#ዩኒቨርስቲ_ገነት_አይደለም‼️
በመምህር [ አበባየሁ ጌታ ] የዩኒቨርስቲ አስተማሪ
ከስር ያያዝኩት የ#Masters_Degreeዬ ውጤት ነው ፤ የዚህ ልጥፍ ዓለማ ራስን ማንቆለጳጰስ ምናምን ሳይሆን ልፋቴ እና የሚከፈለኝ አለመገናኘቱ ሲቀጥል ዩኒቨርስቲ መግባት እና ትምህርት መስቀል ትርጉም አልባነቱን እንዲሁም 12ኛ ክፍል ውጤት ላልመጣላቸው መጽናኛ እንዲሆናቸው ነው።
በአንድ የመንግስት ዩኒቨርስቲ መምህር ነኝ፤ከህይወቴ 17 ዓመት ለመጀመሪያ ድግሪ ሁለት ዓመት ደግሞ ለMasters ድግሪ በአጠቃላይ 19 ዓመታትን ያጠፋሁበት በትምህርት ነው።
በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም Highschool እና መሰናዶ ጓደኛቼ የነበሩ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ እና በተለያዩ የሙያ የንግድ እና የመሳሰሉ ነገሮች ላይ የተሰማሩ በአሁኑ ሰዓት የቤት አከራዮቼ ናቸው ፤ ባለመኪና ባለሆቴል ጽድት ያለ ቡቲክ ብቻ ምን አለፋህ በአጠቃላይ ከእኔ እጅግ በጣም በተሻለ የኑሮ ሁኔታ ነው የሚገኙት!😭
በአሁኑ ሰዓት በመንግስት ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ ድግሪ የያዘ የዩኒቨርስቲ መምህር የሚከፈለው ደመውዝ ግብር ሳይቀነስ 12,579 ብር ነው ፤ 35% ግብር እንዲሁ የጡረታ ሲወጣ ኪሴ የሚገባው 9956(ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ስድስት)ብር ነው።
እንግዲህ በትምህርት ደረጃዬ ሲወራልኝ የዩኒቨርስቲ መምህር ነኝ ፤ ሶስተኛ ድግሪዬን ብሰራ እና ዶ/ር አበባየሁ ጌታ ብባል ወደ 16,000 ብር ከታክስ በፊት እና ወደ 13,000 ብር ገደማ ከታክስ በኋላ እጄ ላይ ይደርሳል።
እና ለምንህ ነው ዩኒቨርስቲ ቀረብኝ ብለህ የምትጨነቀው?
ወዳጄ/ወንድሜ/እህቴ 12 ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት አልመጣልህም?
እሰይ እንኳንም አልመጣልህም! ራስህን ለመቀየር ታትር ፣ አጫጭር ኮርሶችን ከዩቲዩቭ አውርድ ፣ተማር ፣ቪዲዮ ቱቶሪያል ተከታተል ፣ ግራፊክስ እና የመሳሰሉ ገንዘብ ልትሰራ የምትችልባቸው ከምርጥ ኮንተንት ጋር ከመጣህ የዩቲዩብ ስራዎች ብቻ ብዙ ብዙ አማራጮች አሉህ፣ ተስፋ አትቁረጥ! በበሰበሰ ስረዓተ ትምህርት ብዙ ባለድርሻ አካላት ሀላፊነቱን ባልወሰዱበት ከስር ተጀምሮ ባልተሰራ ስራ እና ሰረዓት ተምረህ መጥተህ መጨረሻ ላይ ብትወድቅ(የመስዋዕት በግ ብትሆን) ብቻህን ተጠያቂ አይደለህም! ራስህን ብቻ አትውቀስ! እልፍ በል! ታገል! እመነኝ ታመሰግነኛለህ!
በተመዘገበው ውጤት ልቡ የደማው የአንተው ከርታታው መምህር ወዳጅህ!
እኔም ማለፊያ ውጤት ላስመዘገባቹት ሳይሆን ለቀረባችሁ አልልም ለቀረላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ህይወት ለእናንተ እድል ሰታለች ተጠቀሙበት
http://t.me/ewuketmad