኝም ለብቻዬ አይረሳኝም ለደቂቃ፣
ያፅናናኛል የሀዘኔ ምንጭ እስኪጠፋ፣
ያሳየኛል አዲስ ብርሀን አዲስ ተስፋ፣
ይሰጠኛል ቃሉን አስሮ በዕምነት ማተብ፣
ይሆነኛል የቅርብ አካል በልቤ ላይ የሚታተም፣
የማይሽረው ያልቀዬረው ጊዜና ወቅት፣
በወደዱኝ በሚያደንቁኝ የሚደሰት፣
አይበገር ለጠላቴ ሰይፍ ሰዳጅ፣
እርሱነቱን የሚመክት ጋሻ ነበር የኔ ዎዳጅ፣
የሰው ጋሻ እኔን ነቅቶ የሚጠብቅ፣
ቅር የሚለኝ ችላ ብዬ ከርሱ ስርቅ፣
የኔን ያክል ምኞት ህልሜን የሚጋራ፣
ሳቃልለው ሳጣጥለው ይቅር የሚል የሚራራ፣
ስንፍናዬን ለመሸፈን የሚጀግን፣
የርሱስ ጠና....
ጓደኝነት እዲህ ነው ግን ??
ያሳዝናል....
እኔ እንደርሱ ሳልሆንለት፣
ሞት ቀደመኝ....
ዘመን ገፋው የኔና 'ዕርሱን ጓደኝነት።
✍ኤዶምገነት ፃፈችው
@arifgtmbcha
@arifgtmbcha
@arifgtmbcha