"ሀዋን ማን ገደላት"
( ✍ አብዲ ኢክላስ)
ክፍል ሦስት (3)
....አሁን ከምሽቱ 12 ሰዐት ሆኗል። ሁሉም እጅግ ግራ በተጋባ ስሜት በፍርሀት እና በጭንቀት ተውጠው እርስ በእርስ እየተያዩ ተቀምጠዋል። በአንድ በኩል ሀዋ ሞታለች ብልው እርማቸውን እንዳያወጡ አልያም አልቅሰው ለቀስተኛ እንዳይጠሩ የሀዋ ሬሳ አልተገኘም። አለች ብለውም እንዳያስቡ ሀዋ የት እንዳለች ማወቅ አልቻሉም። ግራ ተጋብተዋል... በሌላ በኩል ሰሚር እየመጣሁ ነው በማለቱ ለሀዋ ያለውን ፍቅር እና አክብሮት ስለሚያውቁ እጅግ በጣም እንደሚጎዳ እንደ ሚደነግጥ እና ህይወቱ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ስላሰቡ በጣም ስግተዋል።
ከሁሉም በላይ ሰሚር ያለበት የልብ ድካም በጣም አስጨንቋቸዋል። ምክንያቱም ከዶክተር የታዘዘለትን መድሀኒት በመውሰድ ላይ የሚገኘው ሰሚር ከፍተኛ የሆነ ደስታም ከፍተኛ የሆነ ሀዘንም ህይወቱን ሊቀማው እንደሚችል ዶክተሩ ነግሮታል። ይህንን መላ ቤተሰቡ በማወቁ ዛሬ ጭንቀታቸውን እጥፍ ድርብ አድርጎታል። ሰሚር ከጥቂት ደቂቃዎች ለኋላ እመጣለሁ ካለ አንድ ሰዐት ቢቆጠርም እሱ እንደማይዋሽ እመጣለው ካለ እንደሚመጣ ስላወቁ እያንዳንዳቸው ሲመጣ የሚዋሹበትን መንገድ የሚሸውዱበትን አልያም እሱን የሚያፅናኑበትን መንገድ በማሰብ ተጠምደው በራሳቸው ሀሳብ ውስጥ እላይ እታች ይባዝናሉ።
ይህ ሁሉ ሲሆን የሙና ስሜት ግን ከሌሎቹ በጣም የተለየ ነው። ከእትዬ መርየም፣ከሱመያ እና ከኻሊድ የሙና ስሜት ቀዝቀዝ ብሏል። ውስጧ ላይ ምን እያሰበች እንዳለ እጅግ ግራ ምታጋባዋ ሙና እንደነሱ ብዙም የፈራች የጨነቃት አትመስልም። እንደውም የምትወደው ባሏ እንደሚመጣ ተነግሯት በጉጉት የምትጠብቅ ሙሽራ መስላ እራሷን እያሰማመረች ትገኛለች። ፈገግታ ከፊቷ ያልተለያት ሙና በጣሙን እሱን የናፈቀች በጣም የምትወ ደው የልጆቿ አባት እየመጣ ያለ እንጂ ሞት የምታረዳው አልያም መጥፎ ዜና የምትነግረው አንድ የእህቷ ባል እየመጣ በጭራሽ አይመስልም። ይህ ሁኔታ ግራ ቢያጋባቸውም እንኳን እሷን ትተው በራሳቸው ሀሳብ ተውጠዋል።
እትዬ መርየም ዛሬ በሙና ስሜት ላለመገረም ሁለት ምክንያት አላቸው። አንደኛው፦ሀዋ እጅግ በጣም ተወዳጅ ስለሆነችና አባታቸውም ከሁለቱ አስበልጦ የሚወደው ሀዋን ስለነበር ሙና በጣም ትቀናለች። ሁለተኛው ደሞ፦ያኔ አቶ ዩሱፍ የሀዋ የሙና አባት ከመሞታቸው ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ብለው ለሁለት ሴት ልጆቻቸው ተናዘዙ። ሁለቱም በራሳቸው መንገድ ባል ለመፈለግ ቢሞክሩም..... ለሙና ሳይሳካላት ሀዋ ቀደመች። ሰሚርን አግብታ ያለውን ንብረት ሰማንያ አምስት በመቶ የወረሰችው ሀዋ የተንደላቀቀ ህይወት እየኖረች እንደሆነ የተረዳችው ሙና እያንዳንዱን ቀን በእህቷ መበለጧ እያብነከነካት ውስጧን እየበላው አመታት ተቆጥረዋል። ዛሬ ግን ቀን ለሙና የወጣላት በሀዋ ላይ የደረሰው ችግር ለሙና ፀሀይ የሆነላት ይመስላል። ምክንያቱም ሀዋ ባለችበት በዚህ ችግር ውስጥ ሙና ለሰሚር የተሻለ ሰው ሆና ለመታየት የምትፈልገውን ከማግኘት ወደኋላ አትልም።ምክንያቱም ሙና ሞገደኛ ስሜት ያላትና ለቤተሰቧ ብዙም ፍቅር የሌላት በራሷ ስሜት ውስጥ የምትኖር ወደክፉ የምታደላ እንስት በመሆኗ ነው።
በአንድ በኩል ኻሊድ እና ሱመያ ሀለቱም በዛ ትንንሽ እጆቻቸው ትቅፍቅፍ ተደታራርገው ፊታቸው ጭር ብሎ በጣም ከፍቷቸው ምንም ሳይተነፍሱ ከ አይናቸው እንባ ይዥጎደጎዳል። ይህን ግዜ እትዬ መርየም ወደ ኻሊድ ጠጋ አሉና አንድ ጥያቄ ጠየቁት በማለት ጥያቄ አቀረቡለት። ይህን ጊዜ ኻሊድ በእንባ በተሞላ ንግግር እንዲህ ሲል መለሰላቸው...ብሎ ንግግሩን ገታ አደረገ። ይህን ግዜ እትዬ መርየም በጣም ለመስማት ቀረብ ብለው..እ..በሌላ በኩል ምን ልጄ?...በማለት ጠየቁት። ኻሊድ ማውራት የፈለገ አይመስልም በአንድ አይኑ ሙናን ተመለከታት። ይሄን ግዜ እትዬ መርየም ነገር የገባቸው ይመስል በማለት መለሱለት። ይሄኔ የትዬ ሀሊድ ጥርጣሬ ልክ ይሁን አይሁን ሳይገባው ግራ በተጋባ ስሜት ልንገራቸው አልንገራቸው ማለት ያዘ። ከዚያምበማለት ቃል ተነፈሰ። ይህን ብሎ እንደጨረሰ ድንገት የጊቢው በር ተንኳኳ ይሄኔ ሁሉም በፍርሀት ከመቀመጫቸው ተነስተው ድንገት ቆም አሉ።
ይቀጥላል.......
Https://t.me/halal_couples