ጥበብ 🚶‍♂️🧑🏿‍መንገደኛ


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


እንኳን ደህና መጣችሁ።
☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘
እንኳን ደህና ቆያችሁ።
በዚህ ጥበብ ሞገደኛ ቻናል ውስጥ
👉አዝናኝና አስተማሪ ፅሁፎች
👉አዳዲስ ኪነጥበባዊ መረጃዎች
👉ግጥም
👉መነባንብ
👉የደራሲያን ስራዎችና ታሪካቸው
👉ትረካ
👉መጽሐፍት
👉ኪነጥበባዊ ኮርስ(ተከታታይ)
የምናቀርብ ይሆናል።
🍂ከጥበብ ጋር አብረን እንጓዝ
ለሌሎች ለማድረስ ✈️SHARE👇
https://t.me/gbw_dan

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




ሕዳር ሲታጠን

እ.ኤ.አ ከ 1914 ዓ.ም እስከ 1918 ድረስ የዘለቀውና የ15 ሚሊዮን ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው ጦርነት በታሪክ የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ተብሎ ይታወቃል፡፡
የጦርነቱ ማብቃት ሊታወጅ ጥቂት ሲቀረውና ዕልቂቱ ቆመ ሲባል
ግን የዓለም ህዝብ ሌላ ፍዳ ማስተናገድ ግድ ሆነበት፤ በሰው ሰራሽ ችግሮች (በዋነኝነት በጦርነት) ተወጥሮ የቆየው መላው የአለም ህዝብ አሁን ደግሞ በእንፍሉዊንዛ በሽታ ከዳር እስከ ዳር ተጠቃ፡፡
በተለምዶ የእሰፓኒሽ ፍሉ ተብሎ የሚታወቀው ይህ ወረርሽኝ መነሻው ከወደ አሜሪካ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ይህም እ.ኤ.አ በጥር ወር 1918 ዓ.ም በአንደኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ ዋዜማ በጦርነቱ ለመካፈል የአሜሪካ ወታደሮች ወደ አውሮፓ ለመጓዝ ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት ከተከሰተው ወረርሽኝ ጋር ይያያዛል፡፡ በካንሳስ በሚገኘው ፉንስተን የወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል የተቀሰቀሰው ወረርሻኙ በሶስት ቀናት ብቻ 45 ሺህ የሚሆኑ ወታደሮችን አጠቃ፤ ወታደሮቹ አትላንቲክን አቋርጠው አውሮፓን እንደረገጡ በሸታውም አውሮፓ ደረሰ፡፡ የእንፍሉዌንዛ በሸታው በአውሮፓ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በፈረንሳይ ቢሆንም በጦርነቱ ምክንያት ፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ ይሆናል በሚል ወረርሽኙ ለህዝብ ሳይገለጽ ተደብቆ ቆይታል፡፡ በሽታው ይፋ የሆነው እ.ኤ.አ በህዳር ወር 1918 ዓ.ም በስፔን በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ መታየቱን ተከትሎ ነበር፡፡ ስፔን በጦርነቱ ተካፋይ አልነበረችምና በአገሪቱ የጦርነት ጊዜ ሳንሱር አልነበረም፤ በመሆኑም የበሽታው መስፋፋት ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን በማግኘቱ ወረርኙ እስፓኒሽ እንፍሉዌንዛ (ስፓኒሽ ፍሉ) የሚለውን ስያሜ አገኘ፡፡

በኢትዮጵያ በሽታው የታየው የመጀመሪያው የበሽታው ምልክት በዓለም ላይ ከታየ ከአስር ወር በኋላ በህዳር ወር 1911 ዓ.ም ነው፡፡ ከህዳር 7 እስከ ህዳር 20 1911 ዓ.ም ለአስራ አራት ቀናት ገደማ የቆየው በሽታው በህዳር ወር የተከሰተ በመሆኑም ህዝቡ የህዳር በሽታ እያለ ይጠራው ጀመር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ይህ በሽታም በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ለበርካቶች ሞት ምክንያት ሲሆን ለበሽታውም የተለያዩ ስያሜዎች ተሰጥተውት ነበር። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ምሁር የሆኑት አቶ አበባው አያሌው የበሽታውን አመጣጥ አስመልክቶም የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መንገድ ስራ በጀመረበት ወቅት በሽታው በመነሳቱ ምክንያት ባቡሩ ያመጣው በሽታ ነው በማለት "የባቡር በሽታ" ይባል እንደነበር ይናገራሉ። በተጨማሪም የተከሰተበትን ወር ተከትሎም "የህዳር በሽታ" ተብሎ መጠራት እንደጀመረም ይናገራሉ።
ብላቴን ጌታ መርስዔ ሀዘን ወልደቂርቆስ የሃያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ በተሰኘው መጽሀፋቸው እንዳሰፈሩት ወረርሽኙ እስከ አርባ ሺህ ኢትዮጵያዊንን ለሞት ዳርጋል፤ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ዘጠኝ ሺህ ዜጎች በበሽታው ሞተዋል፡፡ እንደሚታወቀው የኢትዮጲያ ስታቲክስ እንደተማሪዎች መርጃ መጽሐፍ(Guide book)የተለያየ መረጃዎችን ይሰጠናል፣እናም በሌላ ጥናት በአዲስ አበባ ብቻ ከ6 ሺ ሰው በላይ መግደሉንም የተጠናው ጥናት ያሳያል። ይህንንም ተከትሎ በጀርመን ሀኪሞች ምክክር ህዝቡ ቆሻሻ ከቤታቸው አውጥተው እንዲያቃጥሉ በአዋጅ መለፈፉን አቶ አበባው ይናገራሉ።


በተለይም ህዳር 12 ቀን 1911 ዓ.ም በርካታ ኢትዮጵያዊያን የሞቱበት በመሆኑ ቀኑ በጽዳት ዘመቻ እንዲደረግ በአዋጅ ተነግሮ ስለነበር፣ ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት ይህ ነገር እንደባህል ተወስዶ በየዓመቱ ህዳር 12 ቀን የጽዳት ዘመቻ ይደረግ ጀመር፤ ይህም በተለምዶ ህዳር ሲታጠን የምንለው ነው፡፡

"ይህም የበሽታው መንስዔ ቆሻሻ እንደሆነ በመታመኑ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በሽታው በአየር ይተላለፋል ተብሎ ስለታመነም አየሩን እንደማጠን ይቆጥሩታል" ይላሉ አጥኚዎች።

ከጊዜ በኋላም አየሩ ስለታጠነ ነው በሽታው የጠፋው ተብሎ በየዓመቱ ቆሻሻን ማቃጠልን ህዳር ሲታጠን የሚል ስያሜ ማግኘቱም ከዚህ ተነስቶ መሆኑን ያብራራሉ።


ምንም እንኳን ቆሻሻን ማቃጠል ለአካባቢ ንፅህና ጥሩ ቢሆንም ለአየር ንብረት አሉታዊ አስተዋፅኦ ስላላው ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

"የሚቃጠሉት ቁሳቁሶች በተለይም ፕላስቲክና የባትሪ ድንጋዮች ሃይድሮፍሎሮ ካርበን፣ ሜቴንና ካርበንዳይሞኖክሳይድ የተባሉ ንጥረ-ነገሮችን በውስጣቸው ስለሚይዙ ለአየር ብክለት የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው" ይላሉ።

በዓለም የአግሮ ፎረስትሪ (የግብርናና ደን ማዕከል) ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ለሊሳ ዱጉማ በበኩላቸው የሚቃጠለው ቆሻሻ መጠን እና የሚቃጠልበት አካባቢ ወሳኝ ነውም ይላሉ።

"ገጠር አካባቢ ከሆነ የሚቃጠለው አብዛኘው የተፈጥሮ ተዋፅኦ ስለሆነ ብዙም ችግር ላይኖረው ይችላል። ከተማ አካባቢ ግን የተለያዩ በኬሚካል የተሞሉ ንጥረ-ነገሮች ስለሆኑ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳሉ" በማለት ዶክተር ለሊሳ በጥናታቸው ይገልፃሉ።

አሁንም ከተጋረጠብን ወረርሽኝ ይልቅ በአሉባልታ የጦር ወሬዎች ተጣበን ጽዳትን ዘንግተነዋል፣ ማስኩን ጥለነዋል፣ ሳኒታዘሩን እዚህም እዚያም ደፍተነዋል።
ወገን 'ዋናው ጤና' ሲባል ሰምተናል መቼስ ራሳችንን እንጠብቅ። ሀገርም ምትፈልገን በጤና ሳለን ነው።

🚮🚮🚮🚮🚮🚮
😷@gbw_dan😷
😷@gbw_dan😷
😷@gbw_dan😷


ሃምሳ አለቃ ገብሩንና አባ ገሬንና ታገል ሰይፉንና አለማየሁ ገላጋይን በአንድ መጽሐፍ ውስጥ አገኘኋቸው---አጥቢያ

እናም በአጥቢያ መጽሐፍ-አባገሬ ውስጥ 50አለቃ ገብሩ ይታዩኛል፤ በአለማየሁ ውስጥ ታገልን አገኘኋለሁ (መፅሐፍ የጸሃፊው ነጸብራቅም አይደል)እስቲ አንዱን ባንዱ እንመልከት

....
"አልዋሽም ያጥፋኝ አልዋሽም" ካሉ አይዋሹም።አብዛኛውን ጊዜ መንደርተኛውን በሳቅ የሚያፈርሱት ስለመወገራቸውና ስለሴት አይምሬነታቸው እያወሩ ነው። በይበልጥ በሚስታቸው ስለመወገራቸው።
"አንድ ቀን የምችላት መሰለኝና ምናባቷ ብዬ በሩን ዘጋሁ።በኋላ ያዝ ሳደርጋት ሲሌዬን ለቀም አድርጋ አልጋው ላይ ደብ! አደረገችኝ። "እ" እያለች በምን ልቻላት።በጓሮ በር ጎረቤታችን ገባ። እሱን ሳየው አፈርኩና በአዝማሪ ቋንቋ ከላዬ ላይ እንድትነሳልኝ ለመንኳት "እ" እያለች እምቢ ብትለኝ ወደ ጎረቤታችን ዞር ብዬ እኔ ሚስቴን ስቀጣ አትምጣብኝ አላልኩም? ብዬ ተቆጣሁታ!..." ቤቱ ያወካል።
"አንድ ጊዜ ደሞ..."ይቀጥላሉ "አንድ ጊዜ ደሞ ቀን ሥራ ድንጋይ ሸከማ ገባሁና ሰራርቼ ስመጣ እንደው ለከፈችኝ። ብስጭት ብዬ መቆሚያ ጣቢያ ወጥቼ እንደቆምኩ አንድ ወፈፌ ብጤ የጠጅ ቤት ጓደኛዬ መጣና ምን እንደሆንኩ ጠየቀኝ። ብስጭት ብዬ ብነግረው "ና-ምናባቷንስና" ብሎ ፊት-ፊት ቀደመኝ።እኔም "ጎሽ የወንድ እጅ አሳይልኝ" ብዬ ተከተልኩት።
"ስንደርስ ረታች በር ላይ ቁጭ ብላለች። "አንቺ?" አላት "ምን ሆነሽ ነው ለፍቶ ሲመጣ የሚበላ የምትከለክይው?"
"ና! ወንድ ከሆንክ ሌማት ከፍተህ አንተ ስጠው" አለችው "ሂድ የወንድ እጅ አሳይልኝ" አልኩት። ጓደኛዬን ስገፋፋው ቢያቀምስልኝ እንዴት አንጀቴ ቅቤ በጠጣ ነበር። ገና ጠጋ ሲላት እ አለችና ጠቅልላ ተወችው!!"ቤቱ ያውካካል፦ፀቡ ላይ የነበሩ ቀሪ ነገር ይጠይቃሉ። "ታዲያ ያኔ ጓደኛዎት ሲመታ እርስዎ ምን አሉ?"
"ምነው እኔ ብቻ አንተም ቅመስ'ጂ አልኩታ "
ለቅሶ ቤቱ የፌሽታ ቤት መስሎ ቁጭ ይላል።
አባ ገሬ ሲበዛ ደግ ናቸው።ባለቤታቸው 'ኳ እንደዛ እየደበደቧቸው ትንሽ ፍራንክ ያገኙ እንደሆነ "አቦ ያቺ ረታች ባዶ ቤት ሳትሆን አትቀርም" ብለው ወስደው ይሰጧቸዋል። ብዙ ጊዜም እቤታቸው ጽዋ ገብቶ ሲደገስ ማህበርተኛ ከመግባቱ በፊት የድግሱን ምግብ እየጨረሱ ባለቤታቸውን አስለቅሰዋል። እንዲሁ የአመት በአል ጊዜ ረታች ከቤት ወጣ ያሉ እንደሆነ ገልብጠው ማብላት ነው።...
(ገጽ፦ፈለገው ያግኙት-አጥቢያ)

አስቲ አባገሬን 50አለቃ ገብሩ ውስጥ ከትቼ ላሳያችሁ እና ላስነብባችሁ...

አባገሬ
በእውነት አልዋሽም ያጥፋኝን አልዋሽም
በማለት ጀመሩ የ8ኛው ሺህ አባገሬ ድማም
በለቅሶ ሃዘን ላይ የነበረውም ህዝብ
ባነጋገራቸው እጅጉን በመሳብ
ሃዘኑን ረስተው ለሳቅ በመጎምዠት
እሺ ይቀጥሉ በሚል አስተያየት
ዘወር ሲሉላቸው
ደስ ተሰኝተው
ከእለታት ባንዱ ቀን በወንድ ማዕረግ የኔን ሚስት ለመቅጣት
ከኋላዋ ሆኜ ያዝ አፈፍ ሳደርጋት
"እ" አለችና በተቆጣ ስሜት
ከአልጋው ላይ ጥላኝ እንዲመች ለመምታት
አንድ ጊዜ በቡጢ አንድ ጊዜ በጥፊ
ስታመላልሰው የእጇን አሳላፊ
ጎረቤት ሰማና በጓሮ በር ገብቶ
ደንገጥ በማለት ለመሳቅም ሽቶ
እኔም አፈርኩና በአዝማሪ ቋንቋ
እባክሽን ይብቃሽ ብዬ ብለምናት
እሷ መስሚያ የላት።
እኔም ይህን ግብር አስተዋልኩኝና
ወደጎረቤቴ ዘወር አልኩእና
እንዲህ ነው ምቀጣት በል ልምድ ቅሰም
ልምዴን እያካፈልኩ ነገሩ ቢሆንም
ሚስቴን አየቀጣሁ አትምጣ አላልኩም?
ቢሆንም...ሚል ነገር አይሰራም
ቢሆንም ቢሆንም ቢሆንምምም
በማለት እውነት አላጎድፍም።
ይህንን ሲሰሙ ቤቱ ሳቅ ይሞላል
ሃዘኑ ተረስቶ በደስታ ይተካል።

(ጦማሪ ዳኒኤል አወቀ የዮዲት ልጅ -ዮዳሄ)

የታገል ሰይፉ 50አለቃ ገብሩም እዚህ ላይ ያበቃል
🇪🇹ሠላም ለኢትዮጵያ ሃገራችን!

📚@gbw_dan
📚@gbw_dan
📚@gbw_dan


ያደግንበት
✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳
✴✴✴✴✴✴✴✴
✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳

✍️ገጣሚ➹ታገል ሰይፉ
🎤➠ኳስ_ሜዳው
📁➹2.7mb
🎭🎭🎭🎭🎭🎭
🎭🎭🎭🎭🎭🎭

በቅርብ#መስተዳድር_ደብሩን ይዘንላችሁ ስለምንቀርብ ሼርርር እያረጋችሁ ጠብቁኝ
በቅርብ ቀን👌

▰ ▬ ▮@gbw_dan
▮▬▮ ▮ ▬▬


🏥መድሃኒተ ተባይ🔧

ያ...ሀገርን ሰዳሪ

ድንበር አስከባሪ

ተመቶ ወድቋል አሉ

ሊፈርስ ነው አካሉ።


ግና...የሱ አጥንት መከስከስ

ደሙ...ከቁልቁል ተራራ ከሽቅቡ መፍሰስ

አንቺን ለማቆም ነው ከነሙሉ ክብርሽ

የማንም ነሆለል አንቺን እንዳይፈርስሽ።

አንቺኑ ይገነባል በስጋና በደም

ለራሱ ቁብ የለው እሱ ወድቋል የትም።


የባህል ተጫዋች የተባለላቸው እኚያ ጀግና ተባዮች

አልተቋቋሙትም ቀርተዋል በስላች።

እርሱ በህይወት እያለ

ሀገር ማፍረስ ቀረ።



●●●ዛሬ 3ኛው ወር
✔ዳኒ የዮዲት ልጅ(ዮዳሄ)

🇪🇹@gbw_dan💚💛❤️


ትልቅም ነበርን ......

"ትልቅም ነበርን ትልቅም እንሆናለን" በሚል በዚህ ተረት
ጉድለት ይታየኛል የከፍታ ርቀት ።
ትልቅ ሆኖ ሳለ እንዴት አርቆ ከፍታን ይመኛል
አላስተዋለ እንደሆን ውርቁ እግሩ ስር ይገኛል ።
በነጮች እስታንዳርድ እራሱን ለክቶ
ያባቶችን እውቀት ወደ መሬት ከቶ
ደሃ ነኝ ብሎ አለ ውሉ አፍ አውጥቶ።
ንገረኝ ወገኔ ትርጉሙን የድህነት
መራብ መጠማት ነው እንዲሁም እርዛት
ይሻላልም እኮ ሰውነትን አርክሶ ሆድ እቃ ከመሙላት !!!

ትልቅ ሆኖ ሳለ ካለም ፊት ቀዳሚው
በምን ተለክቶ ደሀ የተባለው ?

አሰተውል ወንድሜ ማዶ ማዶ አትይ
ስንዴ እንዳልመፀወጥክ አሁን ስንዴ አትለምን
አቀርቅረህ ፈልግ ይቅርብህ የሩቁ
እዚው ታገኛለህ አልማዙንም ወርቁ !!!

የሰው ወርቅ አያደምቅ እንዲልስ ቢሂሉ
ባገር ባህል ና ወግ ሲያጌጡ ያምራሉ ።

ይልቅስ ወገኔ ዝጋው ይህን ተረት
ትልቅም ነበርህ አሁንም ትልቅ ነክ
ብቻ አንተ አስተውል እንዳድማስ አስፍተክ
በወሰን አትወስነው የአእምሮህን ልክ
የኋላህን እይ የ ነው መሰረትክ ።


@gbw_dan
@gbw_dan
@gbw_dan
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹


📚ዝ▬▬ጎራ📚
✍️ደራሲ➠ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ
🗣ተራኪ➠አያልቅበት ተሾመ
📂➠3.8Mb
🗞ክፍል➠8
⬜️አዘጋጅ➠ራዲዮ አቢሲኒያ
⬛️አቅራቢ➠ጥበብ መንገደኛ

📚@gbw_dan
📚@gbw_dan
📚@gbw_dan


🔐 አንጋረ ፈላስፋ 🔐

ሰላም ውድ ቤተሰቦቼ እንሆ በቃሌ መሰረት ክፍል ሁለትን ይዤላችሁ ቀርቤያለው መልካም ቆይታ💚💛❤️
📚📚📚📚📚

አፍላጦስ፦ ጥበብን ስትሰበስብ ገንዘብንስ ለምን አልሰበሰብክም ቢሉት ? ጥበብ ፈፅማ የከበረች ትሆን ብዬ ነው ። ጨለማን ከብርሃን ጋር አንድ ያደረገ ማን ነው ? ተኩላን ከበግ ጋር ፣ ነብርን ከፍየል ጋር ፣ አንበሳን ከላም ጋር ያወደደ ማን ነው ? እንደዚ ሁሉ ጥበብ ገንዘብን ከሚወድና ከሚሰበስብ ጋር አይስማማም ብዬ ነው አላቸወው።

ዲዮጋንስ ፦ ሞት እንደምንድናት ቢሉት ሞትስ ለባለ ፀጋዎች የምታስደነግጣቸው ድሆችን የምትናፍቅ ናት አለ።

ፊታጎሮስ ፦ የልብ ፆቲ (አይነቱ) ሁለት ነው። እሱም አድራጊና ተደራጊ መሆን ሲሆን ነው ። አድራጊ ማለት ክፉውን ከበጎ በጎውን ከክፉ የሚያስብ አእምሮ ሲሆን ፤ ተደራጊ የተባለ ራሱ ሀሳብ ነው ።

ጋሊኖስ ፦ እንዲህ አለ ፣ የሥጋው ፍትወት (አምሮት) የገዛቺው የፀናችበትና ያሸነፈቺው ሰው የተናቀና ወራዳ ነው ። ፍትወት በሰውዬው ላይ የሰለጠነች እንደሆን ጠባዩ ልክ ልብ እንደሌላቸው እንደ እንስሶች ይሆናል ።

ሰው ቁጣው ያሸነፈችው እንደሆን ጠባዩ እየጮሁ ያገኙትን ሁሉ እንደ ሚነጥቁ እንደ አንበሶች ጠባይ ይሆናል ።
እግዚአብሔር አባታችን ፣ መንግስተ ሳማይ እርስታችን የምታሰኝ የከበረች መንፈሳዊ ኃይል ግን በሰውዬው ላይ ያደገች እንደሆን እንደ መላእክት ታደርገዋለች ከነሱም ጋር ታስተካክለዋለች ። ( ምድራዊ ሲሆን ሰማያዊ ክብርን ታሰጣዋለች ማለት ነው።)

ኃጥያቱን በደሉን የሚታወን ሰው ዕዳ ደብዳቤውን አስደመሰሰ ሰውነቱንም ከሀጥያት ከቂም ከበቀል ንፁህ አደረጋት የመወዳጀት ስራም እንዲህ ነው ። ወዳጅ ለወዳጁ በሁለተናዊው የሚያምነው በደስታው በሀዘኑም ጊዜ ተካፋይ የሚሆን ሲሆን ነው። ወዳጅ ለወዳጁ ስለ ትልቅነቱ የማይታበል ስለ ድህቱ የሚዋረድለት ጠባዩን የማይለውጥበት በማናቸውም ነገር የማይለየው ሲሆን ነው እውነተኛ ወዳጅነት ማለት ነው ።

ሰው ሊያደርጋቸው የማይገብ 3 ነገሮች አሉ እነሱም
ሀ, እግዚአብሔር በቀባው ንጉስ ላይ መሳለቅ ፤
ለ, በአዋቂና በጀግና ሰው ላይ መዘበት ፤
ሐ, በሚመክርና በሚያስተምር ልባም ሰው ላይ መቀለድ ናቸው ።
ይህ እንደዚህ ያለው ነገር ሰብአዊ ጉድለት ይሆንባቸዋል ።

ዳግመኛ ፦ ቁጣ የአዋቂዎች እውቀታቸውን የምታጠፋባቸው ፤ ለጠቢባን ጥበባቸውን የምታበላሽባቸው ናት ።
👆👆👆 ይቀጥላል ......

ጥበብና ማስተዋልን ያድሎን
በዘር በሀይማኖት ከቶ ሳንቃረን
እንደ ክልል ሳይሆን እንደ ሀገር ሰፍተን
ብዛታችን እንድ ይሁን ፈቅር ይፅደቅብን ።


🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@gbw_dan @gbw_dan
@gbw_dan
@gbw_dan
@gbw_dan
@gbw_dan
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹


📚ዝ▬▬ጎራ📚
✍️ደራሲ➠ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ
🗣ተራኪ➠አያልቅበት ተሾመ
📂➠3.8Mb
🗞ክፍል➠7
⬜️አዘጋጅ➠ራዲዮ አቢሲኒያ
⬛️አቅራቢ➠ጥበብ መንገደኛ

📚@gbw_dan
📚@gbw_dan
📚@gbw_dan


ፍቅር አይዘረፍም
✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳
✴✴✴✴✴✴✴✴
✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳

✍️ገጣሚ➹ታገል ሰይፉ
🎤➠ፍቅር አይዘረፍም
📁➹5.5mb
🎭🎭🎭🎭🎭🎭
🎭🎭🎭🎭🎭🎭

በቅርብ#መስተዳድር_ደብሩን ይዘንላችሁ ስለምንቀርብ ሼርርር እያረጋችሁ ጠብቁኝ
በቅርብ ቀን👌

▰ ▬ ▮@gbw_dan
▮▬▮ ▮ ▬▬


......
#ቃለ_ፅሑፍ

ቃለ-ፅሑፍ ማለት ተውኔት፣ ልብወለድ፣ ወግና ሌላም ህሊናዊ ወይም ነባራዊ ፅሑፍ ሲፃፍ ቃላትን እንደ አገባብ ሥርዓታቸው የመምረጥና አስማምቶ የመደርደር ክንዋኔ ነው። ፀሐፌ-ተውኔቱ፣ ገጣሚው፣ ልብወለድ ፀሃፊው ፣ወግ ተማሪው ወይም በጥቅሉ ደራሲው ሲፅፍ ልዩ ልዩ ግባቶችን የመፍጠር ብቃት ያላቸውን ቃላት ይመርጣል፣ ያቀናጃል፣ ብሎም ከሰዋሰው ሥርዓቱ ጋር እያስማማ በወረቀት ላይ ያሰፍራል።

➠አንድ ደራሲ የሚያስበውን ታሪክ ሁሉ ተጨባጫዊ የሚያደርገው ወደ ቃላት ለውጦ በወረቀት ላይ ሲያሰፍረው ነው። በገለፃ፣ በትረካና በቃለ-ተውኔት የሚቀርቡትን ሃሣቦች ሁሉ ወደ ቁሥ-አካልነት የሚለውጧቸው እነዚሁ ቃላት ናቸው።

➠እንደሚታወቀው በየትኛውም የድርሰት ዓይነት ያሉ ሃሣቦች ሁሉ በደራሲው አዕምሮ ውስጥ የሚፀነሱት ቀደም ብለው ነው። ነገርግን ተጨባጫዊ የሚሆኑት ወደ ቃላት ተለውጠው በወረቀት ላይ ተፅፈው ሲቀርቡ ብቻ ነው።

➠በተውኔት ድርሰት አፃፃፍ ሂደት የቃለ-ፅሁፍ ስልት ሲባል ገፀ-ባህሪያትን ለመቅረፅ፣ መቼቱን ለማዘጋጀት እና ድርጊቱን ለማራመድ እየመረጡ ጥቅም ላይ የሚውሉት ቃላት የአገባብ ሥርዓት የተለየ አይደለም። ለምሳሌ ገፀባህርያትን ብንወስድ በተሰጣቸው ሚና የንግግር ልውውጥ ሲያደርጉ አንድ አይነት መረጃ ማድረሳቸው አይቀርም። ይህም ብቻም አይደለም። ገፀባሕርያት ሲናገሩ ስሜታቸውን፣ አስተሳሰባቸውንና ትርጓሜአቸውን ሁሉ ይገልፃሉ። እነዚህን የገፀባህርያት ክንዋኔም ለማብራራት የሚመረጡትና የሚቀናጁ ቃላት ታዲያ መረጃ ከመስጠትም በላይ መሆናቸውን ለመረዳት አያዳግትም።

🇪🇹ሠላም ለኢትዮጵያ ሀገራችን!!!
💚@gbw_dan @gbw_dan🎭
💛@gbw_dan @gbw_dan🎭
❤️@gbw_dan @gbw_dan🎭


የሉሲፈር : በትር !
----------//--------

ክፍል :- (4)

ክፍል አንድ ላይ ዶ/ር ዋሲሁን በሚስጥራዊ መህበር ወጥመድ ውስጥ እንደ ወደ ቀ እናም በ መህበሩ ልዩ ትእዛዝ ባላሰበው እና ባልጠበቀው

ሰዓት ፓስፖርት እና የጉዞ ብር ተዘጋጅቶለት ከሚኖርባት ጀርመን ወደ አሜሪካ መሄድ እንዳለበት እንደተነገረው እና እሱም በፍፁም

የእነሱ ሀሳብ መፈፅሚያ ላለመሆን ምን ማድረግ እንዳለበት እቅድ እያወጣ ባለበት ሰዓት መጀመሪያ የ ፓስፖርት እና የመመሪያ ወረቀቶች

ከ ቼክ ጋር በመቀጠል የ ሰው እራስቅል በሩ ተኩዋኩቶ እበሩላይ አስቀምጠውለት እንደሄዱ ነበር ያቆምነው!

#እነሆ_ክፍል:- (4)

ዶ/ረ ዋሲሁን እግሮቹ ፈፅሞ መቆም ቸገራቸው ይንቀጠቀጡበት ጀመር በሩ ላይ በደም የራሰ የሰው ልጅ የራስ ቅል እያየ ቁሙዋል በሩን

እንደያዘ የራስቅሉከማን አንገት ላይ እንደተሰየፈ ለማሰብ እኩዋን አቃተው ብቻ ከሰአታት በፊት እንደተገደለ በለው የ ህክምና ልምድ ለይቶታል

ግን የሰውየውን ማንነት ያለዛሬ አይቶት አያቅም ከራስ ቅሉ ጋራ አንድ ወረቀት በደም ተለውሳ አያት ሳያነሳ ጠጋብሎ ተመለከተ በጀርመን ቁዋንቁዋ የትፃፈ ሲሆን

" ያረፈደ እንደካደ ይቆጠርበት እኔ የሱ ባሪያ ነኝ ደሜም ከሱ ወዝ ይቀዳል ይላል 1ሰዓት በፊት በርሊን አየር መንገድ ድረስመልክቱን ካየህ

በውኃላ አቃጥለው ይል ነበር ነገር ግን ዶ/ዋሲሁን ያንን አላደረገም በድንጋጤ እና በመረበሽ ወደ ቤቱ ተመለሰ ጥቂት ለማሰብእንኩዋን ጊዜ አልነበረውም።

ጊዜ ሳያጠፋ ያሉትን ወረቀቶች እና ጥቂት ልብሶችን ሰብስቦ በሩ ላይ የጣሉለትን የራስ ቅል ዘሎ ሊፍቱን መጥሪያ ተጫነ ለዚም ጊዜ አጣ ሊፍቱን መጠበቅ ትቶ ደረጃውን በ እግሩ መውረድ ጀመረ።

አካባቢውን የፖሊሶች ለቅስፈት ተቆጣ ጠሩት መግቢያ እና መውጫዎች ሁላ ፖሊሶች ፈሰዋል ዋሲሁን አንገቱ ላይ ጣልባረጋት እስካርፕ እራሱን ለመሸፈን እየታገለ እጁን ኪሱ ከቶ ወደዋናው መንገድ ሊደርስ ሲል አንድ ፖሊስ ከውኃላ አስቆመው ዋሲሁን አሁን ሰውነቱ ይበልጥ መራድ ጀምሩዋል ምን ቢጠየቅ ምን እንደሚመልስ አያቅምፖሊሱ ተጠጋ እና ወረቀቱ ላይ ያነበበውን ቃል ደገመለት " ያረፈደ እንደካደ ይቆጠርበት እኔ የሱ ባሪያ ነኝ ደሜም ከሱ ወዝ ይቀዳል ክዚ ለቀ ወደ ተጠራህበት ሂድ አለዚያ ጭንቅላትህን አንተም ትሰጣለህ አለው"


ዋሲሁን ጥሎት ፍጥነቱን ጨምሮ ከቦታው ሸሸ እየተቻኮለ ወደ አየር መንገዱ ታክሲ በመያዝ አቀና ታክሲ ውስጥ ያለው ሬዲዮ የቻይና ህዝብ

በ አዲሱ ተላላፊ ቫይረስ በከፍተኝ ሁኔታ እያለቀ እንደሆነ የሙዋቾች ቁጥር በሺውች እየሆነ በ ቫይረሱ የተጥቁት ደሞ 50,000 እንደበለጡ

መጠሪያው የ ኮሮና ቫይረስ እንደሚባል እናወደ ሌሎች ሀገሮችም በከፍተኛ ሁኔታ እየተዛመተ እንደሆነ ይዘረዝራል ዶ/ር ዋሲሁን ነገሩ አሁን

በጣም እየተገለጠለት ነው ሰውዬው ያሉት ደጋግሞ አሁንም ጆሮ ላይ ጮኸበት 40 %

ፐርሰንት የ ዓለምን ህዝብ ለመቀነስ በጥንቃቄ ያቀዱትአላማ መንገዱን ስቱዋል ፍጥነቱን ጨምሮ ካሰቡት በላይ ገዳይ ለመሆን መገድ ላይ ነው ይባስ ብሎ ክትባቱ ሊሰራ አልቻለም ዶ/ረ ዋሲሁንን እረጅም አመታት ወስደው በትምህርት እና በስራ ያሹት አፍሪካ ላይ ላሰቡት አላማ ቀኑ ሲደርስ አጥምቀው ሊልኩት ነበር ነገር ግን በዚ ክስተት ምክኒያት ለ አዲሱ ቫይረስ ክትባት ከሌሎች አባላት ጋር በመሆን ጊዜ ወስዶ እንዲያዘጋጅ ቀድመው በወንጀል አጥምቀው ከፊት ያቆሙት እንዲሁ እያሰላሰለ ቦታው ደረሰ ወደ አሜሪካ እሚበረው አውሮፕላን ገና አንድ ሰዓት እንደሚቀረው ተመለከተ ከ በላዩ አንድ የጀርመን ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰበር ዜናው ዶ/ክተር ዋሲሁንን ፎቶ ሙሉ በሙሉ በመልቀቅ ከስር ኢትዮጲያዊው ዶክተር እሚሰራበት ሆስፒታል በድገተኛ አደጋ የገባውን ሰው እና አንድ ሌላ

ለጊዜው ማንነቱ ያልተለየን ግለሰብ መኖሪያ ቤቱ በር ላይ በዘግናኝ ሁኔታ ገድሎ እንደተሰወረ በዝርዝር ያቀርባሉ ዶ/ዋዲሁን ብርክ ያዘው ሰውነቱ መቀጥቀጥ ጀመረ የያዘውን ሻንጣ በቁሙ ለቀቀው የትም ወዴትም መሄድ ቀርቶ አሁን ማሰብም ከባድ ሁኑዋል ስልኩ በድንገት ጠራ እዛው ጀርመን እምትኖር በቅርቡ

የተዋወቃት ኢትዮጲያዊቱዋ ሄለን ነበረች ዜናውን አይታ እንደደወለች ገምቱዋል አሁን አንስቶ ምንም ቢላትን እንደማታምነው ያቃል ማንንም እንዳያናግር ማስጠንቀቂያም ደርሶታል!



ይቀጥላል.....

📚@gbw_dan
📚 @gbw_dan
📖 @gbw_dan


▬▬▬▬
▮ፍረጂን ▮
▬▬▬▬

ውዲዬ...

የጥንቷ ኢትዮጵያዬ

በደንብ ታዘቢ

ትናንት ላይ ሆነሽ ዛሬ አታሸልቢ

ከሰውነት ገዝፎ ወንበር ሲያበራየን

ፍቅር...ሠላም ታጥቶ ባሩዱ ሲዳኘን።
◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
ሰላም ፈራን ኢትዮጵያያዬ

ሰላም ፈራን አበባዬ

ሰላም እኛን ፈራን

መዋደድ አቅቶን ጦርነት ሸተተን

በቀን ቀን በራሳችን ወንድም

ጠብን እየነዳን ይኸው አጣን ሰላም።
◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
ልክ እንደ ዳቦ ስም የጦር ስም አወጣን

ግራ ዘማዊውን ምንም እንዳልሰራ ጭራቅ አውሬ አልን

እስቲ አንቺ ተመልከች

በአንክሮ እዪን ያንቺን የጦር ህዝቦች

ያ ግራ ዘመሙ

ኢትዮጵያ ትቅደሙ

ምን ለውጥ አመጣ?

ለድሀው ላ'ራሹ መሬትም አልሰጠ?

ታዘቢ አንቺ'ማ

አልደረሰም እንዴ መሬት ለተቀማ?

ቀኝ ዘማዊንም አልናቸው የቀንጅብ

የእጅ አመል ቢኖርም ሰርተዋል እንደ ንብ

የዘመናት ቁጭት

የህዝብ የግርእሳት

አባይን በመድፈር

ላንቺ ለጦቢያ ግብሩን እንዲገብር

ይህንን ገድል ግን በዝምታ ዋጥሽው

ወይ አልወረደልሽ ወይ ቆርጠሽ አልጣልሽው።
◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃◃▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
አሁንም የጦር ስም አስፈለገንና ለዘመቻ ሆይታ

ይኸው እያልን ነው... ሀገራ አሸባሪ አፈራራሽ ጁንታ።

ታዲያ ስለዚህ ግን ምንምን አላውቅም

ባንቺ ትዝብት ሆኜ አልሆንም አፈጽድቅ

ካፈረሰሽ ይፍረስ

ካሳፈረሽ ደም ያልቅስ

ከደፈረሽ በደዌ ይመታ

ካገሩ 'ርቆ በግፍ ይንገላታ

ካኮራሽም ይኩራ ይውጣ ከሰው ተራ

ከፍ ብሎ ይግዘፍ ከዳሽን ተራራ

ፍርዱን ላንቺ ልተው

ፍርድሽ አይበሉ ነው

በጥሊያን ሶማልያ በሁሉ የታየው

እናም ኢትዮጵያዬ ካንቺ ጋ ነው ፍርዱ

ጁንታ የተባሉት ምን እንሚሆኑ።
.. ..
.. ..
.. ..
➦በ3ኛው ወር●●●ዘንድሮ
✍ዳኒ የዮዲት ልጅ(ዮዳሄ)
▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭
@gbw_dan@gbw_dan▮
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬


የሉሲፈር : በትር !
----------//--------

ክፍል:- (3)

ዋሲሁን አንድ ጥንታዊ እሚመስል ያምለኮ ስፍራ እራሱን አገኘ አንድ እድሜአቸዉ ገፋ ያሉ አዛዉንት ከፊት ለፊቱ ተመለከተ ሰዉየዉ ጠጋ ብለዉ ወደ ጆሮዉ ፍጡር

ለፈጣሪዉ መታዘዝ አለበት አንተን ደግሞ ሉሲፈር ታላቁ መንፈስ ፈጥሮሀል ከዛ ብስባሽ ዉስጥ አዉቶሀላ ያዘጋጀህ ለዚ አላማ አልነበረም አንተ ሌላ እቅዱ ነበርክ ለዛ ከፍተኛ ዘግጅት ላይ ነበርን ነገር ግን ከቁጥጥራችን የወጣ አሁን አዲስ ነገር አለ እና በፍጥነት ተጠራህ የጠራህ ፈጣሪህ ነዉ ስለዚ እጅ መንሻህን ለፈጣሪህ ታቀርባለህ ፡፡

ላንተ ሉሲፈር ዋጋ እማይተመንለትን የ ዓለም ጸጋ ሰቶሀል ዋጋህን ልትከፍል ጊዜው ደርሱዋል ከሁለት ቀን በውኃላ ያለህበት ሆስፒታል በቂ ጉርሻ ጋር ያየር ትኬትን ጨምሮ ወዳ ቺካጎ ይልክሀል እዛ እሚቀበል ሰው አለ ሌላው መረጃ እዛው ስደርስ ትሰማለህ ከዚህ ሀገር እስከምቶጣ ከማንም ጋር ግኑኝነት እንዳይኖርህ ትዛዝ ተላልፈህ ሰው ብታገኝ ያሰው ያን ምሽት አያድርም ይወግዳል ደሙም ለልኦል አምላካችን ጥቂቱ መሱዋት ይሆናል ግን ይሄ የደም ዋጋ ላንተ ስርየት አይሆንም ከማንም ጋር email እንዳትፃፍ እራስህን ከዚ ሀገር እስከምቶጣ አግልል ።

ዶ/ር ዋሲሁን እራሱን መኖሪያ አፓርትመንቱ ውስጥ ሶፋው ላይ አገኘው ሰውነቱ ዝሎ እና ተዳክሞ ነበር ከሰመመኑ ሲነቃ እራሱን መልሶ እንዲስት አርገው አገላተው ቤቱ እንደወረውሩት አወቀወደ መታጠቢያ ቤት ገብቶ ፊቱን ውሀ አስነካው በቀዝቃዛ እጆቹ ማጅራቱን እና ጭንቅላቱን ዳበሰ አንገቱን ሲዳብስ ማህተቡን ከንገቱ የለም በጥሰውበታል።

ሚስኪን እናቱ ታወሱት ባህር ማዶ እርቆ ለትምህርት እና ለስራ እንደሚርቅ ሲያቁ በለሊት ነበር ነብሳባታቸውን ጠርተው ፅበል አስረጭተው በሰበብ አስባቡ ከተሜ በወጣ ቁጥር ማተብ ሲበጥስ ነገሩ አላምር ቢላቸው ከመሄዱ በፊት እምነት መሀተቡን እንዳይበጥስ አስገዝተው አሰሩለት የእናቱ የእምነት እዳ መስታውቱን ሰሎ በሀሳብ ታየው እንባው ጉንጮቹን ዳብሰው ከመታጠቢያው ወረዱ

አሁን ነገሩ ሁላ ግራ ሆኖበታል ዶክተር አብርሀም ለማንም እሚያወራው ጉዋደኛም ሆነ ዘመድ የለም የተጠጋው የነካው ሁላ እንደሚረግፍ ነው የነገሩት ብቸኛ ማምለጫው ወይ ሞት ወይ የነሱ ከባድ መንገድ ብቻ ነው።

በሁለት ሀሳብ ተወጥሮ ማምሻውን ጋዋኑ ላይ ያለው በደም የቀረ መልክት ድንገት ከተወጠረበት ሀሳብ አባነነው ያየውን መልክት ደጋግሞ ለማስታወስ ሞከረ በዚ መሀል በሩ በሀይል ተደበደበ ዶ/ር ዋሲሁ

እንደትረበሽ ዳግመኛ እነሱ እምደሆኑ በማሰብ በዝግታ ወደ በሩ ተጠጋ በ በሩ የመስታውት ሽንቁር አሻግሮ ከበሩ ማዶ ያለውን ቃኝ ማንም ምንም አይታይም በእርጋታ በሩን ሲከፍትአንድ በ ካኪ የተጠቀለል ነገር መሬት ተቀምጦ ተመለከተአንስቶት ግራ ቀኙን ተመልክቶ ወደውስጥ ገባ
ጊዜ ሳያጠፋ ካኪ ውስጥ ያሉትን ወረቀቶች አወጣ ብር እና የተፈረምባቸው በስሙ የተፃፈ ቼክ እንዲሁም የ አሜሪካን ፓስፖርት ይገኝበታል

ደጋግሞ እንደማያረገው ሞቱን እንደሚመርጥ ደጋግሞ ለራሱ ማለ እስካሁን ለካ በ እዚ ሚስጥራው የሴጣን መሀበር ሲማርም ሲሰራም እንደኖረ ለራሱ ማሳመን ተሳነው ሰዓቱ 9፡30 ይላል ሳይተኛ ሊነጋ ነው ድካም ቢጫጫነውም አሁን ለሱ መተኛት በራሱ ላይ ገመድ የማጥለቅ ያህል ነው ።

ያ ሽማግሌ ያለው ደጋግሞ በጭቅላቱ ላይ መጣበት ቫይረሱ ከቁጥጥራቸው በላይ ሁኑልዋል በከፍተኛ ደረጃ ሰው እንደቅጠል እይውረገፈ ነው ቀድሞም ዓላማቸው ይሄ ሚሆንም ፈፅሞ ግን በዚ ደረጃ ዓላሰቡትም በዚ ላይ ያዘጋጁት ክትባት አሁን ምክኒያቱን በን በማያቁት መልኩ

ሊሰራ አልቻለም ይሄ ለምን እንደሆነ ፈፅሞ ሊረዱት አልቻሉም ጉዳይ ካቅማቸው ቨላይ ሲሆን ለ እዚ ዓላማም ባይሆን አስተምረው በስራ ልምድም ያዳበሩት ዋሲሁንን ሊጠቀሙት ጊዜው ደርሱዋል ለዛም ዓላማ ነበር ወደ አሜሪካ እንዲሄድ ያስገደዱት

ዋሲሁን ከሚዘጋጀው ክትባት ጋር ሰውነት ውስጥ እሚቀበር ማይክሮ ችፕስ እያንዳንዱ ሰው ከክትባቱ ጋር ማይክሮ ቺፕስ በየ ሰውነቱ ሊቀበር እንደሆነም ሰውዬው በዝርዝር እቅጩን ነግሮታል በዛላይ ሆስፒታል ገብቶ የሞተው ሰው ጋዋኑ ላይ የተወለት መልክት ትዝ አለው እሱ ቀድሞም ፋታ የነሳው ጉዳይስ ነበር።

ዋሲሁን ሁለት አማራጮች መጡለት ባገኘው ሁሉ መገድ አታሎ ኢትዮጲያ ገብቶ እራሱን መሽሽግ ካሎነም ለ አንዱ ላመነበት ሰው አስፈላጊ ዶክመንት እና አንዳንድ የምርምር ሳንፕሎች በማዘጋጀት ላመነበት እና ለሚረዳ

ሰው ወደ ኢትዮኢያ ይዞ እንዲገባ ማረግ ነው
በእነዚ ሁለት ውሳኔውች ተወጥሮ እንዳለ መልሶ በሩ ተደበደበ ዋሲሁን ተደናግጦ እና በ እርጋታ አሁንም ወደ በሩ አቀና በበሩ ስር ወፍራም ሞቃት ድም ወደ ቤቱ ሲገባ ተመለከተ

በድንጋጤ በሩን ስቦ ከፈተው በሚዘገንን ሁኔታ በ ደም የራሰ የ አንድ የሰው እራስ ቅል ነበር ።


ይቀጥላል.....

📚@gbw_dan
📚 @gbw_dan
📖 @gbw_dan


የሉሲፈር : በትር !
----------//--------

ክፍል:- 2

መጀመሪያጊዜ ያፈቀርኩዋት ቫቤላ ትባላለኝ ዩከሬናዊ ሴት ናት እዚ ጀርመን በንቅሳት ሰራ ትተዳደር ነበር እና ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ የፈፀምኩት ከሱዋጋ ነበር አዲስ እና እማላቀዉን ዓለም ነብር በደቂቃዎች ያሳየቺኝ ታዲያ ይሄ ጣፋጭ ጊዜ ገላዪ ላይ ማስታወሻ ሆኖ እንዲኖር የራስሽን ጥሩ ምልክት አኑሪልኝ አልኩዋት

ታዲዲያ ይሂንን የተኩላ እራስ ምልክት ብልቴ ላይ ልትስል ሰትል እንደማየሆን ከዛ በተሻለ ደረቴን መርቼ ደረቴን ሰጠዋት እሱዋ ግን እንብርቴን መረጠች ሲል በወቅቱ እንዲ ሲል

ዋሽቶታል ዉሸት ለጆንሰን የገለባያህል ቀላል ነዉ ደጋግሞ ዋሽቶት ተጋጭተዋል ነገር ግን ጆንሰን የተላከበት አላማ ነበረዉ እና ደጋግሞ ይቅርታ

ጠይቆታል ዋሲሁን ቤተሰቡም ላይ ይሄ የዉሸት አመሉ ደጋግሞ አይቶታል እናቱን መኪና አደጋ ደርሶበት ሆስፒታል እንዳል አርድቱዋት ወደዛ

ስትከንፍ ለከባድ አደጋ ተጋልጣ ሶሰቴ ቀዶ ጥገና አርጋለች አባቱንም እንዲሁ ዋሽቶት በፈጠረዉ ስህተት ለእስር ዳርጎታ በዛ የተነሳ ለእናት እና

ላባቱ መለያየት ምክኒያት እንደሆን ባዶቅት ከባለቤቱ ያፍ ወለምታ ሰምቱዋል በዚ የተነሳ በሀሪዉ እንደሆነ ተረድቶ በየዋህ እነቱ እና ለሱ

ባለዉ ጥሩ አመለካከት ምክኒያት ጥሩ ወዳጅ ሁነዋል የተዋወቁት ሊቨርፑላይ በተዘጋጀ እንድ የህክምና ፌስቲቫል ላይ ሲሆን ዋሲሁን ባቀረበዉ

የባህል መድሀኒቶች ጥናት ላይ ባቀረበዉ እጅግ እንደተደነቀ እሱም በሙያዉ ፋርማሲስት እንደሆን ከ ሚላኖ እንደመጣ ነገር ግን ዶ/ረ

ዋሲሁን እምኖርባት ጀርመን የትዉልድ ሀገሩ እንደሆነች የምዕራቡዋ ጀርመን ተወላጅ እንደሆነ በመንገር በቅርቡ ወደትዉልድ ሃገሩ ጋዙን ጠቅሎ

እንደሚመጣ እና ጥሩ ወዳጅም እንደሚሆኑ በመንገር ነበር ትዉዉቃቸዉ የጀመረዉ፡፡
በርሊን …….. በሚገኝዉ ግዙፍ አፓርትመት መጨረሻላ በሚገኘዉ መኖሪያ ቤቱ ዉስጥ ዶ/ረ ዋሲሁን ሻዉሩን ከፍቶ እርቃኑን እንዳለ በሃሳብ


ነጉዱዋል አይኑ በርበሬ መስሉዋል ሰዉነቱ ትኮራምቶ ፀሀይ የበላዉ የልተወጠር ቆዳ መስሉዋል ወስጡ የቀረዉን የጆንሰንን መርዶ ወሃዉ ያፀዳዉ ይበስል ደጋግሞ ጭቅላቱን አሸ

ጮክ በማለትም “ ለምን ለምን ለምን እኔን ቆይ ለምን እኔን ቆይ ለኔ የሄን ሁሉ ለምን ወይኒ ወይኔ ዋሲሁን

ከመታጠቢዉ ወቶ ፊቱን በፎጣ እየጠራረገ መስታዉቱ ላይ አፈጠጠ ዋሲሁን ሳር ሳሩን ሳር ሳሩን ስትበላ ገደል ጋር ነህ አሁን በል ወይ ዝለል

ወይ ብሎ ሳይጨርስ ስልኩጠራ ካትሪን ነበረች ባስጨኩዋይ ሆስፒታል እንዲደርስ አንድ ሰዓት ባነሰ ጊዜ ዉስጥ ሰርጀሪ መደረግ ያለበት ሰዉ

እንዳለ ነገረችዉ ኬዙ ምንድ ነዉ ሲል ጠየቃት ከባድ የመኪና አደጋ እንደሆን ነገረቺዉ ቆይ ተረኛዉ ሀኪም ሉቫንዶቭ የለም እንዴ ሲለ ጠየቃት

ከሱ አቅም በላይ እንደሆነ ሪፖርት አርጉዋል ደሞም ሰሞኑን ከህመም እንዳገገመ ለእንዲ ያለ ከባድ ኬዝ አቅም እንደሌለዉ ነገረችዉ ምን ምን ማደርግ እዳለባቸዉ አዞ ሲበር ወደ ሆስፒታሉ

ገባ እንደደረሰ ወደ ቀዶ ጥገናዉ ከፍል እያመራ ሳለ ጥቁር ወጠምሻ ቅጥር ነብሰ ገዳይ የመሰሉ ሁለት ነጮች ገላመጡት ዋሲሁንን አይታ የሆነ የመረበሽ ስሜ ቱስጥ ገብተዉ ሲነጋገሩ

ከመቅስፈት ተመልክቱዋል በቀጥታ ወደሰርጀሪ ክፍል ገባ እነ ካትሪን እንዲሁን ሌሎች እረዳቱዋ ሰዉዪዉን በቻሉት አቅም ለማትረፍ ከሞት ጋር ግብግብ ናቸዉ ዶ/ረ ዋሲሁን ፈጥኖ

ተቀላቀላቸዉ ሰዉየዉ ከፍተኛ ደም ከግንማሩ እና ካፍንጫዉ ይፈሳል በዚ የተነሳ የልብ ምቱ እየወረደ ነዉ ካትሪን በድንገት ዜሮ የሆነዉን የልብ ምቱን ለመመለስ ደጋግማ የግንበኛመለሰኛ


በመሰሉ የልብ ምትን መመለሻ መሰሪያ ደጋግማ ደረቱ ላይ በማሳረፍ ሰወዪዉን በኤሌክትሪክ ሾኪንግ ልብ ምቱን ለመመለስ ትጥራለች ዋሲሁን የያዘቺዉን ተቀብሉዋት በተራዉ የሰዉዪዉን ልብ

ምት ለመመለስ ደጋግሞ ሞከረ አጋጣሚዉ ቀናዉ እና የሰዉዪዉን ልብ ምት ለመመስ ተቻለ ኢትዮያዊ መሆኑን የሰውዬውን መልክ ተረድቶ ዶ/ክ ዋሲሁን ገምቱዋል በፍጥነት እሚፈሰዉን ደም

ለማቆም ቀዶ ጥገናዉ ማስጀመር እንዳለባቸዉ በማመን መረባረብ ጀመሩ ዋሲሁን ተጠግቶ የሰዉዪዉን የጉዳት መጠን ለመመልከት ሞከር

ሰዉዬዉ ለተአምር ከሰመመኑ ነቃ በማለት አይኑን በጥቂቱ በቻ ገለጥ በማርግ በደም የተጨማለቀ እጁን እንደምንም በማሳት ዋሲሁን አረጉዋዴ

ጋዉን ላይ ጆንሰን እንብርት እና እሱ ዶክመቶች ላይ ያስተዋለዉን የተኩላ እራስ በደሞ እንደነገሩ ሰርቶ prov 4-14 ብሎ ፃፈበት ወዲያዉ መልሶ እራሱን ሳተ መምታት የጀመረዉ የልብ ምቱ

ላይመለስ መልሶ አቆመ ዶ/ረ ዋሲሁን ጋዉኑ ላይ ደም በነካ ጣቱ የፃፈዉን በፍፁም አላስተዋለዉም
ዳግመኛ የቆመች ትርታዉን ለመመለስ ግብ ግብ ላይ ናቸዉ ነገር ግን አልተሳካም ነበር ሰዉዪዉ ላይመለስ አሸለበ

ዋሲሁን ተስፋ በመቁረጥ እና በድካም ስሜት ዉስጥ በመሆን የለበሰዉን ጋዉን ሲያወልቅ ጋዋኑ ላይ በደምየተጣፈ አንድ ፁሁፍ እና ተኩላ እሚመስል ስዕል ተመለከተ ደንግጦ ግራ በመጋባት ስሜት ሆስፒሉን ለቆ ወደመኪናዉ

ሲያመራ መኪናዉ በር ላይ ጆንሰነንን አገኘዉ ወደ አንድ ቦታ ሁኑኑ ሊወስደዉ እንደሚፈልግ አስቸኩዋይ እንደሆነ ነገረዉ ዋሲሁን በፍፁም

ፍቃደኛ እንዳሎን ነግሮት ወደመኪናዉ ሊገባ ቁልፎቹን ሲያወጣ አምልጠዉት እመሬት ወደቁ ሊያነሳ ጎንበስ ሲል ማጅራቱ ላይ መርፌሲገባ ተሰማዉ እራሱን ስቶ ወዲያዉ መሬት ወደቀ፤፤

ይቀጥላል.........

📚@gbw_dan
📚 @gbw_dan
📖 @gbw_dan


ማዕበል_የአብዮቱ_ማግሥት_ብረሃኑ_ዘሪሁን.pdf
1.6Мб
📚@gbw_dan
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹@gbw_dan
@gbw_dan🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹


ባለፈው ስለ እውቁ ተዋናይና ተራኪ ወጋየሁ ንጋቱ በሰፊው አቅርቤላቹኀለሁ።
ዛሬ ደግሞ እሱ ከተረካቸው መጻሕፍት አንዱ የሆነውን መጽሐፍ ይዤላችሁ መጥቻለሁ
መልካም ንባብ!
🇪🇹ሠላም ለኢትዮጵያ ሀገራችን!!!

📚@gbw_dan
📚 @gbw_dan
📖 @gbw_dan
👇👇👇


ሀሰተኛው @frombooks1234.pdf
45.1Мб
ወደ ረድ ሠርዌ ስመለስ ወፍጮ ቤቱ ላይ እንዳተኮረ ነበር። አውሎ ንፋስ ያግለበለበው የመሰለ የዶቄት ብናኝ ይቦናል። ለፀጉራቸው ብቻ የሚጨነቁ ሴቶች ሻሻቸውን ቆልለው ቡላ ፊታቸውን አስቀድመው ይወጣሉ። ሻኛ የመሰለች የእህል ቋጠሮ ጀርባቸው ላይ አብጣ ትታያለች። ለአንድ ቤተሠብ የአንድ ቀን ፍጆታ ሳይሆን አይቀርም። የመከራ ጊዜው ያለፈ ቢመስልም በየሰው ልብ ውስጥ የተወው ቅሪት ዘልአለማዊ ሥጋት ሰንቅሮ ትቷል። ሰው ሥጉ ፍጡር መሆኑን የሚገልፀው እንዲህ ያለ ቀን ነው። የመከራ ጊዜ ፍላጎት አዘቅት ነው። ቁስ ብንከምር ብንቁልል ዓይናችን አይጠግብም። አንዳንድ ሴቶች እነሱ የማይችሉትን አስፈጭተው በሚችለው አሸክመው እየተገላመጡ ይቀድማሉ። ምናልባት አይን ውስጥ እንዳይገቡ ይሆናል። ከሸክሙ በጥቂት ምዕራፍ ይርቃሉ። እነዚህ ሴቶች ያልተረዱት ቢኖር ያሸከሙት ሰው ከዘረፋ ውጭ ምንም ተስፋ ከሌላቸው ወገን መሆኑን ነው። ነገሩ ዳግም ካገረሸና የከተማው አቅርቦት ድንጋይ ብቻ ከሆነ ድንጋዩን ጨብጠው እህሉ የገባበትን ቤት የሚከቡ ድሆች ይመጣሉ። አግበስባሾች ያግበሰበሱት መጥፊያቸው ይሆናል ።

አለማየሁ ገላጋይ ፤ ሀሰተኛው

📚📖 @gbw_dan
📖 @gbw_dan📚📖 @gbw_dan


50አለቃ ገብሩ
✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳
✴✴✴✴✴✴✴✴
✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳

✍️ገጣሚ➹ታገል ሰይፉ
🎤ተራኪ➹ታገል ሰይፉና ሌሎችም
📁➹4.6mb
#ፍረዱኝ
🎭🎭🎭🎭🎭🎭
🎭🎭🎭🎭🎭🎭

🇪🇹ሠላም ለኢትዮጵያ ሀገራችን✊
🍂ጥበብ መንገደኛ

▰ ▬ ▮@gbw_dan
▮▬▮ ▮ ▬▬


ውድ አባላቶቻችን ይህን ፅሁፍ ያገኘነው #ከሰውና_ፍልስፍናው የቴሌግራም ቻናል ሲሆን ብታነቡት ትጠቀሙበታላችሁ ወይም ትዝናኑበታላችሁ ብለን ነው የጀመርኘው።

ሰውና ፍልስፍናው የቴሌግራም ቻናል እናመሰግናለን!

#እነሆ_ተጀመረ.....

የሉሲፈር : በትር
✦✦✦✦✦✦✦


ዶ/ር ዋሲሁን በሁለት ሃሳብ ልቡ ተከፍሎዋል ምክኒያቱም የሚወደዎ ጃክሰን የሚስጥረኛዉ መህበር አባል መሆኑን እና እሱንም እስካሁን ከትትል እያረገበት እንደሆነ በቀዝቃዛዋ በርሊን አንድ ካፌ ዉስጥ ሳቅ በተሞላዉ ጨዋታቸዉ መሃል ከተደወለለት ጥሪ በዉሃላ አረዳዉ ፡፡


በሚስቱ ብርቱ ጥረት እና በሱ ከባድ ፍላጎት የተነሳ ወደ እዚ ሚስጥራዊ መሃበር እንደገባ ከገባም በዉሃላ ብዙ ሚስጥራዊ ስራዎችም

ለመሃበሩ እንደሰራ እሱም አንዱ የስራዉ አካል እንደነበር በሚስጥራዊዉ መሀበር ዶ/ር ዋሲሁን ከተመለመለ ቡሃላ ጊዜዉ እስኪደርስ ክትትል

እየተደረገበት እንደነበር እንግሊዝ ዉስጥ በከፍተኛ መአረግ እሚያስመርቅ ዉጤት ሳይኖረዉ በመሀበሩ ትእዛዝ እንደተመረቀ ከዛም

አልፎ ጊኒ ፤ኮትዲቫር ፤ሴኔጋልን ጨምሮ ፡ ለእነሱ አላማ በአፍሪካዉያን ስነልቡና የባህል ህክምና አሰጣ እንዲሁም በአፍሪካዉያን የጤና ስርአት

ላይ ሰፊ ጥናት እንዲያካሂድ እንዲሁም ሲንጋቦር፤ እና ታይዋን እንዲሁም ቻይና የባህል እክምና ጥበብ ላይ ምርምር እንዲያካሂድ ከዛም

አልፎ ሆላንድ እና ጀርመን በህክምና እንዲያገለግል በቂ የስራ ልምድ እና እዉቀት እንዲያገኝ እንደተሰራ እሳካሁንም ግራጁዌወት


ካደረገ ቡሃላ የስራ እድልም ሆነ ከኢትዮጲያ ጀምሮ አዉን እስካለባት ጀርመን ለእዚ መድረስ የነሱ እጅ እናዳለበት በቀላሉ አረዳዉ በወቅቱ

ከቀልድ የቆጠረዉ ዶ/ረ ዋሲሁን በፈገግታ ቢያልፈዉም ከኢትዮጲያ አንስቶ አሁን ህክምና እሚሰጥበት ሆስቢታል ድረስ የተፃፃፋቸዉን

ኢሜሎች ላይ እስከዛሬ ግልዕ ያሎኑለትን ምልክቶች ማለትም ኢሜል ሱደረግለት ስድስተኛዉ መስመር ስድስተኛዋ ፊደልጋር ያለች

ምልክት እንዲሁም የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃዎቹ እንዲሁም የትምህርት ማስረጃዎቹ ላይ ያለችዉን ጥያቄ ስቶንበት የኖረችዉን ምልክት

ጃክሰን እንብርት ላይ አንድወቅት ባህሩ ዳርቻ ላይ ሲዝናኑ ተመልክቶ በጠየቀዉ ጊዜ ጆንሰንም ያዉ ወጣት ስቶን እምታደርገዉን አታቅም መጀመሪያጊዜ ያፈቀርኩዋት ቫቤላ ትባላለች

ይቀጥላል.......

አስተያየታችሁን @frombooks1234_bot ላይ አድርሱን


📚@gbw_dan
📚@gbw_dan
📚@gbw_dan

Показано 20 последних публикаций.

1 029

подписчиков
Статистика канала