▬▬▬▬
▮ፍረጂን ▮
▬▬▬▬
ውዲዬ...
የጥንቷ ኢትዮጵያዬ
በደንብ ታዘቢ
ትናንት ላይ ሆነሽ ዛሬ አታሸልቢ
ከሰውነት ገዝፎ ወንበር ሲያበራየን
ፍቅር...ሠላም ታጥቶ ባሩዱ ሲዳኘን።
◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
ሰላም ፈራን ኢትዮጵያያዬ
ሰላም ፈራን አበባዬ
ሰላም እኛን ፈራን
መዋደድ አቅቶን ጦርነት ሸተተን
በቀን ቀን በራሳችን ወንድም
ጠብን እየነዳን ይኸው አጣን ሰላም።
◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
ልክ እንደ ዳቦ ስም የጦር ስም አወጣን
ግራ ዘማዊውን ምንም እንዳልሰራ ጭራቅ አውሬ አልን
እስቲ አንቺ ተመልከች
በአንክሮ እዪን ያንቺን የጦር ህዝቦች
ያ ግራ ዘመሙ
ኢትዮጵያ ትቅደሙ
ምን ለውጥ አመጣ?
ለድሀው ላ'ራሹ መሬትም አልሰጠ?
ታዘቢ አንቺ'ማ
አልደረሰም እንዴ መሬት ለተቀማ?
ቀኝ ዘማዊንም አልናቸው የቀንጅብ
የእጅ አመል ቢኖርም ሰርተዋል እንደ ንብ
የዘመናት ቁጭት
የህዝብ የግርእሳት
አባይን በመድፈር
ላንቺ ለጦቢያ ግብሩን እንዲገብር
ይህንን ገድል ግን በዝምታ ዋጥሽው
ወይ አልወረደልሽ ወይ ቆርጠሽ አልጣልሽው።
◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
አሁንም የጦር ስም አስፈለገንና ለዘመቻ ሆይታ
ይኸው እያልን ነው... ሀገራ አሸባሪ አፈራራሽ ጁንታ።
ታዲያ ስለዚህ ግን ምንምን አላውቅም
ባንቺ ትዝብት ሆኜ አልሆንም አፈጽድቅ
ካፈረሰሽ ይፍረስ
ካሳፈረሽ ደም ያልቅስ
ከደፈረሽ በደዌ ይመታ
ካገሩ 'ርቆ በግፍ ይንገላታ
ካኮራሽም ይኩራ ይውጣ ከሰው ተራ
ከፍ ብሎ ይግዘፍ ከዳሽን ተራራ
ፍርዱን ላንቺ ልተው
ፍርድሽ አይበሉ ነው
በጥሊያን ሶማልያ በሁሉ የታየው
እናም ኢትዮጵያዬ ካንቺ ጋ ነው ፍርዱ
ጁንታ የተባሉት ምን እንሚሆኑ።
.. ..
.. ..
.. ..
➦በ3ኛው ወር●●●ዘንድሮ
✍ዳኒ የዮዲት ልጅ(ዮዳሄ)
▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭
▯@gbw_dan@gbw_dan▮
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬
▮ፍረጂን ▮
▬▬▬▬
ውዲዬ...
የጥንቷ ኢትዮጵያዬ
በደንብ ታዘቢ
ትናንት ላይ ሆነሽ ዛሬ አታሸልቢ
ከሰውነት ገዝፎ ወንበር ሲያበራየን
ፍቅር...ሠላም ታጥቶ ባሩዱ ሲዳኘን።
◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
ሰላም ፈራን ኢትዮጵያያዬ
ሰላም ፈራን አበባዬ
ሰላም እኛን ፈራን
መዋደድ አቅቶን ጦርነት ሸተተን
በቀን ቀን በራሳችን ወንድም
ጠብን እየነዳን ይኸው አጣን ሰላም።
◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
ልክ እንደ ዳቦ ስም የጦር ስም አወጣን
ግራ ዘማዊውን ምንም እንዳልሰራ ጭራቅ አውሬ አልን
እስቲ አንቺ ተመልከች
በአንክሮ እዪን ያንቺን የጦር ህዝቦች
ያ ግራ ዘመሙ
ኢትዮጵያ ትቅደሙ
ምን ለውጥ አመጣ?
ለድሀው ላ'ራሹ መሬትም አልሰጠ?
ታዘቢ አንቺ'ማ
አልደረሰም እንዴ መሬት ለተቀማ?
ቀኝ ዘማዊንም አልናቸው የቀንጅብ
የእጅ አመል ቢኖርም ሰርተዋል እንደ ንብ
የዘመናት ቁጭት
የህዝብ የግርእሳት
አባይን በመድፈር
ላንቺ ለጦቢያ ግብሩን እንዲገብር
ይህንን ገድል ግን በዝምታ ዋጥሽው
ወይ አልወረደልሽ ወይ ቆርጠሽ አልጣልሽው።
◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
አሁንም የጦር ስም አስፈለገንና ለዘመቻ ሆይታ
ይኸው እያልን ነው... ሀገራ አሸባሪ አፈራራሽ ጁንታ።
ታዲያ ስለዚህ ግን ምንምን አላውቅም
ባንቺ ትዝብት ሆኜ አልሆንም አፈጽድቅ
ካፈረሰሽ ይፍረስ
ካሳፈረሽ ደም ያልቅስ
ከደፈረሽ በደዌ ይመታ
ካገሩ 'ርቆ በግፍ ይንገላታ
ካኮራሽም ይኩራ ይውጣ ከሰው ተራ
ከፍ ብሎ ይግዘፍ ከዳሽን ተራራ
ፍርዱን ላንቺ ልተው
ፍርድሽ አይበሉ ነው
በጥሊያን ሶማልያ በሁሉ የታየው
እናም ኢትዮጵያዬ ካንቺ ጋ ነው ፍርዱ
ጁንታ የተባሉት ምን እንሚሆኑ።
.. ..
.. ..
.. ..
➦በ3ኛው ወር●●●ዘንድሮ
✍ዳኒ የዮዲት ልጅ(ዮዳሄ)
▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭
▯@gbw_dan@gbw_dan▮
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬