Репост из: ...ነጠብጣብ ✨💙
✨✨ሴራሚክ የተነጠፈበት ቤት አልወድም....አለችኝ፨
ለምን ?
ይቀዘቅዘኛል..!! ረገጥ አድርጋ ያወጣቻቸዉ ቃላቶቿ ይባረዳሉ፨
የተለመደዉ የእሁድ ከሰዓት ዉሏችን ነዉ፨እሁድን ከምናፍቅባቸዉ ምክንያቶች ቀዳሚዉ እርሷን ማግኘት ነዉ፨አልፎ አልፎ ብቻ በአጋጣሚዎች ካልሆነ በቀር የማይታጎል የጋራ ጊዜያችን ነዉ እንደመሻታችን የምናሳልፈዉ፨ጓደኛዬ ናት፨
ፊልም ለማየት ፍራፍሬዎችና መጠጦችን ይዘን ፍራሽ ላይ እየተደላደልን ነዉ፨
እየሰማሁሽ ነዉ...አልኳት፨
ልጅ እያለሁ ከጎረቤታችን በጊዜዉ እና በአካባቢው የደረጃ ስሌት ሀብታም የሚባሉ ጎረቤቶች ነበሩን፨ዘመናዊ እቃዎች ሁሉ ቀድመዉ የሚገኙት እነርሱ ቤት ነዉ፨ቴሌቭዥን ለማየት ተጋድሎ የማያደርግ የሰፈር ልጅ አልነበረም፨ታዲያ ቤታቸዉ ሴራሚክ ነበር ጫማ ተወልቆ የሚገባበት፨ከሁለተኛ ሴት ልጃቸዉ ጋር የአንድ ክፍል ተማሪዎች ነበርን፨ጎበዝ ተማሪም ስለነበርኩ አብረዉ ቢያጠኑስ የምትል የጎረቤታሞች ጥያቄ ቤታችን አንኳኳች፨ለሌሎች በቀላሉ የማይታለፈዉ የግቢያቸዉ በር ለእኔ ክፍት ነበር...የልጅ ነፍሴን የሚወጋጉ ጥቃቅን እሾሆች ቢኖሩትም...
ዝም አለች...አልረበሽኳትም ...ቀጠለችልኝ...
ቤታቸዉ ሥርዓት እንጂ ሕይወትም ሙቀትም የለዉም፨የልጅ ነፍስ አያስቦርቅም፨አብዛኛዉ የልጅነት ዘመኔ እዛ ቀዝቃዛ ቤት ነበር ያለፈዉ:ከእግሮቼ ስር ያስተናገድኩት ቅዝቃዜ እንደሎጥ ሚስት የጨዉ ሃዉልት ስላላደረገኝ እገረም ነበር፨አንዳንዴ በተለይ መወሰን የማትችይባቸዉ ጊዜያቶችሽ ላይ የማታስቆሚያቸዉና የማትናገሪያቸዉ ተደጋጋሚ ክቦችን መዞር ይጠበቅብሻል፨
በእርግጥ የተማርኳቸዉ ብዙ ነገሮችም አሉ ግና አንዳንዴ በጣም የተሰሙሽን ነገሮች አትረሽም፨በአጋጣሚ የተገኘሁበት ቦታ ሸራርፎኛል፨የሆነ እዉነተኛ ዋጋሽን የማታይበት ቦታ የለም...ሰዎች መቼም እንደማያጡት የሚያስቡት:ቢሄድስ ብለዉ የማይፈሩለትን ሰዉ የሚያዩበት የማትታይ ግን የምትሰማ ቁልቁል አተያይ ነገር ...
ታዉቂያለሽ አንዳንድ ትናንት መቼም የማያድግ ህፃን ልጅ ነዉ፨የፈለገ ከእርሱ ርቀሽ ለመሄድ ብትሞክሪ እንኳን ከኋላ ቀሚስሽን እየጎተተ መከተሉ አይቀርም ...በምታየዉ መስኮት በኩል በሃሳብ ሄደች...
ቤቷን እንደአዲስ ቃኘሁት፨እንከን የማይወጣለት ዘመናዊ ቪላ ነዉ፨ገና የመጀመሪያ እርምጃዉን ወደ ቤቷ ያስገባ ሰዉ ነፍሷ ትገባዋለች፨ሕይወትም ድምቀትም አለዉ፨የቤቷ ሙሉዉ ቀለም ነጭ እና ንፁህ ነዉ፨መጋረጃዎቹ ላይ ብዙ የቢራቢሮ ቅርፆች አሉበት፨ግድግዳዎቹ በዉብና ታሪካዊ ስዕሎች ያጌጡ ናቸዉ፨በአንደኛዉ ጥግ ግዙፍ "ምስለ ፍቁር ወልዳ"ምስለ ስዕሏ ስር በገናና ክራር በክብር ተቀምጠዋል፨ቢተኙበት የማይቆረቁረዉ የቱርክ ምንጣፍ ሌላዉ የቤቱ ዉበት ነዉ፨የቤት እቃዎቿ በጥንቃቄ የተመረጡ መሆናቸዉን ቃል ሳያወጡ ይናገራሉ፨የምትፈልገዉ አይነት ቤት ነዉ ያላት...ምናልባትም የዛሬ ህልሞቻችን በልጅነታችን ያጣናቸዉ ነገሮች ይሆኑ እንዴ....?
እርሷ ባለችበት ማንም ሰዉ ዝቅ እንዲደረግ አትፈቅድም፨ሰዉ የምታከብርበት መንገድ የተለየ ነዉ፨ከሰዎች ጋር ተግባብታ የምትኖርበት መንገድ ያስቀናኛል...ዛሬ እንደምትወዳቸዉ ቢራቢሮዎች ክንፎቿን አድሳ የምትበር ሴት ናት፨
ብቻ ግን ያለፉት ነገር ሰብሮ ያላስቀራቸዉ ነፍሶች የሕይወት ዉበቷ ናቸዉ፨ልቤ ታከብራታለች💙
✍️𝓮𝓶𝓾𝔂𝓮𝓮
https://t.me/yeesua_queen