ሃምሳ አለቃ ገብሩንና አባ ገሬንና ታገል ሰይፉንና አለማየሁ ገላጋይን በአንድ መጽሐፍ ውስጥ አገኘኋቸው---አጥቢያ
እናም በአጥቢያ መጽሐፍ-አባገሬ ውስጥ 50አለቃ ገብሩ ይታዩኛል፤ በአለማየሁ ውስጥ ታገልን አገኘኋለሁ (መፅሐፍ የጸሃፊው ነጸብራቅም አይደል)እስቲ አንዱን ባንዱ እንመልከት
....
"አልዋሽም ያጥፋኝ አልዋሽም" ካሉ አይዋሹም።አብዛኛውን ጊዜ መንደርተኛውን በሳቅ የሚያፈርሱት ስለመወገራቸውና ስለሴት አይምሬነታቸው እያወሩ ነው። በይበልጥ በሚስታቸው ስለመወገራቸው።
"አንድ ቀን የምችላት መሰለኝና ምናባቷ ብዬ በሩን ዘጋሁ።በኋላ ያዝ ሳደርጋት ሲሌዬን ለቀም አድርጋ አልጋው ላይ ደብ! አደረገችኝ። "እ" እያለች በምን ልቻላት።በጓሮ በር ጎረቤታችን ገባ። እሱን ሳየው አፈርኩና በአዝማሪ ቋንቋ ከላዬ ላይ እንድትነሳልኝ ለመንኳት "እ" እያለች እምቢ ብትለኝ ወደ ጎረቤታችን ዞር ብዬ እኔ ሚስቴን ስቀጣ አትምጣብኝ አላልኩም? ብዬ ተቆጣሁታ!..." ቤቱ ያወካል።
"አንድ ጊዜ ደሞ..."ይቀጥላሉ "አንድ ጊዜ ደሞ ቀን ሥራ ድንጋይ ሸከማ ገባሁና ሰራርቼ ስመጣ እንደው ለከፈችኝ። ብስጭት ብዬ መቆሚያ ጣቢያ ወጥቼ እንደቆምኩ አንድ ወፈፌ ብጤ የጠጅ ቤት ጓደኛዬ መጣና ምን እንደሆንኩ ጠየቀኝ። ብስጭት ብዬ ብነግረው "ና-ምናባቷንስና" ብሎ ፊት-ፊት ቀደመኝ።እኔም "ጎሽ የወንድ እጅ አሳይልኝ" ብዬ ተከተልኩት።
"ስንደርስ ረታች በር ላይ ቁጭ ብላለች። "አንቺ?" አላት "ምን ሆነሽ ነው ለፍቶ ሲመጣ የሚበላ የምትከለክይው?"
"ና! ወንድ ከሆንክ ሌማት ከፍተህ አንተ ስጠው" አለችው "ሂድ የወንድ እጅ አሳይልኝ" አልኩት። ጓደኛዬን ስገፋፋው ቢያቀምስልኝ እንዴት አንጀቴ ቅቤ በጠጣ ነበር። ገና ጠጋ ሲላት እ አለችና ጠቅልላ ተወችው!!"ቤቱ ያውካካል፦ፀቡ ላይ የነበሩ ቀሪ ነገር ይጠይቃሉ። "ታዲያ ያኔ ጓደኛዎት ሲመታ እርስዎ ምን አሉ?"
"ምነው እኔ ብቻ አንተም ቅመስ'ጂ አልኩታ "
ለቅሶ ቤቱ የፌሽታ ቤት መስሎ ቁጭ ይላል።
አባ ገሬ ሲበዛ ደግ ናቸው።ባለቤታቸው 'ኳ እንደዛ እየደበደቧቸው ትንሽ ፍራንክ ያገኙ እንደሆነ "አቦ ያቺ ረታች ባዶ ቤት ሳትሆን አትቀርም" ብለው ወስደው ይሰጧቸዋል። ብዙ ጊዜም እቤታቸው ጽዋ ገብቶ ሲደገስ ማህበርተኛ ከመግባቱ በፊት የድግሱን ምግብ እየጨረሱ ባለቤታቸውን አስለቅሰዋል። እንዲሁ የአመት በአል ጊዜ ረታች ከቤት ወጣ ያሉ እንደሆነ ገልብጠው ማብላት ነው።...
(ገጽ፦ፈለገው ያግኙት-አጥቢያ)
አስቲ አባገሬን 50አለቃ ገብሩ ውስጥ ከትቼ ላሳያችሁ እና ላስነብባችሁ...
አባገሬ
በእውነት አልዋሽም ያጥፋኝን አልዋሽም
በማለት ጀመሩ የ8ኛው ሺህ አባገሬ ድማም
በለቅሶ ሃዘን ላይ የነበረውም ህዝብ
ባነጋገራቸው እጅጉን በመሳብ
ሃዘኑን ረስተው ለሳቅ በመጎምዠት
እሺ ይቀጥሉ በሚል አስተያየት
ዘወር ሲሉላቸው
ደስ ተሰኝተው
ከእለታት ባንዱ ቀን በወንድ ማዕረግ የኔን ሚስት ለመቅጣት
ከኋላዋ ሆኜ ያዝ አፈፍ ሳደርጋት
"እ" አለችና በተቆጣ ስሜት
ከአልጋው ላይ ጥላኝ እንዲመች ለመምታት
አንድ ጊዜ በቡጢ አንድ ጊዜ በጥፊ
ስታመላልሰው የእጇን አሳላፊ
ጎረቤት ሰማና በጓሮ በር ገብቶ
ደንገጥ በማለት ለመሳቅም ሽቶ
እኔም አፈርኩና በአዝማሪ ቋንቋ
እባክሽን ይብቃሽ ብዬ ብለምናት
እሷ መስሚያ የላት።
እኔም ይህን ግብር አስተዋልኩኝና
ወደጎረቤቴ ዘወር አልኩእና
እንዲህ ነው ምቀጣት በል ልምድ ቅሰም
ልምዴን እያካፈልኩ ነገሩ ቢሆንም
ሚስቴን አየቀጣሁ አትምጣ አላልኩም?
ቢሆንም...ሚል ነገር አይሰራም
ቢሆንም ቢሆንም ቢሆንምምም
በማለት እውነት አላጎድፍም።
ይህንን ሲሰሙ ቤቱ ሳቅ ይሞላል
ሃዘኑ ተረስቶ በደስታ ይተካል።
(ጦማሪ ዳኒኤል አወቀ የዮዲት ልጅ -ዮዳሄ)
የታገል ሰይፉ 50አለቃ ገብሩም እዚህ ላይ ያበቃል
🇪🇹ሠላም ለኢትዮጵያ ሃገራችን!
📚@gbw_dan