🥀ከዚህም በኋላ ወደ ሕዝብ መካከል ወጣ እያለቀሰ ጸለየ እንዲህም አለ አቤቱ በጌትነትህ ክብር ፊት የረከሰች እፌን እንዴት እገልጣለሁ በኃጢአት ብዛት የጠቆረ ፊቴንስ እንዴት ቀና አደርጋለሁ ነገር ግን እንደ ይቅርታህ ገናናነት እንደ ቸርነትህም ብዛት ሕዝብህን ይቅር በል አንተ መሐሪና ይቅር ባይ ነህና በዚያንም ጊዜ ብዙ ዝናም ወረደ እርሱም ጸሎቱንና ንስሓውን እግዚአብሔር እንደ ተቀበለው ኃጢአቱንም እንደ ተወለት አወቀ።
🥀ከዚህም በኋላ አስቀድሞ እንደሚሠራው ተግቶ መጸለዩንና መሰገዱን አላጐደለም ነፍሱንም ዳግመኛ በኃጢአት ውስጥ እንዳትወድቂ ተጠበቂ በማለት ይገሥጻት ነበር ከዚህም በኋላ ዕድሜውን አድርሶ እግዚአብሔርንም አገልገሎ በሰላም አረፈ።
#ቅዱስ_አባ_ዕብሎይ_ገዳማዊ (የባሕታውያን አለቃ)❤️
🥀በዚህችም ዕለት የባሕታውያን አለቃ ኑሮው የመላእክትን ኑሮ የሚመስል ከትሩፋቱም የሃይማኖት ፍሬ የተገኘ የከበረ አባት ዕብሎይ አረፈ።
🥀ቅዱስ አትናቴዎስም ከተሰደደበት በተመለሰ ጊዜ ወደ ቂሣርያ ኤጲስቆጶስ ወደ አባ ባስልዮስ ዘንድ መጥቶ ሁለቱም በአቡቂር ቤተ ክርስቲያን አደሩ በግብጽ ገዳማት ስለሚኖሩ ቅዱሳን እርስ በርሳቸው ሊነጋገሩ ጀመሩ አባት ሊቀ ጳጳሳት አትናቴዎስ አባ ጳኵሚስ አለ ብሎ ተናገረ አባ ባስልዮስም አባ እንጦንዮስና አባ አሞኒ አሉ አለ በእንዲህ ያለ ነገርም ከእርሳቸው የሚልቀውን ሊረዱ ሽተው ሳሉ የካቲት አምስት ቀን በመንፈቀ ሌሊት አባ አትናቴዎስ ራዕይን አየ።
🥀እስከ ሰማይ የምትደርስ ታላቅ ዛፍ ነበረች ቅርንጫፎቿም እስከ ባሕር ደርሰዋል ብዙ ሰዎችም ከቅርንጫፎቿ በታች ተጠልለዋል በመካከሏም ታቦት መሠዊያ አለ ከዚህም ራእይ የተነሣ እየተደነቀ ሳለ እነሆ የመላእክት አለቃ የከበረ ሚካኤል ከሰማይ ወርዶ ይህን ያየኸውን ከባስልዮስ ጋር ተነጋገር እኔም እገልጥላችኋለሁ አለው።
🥀እንዲህ ብሎ ተረጐመላቸው ያየሃት ዛፍ በግብጽ አውራጃዎች ውስጥ የሚሠራ ገዳም ነው ቅርንጫፎቿም መነኰሳት ናቸው መሠዊያውም መላእክት የሚጐበኙት የእግዚአብሔር ማደሪያ ይህ ርኵሳን መናፍስትን የሚሽር የሐዋርያት አለቃ የጴጥሮስ አምሳል የሆነ አባ ዕብሎይ ነው።
🥀በእስክንድርያ የሚኖር አንድ የመቶ አለቃ የአባ ዕብሎይን ዜና ሰምቶ በረከቱን ይቀበል ዘንድ ወደ አባ ዕብሎይ እንዲልከው ሊቀ ጳጳሳት አትናቴዎስን ማለደው። እርሱም ከሰባት መነኰሳት ጋር ሰደደው እነርሱም አባ ኤስድሮስ፣ አባ ዮሐንስ፣ አባ ብሶይ፣ አባ አሞኒ፣ አባ ፊቅጦር፣ አባ አግሮኒኮስና አባ ካሉናስ ናቸው። በደረሱም ጊዜ አባ ዕብሎይ በደስታ ተቀበላቸው ከመነኰሳቱም ጋር የመጣው የመቶ አለቃ አንዲቷ ዐይኑ የታወረች ናት አባ ዕብሎይን በተሣለመው ጊዜ ዐይኑ ተከፈተች እርሱም በዓለም የሚያበራ ኮከብ ብሎ ተናገረ።
🥀ዳግመኛም አባ ዕብሎይን ለመነው እንዲህም አለው ሚስቴ በለምጽ ደዌ ትጨነቃለች እርሷም በአስኬማህ የተማጸነች ናት እኔ ያገኘሁት ጸጋህ ለርሷም ይድረሳት። አባ ዕብሎይም በክብር ባለቤትም ጌታችን ስም ፈውስ ይሁንላት አለ ይህም ቃል ከአፉ እንደወጣ ድና ጤንነትን አገኘች።
🥀በአንዲትም ዕለት አባ ዕብሎይ ከመነኰሳት መካከል ቁሞ ቤተ ክርስቲያን የምትሠራበትን ያስገነዝበን ዘንድ መድኃኒታችን ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ይመጣልና አንዱም አንዱ ከእናንተ አይሒድ ከዚህ ይኑር እንጂ አላቸው።
🥀ያን ጊዜም በዚያ ቦታ ብርሃን ወጣ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከከበሩ ደቀ መዛሙርቱና ከመላእክቶቹ ጋር መጣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃዋ የሚመሠረትበትንም አሳያቸው።
🥀እርሱም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ ፍቅርንም ያጸኑ ዘንድ ልጆቹን ይመክራቸው ነበር እየመከራቸውም ፊቱ ተለውጦ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ፊት ሆነ ሁለመናውም እንደሚነድ እሳት ሆነ እነርሱም ፈሩ። እርሱም ልጆቼ አትፍሩ እነሆ እኔ እሰናበታችኋለሁ አላቸው። ይህንንም ብሎ ነፍሱ ተመሠጠች በጎ መዓዛም ሸተተ ወዲያውኑ ዐይኑ ተገለጠና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ርዳኝ ነፍሴንም ወዳንተ ተቀበል አለ ይህንንም ብሎ አረፈ። የቀረውም ዜናው በጥቅምት ሃያ አምስት ቀን ተጽፎአል።
🙏ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_የካቲት)
https://t.me/degnitKindness
https://t.me/degnitKindness