ከመፅሐፍ ገፅ ®


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


፦ በዚህ ቻናል የሚዳሰሱ ነገሮች
፦ የሀገራችን ታሪኮች
፦ እውነታዎች
፦ የ ሀገር እና ባህር ማዶ ፍልስፍናዎች
፦ የስነ ልቦና ምክሮች
፦ የአያቶቻችን ተረቶች (Bed time story )ይሉታል ነጮቹ
፦ ፖለቲካዊ አድምታ በእኔ እይታ
፦ PDF መፅሐፍት እና ግጥሞች
Group @ewuketmad2
አስታየት፡ ጥያቄ እና ጥቆማ
@Areg05
@Areg07 አድርሱን

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




✝✝✝✝✝✝✝✝✝🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 🌈
🌈 አላስፈላጊ ነገሮች ላይ ማትኮር ኃላፊነታችን ያስዘነጋናል።
"

"
አስቡት እስኪ … በማይረባ ነገር ላይ የሚያተኩር አእምሮ መከናወን የሚጋባቸውን ነገሮች ከማድረግ ይልቅ ሀላፊነቱን በሌላ ላይ ለማላከክ ይባትናል

ጥንታዊ ህንዳዊያን ጥበብ የመጀመሪያ ሀላፊነትን ለአለንበት ማህበረሰብ ፡ ሁለተኛ ለቤተሰቦቻችን ፡ ሶስተኛ ደግሞ ለገዛ ራሳችን መሆኑን ያስተምራሉ ። ይህ ተዋረድ ከተገለበጠ፡ ማህበረሰብ መፍረክረክ ይጀመራል ። ማህበራዊ ሀላፊነት የእያንዳንዱ ዜጋ መሆን ይገበዋል ። ሀላፊነት እና ነፃነት ጎን ለጎን ይሄዳሉ ። የመልካም ዜጋ አይነተኛ መለያው ተገቢውን የስራ ድርሻውን ለመፈፀም ፍቃደኛ ሆኖ መገኘቱ ነው

" የሀያልነት ዋጋው ሀላፊነት ነው "
:
:
:
የሚቀድመውን እናስቀድም
ሀላፊነትን እንቀበል
በአንድ ወቅት አንድ ህፃን እማዬ አለ
እናትም ወዬ አለችው
ህፃኑ ፡ ዳኒ መስታወቱን ሰበረው አለት
አናት ፡ ምን አድርጎ
ህፃኑ ፡ ድንጋይ ሰወረውበት ጎንበስ ብሎ አለት
ለጠፋነው ነገር ሀላፊነት እንቀበል
ምክንያቱም የጥፋቱ ባለቤት እኛ ስለሆን
ከተጠያቂነት አሽሽ ሁሉንም ትክክለኛው ስፍራና ሰዓት አንጋፈጥ ። ሀላፊነታችንን ከልተቀበልን ማን ሊቀበልልን ።

💯💯😌💯Don't Feel Your Fear 💯💯💯💯💯💯
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏


http://t.me/ewuketmad


አቅሙ አለኝ የምትሉ ሰዎች በተገለፁት ዘርፍ መወዳደር ትችላላችሁ


ሁዳረም የኪነት ውድድር

🔔🔔🔔3ተኛው ዙር የኪነት በዮዳኒ ኪነታዊ ውድድር እንደ አውደዓመት አመቱን ጠብቆ በተደራጀ መልኩ መጣ📢


የመወዳደሪያ ዘርፎች

🎬ትወና [ከ2 ደቂቃ ያልበለጠ ተንቀሳቃሽ ምስል-Video]

🎤በድምፅ[የፈለጉትን አይነት ዜማ በማንጎራጎር በድምፅ በመላክ]

🎨በስዕል [የእጅ ስዕል፣ ውበት ያረፈባቸው ስዕሎች]

📸ፎቶ ማንሳት[በዝምታ ብዙ የሚናገሩ ጥንቅቅ ያሉ ተናጋሪ ፎቶዎችን አንስቶ በመላክ]

📝በስነ-ጽሁፍ [አጭር ወግ፣ አጫጭር ታሪኮች፣ ግጥም፣ እና የተለያዩ ፈጠራ የታከለባቸው ስነጽሑፎች]

📚ንባብ እና ትረካ[የግጥም ወይም የወደዱትን የመጽሀፍ አልያም የወግ ትረካን ማራኪ በሆነ መልኩ ተርኮ እና አንብቦ በድምፅ መላክ]

🪗የዜማ መሳሪያ መጫወት[ባህላዊም ሆነ ዘመናዊ የዜማ መሳሪያዎችን እየተጫወቱ በተንቀሳቃሽ ምስል ከ2 ደቂቃ ሳይበልጥ መላክ]



በውድድሩ መጨረሻ

🥇1ኛ የወጣ/ች 500ብር
🥈2ኛ የወጣ/ች 300ብር
🥉3ኛ የወጣ/ች 200ብር
🏅4ኛ የወጣ/ች 100ብር
🎖5ኛ የወጣ/ች በቻናሉ የአድሚንነት ድርሻ ይሰጣል
🏵6ኛ የወጣ/ች በቻናሉ የአድሚንነት ድርሻ ይሰጣል
🏵7ኛ የወጣ/ች በቻናሉ የአድሚንነት ድርሻ ይሰጣል



ማሳሰቢያ

💬በውድድሩ የገንዘብ አሸናፊዎች በራሳቸው ፈቃድ በጥቅሉ እስከ 2ሺህ ብር ለ "ስለ እናት down syndrome እና otisem የተጠቁ ህፃናትን እና ወላጅ ያጡ ህፃናትን ማሳደጊያ"  አዲስ አበባ ፤ ሣር ቤት በተለምዶ ቫቲካን ኤንባሲ አካባቢ  ለሚገኘው የተራድኦ ድርጅት ገቢ ማስድረግ ፤ በተጨማሪም በአካል በቦታው መገኘት ለሚችሉ ያሉትን መጠየቅና አዝናኝ የሆነ መርሃግብርን ለተራድኦ ድርጅቱ ማህበረሰብ አቅርቦ መመለስን ያካተተ።

💬 ማንኛውም በዚህ ውድድር ላይ የሚቀርብ የተወዳዳሪዎች ስራ የባለቤትነት መብቱ በ2ሺህ ሰዎች ፊት የተጠበቀ ነው።

💬ዳኝነቱ 60 በመቶ ከውድድሩ አዘጋጆች በተሰየሙ ዳኞች፤ 40 ከመቶ በተመልካች

💬 ውድድሩ ዙሮች የሚኖሩት ሲሆን፤ ከአንደኛው ዙር ወድድር በኋላ በይፋ ቀጣዮቹን ዙሮች የምናሳውቅ ይሆናል

💬ደንብና ግዴታዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ።

🕐ማንኛውም መወዳደር የሚፈልግ ሰው ከዛሬ ማለትም ከቀን 18/7/2016 ዓ.ም እስከ 30/7/2016 ዓ.ም ድረስ መወዳደሪያ ስራችሁን ስም፣ አድራሻ እና ስልክ-ቁጥር በማያያዝ ከዚህ በታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ማስገባት ይችላል:-👇

@Dayanuna

@MAHiiiiiiTA

@Yoakin_92




💬ከውድድሩ ውጪ በፈቃደኝነት ሳርቤት ያሉ
"ስለ እናት down syndrome እና otisem የተጠቁ ህፃናትን እና ወላጅ ያጡ ህፃናትን ማሳደጊያ"  አዲስ አበባ ፤ ሣር ቤት በተለምዶ ቫቲካን ኤንባሲ አካባቢ  ለሚገኘው የተራድኦ ድርጅት ወገኖቻችን በአካል መጠየቅ ለምትፈልጉ
@znetsebrak በውስጥ አውሩን።

ተጀመረ.................

@gbw_dan

Share Share->->->


(ምንድነው ንግድ ባንክ CBE ብር ምናምን ለማንኛውም ይሄን ታሪክ ተጋበዙልኝ ትዝታን ሳሰላስል የዘመኑ ሌባ ማለቴ-ዳንኤል ክስረት ትዝ አለኝ 😐)


የታጠቁ ዘራፊዎች ወደ ባንክ ገብተው “አንድም ሰው እንዳይንቀሳቀስ!ገንዘቡ የመንግሥት ነው፤ ህይወታችሁ ግን የእናንተ ነው” ሲሉ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ፡፡ሁሉም ሰው ወለሉ ላይ በደረቱ ተኛ፡፡ ይኼ “Mind Changing Concept” `ይባላል፤ ከተለመደው ወጣ ባለ መልኩ የሰዎችን አስተሳሰብ መቀየር ነውና፡፡ ጠረጴዛ ላይ ተደፍታ የነበረች አንዲት ሴት የማጉረምረም ድምጽ ስታሰማ፣ ከዘራፊዎች አንዱ ቆጣ ብሎ፣ “እመቤት እንደሰለጠነ ሰው አስቢ እንጂ፡፡ ይህ እኮ ዘረፋ እንጂ አስገድዶ መድፈር አይደለም ” አላት፡፡ ፀጥ አለች፡፡ ይኼ “Being Professional” ነው፤ በሰለጠንክበት ጉዳይ ላይ ብቻ ትኩረት ታደርጋለህ፡፡ ከመዘረፍም በላይ መደፈርም አለና። ዘራፊዎቹ ያለምንም ችግር ቤታቸው ገቡ፡፡

ከዘራፊዎቹ መካከል ልጅ እግሩ እና የMaster of Business Administration ተመራቂው የተዘረፈው ገንዘቡ እንዲቆጠር ሃሳብ አቀረበ፡፡ ነገር ግን በዕድሜ ታላቅ የሆነውና እስከስድስተኛ ክፍል ብቻ የተማረው ዘራፊ፣ በቁጣ “አንተ የማትረባ ደደብ! ይህን ሁሉ ገንዘብ ማን ይቆጥራል? ዛሬ ማታ በቴሌቪዥን ዜና ላይ ስንት እንደዘረፍን ይነግሩናል፡፡” ይኼ “Experience” ይባላል፡፡ ዛሬ ዛሬ በትምህርት ከሚገኝ ዕውቀት  ይልቅ ‘ልምድ’ የበለጠ ዋጋ አለው፡፡ ዘረፋው ከተፈፀመ በኋላ፣ የባንኩ ማናጀር የባንኩን ሱፐርቫይዘር ጠርቶ በአስቸኳይ ፖሊስ እንዲጠራ ነገረው፡፡ ሱፐርቫይዘሩ ግን፣ “ቆይ ተረጋጋ! እየውልህ፣ መጀመሪያ ከካዘና 10 ሚሊየን አንስተን ለራሳችን እንውሰድ፡፡ ከዚያም ባለፉት ወራት የወሰድነውን 70 ሚሊየን እንጨምርበት፡፡ ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ያለብን ይህን ገንዘብ ዛሬ ከተዘረፈው ጋር ደምረን ነው” አለው፡፡ ይኼ “Swim with the tide” ይባላል፡፡ የተፈጠረን አስቸጋሪ ሁኔታ ለራስ ጥቅም ማዋል እንደማለት፡፡ ሱፐርቫይዘሩም አለ፣ “በየወሩ ዘረፋ ቢካሄድብን እንዴት መልካም ነበር!”

በሚቀጥለው ቀን፡፡ ከባንኩ የተዘረፈው ገንዘብ 100 ሚሊየን እንደሆነ በቴሌቪዥን ዜና ተነገረ፡፡ዘራፊዎች ደነገጡ፤ የዘረፉትንም መቁጠር ጀመሩ፤ ማመን አቃታቸው፤ ደግመው ቆጠሩ፤ ያው ነው፡፡ ትንሽ ቆይተው እንደገና መቁጠር ጀመሩ፤ ተመሳሳይ መጠን 20 ሚሊየን ብቻ! በጣም ተናደዱ፣ “እኛ ህይወታችንን ለአደጋ አጋልጠን 20 ሚሊየን ብቻ ስናገኝ፣ የባንክ ማናጀሩ ቁጭ ብሎ 80 ሚሊየን እንዴት ያገኛል?” ከንፈራቸውን ነከሱ፣ ጠረጴዛውን በቡጢ ነረቱ፡፡ ሌባ ከመሆን መማር ይሻላል ማለት ይህ አይደል?i (Africa’s elites are lords of poverty! ያለው ማን ነበር?) የማናጀሩ ፊት በፈገግታ እንደ ማለዳ ፀሐይ አብረቅርቋል፤ የደስታ ግምጃ አድምቆታል፡፡ በሽርክና ገበያው የተፈጠረበት ጉድለት ተሞልቶለታልና፡፡ ይኼንን “Seizing the opportunity” ይሉታል፡፡ ዋነኞቹ ዘራፊዎች እነማን ናቸው? የሚል ጥያቄ ማስቀመጥ ፈልጌ የነበረ ቢሆንም የንግድ ባንክ ማናጀሮችን ፈራዋቸው 😊


Source some where


rel='nofollow'>Http://t.me/ewuketmad


ከ 100 ዓመታት በፊት የተቀረፀ የ አጤ ምኒልክ ትክክለኛው ድምፃቸው ነው ከግዜያት በኋላ ስለማናገኘው እባካችሁ ለትውልድ እናስቀምጥ ለዛሬ ላስረከቡን እጅ እንነሳለን !!🙏🙏🙏


http://t.me/ewuketmad


#ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ

• ከመተኛትህ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ አእምሮህ ዉስጥ ያሰብከዉ ሰዉ ለደስታህ አለበለዚህ ለሀዘንህ ዋናዉ ምክንያት ነዉ

• የምትወደዉን ሙዚቃ ስትሰማ ደስ የሚልህ ከሙዚቃዉ ጋር የተገናኘ የሆነ ትዝታ ስላለህ ነዉ

• በሰዉ ቸል የመባል ህመም 'ሰዉነት ላይ እንደደረሰ አደጋ' አይነት ከባድ ነዉ

• ከዚህ በፊት ስለሆነ ነገር ለማስታወስ ስትሞክር ለመጨረሻ ጊዜ መቼ እንዳስታወስከዉ ለማወቅ እንጂ የፈፀምከዉን ድርጊት አይደለም

• የሆነ ሰዉ መጥቶ “አንዴ የምጠይቅህ ጥያቄ አለኝ ” ካለህ በቅርቡ የፈፀምካቸዉን መጥፎ ነገሮች አእምሮህ ማሰብ ይጀምራል

• በደስታ ካለቀስክ የመጀመሪያዉ የእንባህ ዱብዳ የሚወጣዉ ከቀኝ አይንህ ሲሆን በመጥፎ ስሜት ካለቀስክ ደግሞ የግራዉ አይንህ እንባ ቀድሞ ይፈሳል

• በቀላሉ ነገሮችን ለማስታወስ አይንን መጨፈን ጠቃሚ ነዉ

• 80 ፐርሰንት የሚሆነዉ የሰዉ ልጅ ህመሙን ለመርሳት ሙዚቃን እንደማምለጫ መሳሪያ ይጠቀማል

• ስትሞት በህይወት ዘመንህ ስለነበሩህ እቅዶችና ስለሰራሃቸዉ ነገሮች ለ 7 ደቂቃ ያህል በትዝታ ትጓዛለህ

• በአንድ ጊዜ እስከ 5 የተለያዩ ነገሮች አእምሮህ ማሰብ ይችላል

• ከተለመደዉ ጊዜ በላይ የሚምሉ ሰዎች ዝም ከሚሉ ሰዎች ይልቅ ታማኝ ናቸዉ

• ከመጠጥ ጠርሙስ ላይ ወረቀቱን ማንሳት ከጀመርክ የወሲብ ስሜትህ እየተነሳሳ ነዉ

• ትልቅ አይኪዉ ያላቸዉ ሴቶች የሚፈልጉትን አይነት ወንድ ጓደኛ ለማግኘት በጣም ይቸገራሉ

rel='nofollow'>Http://t.me/ewuketmad


🇪🇹🇪🇹አድዋ🇪🇹🇪🇹

ምኒሊክ ተወልዶ በያነሣ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ጊዜ ሃበሻ።

ገበየው ቢሞት ተተካ በባልቻ
መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ።

የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው
ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው።
.
.
.
.
የአድዋ ድልየኢትዮጲያ ብሔራዊ ከብር ማኅተብ ፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንድል ነው። የመላው አለም የተፈጥሮአዊ ግብር እና ሰበአዊ ክብር የተደሠው፤ በእውነት እና ፍትህ ህልውናና ምልክት ላይ የተሰካ ትልቅ ጥርስ የተነቀለው …… በአድዋ ታላቅ ህዝቦች ታላቅ ድል ነው።




የአድዋ ድል ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረው በሠባተኛ አመቱ በ1895 ዓ.ም አሁን ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ያለበት ሥፍራ ምኒሊክ አደባባይ ነው።




ይህንን ድል ለአቀናጁን ቀደምት አያቶቻችን ክብርና ምስጋና ይግባቸው። ሁሌም ስማቸው በሰሩት ታሪክ ከመቃብር በላይ ይሆናል ።
🇪🇹🇪🇹ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ ።🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹ክብር ለጀግኖቻችን፡ ክብር ለአፈሰሱት ደም።🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹ከሁሉም በላይ ክብር እምዬ ምኒሊክ🇪🇹🇪🇹


🇪🇹🇪🇹ክብር ለእናት ሀገራችን ኢትዮጲያ ሁሌም በጀግኖችሽ ከፍ ትያለሽ🇪🇹🇪🇹

🇪🇹እንኳን ለታላቁ የአድዋ ድል አደረሳቹ🇪🇹🇪🇹




credit to፦ @areg07


http://t.me/ewuketmad


#ጣፋጩ_ገዳይ_መርዝ!

በሰሜን አንታርቲካ ላይ የሚኖሩ እስኪሞ የተባሉ ጎሳዎች ተኩላ ለመግደል ሲፈልጉ የሚዘይዱት ዘዴ አለ፡፡ በበረዶ ውስጥ ጫፉ በጥቂቱ የወጣ ቢላ ይደብቃሉ፤ በላዩ ላይ ጥቂት የበግ ደምን ያደርጉበታል:: ተኩላው ደሙን አሽትቶ ይመጣል፡፡ በረዶው ላይ ያለውን ደም መላስ ይጀምራል።

ደሙ ይጣፍጠዋልና ፍጥነቱን እየጨመረ መላስ ይጀምራል፡፡ በዚህ ፍጥነት ውስጥም እያለ ሳያስበው ደም የተቀባው ቢላዋ ምላሱን ይቆርጠዋል፡፡ ነገር ግን ደም መላሱን አያቆምም፡፡ አሁን ላይ ይህ ተኩላ ባለማወቅ ከራሱ ምላስ የሚፈሰውን ደም እየላሰ ነው፣ ሆኖም ጣፍጦታል እና በፍጥነት መላሱን ይቀጥላል። ከመጠን በላይ ደምም ይፈሰዋልና በነጋታው ተኩላው ሞቶ ይገኛል። የራሱን ደም እየጠጣ እንደነበረም አልታወቀውም።

ይህ ተኩላ ከእኛ ታሪክ ጋር ይቆራኛል፡፡ ብዙዎቻችን ጊዜያችንን የምናሳልፈው በስልካችን ላይ አልያም በቴሌቪዥን ላይ ረብ የለሽ ነገር ስናስስ ነው... ጊዜያችንን ሳንጠቀምበት እንዲሁ ያልቃል... ይጣፍጣልና፤ ጥቂት ብቻ አይበቃንም፤ በፍጥነት እና በኃይልም ህይወታችንን፣ ጊዜያችንን ልሰን እየጨረስነው ነው:: በተቻለህ መጠንም ከስራህ እና ከማሰብ ከሚያስተጓጉሉህ ነገሮች ሁሉ ለማራቅ ሞክር።
#ሼር
ምንጭ፦ ድብቁ አእምሮ ድብቁ ኃይል
___//____



http://t.me/ewuketmad


(በዶስቶይቭስኪ እና በሶቅራጥስ መካከል ጠንካራ ውይይት እዚጋ ነበር imagination Discussion)

-ሶቅራጠስ: ሞትን ትፈራለህ?

-ዶስቶቭይስኪ: አይ ጊዜን እፈራለሁ

-ሶቅራጠስ: አትጨነቅ ይህም ጊዜ ያልፋል

-ዶስቶይቭስኪ: ይህ ጊዜ ግን እድሜዬ ነው!።

-ሶቅራጠስ: ልክ ነህ ብቻውን አይሄድም።

-ዶስቶይቭስኪ: ምን ይዞህ ነው የሚሄደው¿

-ሶቅራጠስ: ማጣት የምንፈራውን፤ ሞት የሚወስደው ጊዜ የቀረውን ብቻ ነው።

-ዶስቶይቭስኪ: ሞትን ትፈራለህ?

-ሶቅራጥስ: ይልቁንስ ሕይወትን እፈራለሁ።

-ዶስቶይቭስኪ: ለምን ግን?

-ሶቅራጠስ: ምክንያቱም አሸናፊ የሚያደርገኝ የመኖር ፍላጎት እንጂ ሞትን መፍራት አይደለም።

-ዶስቶይቭስኪ: እንዴት ይህን ፍላጎት እናሸንፋለን?

-ሶቅራጥስ: ከህይወት ዋጋ በላይ የሆነ ነገር በአንተ ውስጥ እንዲኖርህ መፍቀድ

-ዶስቶይቭስኪ: እንዴት ዓይነት¿

-ሶቅራጠስ: ታላቅ እምነት ወይም ታላቅ ፍቅር..!


rel='nofollow'>Http://t.me/ewuketmad


`` ጥሩ ነው ወጣት መሆን። ገንዘብ ባይኖርህ ጤና ይኖርሃል፤ መልክ ባይኖርህ አንጎል ይኖርሃል፤ እውቀት ባይኖርህም ጉራ ይኖርሃል፤ ፍቅር ባይኖርህም ተስፋ ይኖርሃል...ደስታ ባይኖርህም ንዴት ይኖርሃል...መጨነቅህ ቢበዛህ ሪቮልሽን ታስነሳለህ...መኖር ቢያስጠላህ ወይ ቢያቅትህ ራስህን ትገድላለህ...ሰው ባያውቀውም ቅሉ ታሪክ ይኖርሃል ወጣት ነህና..!። ``


፦ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር-ትኩሳት 📖


http://t.me/ewuketmad


📍ቢላ ካልተሞረደ ዶልዱሞ እንደሚቀር ሁሉ የሰውም ልጅ ጠንካራና ብልህ እንዲሆን በተለያዩ ውጣውረድ ማለፍ ግድ ይለዋል።እኚ ውጣውረዶች በሕይወታችን ውስጥ መከሰታቸው ተፈጥሯዊ ነው፣ እኛኑ ለማጎበዝ እኛኑ ለማንቃት እኛኑ ለማጠንከር እኛኑ ለማጀገን ነው ፣የዶሎዶመ ቢላ ለመቁረጥ ከማስቸገርም አልፎ ድካም ነው የሚሆንብን እንጂ እንደተመኘነው አይቆርጥልንም።

📍ያልተፈተነ ማንነትም ከተራራው ጫፍ የሚያደርስ ጽናትን አያላብሰንም። እውነታው መሞረድ ነው እውነታው መሳል ነው፣እውነታው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ማለፍና ራስን ማጠንከር ነው። የሰው ልጅም ዛሬ በሁኔታዎች እራሱን እየፈተነ ማንነቱን ያጠነክራል። ዛሬ በሁኔታዎች ልቡን እያጠነከረ ለነገው ይዘጋጃል፣ዛሬ በሁኔታዎች መንፈሱን እያጠነከረ የወደፊቱን መንገድ በቀላሉ ያቅዳል።

🔑ውስጣችንን አጠንክረን የገባንበትን ፈተና በድል እንወጣው። ቁስላችን ስብራታችን ውድቀታችን ሁሉ ያጠነክሩናል እንጂ አይገሉንም፡፡

http://t.me/ewuketmad


---------------------------
አንድ ጊዜ አባት ከቢሮ ድክም ብሎት
ቤት ሲገባ ልጁ ሁለት ፖም🍏 ይዞ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሏል፡፡ አባት ፈገግ አለና ልጁን አንዱን ፖም እንዲሰጠዉ ጠየቀዉ፡፡ ይህን የሰማዉ ልጅ ሁለቱንም ፖሞች አንድ አንዴ ገመጥ ገመጥ አደረጋቸዉ፡፡

#በዚህ_ጊዜ አባት ተቆጣ... “አንተ ሆዳም! እንደዚህ ይደረጋል! አንዱ አይበቃህምና ነዉ ሁለቱንም ለመብላት የምትጣደፈዉ...!” እያለ የንዴት መትረየሱን አርከፈከፈዉ፡፡

ልጅ አዝኖ እንዲህ አለ “አባዬ እኔኮ ሁለቱንም የገመጥኩት ከሁለቱ የትኛዉ በጣም እንደሚጣፍጥ ለማወቅ ነዉ ... ይሄ በጣም ይጣፍጣል... ስለዚህ እንካ ላንተ! እኔ የቀረዉን ልብላ' ብሎት ለአባቱ የሚጣፍጠዉን ፖም ሰጠዉ:: አባት እንባዉን መቆጣጠር አልቻለም፡፡

#አንዳንዴ_ነገሮች ምንም ሳይገቡን መጮህ፣ መናደድና መቆጣት እንፈልጋለን፡፡ አንድን ነገር ዉጤቱን ገምተን ከምንጀምር ቀረብ ብለን ከመሰረቱ ብንረዳ የበለጠ መልካም ነዉ፡፡



http://t.me/ewuketmad




ሰውዬው በሞት ጣዕር ተይዞ በተኛበት አልጋው አጠገብ የቆሙት ካህን ``ልጄ! እንግዲህ በዚህ ሰዓት ካንተ መስማት የሚገባኝ ኑዛዜ አለ`` ይሉታል። ሰውዬውም የካህኑን ጥያቄ ለመመለስ መስማማቱን በአንገቱ ንቅናቄ ገለፀ።

ካህኑም ``በዚህ ሰዓት ዲያብሎስን ክጃለሁ በማለት ተናዘዝ`` አሉት። ሰውዬው ግን በካህኑ ጥያቄ አልተስማማም። ከአንገቱ ቀና ለማለት እየሞከረ በጣዕር ድምፅ “አባቴ፤ ከዚህ በኋላ ጠላት የማፈራበት ሰዓት ላይ አይደለሁም” በማለት ተመልሶ ተጋደመ።🙂



         ፦ ጥበብ ቅፅ 2 📖


httl://t.me/ewuketmad


አባቶቻችን እንዲህ አ

"እሳትና ውኃን ማዋሐድ እንደማይቻል በሌሎች ኃጢአት መፍረድም በራስ ኃጢአት ከመጸጸት ጋር አብሮ አይሔድም" ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

"የማያማትብ እጅ ቀኙም ግራውም አንድ ነው" አባ ፓስዮስ ዘደብረ አቶስ

"እግዚአብሔር ለኃጢአተኛ ሰው ያለው ፍቅር
ጻድቅ ሰው ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር ይበልጣል"
አባ አርሳኒ

"ሕፃን ልጅ እናቱ ስታጥበው ያለቅሳል:: ሕፃን እምነት (ትንሽ እምነት) ያላቸው ሰዎችም ነፍሳቸውን የሚያጥብ መከራ ሲመጣባቸው እግዚአብሔርን ያማርራሉ"  አባ ስምዖን

"ዕለትን የሠጠህ እርሱ ለእለት የሚበቃህንም ይሠጥሃል"  ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

"እጅግ ምርጡ ጸሎት "ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ" ማለት ነው"
ባሕታዊ ቴዎፋን

"ሲያመነዝር ያየኸውን ሰው አንተ ንጹሕ ብትሆንም አትናቀው:: ምክንያቱም አታመንዝር ያለው ጌታ አትፍረድም ብሏል"  አባ ቴዎዶር

"አንድ ሰው ኃጢአት ሲሠራ ብታይ እንኳን አትፍረድበት:: አንዳንዴ ዓይንህም ሊሳሳት ይችላል"
ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

"ለኃጢአተኛው ክንፍህን ዘርጋለት:: ኃጢአቱን ልትሸከምለት ባትችል እንኳን ሸፍንለት"
ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ

ከአበው አንዱን ትሕትና ምንድርን ነው? ብለው ጠየቁት:: እርሱም "ትሕትና ማለት ወንድምህ በበደለህ ጊዜ እርሱ ይቅርታ ሳይጠይቅህ በፊት ቀድመህ ይቅር ማለት ነው" አለ::

"ይቅር ካላልክ ገነትም ይቅርብህ" አባ ኤፍሬም አረጋዊ [ If you don’t forgive, forget heaven]

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ለመምህራችን ቃለ ህይወት ያሰማልን

https://t.me/ewuketmad


#ዩኒቨርስቲ_ገነት_አይደለም‼️
በመምህር [ አበባየሁ ጌታ ] የዩኒቨርስቲ አስተማሪ

ከስር ያያዝኩት የ#Masters_Degreeዬ ውጤት ነው ፤ የዚህ ልጥፍ ዓለማ ራስን ማንቆለጳጰስ ምናምን ሳይሆን ልፋቴ እና የሚከፈለኝ አለመገናኘቱ ሲቀጥል ዩኒቨርስቲ መግባት እና ትምህርት መስቀል ትርጉም አልባነቱን እንዲሁም 12ኛ ክፍል ውጤት ላልመጣላቸው መጽናኛ እንዲሆናቸው ነው።

በአንድ የመንግስት ዩኒቨርስቲ መምህር ነኝ፤ከህይወቴ 17 ዓመት ለመጀመሪያ ድግሪ ሁለት ዓመት ደግሞ ለMasters ድግሪ በአጠቃላይ 19 ዓመታትን ያጠፋሁበት በትምህርት ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም Highschool እና መሰናዶ ጓደኛቼ የነበሩ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ እና በተለያዩ የሙያ የንግድ እና የመሳሰሉ ነገሮች ላይ የተሰማሩ በአሁኑ ሰዓት የቤት አከራዮቼ ናቸው ፤ ባለመኪና ባለሆቴል ጽድት ያለ ቡቲክ ብቻ ምን አለፋህ በአጠቃላይ ከእኔ እጅግ በጣም በተሻለ የኑሮ ሁኔታ ነው የሚገኙት!😭

በአሁኑ ሰዓት በመንግስት ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ ድግሪ የያዘ የዩኒቨርስቲ መምህር የሚከፈለው ደመውዝ ግብር ሳይቀነስ 12,579 ብር ነው ፤ 35% ግብር እንዲሁ የጡረታ ሲወጣ ኪሴ የሚገባው 9956(ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ስድስት)ብር ነው።

እንግዲህ በትምህርት ደረጃዬ ሲወራልኝ የዩኒቨርስቲ መምህር ነኝ ፤ ሶስተኛ ድግሪዬን ብሰራ እና ዶ/ር አበባየሁ ጌታ ብባል ወደ 16,000 ብር ከታክስ በፊት እና ወደ 13,000 ብር ገደማ ከታክስ በኋላ እጄ ላይ ይደርሳል።

እና ለምንህ ነው ዩኒቨርስቲ ቀረብኝ ብለህ የምትጨነቀው?

ወዳጄ/ወንድሜ/እህቴ 12 ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት አልመጣልህም?

እሰይ እንኳንም አልመጣልህም! ራስህን ለመቀየር ታትር ፣ አጫጭር ኮርሶችን ከዩቲዩቭ አውርድ ፣ተማር ፣ቪዲዮ ቱቶሪያል ተከታተል ፣ ግራፊክስ እና የመሳሰሉ ገንዘብ ልትሰራ የምትችልባቸው ከምርጥ ኮንተንት ጋር ከመጣህ የዩቲዩብ ስራዎች ብቻ ብዙ ብዙ አማራጮች አሉህ፣ ተስፋ አትቁረጥ! በበሰበሰ ስረዓተ ትምህርት ብዙ ባለድርሻ አካላት ሀላፊነቱን ባልወሰዱበት ከስር ተጀምሮ ባልተሰራ ስራ እና ሰረዓት ተምረህ መጥተህ መጨረሻ ላይ ብትወድቅ(የመስዋዕት በግ ብትሆን) ብቻህን ተጠያቂ አይደለህም! ራስህን ብቻ አትውቀስ! እልፍ በል! ታገል! እመነኝ ታመሰግነኛለህ!

በተመዘገበው ውጤት ልቡ የደማው የአንተው ከርታታው መምህር ወዳጅህ!


እኔም ማለፊያ ውጤት ላስመዘገባቹት ሳይሆን ለቀረባችሁ አልልም ለቀረላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ህይወት ለእናንተ እድል ሰታለች ተጠቀሙበት


http://t.me/ewuketmad


..
አባትና ልጅ ተያይዘው ሽርሽር ሲሄዱ ከ አማኑኤል ሆስፒታል አጠገብ ይደርሳሉ። አባት ለልጁ ይህ የእብዶች ሆስፒታል ነው ብሎ ያሳየዋል። ልጅም አባቱን ማነው ሚጠብቃቸው? ብሎ ይጠይቀዋል። አባትም በር ለይ የቆሙትን ሁለት ኮስማና ዘበኞች ያሳየውና እነሱ ናቸው ይለዋል። ልጁም ይገረምና ይህ ሁሉ እብድ ተባብሮ ቢመጣባቸው ምን ያደርጋሉ ? ብሎ እንደገና ይጠይቀዋል። አባትም የኮረኮሩት ያህል ይስቅና፦
እብዶች ምን ጊዜም ቢሆን ሊተባበሩ አይችሉም ! ብሎ መለሰለት።
___

#ደራሲው
( በዓሉ ግርማ )


እኛስ በሀገር ጉዳይ መተባበር ያቀተን እብድ ሆነን ነው ወይስ ?
      💚💛❤
   ••●◉Join us share◉●••
http://t.me/ewuketmad


በማህበራዊ ህይወትህ በተግባቦት ለመኖር ሊረዱህ የሚችሉ አንዳንድ ማህበራዊ ህጎች፡-

1. አንድን ሰው ያለማቋረጥ ከሁለት ጊዜ በላይ አትጥራ!

2. የተበደርከውን እቃ ወይም ገንዘብ፥ የተበደርከው ሰው ሳያስታውስህ ወይም ሳይጠይቅህ መልስለት። የአንተን የታማኝነት ባህሪ ያሳያልና።

3. የሆነ ሰው ምሳ ወይም እራት ሲጋብዝህ ውድ የሆነውን አትዘዝ።

4. ‘እስካሁን አላገባህም?’ ወይም ‘ልጆች የሉህም?’ ወይም ‘ለምን ቤት አልገዛህም?’ ወይም ‛ለምን መኪና አትገዛም?’ የሚሉ የማይጠየቁ ጥያቄዎችን አትጠይቅ።

5. ከጓደኛህ ጋር በታክሲ ስትሄድ፥ እሱ ዛሬ ከከፈለልህ በሌላ ቀን አንተ ክፈል።

6. የሀሳብና የእይታ ልዩነቶች አክብር። ለአንተ 6 የሆነውን በሌላው ዘንድ 9 ሊሆን ይችላል።

7. ከማንም ጋር ስታወራ የሰው ሀሳብ አታቋርጥ። እስኪጨርስ ጠብቀው።

8. ማንም በምን ነገር ከረዳህ "አመሰግናለሁ" ማለትን ይልመድብህ።

9. ማንንም ስታመሰግን በአደባባይ አመስግን። ትችትህ ደግሞ በግል ይሁን።

10. የሆነ ሰው ስልኩ ሰጥቶህ፥ ከስልኩ ላይ ፎቶ ሲያሳይህ፤ ካሳየህ ፎቶ ሌላ ለማየት አትሞክር።

11. አንድ የምታውቀው ሰው፥ የሀኪም ቤት ቀጠሮ እንዳለው ቢነግርህ፤ ለምን እንደሆነ አትጠይቅ! "መልካሙን ያሰማህ" በለው እንጂ!

12. አንድ ሰው ከአንተ ጋር እያወራ፣ ስልክህ ላይ ማፍጠጥ ነውር ነው።

13. እስካልተጠየቅክ ድረስ በጭራሽ ምክር አትስጥ።

14. ከብዙ ጊዜ በኋላ ከአንድ ሰው ጋር ስትገናኝ፣ ስለእድሜውን እና ደመወዙን አትይጠይቀው። እርሱ ራሱ ለማውራት ጀምሮት፤ ፈቃደኛ እስከሚሆን

15. በቀጥታ በማያሳትፍህ፣ በማያገባህ ነገር አትግባ።

16. በመንገድ ላይ ከማንም ጋር እየተናገርክ መነፀር አድርገህ እንደሆነ አውርደው። የአክብሮት ምልክት ነው። የዓይን ለዓይን ግንኙነት እንደ ንግግርህ አስፈላጊ ነውና!

17. በድሆች መካከል ስለ ሀብትህ ፈጽሞ አትናገር። እንዲሁም በመካኖች መካከል ስለ ልጆችህ ፈፅሞ አታውራ።

18. እንዲህ አይነቱ፦ ጥሩ መልእክት ካነበብክ በኋላ "ስለመልእክቱ አመሰግናለሁ" ማለትን አትርሳ።

https://t.me/ewuketmad


😄ንጉሡ በከተማው የሚገኝ ከሁሉ የሚበልጠውን ሊቅ እንዲያመጡለት ባለሟሎቹን አዘዘ። ባለሟሎቹን በጥበቡ፣በበማስተዋሉም እጅግ የላቀ የሚሉትን ጠቢብ አመጡለት።ንጉሡም ወደ ጠቢቡ እየተመለከተ "ሶስት ጥያቄዎች እጠይቅሃለሁ የመጀመሪያው ጥያቄዬ እግዚአብሔር የት ነው የሚኖረው?"

⭐ጠቢቡም እጅ ነስቶ ይህን ጥያቄ ለመመለስ ትኩስ ወተት እና ስኳር ያስፈልገኛል አለ።ንጉሡም እንዲመጣለት አደረገ። ጠቢቡም ስኳሩን ወተት ውስጥ ጨምሮ አማስሎ ለንጉስ ሰጠው እንዲቀምሰው
"ግርማዊነቶ ወተቱ እንዴት ያለ ጣዕም አለው?" አለው
ንጉሱም"ይጣፍጣል"አለው
ጠቢቡም መልሶ"ከወተቱ ውስጥስኳሩን ማየትይቻላል? "ብሎ ጠየቀው
ንጉሱም"አይቻልም ስኳሩ ሟምቷል።"አለው
ጠቢቡም "ልክ እንደሟሟው ስኳር እግዚአብሔር ሁሉም የአለም ስፍራ ላይ አለ አናየውም እንጂ"አለው

⭐ንጉሡ በመልሱ ረክቶ ሁለተኛው ጥያቄ ጠየቀው"ፈጣሪን እንዴት ልናገኘው እንችላለን?"

🟡**ጠቢብም ግርማዊነቶ ይህንን ለመመለስ የወተት ክሬም ያስፈልገኛል አለ። ንጉሡም እንዲያመጡለት አዘዘ።
ጠቢቡም እጅ ነስቶ"ግርማዊነቶ በክሬሙ ላይ በቅቤ ይታያል?"ብሎ ጠየቀው**
ንጉሡም"ክሬሙን ብንናነሳው ቅቤ ከስር እናገኛለን ከላይ ግን አይታይም "አለው
ጠቢቡም"የሁለተኛ ጥያቄዎም መልስ እንዲህ ነው ፈጣሪም በእውነተኛ ማንነታችንን ወደ ልባችንን ስንመለስ እናገኘዋለን"አለው።

🟡ንጉሡም በጠቢቡ ተደንቆ ወደ መጨረሻው ጥያቄ አለፈ"እግዚአብሔር ምን ማድረግ ይቻለዋል? "አለው

ጠቢቡም ከንጉሡ ሎሌዎች አንዱ እንዲቀርብለት ጠየቀ። ንጉሡም አስጠራለት። ጠቢቡም"ይህ ጠባቂዎ ንጉሠ ነገሥት ነው እንበል እናም ግርማዊነቶ ለንጉሥ ዙፋን ይገባዋል እና እርሶ ከእኔ ለጎን ይቆማሉ ጠባቂዎ ደሞ በዙፋኖ ይቀመጣል "አለ
ንጉሱም በመስማማት ዙፋኑን ለሎሌው ለቀቀ።
ጠቢቡ ወደ ንጉሡ እያየ" ፈጣሪ ሎሌን ጌታ፤ጌታን ሎሌ ማረግ ይችላል"አለው።
***


http://t.me/ewuketmad

Показано 20 последних публикаций.

455

подписчиков
Статистика канала