አዲስ ነገር የለም
""""""""""""""""""""""
ከሰማዩ በታች የለም አዲስ ነገር፣
ጊዜ የገዛትን ታሪካዊት ምድር ጠይቋት ትናገር፣
ካንዱጋር ዳንኪራ ከሌላጋር ሀዘን፣
አንዱ ሲረጋጋ አንደኛው መባዘን፣
መጪ ስንቀበል ሌላው ተሰናባች፣
ተወለደ ሲባል እዛጋ ደሞ ሟች፣
የለም አዲስ ነገር ሆኖ እንጂ ለየቅል፣
ጊዜ ንጉስ ሆኖ አውርዶ ሲሰቅል፣
እኛም ሆነንለት ተጎናባሽ አሽከር፣
እንከተላለን ....
በመሬት ዙሪያላይ ይዞን ሲሽከረከር፤
በዚች በቆምኩባት ባለሁበት ምድር፣
የወለደ ሲሞት ያሳደገ ሲድር፣
ጥንዶች ሲጫዎቱ የፍቅር ጫዎታ፣
ያረገዘች ስትወልድ ያገባ ሲፈታ፣
አማኝ የገዳም ሰው ወይም በግልባጭ፣
ጠንባዛ ሰካራም አንቡላ አንጫላጭ፣
መፍትሄ ጠፍቶበት ኑሮ ያቀወሰው፣
አይቻለሁ ባይኔ ....
ጨርቁን ጥሎ ሲያብድ ጤነኛ ያልኩት ሰው፤
አዲስ ነገር የለም
ስጠይቅ እራሴን ....
ለምን እንደሆነ አንዱ አለፈ ሲባል ሌላው የሚተካ፣
ሲገባኝ እውነቱ ....
ክብ አለም መዞር ነው ሂዎት ማለት ለካ።
✍ኤዶምገነት ፃፈችው
@arifgtmbcha
@arifgtmbcha
""""""""""""""""""""""
ከሰማዩ በታች የለም አዲስ ነገር፣
ጊዜ የገዛትን ታሪካዊት ምድር ጠይቋት ትናገር፣
ካንዱጋር ዳንኪራ ከሌላጋር ሀዘን፣
አንዱ ሲረጋጋ አንደኛው መባዘን፣
መጪ ስንቀበል ሌላው ተሰናባች፣
ተወለደ ሲባል እዛጋ ደሞ ሟች፣
የለም አዲስ ነገር ሆኖ እንጂ ለየቅል፣
ጊዜ ንጉስ ሆኖ አውርዶ ሲሰቅል፣
እኛም ሆነንለት ተጎናባሽ አሽከር፣
እንከተላለን ....
በመሬት ዙሪያላይ ይዞን ሲሽከረከር፤
በዚች በቆምኩባት ባለሁበት ምድር፣
የወለደ ሲሞት ያሳደገ ሲድር፣
ጥንዶች ሲጫዎቱ የፍቅር ጫዎታ፣
ያረገዘች ስትወልድ ያገባ ሲፈታ፣
አማኝ የገዳም ሰው ወይም በግልባጭ፣
ጠንባዛ ሰካራም አንቡላ አንጫላጭ፣
መፍትሄ ጠፍቶበት ኑሮ ያቀወሰው፣
አይቻለሁ ባይኔ ....
ጨርቁን ጥሎ ሲያብድ ጤነኛ ያልኩት ሰው፤
አዲስ ነገር የለም
ስጠይቅ እራሴን ....
ለምን እንደሆነ አንዱ አለፈ ሲባል ሌላው የሚተካ፣
ሲገባኝ እውነቱ ....
ክብ አለም መዞር ነው ሂዎት ማለት ለካ።
✍ኤዶምገነት ፃፈችው
@arifgtmbcha
@arifgtmbcha