Halal islamic post🕌


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


AS WR WB
in this islamic chanal we talk about our deen yes i'm not sheekh or mufatih but i'm muslim to do this😊

MAKE YOUR LIFE HALAL!

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


📸😘😍❤️💋❤️

@halal_couples


"ሀዋን ማን ገደላት"
(✍ አብዲ ኢኽላስ)

ክፍል ሰባት(7)

እትዬ መርየም ለሙና ጥያቄ መልስ መስጠት የቻሉ አይመስልም። ምክንያቱም ሙና እዳለችው እትዬ መርየም ትላንትና የሰሚር ክፍል ውስጥ ነበሩ። ትልቁ መኝታ ቤት ላይ የተከበረ የባል እና ሚስት አልጋ ላይ ሰሚር ወይስ እትዬ መርየም? እጅግ ግራ ስለተጋቡ ነገሩን ማድበስበስ አስበው "አንቺ እ ...ህ ምንድ ነው ምትይው እኔ እኔ እኔ...እኔ አይደለሁም እዛ የነበርኩት። አንቺ አነበርሽ እንዴ የነ..የነበረሽው" ብለው ተንተባተቡ። ሙና ይበልጥ ግራ ተጋባች። ምክንያቱም እትዬ መርየም ሰሚርን ማድረስ የሚችሉ ትልቅ እናት ናቸው ። የተከበሩ እና በእንደዚ አይነት ጉዳይ በፍጹም የማይጠረጠሩ እናት ናቸው። ምናልባት ግን ከሰሚር ጋር ሚያወሩት የሆነ የተደበቀ ነገር ይኖራቸው ይሁን ብላ በጣም ሰጋች። ምክንያት ሙና ሰሚርን ወዳዋለችና።

ሙና ዛሬ የሰሚርን መምጣት ምጠብቀው አንዳች ነገር ለመግለፅ ነው። ምናልባትም ውስጧ ላይ ሚሰማትን እጅግ ሀያል ነበልባል በሀዋ ላይ ያላትን ቅናት የመጨረሻ የምታደርግበትን ታላቅ ነገር .. ምናልባት ግን ከሰሚር ጋር የሚያወሩት የሆነ የተደበቀ ነገር ይኖራቸው ብላ በጣም ሰጋች። ምክንያት ሙና ሰሚርን ወዳዋለችና። ሙና ዛሬ የሰሚርን መምጣት ምጠብቀው አንዳች ነገር ለመግለፅ ነው ። ምናልባትም ውስጧ
ላይ የሚሰማትን እጅግ ሀያል ነበልባል በሀዋ ላይ ያላትን ቅናት የመጨረሻ የምታደርግበትን ታላቅ ነገር ..ለሰሚር ዱብዳ ይሁን መልካም ዜና ብቻ ለሰሚር መንገር ትፈልጋለች ።ለዚህም ይመስላል ምናልባት እትዬ መርየም እና ሰሚር ሲያወሩ የነበሩት እቅዴን የሚያበላሽብኝ ነገር ይሁን እንዴ ብላ የሰጋችው።

እትዬ መርየም ሰሚርን አብዝተው ይወዱታል። እሱ እጅግ ወንዳወንድ ነው። ልዩ ወንድ ነው ።በጣም ጀግና ወንድ ነው ።እንደ እናት ሳይሆን ልክ እንደ እህት ልክ እንደ ሚስት ሆነው ያሞካሹታል። ሙና ግን አንድ ነገር ማረግ እንዳለባት አምናለች። በሀሳቧ የሚስማማ ከቤት ውስጥ ብዙ ድምፅ የሚሰጣትን ሠው ካገኘች ነገሩ ወደሷ ይቀለበሳል። ምናልባት የመውደድ እና የእኩይ ተግባሯ የክፉ ሀሳብ ሆነ ነገር እንጂ ሰሚር በምን አቅሙ በምን ልቡ በምንስ አይምሮ በምን ጭንቅላቱ ሀዋን የመሰለችዋን ሚስቱን የልጆቹን እናት እረስቶ ቅልብልባን ሙና እንዴት ወደልቡ ያስገታል? እንዴትስ ሊቀበላት ይችላል? ሞኝነት እና ፍቅር አውሯት በቀላሉ ወደ እሷ ምታመጣው መሰላት እንጂ ነገሩስ ሚገፋ አይደለም ።ሙና አንድ ነገር ማረግ እንዳለባት ያመነችው እቤት ውስጥ ካሉ ሶስት ሰዎች መካከል አብላጫውን ድምፅ ለኔ ይደግፉ በማለት ነው። ግን ሱመያ እና ሀሊድ በሀሳባ ቢስማሙ እንኳን ህፃናት ስለሆኑ ሀሳባቸው ብዙም አይደለም ።እትዬ መርይም ግን በዚ ሀሳብ ቢስማሙ ነገሮች ይሰምራሉ። እሳቸው ሰሚርን ማሳመን ይችላሉ። ሰሚርም እሳቸውን ያከብራል። ሀሳባቸውን ሳያወዳድር ይቀበለዋል። ግና ሰሚርን ሰሚርን የማሳመን ያህል ከባድ የሆነውትልቁ ፈተና እትዬ መርየም በዚ ትልቅ ማንነታቸው በቁም ነገረኛነታቸው እና በእናትነት አንጀት እንዴገው አርገው በዚ ሀሳብ ተስማምተው ሰሚርን ለማሳመን እሺ ይሉ ይሁን? የሙና ትልቁ ፈተና ነው ።

ግን አንድ ነገር ይዛለች ለእትዬ መርየም በጠየቀቻቸው ጥያቄ መፍራትና መደናበራቸውን ስለወቀች ምናልባትም ለሀሊድ፣ለሱመያ እና ለሀዋ ነግርብሻለው እኔ ባልኩሽ ሀሳብ ማትስማሚ ከሆነ የእናትነት ወግሽን ታጪዋለሽ። መጥፎ ነገር ተመልክቻለው:: ብላ እትዬ መርየምን ማሳመን ትችል እንደሆን ለመሞከር ጉሮሮዋን ጠራረገች። ይሄን ጊዜ እትዬ መርየም ከንግግራ ቀደም ብለው "እ..ዛሬ ለሰሚር ሁሉንም ነገር መንገር አለብን። በቃ ማወቅ አለበት።" አሏት። ይሄኔ ሙና ግራ ተጋባች። ይህ ነገር ለሰሚር ከተነገረው በሀላ በትካዜ እና በጭንቀት ውስጥ ባለበት ሁኔታ የኔ ወደሱ መምጣት ብስራት ይሆንልኛል? ወይስ በጭንቀቱ ላይ ሌላ ጭንቀት? ሙና ግራ ተጋባች። ግን እራሳን ትጠይቃለች።"እኔ ሰሚርን ለምን ወደድኩት? ለምን ተመኘሁት? እሱ እኮ የእህቴ ባል ነው ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ሰሚርን መመኘቴ የጤና ነው? "እራሳን ትጠይቃለች። ግን ይህ እኩይ ተግባሯን ከመፈፀም ወደሀላ እንደማትል ልቧ አስረግጦ ነግሯቷል። ስለዚህ ዛሬ ሰሚር ከሁለቱ ዱብዳ አንዱን ይሰማል። ወይ ያቺ ውድ እና ልእልቱ የሆነችውን ሀዋን እቤት ውስጥ አለመኖሯን የደረሰችበትን እንደማያቁ የሚሰማው መርዶ..አልያም እኔ ያንተ የእጮኛህ ኧረ የምን እጮኛህ የውዷ ሚስትህ የሚስትህም አደለም የልጆችህ እናት የሷ እህት የሆንኩት ሙና አንተን ወድጄሀለው። እፈልግሀለው። ላገባህም እመኛለው። ከሁለቱ ዱብዳዎች ሰሚር ዛሬ ምሽት አንዱን የግድ ይሰማል።

አሁን ሰአት መሽቷል። ሰሚር ሚመጣበት ሰአት ደርሷል። ሁሉም በየራሳቸው ፊና ሆነው ዛሬ ሚናገሩትን አስበዋል። ምናልባት እነሱ ማሰማት ያሰቡት የሀዋን አለመኖር ከሆነ ሀላፊነቱ የእትዬ መርየም ነው። በዛ ፋንታ ለሱ ያላትን ስሜት የምትገልፅበት ከሆነ ደሞ ሀላፊነቱ የሙና ነው ። ምግብ አቀራርበው እራት ለመብላት እየዳዱ ከጥቂት ሰከንዶች በሀላ ሰሚር በሩን ከፍቶ ገባ። መልካም ሰላምታ ከሰጣቸው በሀላ በድካም መንፈስ አረፍ አለ። ምግቡን ሲመለከት ብዙም ለመብላት ፍላጎት እንደልለው ውስጡ ስለነገረው ምናልባት የድካም ይሆናል ብሎ በማሰብ ወደ ባጆ ቤት አቀና።" እስከዛ ተመገቡ ሻወር ወስጄ እመለሳለው። ትንሽ ድካምም ስላለብኝ ቀለል ይለኛል። "አለ። የሱ ሻውር መውሰድ ለነሱ መልካም አጋጣሚ ነው። ሰሚርን ስላዩት ማን እንደሚነግረው ይወያያሉ። ግና ሳያስቡት ድምፃቸው መጮህ ጀመረ። አንቺ ንገሪው አንተ ንገራት አንቺ ንገሪው እራስሽ ንገሪው አንተ ንገራት በዚህ ንትርክ ውስት ሰሚር መስማት የሌለበትን ሰማ። ማወቅ የሌለበትን አወቀ። ድንገት በመከራከር ላይ ሳሉ ፎጣ እንደ ጠቀለለ ወደ ሳሎን ብቅ አለ። በድንጋጤ እና በፍርሀት እጁ እየተንቀጠቀጠ እየተመለከታቸው " አ. አ አል...አል አልሰማሁም። ማለት ም ን ም አልሰማሁም። እ እንዴ ኧረ ብሰማ እራሱ አልገባኝም። ምንድነው?" ብሎ ጠየቀ።

ሰሚር ከበር ሲገባ ዛሬም ሀዋ ባለመኖሯ ውስጡ እንደደበረው ያስታውቅ ነበር። ግና እነሱን ላለማስከፋት ወይም ደሞ ያለችበት ሁኔታ መልካም አገልግሎት ላይ ነችና ክፉ ሰው ላለመሆን ሲል በዝምታ ተቀብሎት ነበረ ። ግን ሀዋ የለችም የሀዋን መሞት ሀዋ እኮ ጠፍታለች ። የሚሉት ድምፆችን ደጋግሞ ስለሰማ የሰማውን ማመን አልቻለም። ለዚህም እየተርበተበተ ቅልጭ ባለ አማርኛ እንዲያስረዱት እንዳልገባው ሆኖ ጠየቃቸው። ይሄኔ ምንም ንግግር ሳይተነፍሱ ሁኔታውን ተረዳ። ምክንያቱም የሀሊድ አይኖች እንባ አዘሉ። ማዘል ብቻ አይደለም። ሀሊድ ሳያስበው እንባው እየዥጎደጎደ በግንጮቹ መሀል ሲወርድ ሰሚር የተባለው እውነት እንደሆነ ገባውና በቀኝ እጁ እራሱን ደግፎ በግራ እጁ ልቡን ጨምቆ በሲቄ ስሜት እየተብከነከነ እራሱን ስቶ ወደቀ።



ክፍል ስምንት ይቀጥላል ....

Https://t.me/halal_couples


😍😘😘
@halal_couples


"ሀዋን ማን ገደላት"
( ✍ አብዲ ኢኽላስ)

ክፍል ስድስት (6)

ኻሊድ ድንገት ሳያስበው በሰሚር መምጣት ምክንያት ፖሊስ ብሎ ተነፈሰ። ይሄኔ ሰሚር በጣም ግራ ትጋብቶ በማለት ጥያቄ አቀረበለት።ይሄን ግዜ ኻሊድ ተደናግጦ ብሎ ነገሩን አድበሰበሰው። ይሄኔ ሰሚር ነገሮችን አላስተዋለምና ቀለል አድርጎ ብሎ ተሰናብቶት ወጣ። ኻሊድ አይተንፍሱ መተንፈስ እየተነፈሰ በዛ ልጅ አቅሙ በዛ ጨቅላነቱ በማያውቀው ጭራሽ በማያገባው ሁኔታ እናቱ መጥፋቷ ሳያንስ በነገሮች በጣም ተስቃየ። እጅጉን የተጨነቀው ኻሊድ በሩጫ ወደ እቤት ገባ።

እትዬ መርየም ብቻቸውን ተቀምጠው ሀሳብ አስምጧቸዋል። እያሰቡ ያሉት ስለ ሙና ነው። ሙና ትላንት ምሽት ሰሚር ክፍል ምን ፈልጋ መጣች? ለምን ነበር የመጣችው? ምን አልባት ከውስጥ ሆኜ ዝም ብላት ምን ትልነበር ብለው ግራ ይጋባሉ። መርየም የሙና እናት ናቸው ለሀዋ ግን የእንጀራ እናት የትዬ መርየም ያውድ ባሏ አቶ የሱፍ ዛሬ በህይወት የሉም። አቶ ዩሱፍ መርየምን ከማግባታቸው በፊት የሀዋን እናት አግብተው ነበር። ከሀዋ እናት ሀዋን እንደወለዱ እናትየው በምጥ ምክንያት በፈሰሳት ከፍተኛ ደም በዛው አረፈች። ከሆስፒታል ገና ሳትወጣ የሞተችው የሀዋ እናት እጅግ መልከ መልካም ሴት እንደነበረች አቶ ዩሱፍ ይተርካሉ። ሁሌም ቢሆን ስለሷ መልካምነት አውርተው የማይጨርሱት አቶ ዩሱፍ እትዬ መርየምን እንዳበሳጩ ነው። እትዬ መርየም እጅግ በጣም የሚከፋቸውና ሲያስታውሱት እንኳን የሚገርማቸው አቶ ዩሱፍ በሞት እና በህይወት መሀል ጣር ላይ ሆነው እንኳን ስለሀዋ እናት ማድነቃቸውና ማዳነቃቸውን አለመተዋቸው ነው።

.....እንዲህ ሲሉም ያስታውሱታል። አቶ ዩሱፍ ከፍተኛ ህመም አሟቸው የአልጋ ቁራኛ ሆነው ለሞት የዳረጋቸውን በሽታ እየተፋፈጉ በነበረበት በዚያ ግዜ ስብርብር ባለችና በምጣፍጥ አንደበታቸው እንዲህ ይሉ ነበር። > ይህ ቃል ከትዬ መርየም አእምሮ ውስጥ አንድም ቀን ወጥቶ አያውቅም ነበር። ሁሌም እትዬ መርየም ለምን ይሆን ዩሰፍ የሀዋን እናት እንዲ አብዝቶ ሚወደው? እኔ ቆይ ምን አጉድዬበት ነው? እይሉ ይጠይቃሉ። አቶ ዩሱፍ የሀውን እናት ካገቡ በኋላ ሀዋን ብቻ ወለዱ ከዛም ሀዋን በማሳደግ ላይ ሆነው ከ እትዬ መርየም ጋ ተዋወቁ። ከእሳቸው ጋርም ልክ እንደ ሀዋ እናት የወለዱት አንዲት ልጅ እሷም ሙናን ብቻ ነበር። ነገር ግን እትዬ መርየም ከዩሰፍ ጋ ከመጋባታቸው በፊት ገና በትዳር ላይ ሳይጣመሩ አንድ ልጅ ነበራቸው። ይህ ልጃቸው ገና በልጅነቱ ብዙ እየተስቃየባቸውና ሊያሳድጉበት ወደማይችሉት ደረጃ ሲመጣ ለማደጎ ስጡት።

እትዬ መርየም ይህ ልጃቸው ከአመታት ለማግኘት ቢፈልጉት እንኳን ሊያገኙት አልቻሉም። የማደጎ አስተዳዳሪዎች ልጁ ከፍተኛ የሆነ ጭንቅላት ስለነበረው ስኮላርሺፕ (የውጪ የትምህርት እድል) አጋጥሞት መሄዱን ነገሯቸው። በዚህም ይመስላል እትዬ መርየም ወንድ ልጅ አብዝተው ሚወዱት...በዚህም ለሰሚር ልባቸው ሚከፈተው ሁልግዜም ይሉታል። ሙና በዚህ ትቀናለች። ምክንያቱም እትዬ መርየም ሙናን ብዙ ግዜ አያሞካሿትም ብዙ ግዜ ይሰድቧታል...ይናገሯታል..አንቺ አታውቂም ታጠፊያለሽ ይሏታል። ነገር ግን የሩቅ ልጅ የሆነውን ሰሚርን ሲያዳንቁ ታስተውላለች።

ሀዋ አባቷን አብዝታ ትወድ የነበረች ለአባቷ ያላት ፍቅር በቃላት የማይገለፅ ነበር። አባቷ ሲሞቱ በወጣትነቷ ከ አንድም ሁለት ግዜ እራሷን ለማጥፋት ሞክራለች። ነገር ግን አዲሱ ባሏ ሰሚር ከዚህ ድርጊቷ እንድትቆጠብ ነገሮችን ትታ ወደነበረችበት እንድትመለስ ሂወቷን መልሳ እንድትኖር ብዙ እጅግ ብዙ ረድቷታል። ለዚህም ነው አብዝታ የምትወደው....ሰሚር እና ሀዋ የተገናኙት እጅግ በሚያስገርም በሚይስደንቅ ድራማ በመሰለ አጋጣሚ ነውና ሁሌም ሁለቱ ለግንኙነታቸው ልዩ ቦታ አላቸው። ሰሚር እና ሀዋ የትገናኙት ድንገት በአንድ ምሽት ሰሚር መኪና እየነዳ በፍጥነት እያሽከረከረ ድንገት ሀዋ ትገባበታለች...ሳያስበው ክፉኝ ገጭቷት ይሄዳል። ትንሽ እንደራቀ ሰአቱ መምሸቱን ሰው ሊደርስላት እንደማይችልና በጣም ቆንጆ ለጋ ወጣት አሆኗን ሲያውቅ ብዙ ሂወት የሚጠብቃትን ይቺን ልጅ አበላሸው ብሎ ራሱን ወቀሰ። ትንሽ እንደተጓዘም አእምሮ ከለከለውና መኪናውን አንድ ዳር አቁሞ ልክ እንደ እግረኛ ገጭቷት የሄደ ሳይሆን ድንገት መንገድ ላይ እንዳገኛት መልካም ሰው አርጎ እራሱን ወደ ሆስፒታል ይዟት እሮጠ። ድንገት መኪና ገጭቷት መንገድ ላይ ወድቃ ነው ያገኘኋት ብሎ ዶክተሮቹን አሳመነ። በዚህም በፍጥነት ህክምና ተደረገላት ሀዋ ለቀናት እራሷን ስታ ሳትነቃ ከሆስፒታል ቆየች።

ሰሚር ስራውን ፈቶ እቤቱን ጥሎ እሷን ማስታመሙን ተያያዘው ለቀናት በቆየው ህክምና እየተመላለሰ በእጅጉ ተንከባከባት በልዩ እንክብካቤ አጠገቧ ሆኖ ማስታመሙን ተያይዞት ሳለ እራሷን መሳቷን ተገን አድርጎ ሁሌም ቢሆን በጆሮዋ አንድ ነገር ሹክ ይላት ነበር። እያለ ጆሮዋ ላይ ያሾካሹካል። ነገር ግን ሀዋ እራሷን ስታ የማትሰም ይምሰለው እንጂ አካሏን ማቀሳቀስ አይኗን መግለጥ አንገቷን ማዟዟር ይሳናት እንጂ ጆሮዎቿ ግን እያንዳንዱን ቃላት መስማት ይችላሉ። ሀዋ እኮ እጅግ በጣም መልካም የዋህ ሴት ናት ገና ከታመመችበት ሳትነቃ በጆሮዋ በምትሰማው ገና መልኩን እንኲን ሳታየው እዛው ነበር ይቅር ያለችው። እዛው ነበር የወደደችው።እዛው ነው ለህይወቷ ያጨችው።

አቶ ዩሱፍ ለሀዋ እና ለሙና ቀድሞ ለሚያገባ ሰው የንብረቴን ሰባ አምስት ፐርሰት አወርሰዋለሁ ትልቁን ንብረት ይወስዳል በማለታቸው ሁለቱም የባል ፍልጋ ላይ ነበሩ። የሚያፈቅሩትን የሂወታቸው ጀግና እያፋለጉ የነበሩት ሁለቱ ሴቶች ሀዋ የቀደመች ይመስላል። ይህን ሁሉ ሀሳብ በእዝነ ህሊናቸው የሚያመላልሱት እትዬ መርየም ትክዝ ብለው ስለ ድሮ በማሰብ ላይ ስሉ ድንገት ሙና አጠገባቸው ቆማ ከ ሀሳብ አባነነቻቸው። ፊት ለፊታቸው እንደ ጅብራ ተገትራ ያስደነገጣቸውን ጥያቄ ጠየቀቻቸው። ብላ ጠየቀች እውነትም ሙና ምናልባት ትልቁ መኝታ ቤት የሀዋ እና የሰሚር መኝታ ቤት ነበር የሄደችውና እዛ እትዬ መርየም ገብተው ሰሚር ወጥቶ ነው? ወይንስ እቤት ተቀያይረው ነው? ወይንስ እሱ ውስጥ ነበር? ለረጅም ደቂቃ ሙና ተመስጣበትና ተጨንቃበት የነበረው ሀሳብ ነው። ጥያቄውን ስታቀርብ እትዬ መርየም ደንገጥ አሉ።


ይቀጥላል......


Good morning members❤️😍


Репост из: كيف حيتن شبب
የፎዚያ መልክት:
ፎዚያ እባላለው፣ ሁለት ልጆች አሉኝ፣ 26 አመቴ ነው
ይህንን መልክቴን ለሁሉም ጓደኞቻቹ በስፋት እንድታሰራጬልኝ እንደ አንድ
ሙስሊም እጠይቃቹሀለው!
ዱዐ እንድታደርጉልኝ እጠይቃቹሀለው ምክንያቱም የCancer በሽተኛ
ሆኛለው፤ አላህን የምትወዱት ከሆነ ለሁሉም page መልክቴን አድርሱልኝ፤
በሀቅ የሚገዙት አምላክ የለም ከሙሀመድ/ሰዐወ/ ጌታ ውጪ እሱም
የአላህ መልክተኛ ነው!
በአላህ እጠይቃቹሀለው በሁሉም group አሰራጭታቹ ዱዐ እንድታረጉልኝ፤
አላህ እንዲፈውሰኝ፣ እንዲአዝንልኝ ዱዐ አርጉልኝ!!!


"ሀዋን ማን ገደላት"
( ✍ አብዲ ኢኽላስ)

ክፍል አምስት (5)

እሁን ከጠዋቱ 3:30 ሆኗል። ሁሉም ከጠረቤዛ ተቀምጠው ቁርስ በመቀማመስ ላይ ይገኛሉ። እትዬ መርየም ማታ ሙና ባደረገችው ድርጊት እጅግ መበሳጨታቸውን እይታቸው ያሳብቃል። ነገር ግን ስሜታቸውንና የተፈጠረውን ማንም እንዲያውቅ ስላልፈለጉ ስሜታቸውን ገታ ንግግራቸውንም ቆጠብ አርገውታል። ምግቡን በመቃመስ ላይ ሳሉ እትዬ መርየም ምን አልባት ሁኔታውን ለሰሚር ቢነግሩት ምን ሊፈጠር እንደሚችል ውስጣቸው ቢያውቅም እንኳን ሁኔታዎች ከተቀየሩ ብለው ነገሮችን ለመገመት የጥርጣሬ መንፈስ በሚመስል ሁኔታ አንዳንድ ነገሮችን ወደሰሚር ለመሰዘር ሞከሩ።

የመጀመሪያ ጨዋታቸውንም እንዲህ በማለት ጀመሩ። ብለው ጠየቁት። ሰሚር ግን መልስ መስጠት አልፈለገም። ፊቱ ጥቀርሻ ሲመስል አይኖቹ ሲቀሉ እጅጉን በጣም ሲበሳጭና የማይሆን ስሜት ውስጥ ሲገባ ያሳብቃል። ምክንያቱም እትዬ መርየም እያሉ ያሉት እኔ እና አንተ ለሀዋ የስጋ ዝምድና የለንም ትናንሾቹ ልጆችና ሙና ግን ከሀዋ ጋ በስጋ ዝምድናም ጨምር ይቆራኛሉ እና አንተ እና እኔ ይበልጥ አንገባም ይበልጥም አንጎዳም እያሉ እንደሆነ በደንብ ገብቶታል። ነገር ግን እጅጉን ስለሚያከብራቸው እና ስለሚፈራቸው ቃል መተንፈስ አልፈለገም። ምግቡ ተበልቶ ያለቀውን ሰሀን በጣቱ እየጠረገ ለመላስ ሞከረ።

ይሄኔ ወሬ አዳኟ ንግግር የማያመልጣት ሙና ድንገት ጣልቃ ገብታ አለች። ብዙም በማይማርክ አነጋገር ምክንያቱም እየተወራ ያለው ለሀዋ ማን ስጦታ ይስጣት የሚል ሳይሆን ሀዋ አንድ ነገር ብትሆን ማን ክፉኛ ይጎዳል የሚል ከባድ ርዕስ ነውና። ሰሚር ምንም አይነት መልስ አልሰጠም። በልስ ያልሰጠበት ምክንያት ለ እትዬ መርየም በእጅጉኑ ገብቷቸዋል። ምክንያቱም የሀዋ እና የሰሚርን ፍቅር ከሳቸው የበለጠ የሚያውቅ ሰው የለምና ነው። ሀዋ እና ሰሚር እኮ ፍቅራቸው እንኳን ላየው እንኳን ለኖረው ለሰማው እራሱ አጀብ የሚያሰኝ ነው። ለትንሽ ሰከንዶች ድሮ ሀዋ እና ሰሚር እንዴት ይፋቀሩ እንደነበር እስከ ቅርብ ቀናት የሀዋ ደብዛ እስከጠፋበት ግዜ ድረስ የነበራቸውን ያን የሚያስቀና ፍቅራቸውን እትዬ መርየም በአይምሮአቸው መኮምኮም ጀመሩ።

ሰሚር ወደስራ የሚገባው ዘውትር ሁለት ሰአት ላይ ነው። ወደስራ ለመሄድ የሚነሳው አንድ ሰአት ላይ ነው ከእንቅልፉ የሚነቃው ደግሞ አስራ ሁለት ሰአት ላይ ሰሚር እጅግ በጣም ጠንካራ ሰራተኛ ነው።በዚህም ከንቅልፉ ከነቃ በኋላ ሁሉን ጣጣውን ጨራርሶ ቁርሱን በልቶ ልብሱን ለባብሶ ልጆቹን እና ባለቤቱን ተሰናብቶ ሁሉን አድርጎ አንድ ሰአት ላይ ከቤት ይወጣል። ነገር ግን ሁሌም ቢሆን አንድ ነገር መርሳቱ አይቀርም ወይ መነፅሩን ወይ ኮፍያውን ወይ ከረባቱን ወይ ቦርሳውን ብቻ ሞባይሉንም ይሁን አንዳች ነገር ሆን ብሎ አስቀምጦ ይወጣል። ይህን የምታውቀው ሀዋ የረሳውን ነገር ቶሎ አፋልጋ ድንገት ካስቀመጠበት በማግኘት በመስኮት በኩል ብላ ታስቆመውና እየሮጠች ተንደርድራ ሄዳ ትሰጠዋለች። ከሰጠችው በኋላ ምንም ቢመጣ የሚያላቃቸው አይመስልም በጣም ይተቃቀፋሉ። አብረው የነበሩ አብረው ምሽቱን ያሳለፉ ሳይሆን ተነፋፍቀው እንደተገናኙ ሰዎች ተቃቅፈው ለትንሽ ደቂቃ የሚያላቃቸው አጥተው በሀይል ይተቃቀፋሉ።

በዚህ ሁኔታ ትንሽ እንደቆዩ አቅፎ ወደ እቤት ካላስገባት በፍፁም እንደማትለቀው ነግራው ሁሌም እያቀፈ ወደ መኝታ ክፍል ይዟት ይገባል። ነገር ግን አልጋው ላይ ቆይተው ሲጫወቱ ሲላፉ እና ሲሳሳቁ እረጅም ሰአታትን ሳያሳልፉ አሁንም መለያየት ይሳናቸዋል። ይህ ሲሆን አንድ ሰአት የተነሳው ሰሚር ብዙ ሰአታትን አሳልፎ ከሁለት ሰአት ሶስት ሰአት እና ሶስት ተኩል በኋላ ወደስራ ለመሄድ ድንገት ይቆማል። የፍቅር ውሎዋቸው በዚህ አያበቃም። በነሱ ነገድ በነሱ ቤት አብዝቶ መናፈቅ አብዝቶ መውደድ እጅግ አርጎ ማፍቀር እንጂ መኩራት እና ስሜት መቀነስ መቀዛቀዝና መስመሰል ፈፅሞ ቦታ የላቸውም። ለዚህ ይመስላል ሁሌ ቢሮ ሲገባ ምሳ ሰአት እንደደረሰ ሀዋ የቋጠረችለትን ምግብ ካልሆነ ንክች ማያደርገው ይህ ውድ ባሏ ሰሚር ልክ ምሳቃውን ከፍቶ መመገብ ሲጀምር ሁሌም ምግቡ ላይ ጨው ያንሰዋል።

ሰሚር እጅግ በጣም የተካነ ሼፍ ከመሆኑ ባለፈ ምግብን በጣም አጣጥሞ የሚያውቅና ለጥሩ ምግብ እጅ የሚሰጥ ሰው በመሆኑ ጨው ያነሰበት ምግብ እንብዛም አይወድም። ታድያ ገና ምግቡን ከፍቶ አንድ ጎርሶ ምግቡ ጨው እንደሌለው ሲያረጋግጥ ፈገግ ይላል። ለጥቂት ሰከንዶች ውዷ ሚስቱን ሀዋን ያስታውሳል። በዚህም በትንሽ ተመስጦ ሰከንዶች ያልፋሉ። ታድያ ሀዋም እጅግ የፍቅር ተንኮለኛ ነችና ወድያውኑ በር ታንኳኳለች። ልክ እንደ ባለጉዳይ ድምጿን አጎርንና የምትናገረው ሀዋ በሩን አንኳኩታ ትገባለች። ያኔ በቦርሳዋ ውስጥ እሱን ለማየት ሰበብ እንዲሆናት ብቻ ጨው ይዛለት ብዙ ኪሎ ሜትር አቆራርጣ ትመጣለች። ታድያ ይሄን ካደረጉ በኋላ አብራው ትቆያለች አብራው ስራውን ታሰራዋለች። ግን ለሰሚርም ጭምር የሚገርመው አብራው ከቆየችና አብራው ከዋለች በኋላ ከስራው መውጫ ጥቂት ሰአታት ሲቀሩ ደሞ ጥላው ወደ ቤት ብርር... ብላ ትሄዳለች። አብረው መቆየት አብረው መዋል አብሮ መሆን ካለ አብረው ወደ እቤት መሄድ እየቻሉ ቀድማው የምትሄድበት ብቸኛ ምክንያት እቤት ሲገባ ልክ እንደ አዲስ ሰው አመታት እንደተነፋፈቀ አይነት ሰው ቁንጅትጅት ብላ ደሞ በአዲስ ስሜት ትቀበለዋለች። ይሄን ውድ እና ጣፋጭ የፍቅር ታሪክ በእዝነ ህሊናቸው እያመላለሱ ያሉት እትዬ መርየም ድንገት የጊቢው በር ሲንኳኳ ከሀሳባቸው ነቃ አሉ።

ኻሊድ የተንኳኳውን በር ለመክፈት ከሁሉም ቀድሞ በሩጫ ሄደ። ነገር ግን በሩን ሲከፍተው ደንግጦ ቀረ። ያንኳኳው ይህን ጉዳይ በምርመራ የያዘው ኢንስፔክተር ግርማ ነው። ከውስጥ ደሞ ሰሚር ተቀምጧል። ሰሚር ባለበት ሁኔታ ኢንስፔክተር ቢገባ ጉዳዩ እዚ ይፈርጣልና ....ኻሊድ ድንገት ተቅለብልቦ ብሎ መለሰ።ግርማም ብዙ አላንገራገረም በማለት ጥያቄ አቀረበ። ኻሊድም ግርማ ብዙ አላንገራገረም በማለት ቀለል ባለ አማርኛ ተሰናበተው። ኻሊድም በሀይል እየተነፈሰ በሩን ዘጋ። ነገር ግን ድንገት በሩን ዘግቶ ሲቆም ከኋላው ሰሚር ቆሟል። ጠየቀው ኻሊድ ድንጋጤ ላይ ነበርና ያለውን እንኳን ሳያውቀው ድንገት ከአፉ አምልጦ >ብሎ ተነፈሰ።


ይቀጥላል.......

Https://t.me/halal_couples




😍😍😍😍
Halal is more beautiful 👌❣
@halal_couples


"ሀዋን ማን ገደላት"
( ✍ አብዲ ኢክላስ)

ክፍል አራት (4)

......ሁሉም በፍርሀት እና በጭንቀት ቀጥ ብለው እንደቆሙ ይገኛሉ። ከውጪ ያለው ማንኳኳት ግን ደጋግሞ መንኳኳቱን ተያይዞታል። የግቢው በር በተደጋጋሚ በመንኳኳቱ ግራ የሚገባ ስሜት ውስጥ ገቡ። ምክንያቱም ሰሚር ከሆነ የመጣው የግቢውም ሆነ የሳሎኑ ቁልፍ አለውና ለምን እራሱ ከፍቶ አልገባም ሲሉ እራሳቸውን ይጠይቃሉ። ሰሚር ካልሆነ ደሞ በዚ ምሽት የሚያንኳኳው ምን አልባትም ሀዋ ላይ ክፉ ድርጊት የፈፀመባት ይህ እኩይ ሰው ሊሆን ይችላልና ማን ከመሀከላቸው ከፍቶና ደፍሮ ሊወጣ እንደሚችል ግራ ተጋብተው ይተያያሉ።

በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ከተደጋጋሚ ማንኳኳቶች በኋላ ድንገት የሳሎኑ በር ተከፍቶ አንድ ሰው ብቅ አለ። ያ ባለግርማ ሞገሱ ፊቱ የሚያበራው ውድና ተወዳጁ ሰሚር ድንገት ገባ። እስካሁን ድረስ ቁልፍ እያለው ደጅ ላይ ሆኖ ሲያንኳኳ የነበረው ከሰአታት በፊት ደውሎ በነበረበት ሰአት ያናገረችው ሙና ነበረችና ምን አልባት ዛሬ እቤታቸው መጥተው በነበሩበት ሰአት አይብ ይኖራቸዋልና ድንገት ከፍቼ ብገባባቸው የማይሆን ነገር እንዳልመለከት ሲል ሀያእ አርጎ ነበር። ሰሚር ገና ከደጅ ሲገባ ልክ ሰው ከኤርፖርት እንደሚቀበሉ ነገር ሁሉም ተደርድረው ሲጠብቁት ግር መሰኘቱ አልቀረም። ከዛም ኻሊድ እና ሱመያ ተሯሩጠው አባታቸው ላይ ተጠመጠሙ። ናፍቆታቸውንም እቅፍ እና ሳም አርገው ከትወጡ በኋላ እትዬ መርየምን እና ሙናን አከታትሎ የሚገባቸውን ሰላምታ ስጣቸው። በመቀጠልም ከወንበሩ ቁጭ አለ።

የሰሚር እና የሀዋ ቤት እጅግ ላይን የሚማርክ ውብና ግማሽ ሶፋ እንደዚሁም በግማሽ አረቢያን መጅሊስ በሚያምር ጂብሰን የተቃኘ ውብ ቤት ነው። ሰሚር ለጥቂት ሰከንዶች ብቻ አረፍ እንዳለ ውድያውኑ ተጠባቂውን ጥያቄ አፈፍ አረገው። በማለት ቀልድ የታጀበ ጥያቄ አቀረበ። ይሄን ግዜ ሙና ተቅለብልባ ወድያውኑ ሳታስበው በማለት መለሰች። ሰሚርም ደንገጥ ብሎ በማስከተል በማለት ጠየቃት። ሙናም በማለት መለሰችለት። ነገር ግን ሰሚር ዝም አላለም በማለት ጠየቃት። ይሄን ግዜ ሙና ደንግጣ ዝም ስትል...እትዬ መርየም ጣልቃ ገብተው ብለው መለሱለት።

ይሄኔ ሰሚር እትዬ መርየም እና ሙና ለምን ዛሬ እዚ ቤት እንደመጡ መልስ ያገኘ ይመስል አረፍ አለ። ምክንያቱም ትናንሽ ልጆቹን የሚጠብቁ ሰዎች ስለሚያስፈልጉ ሀዋ እዛ ካደረች የሁለቱ እዚ መምጣት የሚያስገርም አይደለም ብሎ ለራሱ መልስ ሰጠ። ግና ነገሮችን አምኖ ተረጋግቶ እንዲቀመጥ የፈቀዱለት አይመስልም። እይታዎቻቸው፣ ድርጊቶቻቸው እና እርስ በእርስ መተያየታቸው ለሰሚር ከፍተኛ የሆነ የጥርጣሬ በር የሚከፍትለት ቢሆንም ሰሚር ግን መጠራጠር የፈለገ አይመስልም። ይሁን እንጂ የሰሚር አይኖች ውዷን ሀዋን እንደናፈቁ እጅግ በጣም ያሳብቃሉ። እሷን እሷን እየማተረ እንዳለ ልቡ ስለሷ እያሰበ እንዳለ አይኖቹ ልዩ ምስክሮች ናቸው። ይህ ስለሆነም ይመስላል ዛሬ ብዙም መጫወት ሳይፈልግ ድንገት ቀለል ባለ ሰላምታ ብቻ ተሰናብቷቸው ወደ መኝታ ክፍሉ ገብቶ ጥቅልል ብሎ ለመተኛት የተገደደው። የሰሚር መተኛት ሀዋን መናፈቁ ቢገባቸውም እንኳን እነሱ ግን ይሄን አጋጣሚ አስቸኳይ ስብሰባ ለማድረግ እድሉን ተጠቀሙበት። በስብሰባቸውም ዛሬ በሸወዱበት መንገድ ነገ እና ከነገ ወዲያ ሰሚርን ስለማይሸውዱት እንዲያውም ሀዋ ከ አንድ ቀን በላይ እዛ አድራለች ብለው ለቅሶ ቤት ነው ያለችው ብለው መሸውድ እንደማይችሉ ልቦናቸው ስለተረዳ....ያለውን አጋጣሚ በመልካም ተጠቀሙት። በዚህም መፍትሄ ለማበጀት ይበልጡን ተጠጋጉ።

በውይይታቸው ላይም የተለያዩ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን ከተሰነዘሩ ሀሳቦች መሀከል...ምን አልባት ልጅቷ ብቸኛ ስለሆነች ሀዋ ቤተሰቦቿን እያስተናገደች.....አልያም ደግሞ ሟች ክፍለ ሀገር ስለሆነ ቤተሰቦቿ ያሉት ልታስቀብር እዛው ሄዳ....ወይም ደሞ ዛሬ የመጣው ለቀስተኛ በጣም ብዙ ስለሆነ ሀዋ ምንም አይነት መውጫ እና መፈላፈያ ስላላገኘች እዛው ደጋገማ ለማደር ተገዳለች እና የመሳሰሉትን ሀሳቦች......ለስብሰባው ሰነዘሩ። ግን የትኛውም ሀሳብ አመርቂ ሆነው አላገኙም...ምክንያቱም በሰሚር አመለካከት ሀዋ ባሏ ከፊልድ መጥቶ ሰሚር እቤት ድረስ ትገኝቶ እንኳን ሰው ሞተ ብላ እራሷ እንኳን ብትሞት መቃብሩን ፈንቅላ ትመጣለች እንጂ እዛው የምትቀር አይደለችም። ይህን አመለካከቱን አሳምረው ስለሚያውቁ የትኛውም ሀሳብ አላጠገባቸውም። ይህን አየትባባሉ እየተወየዩ እና እየተነታረኩ መፍትሄ ላይ ሳይደርሱ ሁሉም ወደ መኝታቸው አመሩ።

ሁሉም በከፍተኛ እንቅልፍ ተውጠው አለማቸውን እረስተዋል። ነገር ግን አንድ አይን ብቻ እንቅልፍአልወሰደውም። እሷም ሙና....ሙና ዛሬ እንቅልፍ አልወሰዳትም። ምን እንዳሰበች አይታወቅም ቅጥ ያጣ አለባበስ ለብሳ እራሷን አቆነጃጅታ ከክፍሏ ድንገት ወጣች። ከዛም በሩጫ ሄዳ አንድ የመኝታ ቤት በርን በለሆሳስ ማንኳኳት ጀመረች። በንግግሯም ድምጿን እንዳሰሙ ቀንሳ በማለት ድምጾቿን አሰማች። ይህን ግዜ ሰከንዶችም ሳይቆጠትሩ እያንኳኳች የምትገኘው በር ድንገት ተከፈተ። ይሄኔ ያየችውን ሰው ማመን አቅቷት ደርቃ ቀረች። በሩ ከፍተው የወጡት እትዬ መርየም እንጂ ሰሚር አይደለም። መኝታ ቤቱን ተሳስታ ኖሮ ድንገት ሳታስብ የሳቸውን በር አንኳኩታ ነው።


ይቀጥላል........

https://t.me/halal_couples


✨✨✨✨✨✨✨✨✨
✨✨✨✨✨✨✨✨✨
🕌jumea mubarek🕌
✨✨✨✨✨✨✨✨✨
✨✨✨✨✨✨✨✨✨

@halal_couples


Ohhh habibi you make my life brightly✨🌸

@halal_couples


"ሀዋን ማን ገደላት"
( ✍ አብዲ ኢክላስ)

ክፍል ሦስት (3)

....አሁን ከምሽቱ 12 ሰዐት ሆኗል። ሁሉም እጅግ ግራ በተጋባ ስሜት በፍርሀት እና በጭንቀት ተውጠው እርስ በእርስ እየተያዩ ተቀምጠዋል። በአንድ በኩል ሀዋ ሞታለች ብልው እርማቸውን እንዳያወጡ አልያም አልቅሰው ለቀስተኛ እንዳይጠሩ የሀዋ ሬሳ አልተገኘም። አለች ብለውም እንዳያስቡ ሀዋ የት እንዳለች ማወቅ አልቻሉም። ግራ ተጋብተዋል... በሌላ በኩል ሰሚር እየመጣሁ ነው በማለቱ ለሀዋ ያለውን ፍቅር እና አክብሮት ስለሚያውቁ እጅግ በጣም እንደሚጎዳ እንደ ሚደነግጥ እና ህይወቱ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ስላሰቡ በጣም ስግተዋል።

ከሁሉም በላይ ሰሚር ያለበት የልብ ድካም በጣም አስጨንቋቸዋል። ምክንያቱም ከዶክተር የታዘዘለትን መድሀኒት በመውሰድ ላይ የሚገኘው ሰሚር ከፍተኛ የሆነ ደስታም ከፍተኛ የሆነ ሀዘንም ህይወቱን ሊቀማው እንደሚችል ዶክተሩ ነግሮታል። ይህንን መላ ቤተሰቡ በማወቁ ዛሬ ጭንቀታቸውን እጥፍ ድርብ አድርጎታል። ሰሚር ከጥቂት ደቂቃዎች ለኋላ እመጣለሁ ካለ አንድ ሰዐት ቢቆጠርም እሱ እንደማይዋሽ እመጣለው ካለ እንደሚመጣ ስላወቁ እያንዳንዳቸው ሲመጣ የሚዋሹበትን መንገድ የሚሸውዱበትን አልያም እሱን የሚያፅናኑበትን መንገድ በማሰብ ተጠምደው በራሳቸው ሀሳብ ውስጥ እላይ እታች ይባዝናሉ።

ይህ ሁሉ ሲሆን የሙና ስሜት ግን ከሌሎቹ በጣም የተለየ ነው። ከእትዬ መርየም፣ከሱመያ እና ከኻሊድ የሙና ስሜት ቀዝቀዝ ብሏል። ውስጧ ላይ ምን እያሰበች እንዳለ እጅግ ግራ ምታጋባዋ ሙና እንደነሱ ብዙም የፈራች የጨነቃት አትመስልም። እንደውም የምትወደው ባሏ እንደሚመጣ ተነግሯት በጉጉት የምትጠብቅ ሙሽራ መስላ እራሷን እያሰማመረች ትገኛለች። ፈገግታ ከፊቷ ያልተለያት ሙና በጣሙን እሱን የናፈቀች በጣም የምትወ ደው የልጆቿ አባት እየመጣ ያለ እንጂ ሞት የምታረዳው አልያም መጥፎ ዜና የምትነግረው አንድ የእህቷ ባል እየመጣ በጭራሽ አይመስልም። ይህ ሁኔታ ግራ ቢያጋባቸውም እንኳን እሷን ትተው በራሳቸው ሀሳብ ተውጠዋል።

እትዬ መርየም ዛሬ በሙና ስሜት ላለመገረም ሁለት ምክንያት አላቸው። አንደኛው፦ሀዋ እጅግ በጣም ተወዳጅ ስለሆነችና አባታቸውም ከሁለቱ አስበልጦ የሚወደው ሀዋን ስለነበር ሙና በጣም ትቀናለች። ሁለተኛው ደሞ፦ያኔ አቶ ዩሱፍ የሀዋ የሙና አባት ከመሞታቸው ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ብለው ለሁለት ሴት ልጆቻቸው ተናዘዙ። ሁለቱም በራሳቸው መንገድ ባል ለመፈለግ ቢሞክሩም..... ለሙና ሳይሳካላት ሀዋ ቀደመች። ሰሚርን አግብታ ያለውን ንብረት ሰማንያ አምስት በመቶ የወረሰችው ሀዋ የተንደላቀቀ ህይወት እየኖረች እንደሆነ የተረዳችው ሙና እያንዳንዱን ቀን በእህቷ መበለጧ እያብነከነካት ውስጧን እየበላው አመታት ተቆጥረዋል። ዛሬ ግን ቀን ለሙና የወጣላት በሀዋ ላይ የደረሰው ችግር ለሙና ፀሀይ የሆነላት ይመስላል። ምክንያቱም ሀዋ ባለችበት በዚህ ችግር ውስጥ ሙና ለሰሚር የተሻለ ሰው ሆና ለመታየት የምትፈልገውን ከማግኘት ወደኋላ አትልም።ምክንያቱም ሙና ሞገደኛ ስሜት ያላትና ለቤተሰቧ ብዙም ፍቅር የሌላት በራሷ ስሜት ውስጥ የምትኖር ወደክፉ የምታደላ እንስት በመሆኗ ነው።

በአንድ በኩል ኻሊድ እና ሱመያ ሀለቱም በዛ ትንንሽ እጆቻቸው ትቅፍቅፍ ተደታራርገው ፊታቸው ጭር ብሎ በጣም ከፍቷቸው ምንም ሳይተነፍሱ ከ አይናቸው እንባ ይዥጎደጎዳል። ይህን ግዜ እትዬ መርየም ወደ ኻሊድ ጠጋ አሉና አንድ ጥያቄ ጠየቁት በማለት ጥያቄ አቀረቡለት። ይህን ጊዜ ኻሊድ በእንባ በተሞላ ንግግር እንዲህ ሲል መለሰላቸው...ብሎ ንግግሩን ገታ አደረገ። ይህን ግዜ እትዬ መርየም በጣም ለመስማት ቀረብ ብለው..እ..በሌላ በኩል ምን ልጄ?...በማለት ጠየቁት። ኻሊድ ማውራት የፈለገ አይመስልም በአንድ አይኑ ሙናን ተመለከታት። ይሄን ግዜ እትዬ መርየም ነገር የገባቸው ይመስል በማለት መለሱለት። ይሄኔ የትዬ ሀሊድ ጥርጣሬ ልክ ይሁን አይሁን ሳይገባው ግራ በተጋባ ስሜት ልንገራቸው አልንገራቸው ማለት ያዘ። ከዚያምበማለት ቃል ተነፈሰ። ይህን ብሎ እንደጨረሰ ድንገት የጊቢው በር ተንኳኳ ይሄኔ ሁሉም በፍርሀት ከመቀመጫቸው ተነስተው ድንገት ቆም አሉ።

ይቀጥላል.......

Https://t.me/halal_couples


Habibty you are my nesib❤️💜

@halal_couples


🌞ነጋልን ደግሞ ቁርስ ልንበላ ነው☕️😁

✨ #ሸጋ_ቁርስ ✨ #ሸጋ_ቀን ✨

@halal_couples. Join




👨‍👩‍👧ቤተሰብህ የደስታህ ምንጭ ነዉ✨....ሚስትህ🧕 ህይወትህ ልጅህ👧 አለምህ ናት💞

💞እነሱን በመንከባከብ ብልጥ ሁን!!!💞

💞✨💞✨💞✨💞✨💞✨💞✨💞

@halal_couples


😁 ፈገግታ ሱና ነው ፈገግ በሉልኝ 😁

ቤት ቁጭ ብለን ማዘር የሌለ
አስነጠሰች..🤧

#ፋዘር፡ የርሃሙኪላህ

#እኔ፡ 👀👀👀

በድጋሚ በሃይል አስነጠሰች🤧🤧

አሁን #እኔ እና #ፋዘር ወደ ስልክ
መደውያው ሩጫ..🏃‍♂🏃‍♂

"ሄለው ቴሌ!! ማነው እጥጥ ጤና
ጥበቃ በኮሮና የተጠረጠረ
ሰው አለን😂😂😁


@halal_couples


"ሀዋን ማን ገደላት"
( ✍ አብዲ ኢክላስ)

ክፍል ሁለት (2)

ሀዋ ከፍተኛ የይድረሱልኝ ሲቃ እና ጥሪ ብታሰማም ሀሊድ እና ሱመያ ድንገት ሳያስቡት እንቅልፍ ወስዷቸዋልና የሚደርስላት ሳታገኝ በሲቃ ታፍና ረጅም ሰአታትን ቆየች። ነገር ግን ምን እንደተፈጠረ ሳይታወቅ ምሽቱ ነግቶ ጨለማው ለፀሀይ ቦታ ለቀቀ። ጠዋት ሀሊድ ከተኛበት ቦታ ሲነሳ ቁርዐኑን እየቀራ ባለበት አንገቱን ወደ ቀኝ ሰብሮ ሳያስበው እንቅልፍ ሸለብ አርጎት በዛው ነውና የተኛው አንገቱን በጣም አሞት ነቃ። ልክ እንደነቃ የተኛበትን ሁኔታ ሲመለከት ማታ የነበረውን ሁሉ አስታወሰ ወድያው እናቱን ለመፈለግ ወደሳሎን እሮጠ።

ወደሳሎን እሮጦ ሀዋ...ሀዋ....እያለ እየጮህ በየእቤቱ በየኩሽናው ቢፈልጋት ሀዋን የበላት ጅብ አልጮህ አለ። ነገር ግን ሱመያ ከተኛችበት መኝታ ቀስቅሶ መረበሽ ስላልፈለገ በእርጋታ ነገሮችን ማሰብ ጀመረ። የመጀመሪያ ስራው ሊሆን የሚችለው ሀዋ ጋ ስልክ መደወል ነበርና የሞባይል ስልኩን አውጥቶ የሀዋን ቁጥር መታ። ስልኩን ደውሎ ገና ወደ ጆሮው እንዳስጠጋ ግቢ ውስጥ አንድ ስልክ በጣም ሲጮህ ሰማው ይህ ስልክ የሀዋ መሆኑን በጥሪው ያውቀዋል። ሀሊድ እየተንደረደረ ወጥቶ ከግቢ ውስጥ የ ሀዋ ስልክ ወደ ሚጮህበት አቅጣጫ ሲሄድ የሀዋ ስልክ መሬት ወድቆ በደም ተለውሶ ተስብሮ አገኘው። ይሄን ግዜ ሀሊድ የሚሆነውን አጣ የያዘውን ስልክ ድንገት ሳያስበው ለቀቀው ብርክ ብርክ አለው እጁ መንታቀጥቀጥ ጀመረ የሚናገረውን አጥቶ ከመሬት ቁጭ አለ።

ይሄን ግዜ የሳሎኑ በር ተከፍቶ ሱመያ ከ እንቅልፏ ገና እንደነቃች አይኗን እያሻሸች ወደ ሀሊድ መጥታ የሆነውን ሁሉ ተመለከተች። ይህን ግዜም ጠየቀችው ብላ ሀሊድን ጠየቀችው። ሀሊድ የሚመልስላት መልስ ቢያጣ ከአይኖቹ እንባ እየፈሰሰ ሱመያን እቅፍ አርጎ ወደ ደረቱ አስጠጋት ለማባበል ቢሞክርም እየሸወዳት እንደሆነ ስለተረዳች ሱመያ ሀሊድን አጥብቃ ጠየቀችው። ይሄን ግዜ እናታቸው የሄደችበትን እሱም እንደማያውቅ እሱም ግራ እንደገባውና ቤተሰቦቻቸው ጋ መደውል እንዳለባቸው ተስማምተው ቤተሰቦቻቸው ጋ ደወሉ። ወድያው የሀዋ እንጀራ እናት ጋ ስልክ ጠራ። ሀሊድ ለሀዋ እንጀራ እናት በጣም ለምትወዳቸው ውዷ እናትየው ስልክ እንደደወለ እናትየው እትዬ መርየም በጣም ተደናግጠው ከ አንዲት ልጃቸው ከሙና ጋ እየተሯሯጡ መጡ።

ሙና የሀዋ እኩያ ስትሆን በአባት ብቻ የምትገጥማት እህቷ ነች። እንጀራ እናትየውም ለሙና ወላጅ እናት ናቸው። ይሄን ግዜ ሙና እና እናትየው ተሯሩጠው ወደ እቤት ገቡ እንደገቡ ያለውን ሁኔታ ሲያዩ በጣም ደነገጡ። ሙና ለውትሮ ከሀዋ ጋ ምትስማማ ትምሰል እንጂ በጣም እልህ ያለባት በሀዋ የምትቀና በሀዋ ቁንጅና ሰዎች ለሀዋ በሚስጧት መውደድና እያንዳንዱ ነገሮቿ የሚያስቀናት እኩያማች እህቷ ነች። ሀዋ እና ሙና መንትያ የሚመሳሰሉ ሁለቱም የሚያምሩ ናቸው ።

እትዬ መርየም ወደ እቤት እንደገቡ ሀሊድን እቅፍ አድርገው የተፈጠረውን ሁሉ ጠየቁት። እሱም አንድ በአንድ ከምሽት ጀምሮ ሀዋ ከነበረችብት ስሜት አንድ ሳያስቀር እያንዳንዱን በዝርዝር አስረዳቸው። ይሄን ግዜ እትዬ መርየም እጅግ ግራ ተጋቡ ብለው እንባቸውን ለቀቁት። ይሄን ግዜ ሙና በእናትየው ለቅሶ ተናዳ ብላ በንዴት እናትየው ላይ ጮህች ነገር ግን እትዬ መርየም የሙናን ነገር ያውቁታልና ምንም ሳይመልሱላት ስልካቸውን አውጥተው ወደ ፖሊስ ጋ ደወሉ።

......ከሰአታት በኋላ ግቢውን ፖሊስ ወረረው እያንዳንዱን ቦታ ፎቶ ቢያነሳ መረጃ ቢያፋልግም እንኳን ሀዋ የገባችበትን ያገኘ ያያት እንኳን እኔ አለሁ የሚል አንድም ሰው አልተገኘ አንድም ጅብ አልጮህም። በዚ ሁኔታ ቀኑ ወደ መምሽቱ ተቃርቧል በዚህ ወቅት ድንገት የ ሀዋ ስልክ ጠራ ሁሉም ወደ ሀዋ ስልክ አይናቸውን ሲያደርጉ ስልኩ ላይ #የኔ_ውድ_ባል_ሰሚር ይላል ይሄን ግዜ ሁሉም በጣም ፈሩ እጃቸው ተብረከረከ ከመሀከላቸው ደፍሮ ስልኩን የሚያነሳ አንድ ሰው ጠፋ።

ሰሚር እጅግ መልከ መልካም የዋህ በጣም ተውዳጅ የቀይ ዳማ ፊት ያለው እና ባለሉጫ ፀጉር ረዘም ያለ ወጣት በጣም ሲበዛ ሀዋን የሚውድ በፍቅራቸው የሚቀናባቸው ለባለቤቱ ትገቢውን ግዜ መስጠት የሚችል ልጆቹን እና ቤተሰቡን የሚወድ እጅግ በጣም ተወዳጅ ወንድ ነው። ሰሚር ስልኩን ሲደውል ሙና ድንገት ተቅለብልባ ስልኩን አነሳችው ወድያውኑ አለች በዚህ ሁኔታዋ ሁሉም ግራ ተጋቡ። እትዬ መርየም በቆሪጥ ወደ ጎን ትመልክተዋት አፋቸውን እንደማሽሟጠጥ አሉ። ይህ የሆነበት ምክንያት ሙና ለሰሚር ያላት ስሜት እጅግ ግራ ስለሚያጋባና በጣም በሀዋ ስለምትቀናባት ከእህቷ ቀምታ የምትወስድ ስለምትመስል እጅግ ስለምትወደው ነው።

በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሰሚር አንድ ጥያቄ ጠየቀ ሲል ሙና ተቅለብልባ ቀለል ባለ ስሜት ብላ ቀለል ባለ ስሜት መለሰችለት። ነገር ግን የሰሚር ምላሽ እንደ ሙና ቀላል አልነበረም ብሎ ቆሌዋን ገፈፈው ይህን ግዜ ሙና ደንግጣ ስልኩን ከ እጇ ላይ ለቀቀችው።

ይቀጥላል.......

👉 https://t.me/halal_couples


ለአላህ ብላቹ ሳታነቡ እንዳታልፉ

ጂብሪል ዐ ሰ አንድ ቀን ያለወትሮው ረሱል ሰዐወ ዘንድ ፊቱ ጠቁሮ
መጣ።
ረሱል ሰ ዐ ወ በዚህ ሁኔታ ሲያዩት ግዜ፦"አንት ጅብሪል ምነው ፊትህ
እኮ ተቀየሯል?" አሉት። ጅብሪልም፦"አንተ ሙሀመድ አሁን የመጣሁት
ሰዐት የጀሀነም አቀጣጣዮችን አላህ እንዲያቀጣጥሏት ባዘዛቸው ሰዐት
ነው። ጀሀነም እውነት መሆኗን ላወቀ፣እሳትም እውነት መሆኗን
ላወቀ፣የቀብር ቅጣት እውነት መሆኑን ላወቀ፣የአላህ ቅጣት ትልቅ
መሆኑን ላመነ ሰው ከሷ መትረፉን ሳያረጋግጥ መረጋጋት የለባትም"
ብሎ መለሰላቸው።
ረሱል ሰ ዐ ወ፦"አንተ ጅብሪል እስቲ ስለጀሀነም ንገረኝ" አሉት።
ጅብሪልም ዐ ሰ፦"አዎ አላህ ጀሀነምን 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ቀይ
እስክትሆን ድረስ
ከዚያም 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ነጭ እስክትሆን ድረስ ከዚያም
1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ጥቁር እስክትሆን ድረስ.....አሁን /ጀሀነም
ጥቁር ጨለማማ ናት።ነበልባሏ እና ፍሟ አይጠፋም
ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ. የመርፌ ቀዳዳ
ያህል ጀሀነም ብትከፈት ዱንያ ላይ ያለ ነገር ሁሉ ከሙቀቷ ብዛት
ይቃጠል ነበር።
ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ.ከጀሀነም ሰዎች
ልብስ አንዷ በሰማይና በምድር መሀከል ብትንጠለጠል ከግማቱ የተነሳ
ምድር ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ ይሞት ነበር። ያ በዕውነት ነቢይ አድርጎ
በላከህ አላህ እምላለሁ...አላህ ቁርአን ላይ የጠቀሰው የጀሀነም
ሰንሰለት አንዷ እንኳን በተራራ ላይ ብትቀመጥ ተራራው እስከ ሰባተኛው
መሬት ድረስ ይቀልጣል።
ያ በዕውነት በላከህ አላህ እምላለሁ. በምዕራብ አንድ ሰውዬ በጀሀነም
ቢቀጣ ኖሮ በምስራቅ ያለው ሰው ከሙቀቷ ብዛት ይቃጠል ነበር።
ሙቀቷ ጠንካራ ነው፣ጥልቀቷ እሩቅ/ስምጥ ነው፣ጌጧ ብረት
ነው፣መጠጧም የፈላ ውሀ እና ምግል ሲሆን፣ልብሷም ከእሳት የተለካ
ነው።
7 በሮች አሏት።
ለያንዳንዱ በር የተለያዩ በሮችም አሏቸው ለሴቶችም ለወንዶችም" ብሎ
መለሰላቸው።
ረሱልም ሰዐወ፦"እኛ እንደምንጠቀመው አይነት በር ነው?" ብለው
ሲጠይቁት
ጅብሪልም ዐ ሰ፦" አይ አይደለም ከላይ ወደ ታች የተደረደረ በር
ነው።ከአንደኛው በር ወደ ሌላኛው በር ያለው ርቀት 70 አመት
ያስኬዳል።
እያንዳንዱ በር ከሌላኛው በር ግለቱ በ70 እጥፍ ይበልጣል። የአላህ
ጠላቶች ወደጀሀነም ይነዳሉ። ልክ በሯ ላይ እንደደረሱ ዘባኒያ የተባሉ
የጀሀነም ወታደሮች በሰንሰለት ይቀበሏቸዋል። ሰንሰለቱን በአፋቸው
አስገብተው በመቀመጫዎቻቸው ያስወጡታል።
ግራ እጁ ከአንገቱ ጋር ይጠፈራል ቀኝ እጁም ከልቡ ጋር ተጠፍሮ
ይታሰራል።
እያንዳንዱ ሰው ከሸይጧን ቁራኛው ጋር በሰንሰለት ይጠፈራል። ከዚያም
በፊቶቻቸው እየተጎተቱ መላዕክት ደግሞ ከብረት በሆነ መዶሻ
ይመቷቸዋል።
ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት ሲሞክሩ ወደዛው ይመልሷቸዋል"ብሎ
መለሰላቸው።
ነቢያችንም ሰ ዐ ወ፦"በነዚህ በሮች የሚገቡት እነማን ናቸው?" ብለው
ጠየቁት።
ጅብሪልም ዐ ሰ፦
"በታችኛው በር የሚገቡት
1፦ሙናፊቆች
2፦በዒሳ ዐሰ ማዕድ የካዱት
3፦"የፊርዐውን ቤተሰቦች...ሲሆኑ የበሩ ስም ሀዊያ ይባለል። ሁለተኛው
በር ስሙ ጀሂም ሲሆን በሱ የሚገቡት ሙሽሪኮች ናቸው።
ሶስተኛው በር ሳብያኖች ነው የሚገቡበት ስሙም ሰቀር ይባላል።
በአራተኛው በር ኢብሊስ እና ተከታዮቹ መጁሶችም ይገቡበታል ስሙም
ለዟ ይባላል።
አምስተኛው በር የሁዶች የሚገቡበት ሲሆን ስሙም ሁጠማ ይባላል።
ስድስተኛው በር ስሙ ዐዚዝ ሲሆን የሚገቡበት ክርስቲያኖች
ናቸው።"ብሎ ከዘረዘረላቸው በኋላ ሰባተኛውን ለመጥቀስ ፍርሀት
ያዘው።
ነቢያችንም ሰ ዐ ወ፦"ሰባተኛውን በር ለምን አትነግረኝም?" ብለው
ሲጠይቁት
ጂብሪልም ዐ ሰ፦"በሱ በር የሚገቡት ካንተ ዑመት የሆኑ ትላልቅ
ወንጀሎችን ሰርተው ሳይቶብቱ/ሳይፀፀቱ የሞቱ ናቸው" ብሎ
ሲመልስላቸው ረሱል ሰ ዐ ወ እራሳቸውን ስተው ወደቁ። ከዚያም
ጅብሪልም የረሱልን ሰ ዐ ወ ጭንቅላት ታፋው ላይ አሳረፈ።ልክ ሲነቁ
ቀና አሉና፦"አንተ ጅብሪል ችግሬ በዛ ሀዘኔም በረታብኝ ከኔ ኡመት
ጀሀነም ሚገባ አለ እንዴ?" ብለው ሲጠይቁት
ጅብሪልም ዐ ሰ፦" አዎን ካንተ ኡመት የትላልቅ ወንጀል ባለቤቶች
ይገባሉ"ብሎ መለሰላቸው፣ የዐይናችን ማረፊያ ከእናት ከአባት በላይ ለኛ
አዛኝ የሆኑትም ነቢይ ይሄን ሲሰሙ ተንሰቅስቀው ማልቀስ
ጀመሩ።ጅብሪልም አብሯቸው አለቀሰ።
/ፊዳከ አቢ ውኡሚ ያ ረሱለላህ/
ረሱል ሰ.ዐ.ወ ይህኔ፦"ያጅብሪል አንተም ታለቅሳለክ?" አሉት ።
ጅብሪልም፦"እንዴት አላለቅስ የኔንስ መጨረሻ በምን አውቃለሁ?
እብሊስ እኮ ከመላእክት በላይ አላህን ይገዛ ነበር አላቸው ።
__
አላህ ይሄን መልዕክት የፃፈውንም ያነበበውንም አንብቦ ለሌላው
ያስተላለፈውንም ከዚህ አስፈሪ ቅጣት ይጠብቀው። አሚን..

ለአላህ ብላቹ ሳታነቡት እንዳታልፉ
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
"Have fear of allah wherever you are"
# Join and Share @
👍👍 https://t.me/joinchat/AAAAAEfDukA0z9K6SwI73g

Показано 20 последних публикаций.

282

подписчиков
Статистика канала