GROW_TO_GOD


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


➣ በ GROW_TO_GOD የተለያዩ መንፈሳዊ የሆኑ
👉መልዕክቶች ፣
👉ትምህርቶች ፣
👉ሀሳቦች
የምተላለፉ ስሆን ለበረከትነት የምዉል channel ነው ።
📖 “ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤” ኤፌሶን 4፥15
📩 ለሀሳብ @Peni0412
https://www.facebook.com/104100875399608/

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




.... ምክኒያቱም እርሱ አባቴ ነው !

በአንድ ወቅት አንድ ሰው በጣም የምያስገርም ትርዕት ብዙ ሰዎች በተሰበሰቡበት ያቀርባል ። ትርዕቱም በትልቅ ወንዝ ላይ ከዳር እስከዳር ገመድ ተዘርግቶ በገመዱ ላይ ተራምዶ መሻገር ነበር ። ሰውየውም በምገርም ሁኔታ ገመዱ ላይ ስራመድ የምያዩ ታዳሚዎች " በርታ በርታ ወደ ፍት ብቻ እይ .... ጠንቀቅ እያልክ " እያሉ ያበረታቱት ነበር ። ሰውዬውም በምገርም ሁኔታ ገመዱን ተራምዶ ተሻገረ ። ታዳሚ የነበሩ ሰዎችም በአድናቆት " አንተ ጀግና ነህ በጣም አስደናቅ ችሎታ አለህ " እያሉ ደስታቸውን ገለጹለት ።

ሰውየውም ወደ ታዳሚዎች ዞሮ እንድህ አላቸው፦ "እንዳያችሁኝ ገመዱ ላይ ተራምጄ ተሻግሬያለው አሁን ደግሞ አንድ ሰው ተሸክሜ ገመዱ ላይ ተራምጄ መሻገር እፈልጋለው ። እናም ፈቃደኛ የምሆን ሰው ፈልጋለው አለ ። " ቅድም ስያደንቁትና ለችሎታው እውቅና ስሰጡ ከነበሩ ታዳሚዎች መሀል ፈቃደኛ ምሆን ሰው ጠፋ ።

ነገር ግን በመሀል አንድ ትንሽ ልጅ ከሰዎች መሀል እኔ ፈቃደኛ ነኝ በማለት ወደ ሰውየው መጣ ። በትንሹ ልጅ ድርግት እጅግ የተገረሙ ታዳሚዎች የምሆነውን በትኩረትና በአግራሞት ይከታተሉ ጀመር ። ሰውየውም ትንሹን ልጅ ተሸክሞ በገመዱ ላይ ተራምዶ ከወንዙ ማዶ ተሻገረ ። ታዳሚዎቹም እጅጉን ተገረሙ ፤ ከሰውየው ድርጊት ይልቅ የትንሹ ልጅ ቆራጥነት አስገርሟቸው ስጠይቁት የልጁ ምላሽ ይሄ ነበር ፦ " እኔን ተሸክሞ ገመዱ ላይ እንድራመድ ስወስን እንደማይጥለኝ በጣም እርግጠኛ ነበርኩ ምክንያቱም እርሱ አባቴ ስለሆነ " አለ ።

ወዳጆቼ አባትነትንና ልጅነትን ስንረዳ በአባታችን ላይ ያለንን እምነት እናጠናክራለን !!

የተባረካችሁ ናችሁ !!

@grow_to_god
@grow_to_god
@grow_to_god
@grow_to_god




#ጸጋው_በእምነት ....

📖“#ጸጋው_በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤” ኤፌሶን 2፥8

✍ #ጸጋ እና #እምነት የማይነጣጠሉ ነገሮች ናቸው ። ምክንያቱም አንዳቸው ያለ አንዳቸው ሙሉ መሆን አይችሉም ። ለምሳሌ #ጸጋ ብቻውን #እምነት ከለሌ ዋጋ የለውም ። እምነትም እንደዛው ያለ ጸጋ ሙሉ ልሆን አይችልም ።

✍ "#ጸጋው_በእምነት አድኖአችኋል " ብሎ ስል የእግዚአብሔር ጸጋ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ስለበደላችን እና ስለ ኀጥአታችን በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶ እርሱ በሰራው ስራ አምነን በእምነት በኩል እንዳዳነን ይገልጻል ። አያችሁ መዳን የሆነልን #በጸጋው_በእምነት በኩል ነው ። ለዛም ነው ከላይ ጸጋ እና እምነት እንደማይነጣጠሉ የገለጽኩት ። ጌታችን እና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰራው ስራ #በጸጋው መዳን እንደምገኝ #በእምነት ያመኑ ሰዎች ይድናሉ ። መዳን የምገኘው ልያድነን የተገለጠውን ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን ብቻ ስለሆነ ።

✍ መዳናችን #በጸጋው_በእምነት ነው ። ያ ደግሞ የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው እንጂ ከእኛ እንዳልሆነ መጽሐፍ ቅዱሳችን አስረግጦ ይነግረናል ። እግዚአብሔር ዓለምን ( እኛን ) እንድሁ ወዶ ከሞት ወደ ህይወት ከጨለማ ወደ ምደነቅ ብርሀን ልያወጣን ልያድነን አንዲያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ሥጦታ አድርጎ ሰጠን ። የተሰጠን ሥጦታ #በጸጋው_በእምነት አዳነን ። ሀሌሉያ !! የሰው ልጅ በራሱ ጥረትና ስራ ድነትን (መዳንን) ልያገኝ ከቶ አይችልም ። ለዛም ነው መጽሐፍ ቅዱስ "#ጸጋው_በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም" የምለን ። ነገር ግን መልካም የሆኑ ስራዎችን የምንሰራው የምናገለግለው የምንቀደሰው ስለመዳናችን መገለጫ ይሆን ዘንድ ነው ።

✍ ወዳጆቼ ይሄንን ጽሁፍ በተለያዬ አጋጣሚ ኢያነበባችሁ ያላችሁ ፦ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠን #ጸጋ ነው ። ያንን ደግሞ በማመን መዳን እንደምቻል እንድታውቁ ፈልጋለው ። ኑ ወደ ጌታ እርሱ የዘላለም እረፍት ነው ። እርሱ ስጋት የሌለበት መኖሪያ ነው እርሱ የማይጥል የማይረሳ ወዳጅ ነው ። ሰውን ሁሉ የምወድ ሰውን ለማዳን ከአብ ልያስታርቅ የሞቴ ከሞት የተነሳ ወደ አብ ያረገ አሁን በክብር በአብ ቀኝ ያለ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል ይታደግማል ። ያሌሉያ !!

የተባረካችሁ ናችሁ !!

👇 ቻናሉን ይቀላቀሉ 👇

👉 @grow_to_god 👈
👉 @grow_to_god 👈
👉 @grow_to_god 👈
👉 @grow_to_god 👈




1ኛ ዮሐንስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።
² እግዚአብሔርን ስንወድ ትእዛዛቱንም ስናደርግ የእግዚአብሔርን ልጆች እንድንወድ በዚህ እናውቃለን።
³ ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።
⁴ ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።
⁵ ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው?
⁶ በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በውኃውና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም።
⁷ መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው።
⁸ የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ።


https://t.me/grow_to_god




ኢሳይያስ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም። በመጀመሪያው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አቃለለ፤ በኋለኛው ዘመን ግን በዮርዳኖስ ማዶ በባሕር መንገድ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል።
² በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው።
³ ሕዝብን አብዝተሃል፥ ደስታንም ጨምረህላቸዋል፤ በመከር ደስ እንደሚላቸው፥ ሰዎችም ምርኮን ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው በፊትህ ደስ ይላቸዋል።
⁴ በምድያም ጊዜ እንደ ሆነ የሸክሙን ቀንበር የጫንቃውንም በትር የአስጨናቂውንም ዘንግ ሰብረሃል።
⁵ የሚረግጡ የሰልፈኞች ጫማ ሁሉ፥ በደምም የተለወሰ ልብስ ለቃጠሎ ይሆናል፥ እንደ እሳት ማቃጠያም ሆኖ ይቃጠላል።
⁶ ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።
⁷ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።


https://t.me/grow_to_god






ዮሐንስ 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንሥቶ ዳግመኛ ተቀመጠ፥ እንዲህም አላቸው፦ ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?
¹³ እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።
¹⁴ እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል።
¹⁵ እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።
¹⁶ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም።
¹⁷ ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።

ቀናችሁ በጌታ የተባረከ ይሁን !!

https://t.me/grow_to_god


#ተነሣና_ተመላለስ

📖 “ጴጥሮስ ግን፦ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ አለው።" ሐዋርያት 3፥6

🔰 ሐዋርያው ጴጥሮስና ዮሐንስ በጸሎት ህይወታቸው የበረቱና የተጉ ነበሩ ። አንድ ቀን በጸሎት ጊዜ በ9 ሰዓት ወደ መቅደስ ለመጸለይ ይሄዱ ነበር ። አንድ ሰው ሁልጊዜ በቤተመቅደስ ደጅ ላይ ተቀምጦ ከምዕመናኑ ሳንቲም የምለምን ሰው እነ ጴጥሮስ እና ዮሐንስ ለመጸለይ ስመጡ አያቸው ። ልክ ባያቸው ጊዜ ከእነርሱ እጅ ምጽዋት ያገኝ ዘንድ እነርሱም እንድሰጡት በምለምን አይነት ፍት በተስፋ ስመለከታቸው እነርሱም የሆነ ነገር ይሰጡኛል ብሎ ጓጉቶ እየጠበቃቸው እንደነበረ ተገነዘቡ ። ነገር ግን ጴጥሮስ በቤተመቅደስ ደጃፍ ላይ ቁጭ ብሎ ምጽዋት ስለምን የነበረውን ሰው እንድህ አለው ፤ ብርና ወርቅ የለኝም ይህ ያለኝን ግን እሰጥሀለው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ አለው ። ሀሌሉያ !!

✳️ አያችሁ ይህ ሰው በዚህ ጊዜ ያገኘው ተዓምር በህይወት ዘመኑ አስቦትም ገምቶትም የማያውቅ ድንቅ የሆነ ነገር ነው በህይወቱ የሆነው ። ጴጥሮስ ብርና ወርቅ ባይኖረውም ብርንና ወርቅን የፈጠረ የሁሉ ጌታ የሆነው አምላክ በውስጡ እንዳለ አምኖ ነበር ። ያለ ምንም መጠራጠርና ማመንታት ይህን ሰው ከሺባነቱ የምተረትር ድንቅን የምያደርግ ሀይል በውስጡ እንዳለ የተገነዘበ ሰው ነው ። በጣም የምገርመው ደግሞ ጴጥሮስ ይህ ሰው ከዚህ እስራቱ የምፈታበት ጊዜው እንደሆነ ስለተረዳ እንድህ አለው ወደ እኛ ትኩር ብለህ ተመልከት ምክንያቱም ይህ ሰው እንደምፈወስና በእግሮቹ እንደምቆም ጴጥሮስ አምኗል ። ከዛ በኋላ ይህ ዘመኑን ሙሉ ሽባ የነበረ ሰው በጴጥሮስ እና በዮሐንስ ውስጥ ባለው የመንፈስ ቅዱስ ሀይል ተዓምር ሆነለት ፤ እግዚአብሔር ጎበኘው መታወቂያውን ቀየረው እየዘለለም ለእግዚአብሔር ክብርን አመጣ ። ሀሌሉያ!!

✅ ወዳጆቼ እኛም በዚህ ዘመን በተሰጠን ጸጋና የመንፈስ ቅዱስ ሀይል ድንቅንና ተዓምርን ለብዙዎች መፈታትን ለዘመናት ከተሰቃዩበት ስቃይ መላቀቅን ልናደርግ ተጠርተናል ። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ምድርቱን እንድሸፍን እንድሞላ በድንቅ ተዓምራት እና ምልክቶች እንገለጥ ዘንድ ጊዜው ደርሷል ። የዚህ አገልግሎት አካል አንድንሆን ራሳችንን እናዘጋጅ ፤ መንፈስ ቅዱስ በህይወታችን እንድሰራ እንፍቀድ ። ጸጋው ይብዛላችሁ ። አሜን 🙏

⬇️ ቻናሉን ይ🀄️ላ🀄️ሉ ⬇️

❇️ @grow_to_god ❇️
❇️ @grow_to_god ❇️
❇️ @grow_to_god ❇️
❇️ @grow_to_god ❇️


Репост из: GROW_TO_GOD
ይቅርታውም ብዙ ነውና !!

📖 “ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፥ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ።” — ኢሳይያስ 55፥7

✅ በጣም ከሚገርመኝና ከሚደንቀኝ የእግዚአብሔር ባህሪያት አንዱ ይቅር ባይነቱ ነው ፤ እግዚአብሔር ለይቅርታ ያለው ቦታ በጣም ይገርመኛል ። ይቅር ስልም ልክ እንደሰው "አልረሳውም ግን አላነሳውም" እያለ አይደለም ፤ ይልቁን ትቼዋለው ኀጥአትህን ይቅር ብያለው ከዚህ በኋላ ደግመህ አትስራ እያለ እንጅ ። ወዳጆቼ ዛሬ በውስጤ የሞላውን ቃል ላካፍላችሁ ፦ የሰው ልጅ ኀጥአት ስያደርግ ወይንም እግዚአብሔርን ስበድል እግዚአብሔር እጅግ ያዝናል ፤ ነገር ግን ሁል ጊዜ ይቅርታ የምባልን ትልቅ የምህረት ደጅ እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል አዘጋጅቷል ። በዚያ የይቅርታና የምህረት ደጅ ገብቶ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ደግሞ ህይወትን እንደገና ያለመልማታል ፤ እንደገና ፍሬ ማፍራት እንድንችል ይረዳናል ለዛም ነው ምሳሌ 28፥13 ላይ “ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል” ብሎ የምለን ።

✅ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ትንቢተ ኢሳያስ 55፥7 ላይ ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው እያለ ይናገራል ፤ ክፋት በመሰረቱ ከጨለማው ዓለም የምመጣ ሰዎች እግዚአብሔር የሰጣቸውን የሪህራሄን ባህሪ እንድያጡና በተቃራኒው ጨካኞች እንድሆኑ የምያደርግ ነው ። ለዛም ነው ክፉ ሰው የክፋት መንገዱን ይተው የምለን ምክንያቱም ከክፉ መንገዱ የማይመለስ ከሆነ ጭካኔን ይላበሳል ሰባዊነቱን ያጣል ፥ በደለኛ በደልን ከማድረጉ በፍት በአይምሮው ያስባል ያንን ከማሰብ ይተው ፤ አይምሮዋችን የሀሳብ መፍለቅያ ክፍል ነው ሁል ጊዜ ከአይምሮዋችን የምወጣ ሀሳብ ነው የምገዛን ስለዚህ በደለኛም በደልን ከማሰብ ይተው መልካም ነገርን ያስብ ይለናል ቃሉ ። ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛውም ሀሳቡን ትቶ ወደ እግዚአብሔር ይመለስ እርሱም ይምረዋል ሀሌሉያ‼️ ፤ አያችሁ እግዚአብሔር አምላክ ሁል ጊዜ መሀሪ ቸር ይቅር ባይ ነው ምንም አይነት ኀትአትና በደል ብትሰራና ብትወድቅ ነገር ግን ከልብህ ወደ እግዚአብሔር ቀርበህ ምህረት ስትሻ ስትፈልግ እርሱ ይምርሀል ይቅር ይልሀል የቸርነት ደጆቹን ይከፍትልሀል ሀሌሉያ ‼️ ። ለዛም ነው ይቅርታውም ብዙ ነውና የምለን ቃሉ ፤ ምህረቱ አያልቅም ይቅርታው የምቋረጥ አይደለም በእወነተኛ ልብ በንስሃ ወደ እርሱ ለምመለስ ሰው እግዚአብሔር ምህረቱን በዘመኑ ሁሉ ያበዛለታል ።

✅ ወዳጆቼ እግዚአብሔር መሀሪ ነው በተለያዬ የኀጥአት ልምምድ ውስጥ ያላችሁ እግዚአብሔር ይቅር አይለኝም የምወደኝ የምያውቀኝም አይመስለኝም የምትሉ መንፈሳዊ ህይወታችሁ የደከመባችሁ እግዚአብሔር ዛሬም ይወዳችኋል ዛሬም የይቅርታና የምህረት ደጆቹን ከፍቶ ይጠብቃችኋል ፤ በእግዚአብሔር ፍት በንስሃ ቅረቡ እርሱ ይወዳችኋል ካላችሁበት ማንኛውም የኀጥአት ልምምድ ውስጥ ያወጣችኋል ። ዳግም ወደዛ እንዳትመለሱ በጸጋው ይጋርዳችኋል ፤ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ይሁንልን አሜን 🙏

https://t.me/grow_to_god




#አመጣጡ_ሊፈልግና_ሊያድን_ነው !!

📖 “የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና አለው።” — ሉቃስ 19፥10

🔰 ወዳጆቼ ዛሬ በልቤ ያለውን የጌታ የቃሉን ሀሳብ ላካፍላችሁ ፈለኩ ሃሌሉያ ። ብዙ ሰዎች ወደ አካባቢያችሁ ወደ መገኛችሁ ስመጡ የተለያዩ ምክያቶችን ይዘው ይመጣሉ ። ለምሳሌ በጣም ስለምወዷችሁ እና ከእናንተ ፍቅር ስለያዛቸው በምላሹ ከእናንተ የፍቅር ስመታቸውን የምያረካላቸውን የተለያዩ ነገሮች ፍለጋ ይመጣሉ ። በሌላ መልኩ ደግሞ ብዙዎች እናንተን ስለምጠሏችሁ እናንተን ለማጥቃት እናንተን ለማጥፋት ታርካችሁን ለማበላሸት አቅደውና ወጥነው ይመጣሉ ። እንደዚሁም ተቸግረው እርዳታን ፈልገው ለችግራቸው መፍትሄ ፍለጋ ወደ እናንተ ይመጣሉ ። ነገር ግን እነዚ ሰዎች ሁላቸውም አስበው የመጡት ነገር ካልተሳካላቸው ጥለዋችሁ ይሄዳሉ ብቻችሁን ይተዋችኋል ። ዞር ብለው አያዩአችሁም ምክንያቱም እነዚያ ሰዎች ስቀርቧችሁ የነበራቸው ዓላማ ሀሳብ (motive ) ለመጠቀምና የራሳቸውን ሀሳብ ለመፈጸም ብቻ ነው ።

✳️ ነገር ግን አንድ ወዳጅ አለ ሰውን ባለው ነገር አይቶ የማይቀርብ በድሎቱ ብቻ የምፈልግ ሳይሆን በችግሩም ጊዜ ከጎን የምሆን ማንም የለኝም ወዮ ጠፋው ስባል በድንገት ተገኝቶ ታርክ የምቀይር ሀሌሉያ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ይባላል ። በዚህ በሉቃስ 19፥10 ላይ በጣም የምደንቅ ቃል እናገኛለን #የሰው_ልጅ_የጠፋውን_ሊፈልግና_ሊያድን_መቷልና ይላል ። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር ሲመጣ ወደ መገኛችን ሲመጣ በኃጥአታችን ምክንያት ጠፍተን የነበርነውን እኛን ሊፈልግና ሊያድን መጣ ። ማንም ግድ ብሎት ለእኛ የምጨነቅ ልያድነን የምችል በጠፋበት ከኃጥአታችን ልያድነን አንዱ የእግዚአብሔር ልጅ #አስታራቂያችን #አማላጃችን እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ መጣልን ሀሌሉያ !! እርሱ #ቤዛችን ሆነ እርሱ ተቤዠን እርሱ ከሞት ወደ ህይወት አሸጋገረን ጠፍተን የነበርነውን ፈልጎ አገኘን አዳነንም ይህ እጅግ ድንቅ ነው ።

✅ የተወደዳችሁ ወዳጆቼ ይህ ጌታ የጠፋውን ልፈልግ የመጣ አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬም በኀጢአት እስራት በዓለም ግዛት ውስጥ ጠፍተው ያሉትን ሊፈልግና ሊያድን አለ ። በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን መዳን እንደምገኝ ተረድተው ወደ መንግስቱ እንድገቡ ለትውልዱ ሁሉ ይህን የምስራች እንስበክ ነፍስን ከስዖል እንታደግ !!

⬇️ቻናሉን ይ🀄️ላ🀄️ሉ⬇️

❇️ @grow_to_god ❇️
❇️ @grow_to_god ❇️
❇️ @grow_to_god ❇️
❇️ @grow_to_god ❇️


የተወደዳችሁ የቻናሌ ቤተሰቦች እግዚአብሔር ረድቶን #500_subscribers ደርሰናል😍❤️ ለዚህ ሁሉ የእናንተም አስተዋጽኦ ስለነበረ ከልቤ አመሰግናችኋለሁ ተባረኩልኝ🙏🙏🙏🙏 እስከ አሁን ስለቀቁ የነበሩ #ትምህርቶች # ጽሑፎች እና #መዝሙሮች እንዴት እንደነበሩ #react በማድረግ ሀሳባችሁን አጋሩኝ ተባረኩ !!


🔑 #የጥበብና_የእውቀት_መዝገብ

📖 “የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና።” — ቆላስይስ 2፥3

✅ በዚህ ዓለም ብዙ የእውቀት ዓይነት አለ ፤ ነገር ግን የሰው ልጅ ከእውቀት ከፍሎ ነው ልያቅ የምችለው ። አንዳንዶች በሆነ የእውቀት ዘርፍ እጅግ ምጡቅ እና ምሁራን ይሆናሉ በተቃራኒው ደግሞ በሌላኛው ዘርፍ ደካማ ይሆናሉ ። ለምሳሌ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ አንቱታን ያተረፉ የሀገራችንና ከውጭው ዓለም በስም የምጠቀሱ ሰዎች አሉ በተቃራኒው ደግሞ በማህበራዊ ዘርፉ ደካማ ሆነው ይገኛሉ ።

✅ ነገር ግን እግዚአብሔር ከዓለም የተሰወረውን ብዙ ምሁራን ያላወቁትን በምድራው እውቀትና ጥበብ ማወቅና መረዳት የማይቻለውን ጥበብና እውቀት የሆነውን ልጁን ክርስቶስ ኢየሱስን ለእኛ ለደካሞች ገለጠልን ሀሌሉያ ።

✅ እግዚአብሔር ፈቅዶ ካልገለጠ በቀር ማንም በአይምሮ እውቀት የእግዚአብሔርን ጥበብ ልያውቅ አይችልም ለዛም ነው ቆላስይስ ምዕራፍ 2፥3 ላይ የተሰወረ የእውቀት እና የጥበብ መዝገብ በእርሱ ዘንድ ነው ብሎ የምነግረን ። አያችሁ እግዚአብሔር ይሄንን የተሰወረውን የጥበብና የእውቀት መዝገብ ለእኛ ለልጆቹ ገለጠልን ፤ ያ የተገለጠልንም ጥበብ ደግሞ ልጁ ኢየሱስ ክርስትስ ነው ሀሌሉያ !! ብዙዎች ጠብባንና ምሁራን ያላወቁት እውቀት ያልተረዱት ጥበብና ያልበራላቸው የህይወት ብርሃን የሆነው ኢየሱስ ለእኛ በርቶልናል ተገልጦልናል ።

✅ ወዳጆቼ እኛ በጌታ አምነን የዳንን እግዚአብሔር የተሰወረውን ጥበብ የገለጠልን ቅዱሳን ፤ እኛ የቀመስነውን ፍቅርና የመዳን ህይወት ሌሎች እንድያውቁ እና እንድረዱ ልንናገር ልናሳውቅ ይገባናል ።

⬇️ ቻናሉን ይ🀄️ላ🀄️ሉ ⬇️

❇️ @grow_to_god ❇️
❇️ @grow_to_god ❇️
❇️ @grow_to_god ❇️
❇️ @grow_to_god ❇️




መዝሙር 119
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በመንገዳቸው ንጹሐን የሆኑ፥ በእግዚአብሔርም ሕግ የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው።
² ምስክሩን የሚፈልጉ፥ በፍጹም ልብ የሚሹት ምስጉኖች ናቸው፤
³ ዓመፅንም አያደርጉም፥ በመንገዶቹም ይሄዳሉ።
⁴ ትእዛዛትህን እጅግ እንጠብቅ ዘንድ አንተ አዘዝህ።
⁵ ሥርዓትህን ለመጠበቅ መንገዶቼ ይቀኑ ዘንድ እወድድ ነበር።
⁶ ትእዛዝህን ሁሉ ስመለከት በዚያን ጊዜ አላፍርም።

ምሽታችሁ የእረፍት ይሁን!!

https://t.me/grow_to_god


GROW_TO_GOD
💽 የመዝሙር ጊዜ 🎬

Singer - ዘማሪ ዘርፌ ከበደ
Title - መዳን በሌላ በማንም የለም
Duration - 12:56
Type - Live worship

@grow_to_god
@grow_to_god

Показано 20 последних публикаций.

632

подписчиков
Статистика канала