ሕዳር ሲታጠን
እ.ኤ.አ ከ 1914 ዓ.ም እስከ 1918 ድረስ የዘለቀውና የ15 ሚሊዮን ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው ጦርነት በታሪክ የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ተብሎ ይታወቃል፡፡
የጦርነቱ ማብቃት ሊታወጅ ጥቂት ሲቀረውና ዕልቂቱ ቆመ ሲባል
ግን የዓለም ህዝብ ሌላ ፍዳ ማስተናገድ ግድ ሆነበት፤ በሰው ሰራሽ ችግሮች (በዋነኝነት በጦርነት) ተወጥሮ የቆየው መላው የአለም ህዝብ አሁን ደግሞ በእንፍሉዊንዛ በሽታ ከዳር እስከ ዳር ተጠቃ፡፡
በተለምዶ የእሰፓኒሽ ፍሉ ተብሎ የሚታወቀው ይህ ወረርሽኝ መነሻው ከወደ አሜሪካ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ይህም እ.ኤ.አ በጥር ወር 1918 ዓ.ም በአንደኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ ዋዜማ በጦርነቱ ለመካፈል የአሜሪካ ወታደሮች ወደ አውሮፓ ለመጓዝ ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት ከተከሰተው ወረርሽኝ ጋር ይያያዛል፡፡ በካንሳስ በሚገኘው ፉንስተን የወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል የተቀሰቀሰው ወረርሻኙ በሶስት ቀናት ብቻ 45 ሺህ የሚሆኑ ወታደሮችን አጠቃ፤ ወታደሮቹ አትላንቲክን አቋርጠው አውሮፓን እንደረገጡ በሸታውም አውሮፓ ደረሰ፡፡ የእንፍሉዌንዛ በሸታው በአውሮፓ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በፈረንሳይ ቢሆንም በጦርነቱ ምክንያት ፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ ይሆናል በሚል ወረርሽኙ ለህዝብ ሳይገለጽ ተደብቆ ቆይታል፡፡ በሽታው ይፋ የሆነው እ.ኤ.አ በህዳር ወር 1918 ዓ.ም በስፔን በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ መታየቱን ተከትሎ ነበር፡፡ ስፔን በጦርነቱ ተካፋይ አልነበረችምና በአገሪቱ የጦርነት ጊዜ ሳንሱር አልነበረም፤ በመሆኑም የበሽታው መስፋፋት ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን በማግኘቱ ወረርኙ እስፓኒሽ እንፍሉዌንዛ (ስፓኒሽ ፍሉ) የሚለውን ስያሜ አገኘ፡፡
በኢትዮጵያ በሽታው የታየው የመጀመሪያው የበሽታው ምልክት በዓለም ላይ ከታየ ከአስር ወር በኋላ በህዳር ወር 1911 ዓ.ም ነው፡፡ ከህዳር 7 እስከ ህዳር 20 1911 ዓ.ም ለአስራ አራት ቀናት ገደማ የቆየው በሽታው በህዳር ወር የተከሰተ በመሆኑም ህዝቡ የህዳር በሽታ እያለ ይጠራው ጀመር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ይህ በሽታም በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ለበርካቶች ሞት ምክንያት ሲሆን ለበሽታውም የተለያዩ ስያሜዎች ተሰጥተውት ነበር። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ምሁር የሆኑት አቶ አበባው አያሌው የበሽታውን አመጣጥ አስመልክቶም የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መንገድ ስራ በጀመረበት ወቅት በሽታው በመነሳቱ ምክንያት ባቡሩ ያመጣው በሽታ ነው በማለት "የባቡር በሽታ" ይባል እንደነበር ይናገራሉ። በተጨማሪም የተከሰተበትን ወር ተከትሎም "የህዳር በሽታ" ተብሎ መጠራት እንደጀመረም ይናገራሉ።
ብላቴን ጌታ መርስዔ ሀዘን ወልደቂርቆስ የሃያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ በተሰኘው መጽሀፋቸው እንዳሰፈሩት ወረርሽኙ እስከ አርባ ሺህ ኢትዮጵያዊንን ለሞት ዳርጋል፤ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ዘጠኝ ሺህ ዜጎች በበሽታው ሞተዋል፡፡ እንደሚታወቀው የኢትዮጲያ ስታቲክስ እንደተማሪዎች መርጃ መጽሐፍ(Guide book)የተለያየ መረጃዎችን ይሰጠናል፣እናም በሌላ ጥናት በአዲስ አበባ ብቻ ከ6 ሺ ሰው በላይ መግደሉንም የተጠናው ጥናት ያሳያል። ይህንንም ተከትሎ በጀርመን ሀኪሞች ምክክር ህዝቡ ቆሻሻ ከቤታቸው አውጥተው እንዲያቃጥሉ በአዋጅ መለፈፉን አቶ አበባው ይናገራሉ።
በተለይም ህዳር 12 ቀን 1911 ዓ.ም በርካታ ኢትዮጵያዊያን የሞቱበት በመሆኑ ቀኑ በጽዳት ዘመቻ እንዲደረግ በአዋጅ ተነግሮ ስለነበር፣ ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት ይህ ነገር እንደባህል ተወስዶ በየዓመቱ ህዳር 12 ቀን የጽዳት ዘመቻ ይደረግ ጀመር፤ ይህም በተለምዶ ህዳር ሲታጠን የምንለው ነው፡፡
"ይህም የበሽታው መንስዔ ቆሻሻ እንደሆነ በመታመኑ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በሽታው በአየር ይተላለፋል ተብሎ ስለታመነም አየሩን እንደማጠን ይቆጥሩታል" ይላሉ አጥኚዎች።
ከጊዜ በኋላም አየሩ ስለታጠነ ነው በሽታው የጠፋው ተብሎ በየዓመቱ ቆሻሻን ማቃጠልን ህዳር ሲታጠን የሚል ስያሜ ማግኘቱም ከዚህ ተነስቶ መሆኑን ያብራራሉ።
ምንም እንኳን ቆሻሻን ማቃጠል ለአካባቢ ንፅህና ጥሩ ቢሆንም ለአየር ንብረት አሉታዊ አስተዋፅኦ ስላላው ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
"የሚቃጠሉት ቁሳቁሶች በተለይም ፕላስቲክና የባትሪ ድንጋዮች ሃይድሮፍሎሮ ካርበን፣ ሜቴንና ካርበንዳይሞኖክሳይድ የተባሉ ንጥረ-ነገሮችን በውስጣቸው ስለሚይዙ ለአየር ብክለት የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው" ይላሉ።
በዓለም የአግሮ ፎረስትሪ (የግብርናና ደን ማዕከል) ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ለሊሳ ዱጉማ በበኩላቸው የሚቃጠለው ቆሻሻ መጠን እና የሚቃጠልበት አካባቢ ወሳኝ ነውም ይላሉ።
"ገጠር አካባቢ ከሆነ የሚቃጠለው አብዛኘው የተፈጥሮ ተዋፅኦ ስለሆነ ብዙም ችግር ላይኖረው ይችላል። ከተማ አካባቢ ግን የተለያዩ በኬሚካል የተሞሉ ንጥረ-ነገሮች ስለሆኑ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳሉ" በማለት ዶክተር ለሊሳ በጥናታቸው ይገልፃሉ።
አሁንም ከተጋረጠብን ወረርሽኝ ይልቅ በአሉባልታ የጦር ወሬዎች ተጣበን ጽዳትን ዘንግተነዋል፣ ማስኩን ጥለነዋል፣ ሳኒታዘሩን እዚህም እዚያም ደፍተነዋል።
ወገን 'ዋናው ጤና' ሲባል ሰምተናል መቼስ ራሳችንን እንጠብቅ። ሀገርም ምትፈልገን በጤና ሳለን ነው።
🚮🚮🚮🚮🚮🚮
😷@gbw_dan😷