አልመኝም ሌላ ❤️
ልትሄጂ ነው አሉ ብቻዬን ጥለሽኝ፤
በቃ ልትርቂኝ ነው ሜዳ ላይ ትተሽኝ።
መፈጠሬን ጠላሁ መንፈሴን አዳከምኩ፤
የተወለድኩባት ያቺን ቀን እረገምኩ።
ህልሜ ቢመክንብኝ
ቀን ቢጨልምብኝ
የማደርገው ባጣ መላው ቢጠፋብኝ፤
ህይወቴን ጠልቼ
ከሰው ዘር ሸሽቼ
ብመንን ከዱሩ ብቻነቴን ሽቼ፤
ግና ምን ዋጋ አለው
በሄድኩበት ሁሉ እየተከተለ፤
ሰላም የሚነሳኝ ትዝታሽ እያለ፤
ተራራን ብወጣ ከውቂያኖስ ብጠልቅ፤
ከከርሰ ምድር ውስጥ ገብቼ ብታመቅ፤
ብሸሽ ብሮጥ ከሱ ብሰወር ብደበቅ፤
ስተወው ካልተወኝ በኔ ተሰላችቶ፤
ጎኔን ካለቀቀ ካሌደ እኔን ትቶ፤
በቃ እንዳሻው ይሁን ይኑር ልቤን ገዝቶ።
...................ግን ውዴ..................
አለም ጭራቅ ሆና እጅግ ብታስፈራ፤
አንቺን የሚያስረሳኝ ጭንቄን የሚጋራ፤
ፍፁም አልመኝም ሌላ ባልንጀራ፤
እኖራለሁ እንጂ ፍቅርሽን ታቅፌ ከትዝታሽ ጋራ።
ግጥሙን ከወደዱት ሼርርርር
JOIN 👇
@hirayeab
@enebante
ልትሄጂ ነው አሉ ብቻዬን ጥለሽኝ፤
በቃ ልትርቂኝ ነው ሜዳ ላይ ትተሽኝ።
መፈጠሬን ጠላሁ መንፈሴን አዳከምኩ፤
የተወለድኩባት ያቺን ቀን እረገምኩ።
ህልሜ ቢመክንብኝ
ቀን ቢጨልምብኝ
የማደርገው ባጣ መላው ቢጠፋብኝ፤
ህይወቴን ጠልቼ
ከሰው ዘር ሸሽቼ
ብመንን ከዱሩ ብቻነቴን ሽቼ፤
ግና ምን ዋጋ አለው
በሄድኩበት ሁሉ እየተከተለ፤
ሰላም የሚነሳኝ ትዝታሽ እያለ፤
ተራራን ብወጣ ከውቂያኖስ ብጠልቅ፤
ከከርሰ ምድር ውስጥ ገብቼ ብታመቅ፤
ብሸሽ ብሮጥ ከሱ ብሰወር ብደበቅ፤
ስተወው ካልተወኝ በኔ ተሰላችቶ፤
ጎኔን ካለቀቀ ካሌደ እኔን ትቶ፤
በቃ እንዳሻው ይሁን ይኑር ልቤን ገዝቶ።
...................ግን ውዴ..................
አለም ጭራቅ ሆና እጅግ ብታስፈራ፤
አንቺን የሚያስረሳኝ ጭንቄን የሚጋራ፤
ፍፁም አልመኝም ሌላ ባልንጀራ፤
እኖራለሁ እንጂ ፍቅርሽን ታቅፌ ከትዝታሽ ጋራ።
ግጥሙን ከወደዱት ሼርርርር
JOIN 👇
@hirayeab
@enebante