Thoughts


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


ቸል የተባሉ እሳቤዎች፥ ያልታዩ እይታዎች የሚፈነጩበት ቤት ነው ፥ እናንተስ ጎራ አትሉም?
comment for the writer : @nhymn
discussion group https://t.me/+uDtKY02cOho2NGZk
Tiktok: https://www.tiktok.com/@the_author_nani?_t=8pGCAO5NksY&_r=1

Since: Dec-10-2022

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: ዳና🐾
~እንኳንም ዩንቨርስቲ አልገባሁ~

∞ ∞ ∞ ∞

ከዱባ ወጥ ቀጥሎ ኢቶጲስ ውስጥ የማይወደድ ነገር ቢኖር ትምህርት ነው ። አለመማር አንድ ነገር ሁኖ ሳለ የተማሩት ላይ መሳለቅ ደግሞ የሚገርም ነው።

ትምህርት አያስፈልግም ብለው የሚናገሩ ሰዎች በኩራት የሚያነሷት ነጥብ "የተማሩ ሰዎች የት ደረሱ" የምትለዋ ቀሽም የማሸማቀቂያ ምክንያት ስትሆን፤ የተማሩት የት እንደደረሱ አብረን እንመልከት።

ከመሰረታዊ ጥናቶች እንጀምር።


#ወንጀል

በ2021 Institute for Securities Studies (ISS) ባሳተመው ጥናት መሰረት 92.7% ገደማ ከባድ ወንጀሎች የሚፈፀሙት ዩንቨርስቲ ባልቀመሱ ግለሰቦች ሲሆን፤ 6.5% ወንጀሎች ዲግሪ ባላቸው እና ቀሪው 0.8% ብቻ ደግሞ ማስተርስ እና ከዛ በላይ ባላቸው ግለሰቦች የሚፈፀሙ ናቸው ይላል።

ይሄ ጥናት ኢቶጲስ ውስጥም የሚሰራ መሆኑን ለማወቅ፤ ስልክ ለመስረቅ ብሎ አንገት በጩቤ የሚወጉትን እና ወጡ ላይ ጨው አበዛሽ ብለው ሚስታቸውን በዘነዘና ከሚገሉት ሰዎች ጀምሮ መመልከት በቂ ነው።

እዚህ ጋር የተማረ ሰው ምን አተረፈ ካልክ? "ህሊና" የሚባል ነገር እልሀለሁ።


#ገንዘብ

ሌላኛው የተማሩ ልጆች ላይ የመዘባበቻ ነጥብ፤ ስራ እና ገንዘብ የማጣታቸው ጉዳይ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ይሄ የነሱ ድክመት ሳይሆን የሀገሪቱ ድክመት ነው፤ እሱን ትተን ወደ ንግድ እንኳ ብንመለስ፤ ንግድ ላይም የተማረ እና ያልተማረ ሰው ቢሳተፍ የተማረው ሰው የተሻለ successful የመሆን እድል እንዳለው የሚያሳዩ ብዙ ዳታዎች አሉ።

ለምሳሌ አለማችን ላይ ካሉ ቢሊየነሮች መሀል 71 ፐርሰንቱ ከዩንቨርስቲ ዲግሪ እስከ PhD የጨረሱ ጎበዝ ተማሪዎች ናቸው። Bill gates ወይም ማርቆስ Zuckerበርግ አይነት በጣም ጥቂት ባለሀብቶች በእርግጥ ከኮሌጅ ት/ት አቁመዋል፤ ነገርግን እነዚህ ግለሰቦች ት/ት ያቆሙት ከ Harvard እና Yale እንጂ ማትሪክ ወድቀው አይደለም።

ታዲያ ኢትዮጵያ ውስጥ ለምን ሀብታሞቹ ደንቆሮ ሆኑ ብለህ ልትጠይቅ ትችላለህ፤ አግባብም ነው። ለዚህ ቀላሉ መልስ "ቁጥር 1ን" ተመልከት ነው፤ የኛ ሀገር ሀብታም በአመዛኙ ደፋር፣ ወንበዴ፣ አጭቤ፣ አምታች ነው። ይሄንን ውንብድና ደፍሮ እንዲሰራ የሚያደርገው ደግሞ አለመማሩ ነው።

∞ ∞ ∞ ∞

ኢትዮጲስ ውስጥ ለምን generational wealth እንደሌለ ታውቃለህ? አባት ሀብታም ሲሆን ልጆቹን ጥሩ ቦታ ያስተምራል፤ ከዛ ልጆች ህሊና ይኖራቸዋል፤ ከዛ የአባታቸውን የወንበዴ ቢዝነስ ማስቀጠል ይከብዳቸዋል፤ አለቀ።

የተማረ ሰው ቁጥር ማነስ ከPolitical Stability፣ ከPoverty Alleviation፣ ከInnovation & ከEntrepreneurship እና አጅግ ብዙ አሁን ላለንበት አዘቅት ምክንያቶች ጋር በብዙ ጥናቶች አስደግፎ ማስረዳት ይቻላል።

∞ ∞ ∞

በአጭሩ ት/ት ምን ያደርጋል የሚልህ ነጋዴ ሂሳቡን የሚያሰራው በተማረ Accountant ነው፣ ሲከሰስ ተከራክሮ ንብረቱን የሚያስመልስለት የተማረ ጠበቃ ነው፣ ህንፆውን የሚያስገነባው በተማረ ኢንጂነር ነው፣ ሲያመው የሚሄደው የተማረው ዶክተር ጋር ነው፤ ከዛ አልፎ ልጁን አጥና እያለ የሚጨቀጭቀው እና ፅድት ያለ international school ልኮ የሚያስተምረው ይሄው ራሱ ሰውዬ ነው።

እና ምን ልልህ ነው፤
አለመማር አያኮራም።
እንኳንም ዩንቨርስቲ አልገባሁ አይባልም፤ ነውር ነው።


©Natnael Afework

#ዳና

431 0 11 2 28

✨ከሻማዋ አልሻልም?✨

"ፈዛዛ ንፋስ ያለበት ቦታ ላይ የበራ ሻማ አይተህ ታውቃለህ? አጥፍቶ አያጠፋት ዝም ብሎ ውልብልብ የሚያደርጋት ሻማ አጋጥሞህ አያውቅም? "

"አይ ማክዳ ምንም አልተለወጥሽም አሁንም ዙርያ ጥምጥም ካልሄድሽ ሀሳብሽን በቀጥታ መናገር ሞት ነው አይደል የሚመስልሽ?!"ብሎ ጥያቄዋን በሌላ ጥያቄ መለሰላት

"እያስረዳሁህ እኮ ነው! የለየለት ንፋስ አንዴ ቢያጠፋት ለሻማዋ የሚሻላት አይመስልህም?! ይሄ ለስላሳ ንፋስ ግን እያውለበለበ ማለቅ ከሚገባት ሰዓት አስቀድሞ እድሜዋን ያጫርሳታል! ምን እንደሚያሳዝን ታውቃለህ?!"

"ምን?!"

"ሻማዋ ያ አጥፍቶ ያላጠፋት ወይ ትቶ ያልተዋት ንፋስ ሆይ! ሆይ! በይ! በይ! ሲላት የደመቀች ይበልጥ ያበራች መስሏት ስትውለበለብ ቶሎ ቀልጣ መቅረቷ ነው

ታድያ እኔ ከአንድ ሻማ መሻል አልነበረብኝም? አንተ " ትዳር ተረጋግቶ ተሰብስቦ መኖር የፋራ ነው" የሚለው አስተሳሰብህ እስኪለወጥ እኔ ቀልጬ መቅረት የለብኝም ለዛ ነው የተለያየነው ደግሞ ያኔ ስንለያይም ይሄንኑ ምሳሌ ነግሬህ ነበረ ያው ችግሩ..."ብላ ፈገግ አለች

"ችግሩ ምን"

"ችግሩ "ልብ በአርባ አመት ነው" እንዲሉ ያኔ ያልገባህ በሀያችን መጀመሪያ ላይ ስለነበርን ይሆናል አሁን አርባችንን ስለያዝን ምናልባት...' የፌዝ ፈገግታዋን አሳየችው

"አሁንም በቁምነገር መሀል ካልነቆርሺኝ ደስ አይልሽም አይደል?!"

✍ናኒ



https://t.me/justhoughtsss




Репост из: የሕይወት እምሻው ወጎች/ Hiwot Emishaw
"ቁርጥ"

========

ያኔ በፍቅር ብን ሲሉ እሱ ገና ለጋ  ወጣት ሳለ፣ የአስራ አምስት አመት ታላቁ ነበረች፡፡



ለቁጥር የሚያዳግቱ ምሽቶችን እጆቻቸውን አቆላልፈው በጎዳና ላይ በመንሸራሸር አሳልፈዋል፡፡
ስንቱን ወሬ አፍ ለአፍ ገጥመው አውርተውታል፤ በስንቱ ነገር አውካክተዋል፡፡
ዓለም ከተፈጠረች አንስቶ ፍቅረኞች ያደረጉትን ሁሉ፣  የሚያደርጉት ነገር ሁሉ አድርገዋል፡፡



ስትስቅ መስመር እያወጣ እድሜዋን የሚያጋልጥ ብዙ ያየ ፊቷን ከእሱ የልጅነት ድምቡሽቡሽ ገጽታ ጋር እያስተያዩ አንገቶቻቸው እስኪጣመሙ ዞር ብለው ከሚገላምጡዋቸው እልፍ አይኖች፣ 
በሽሙጥ ከሚጣመሙ አፎች ፣
ለወሬ ከሰሉ ምላሶች መዋደዳቸውን ልትሸሽግ ከመድከሟ ውጪ ፍቅራቸው እንከን አልነበረውም፡፡




ፍቅር ከጀመሩ ሁለተኛ ዓመታቸውን ባከበሩ ማግስት ግን ቻው እንኳን ሳትለው በድንገት ከአይኑ ተሰወረች፡፡


እልም ብላ ጠፋች፡፡


ቆይቶ ቆይቶ አቻዬ ያለችውን ሰው እንዳገባች በወሬ ወሬ ሰማ፡፡

ባሏ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ነው ሲሉም ሰምቷል፡፡
በሚወዱት መከዳትን የማያውቀው መንፈሱ ተሰብሮ፣ ሰባራ ልቡን ይዞ ለብዙ ጊዜ፣ በየሄደበት፣ ላገኘው ሰው ስሟን እያነሰ ረገማት፡፡

‹‹ ሴትን ያመነ…›› እያለ፡፡


---
ከአስራ ስድስት አመታት በኋላ፣ በአንዱ ተራ አመሻሽ ዓለም ሲኒማ ጋር፣ እሷ ከምትሄድበት ከተቃራኒው አቅጣጫ ቦርሳውን መስቀለኛ አንግቶ ጠደፍ ጠደፍ እያለ ሲመጣ  ፊት ለፊት አየችው፡፡ 



‹‹ጌታ እየሱስ ድረስልኝ! …ብሩክ በሃይሉ…እውነት አንተ ነህ?›› ብላ ጮኸች፡፡


ስሙን ሲሰማ፣ድንገት ቆመ፡፡

ለአፍታ ፊቷን ቢመረምራትም ማንነቷ ጠፋበት፡፡



ክፉኛ አረጀችበት፡፡


በለጋነቱ እንደ ኳስ የተንደባለለበት ለግላጋ ገላዋ ገረጀፈበት፡፡

‹‹እንዴ! ወይንሸት…? በስመአብ! ከየት ተገኘሽ?”


ጠጋ ብላ ፊቷን ለመሳም ስትሰጠው በጉንጩ ፈንታ እጁን ሰጣት፡፡


ጨበጠችው፡፡



“አዲሳባ መጣሁ እኮ! ” አለችው አፈር ብላ.፡፡ “እዚህ ነው የምኖረው”
“ተይ እንጂ!” ፊቱ ላይ የትህትና ፈገግቶ ሰርቶ መለሰላት፤ ከዚያ ግን ወዲያው በአይኖቹ መሃከል በመኮሳተር የተፈጠረ ጉብታ እየታየ፡፡



“ወይ ብሩክ! ሁሌ አስብሃለሁ…የት ገብቶ ይሆን እያልኩ››
‹‹አይቲ ነው የምሰራው አሁን›› መለሰላት፡፡ ‹‹ክፍያ የሚባል ካምፓኒ ነው የምሰራው፡፡ ለገሃር አካባቢ››
‹‹ትዳርስ…?አገባህ?››
‹‹አዎ፡፡ ሁለት ልጆች አሉኝ››
‹‹ጎሽ…ጎበዝ››



በአዲስ መልክ ተምቦርቅቆ የተሰራውና ተቀራርበው የቆሙበት ጎዳና በሰዎች መሞላት ጀመረ፡፡
ከስራ ወደቤታቸው የሚሄዱ ሰዎች በግራም በቀኝም እያለፏቸው ይሄዳሉ፡፡
የጥቅምት ብርድ ምሽቱን ተገን አድርጎ አጥንት መሰርሰር ጀምሯል፡፡



‹‹አንቺስ…ባለቤትሽ ደህና ነው?›› ጠየቃት፡፡
‹‹ደህና ነው፡፡ ሶስት ልጆች አሉን›› መለሰችለት፡፡
‹‹እዚህ የከፈተው…ማለቴ የከፈትነው ትምህርት ቤት ነው የምሰራው አሁን…ምናልባት ታውቀው ይሆናል …ችልድረንስ ፓራዳይዝ?››

ትኩር ብሎ እያያት ነበር፡፡


‹‹እንዴ እሱማ በጣም ፌመስ ትምህርት ቤት ነው፡፡ ክፍያውም ከባድ ነው ደግሞ…በጣም…እ…በጣም ተለወጥሽ…›› አላት፡፡


ተለወጥሽ ሲላት ሊላት የፈለገው አረጀሽ፣ ጨረጨስሽ ነው፡፡


እሷም ገብቷታል፡፡

እንዲህ ሲላት፣ አጠገቡ ቆማ፣ በሰው ጎርፍ መሃል ሆና ብቸኝነት ተሰማት፤ በጫጫታ እና ውክቢያ መሃከል አውቶቢስ ወይ አውሮፕላን ሳትሳፈር ወደ ድሮ ተመለሰች፡፡



ያን ጊዜ ፣ አዋሳ ሲገናኙም የስንት ታላቁ ነበረች፡፡
ግን በአንጻራዊ ሁኔታ ያኔ ወጣት ነበረች፡፡



ፊቷ ጥርት ሰውነቷ ጥብቅ ያለ ነበር፡፡
እሱ የአንደኛ አመት የዩኒቨርስቲው ተማሪ፣ እሷ ደግሞ ስንቱን ያየች የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ክፍል ተቀጣሪ፡፡



አሁን ግን…ወጣትነቷና ውበቷ ተያይዘው፣ ላይመለሱ ጥለዋት ሄደዋል፡፡ ብሩክ ግን ወጣት ነው፡፡ አሁንም ወጣት፡፡



‹‹አያት አካባቢ ነው ቤታችን›› አለችው ባይጠይቃትም በመሃከላቸው የተሰነቀረው ዝምታ አስጨንቋት፡፡
‹‹እስቲ ና እና ጠይቀኝ…ጠይቀን…››
‹‹ደስ ይለኛል›› መለሰላት፡፡
‹‹አንቺና ባልሽ ደግሞ እኛ ቤት ትመጣላችሁ…የእኛም ቤት ሰሚት ነው…ቅርብ ለቅርብ ነን…ሉሲንም በዚያው ትተዋወቂያታለሽ››


ምሽቱ ደንገዝገዝና ቀዝቀዝ ሲል በመሃላቸው የነበረው ስሜትም ያንኑ መሰለ፡፡


‹‹ እኔም ደስ ይለኛል›› አለችው ታግላ፡፡
‹‹ልጆቼንም ታያቸዋለሽ፡፡እንዴት አሪፍ ልጆች መሰሉሽ!››



በድንገት የጎዳናው አዳዲስ የመንገድ መብራቶች ሁሉ በአንድነት ፏ ብለው በሩ፡፡

የአስራ ስድስት አመት የእድሜ ሰምበርን የተሸከመው ፊቷ ለብሩክ ፈራጅ አይኖች ይበልጥ ተመቻችቶ ሲሰጥ ተሰማት፡፡



ያበሩትን እጆች በሆዷ ረገመች፡፡



‹‹ይሄኔ ስንቱ ቤት እንጀራ መጋገሪያ መብራት የለም…ስንቱ ቤት ጨለማ ወርሶታል..ልጆች የቤት ስራ መስራት አልቻሉም እነሱ እዚህ እኔ ፊት ላይ ሚሊዮን ፓውዛ ያበራሉ…መብራት ሃይሎች…እርጉሞች…›› አለች አሁንም በሆዷ፡፡


‹‹በል ልሂድ›› አለች በድንገት፡፡

‹‹መኪና ደርቤ ነው ያቆምኩት፡፡ ይሄኔ ልጁ እየተበሳጨብኝ ነው….ስልክ እንኳን አልሰጠሁትም ፤ ቶሎ እመጣለሁ ብዬ››
‹‹እሺ በይ ቻው›› የቅድሙን እጁን ዘረጋላት፡፡



‹‹ታዲያ መቼ…›› ብላ ከመጀመሯ ግን እጇን ጥሎ ጉዞ ጀመረ፡፡

ቅድም ቦግ ያሉት መብራቶች አንዴ ብልጭ አንዴ ፍዝዝ ማለት ጀመሩ፡፡
ቃላት ለማውጣት አፏን ከፈተች ግን እምቢ አላት፡፡
‹‹ቻ…ው›› አለች ቆይታ፡፡ ጮክ ብላ፡፡


ብሩክ አልዞረም፡፡ መንገዱን አቋርጦ ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ የሚወስደውን ጎዳና ይዞ በፍጥነት መራመድ ጀመረ፡፡

የተሻገረውን ሁለት መንገዶች ብዙ መኪኖች፣ እሷ ቆማ የቀረችበትን የእግረኛ ጎዳና ደግሞ ብዙ አላፊና አግዳሚ ከዚህም ከዚያም ሲሞላው በመሃላቸው ያለው ርቀት ሰፋ፡፡


ብሩክ ከአይኗ ተሰወረ፡፡



ያን ጊዜ ‹‹እንገናኛለን›› ተባባሉ እንጂ አድራሻ እንዳልተለዋወጡ፣ ስልኳን እንዳልሰጠችው አስታወሰች፡፡

ከዚያ ደግሞ የበኩር ልጇ፣
አስራ አምስት አመት የሞላው ጎረምሳ ልጇ፣ ቁርጥ እሱን እንደሚመስል ለብሩክ እንዳልነገረችው አስታወሰች፡፡


Репост из: Harder Copies 📚
Are you in adama and want to buy books?


You are in the right place.

Contact us👇

@HC_orderbot
0905331297/ 0951960965

📍 Free delivery with unbelievable price.

@HarderCopies


The best jazz music of all time onG💯


Репост из: ንባብ ለ ሕይወት
አንድ ደግ ሰው በፈረስ ከሩቅ ሃገር ወደ መንደሩ ሲመለስ በጫካ ውስጥ አንድ ሌባ ሰው የታመመ በመምሰል

ጌታው አትለፈኝ እባክህ? ከባድ የሆነ ሆድ ቁርጠት ይዞኛል በምትወደው ከዚህ ጥለሀኝ ከሄድ እየመሸ ስለሆነ አውሬ ይበላኛል" ብሎ ይማጸነዋል::

ደጉም ሰው ያዝንለትና "አይዞክ ወንድሜ" ብሎ ከፈረሱ ላይ ተሸክሞ ያወጣዋል።

የፈረሱንም ሉጋም ይዞ በእግሩ ፊት ፊት ይመራዋል ሌባውም "ጌታው በግርህ ለራስክ ከመሄድ ይልቅ የፈረሱን ልጓም ይዘክ ስትመራኝ ጀንበር እያዘቀዘቀች ስለሆነ እንቅፋት ይመታካል ተሰናክለክም ብትወድቅ ጉዳት ይሆናልና እርካቡን አስቆንጥጠሀኝ ሉጋሙን አሲዘኝ ቀስ እያልኩ አዘግማለው" ይለዋል::

የፈረሱም ባለቤት በየዋህነት ፈረሱን ለሌባው ይለቅለታል....ይን ጊዜ ሌባው ፈረሱን ኮርኩሮ ሉጋሙን አላልቶ ሽምጥ ጋለበ።

በስላቅም እንግዲህ ደህና አምሽ ጌታው ብሎ ተፈተለከ

ሲጋልብም ሳለ ያ ደግ ሰው ተጣርቶ አንተ ሰው ፈረሱንስ ውሰደው ግን እባክህ አንድ ነገር ልንገርህ ስማኝ አለው

ሌባውም እየጋለበ "ምንድነው እሱ?"

"ይህን ያረከውን ነገር ማንም ሰው እንዳይሰማው ሰው የሰማ እንደሆነ በእውነት ለታመመና ለወደቀ የደግ ሃሳብ ርህራሄ እንዳያደርግለት ይፈራልና ነው!" ብሎ ቢነግረው...ሌባው በዚህ ነገር ልቡ ተነክቶ ተጸጽቶ ፈረሱን መለሰለት ይባላል::

ፍቅር ሁሌ እኔ ምን እሆናለው ሳይሆን ወንድሜ ምን ይሆናል? ነው የሚለው! እንዲህ አይነት ሰው በዚህ ዘመን ይገኝ ይሆን?

✍ከ ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል

🗣
@Tesh5050 ነኝ

ዝም ብላችሁ ቤተሰብ ሁኑ

🗣 TIKTOK....
http://tiktok.com/@tesh5050
🗣 YouTube...
https://www.youtube.com/@teshtube8601
🗣FACEBOOK
https://www.facebook.com/share/19ukNpA2rp/


Репост из: ሸጋዊያንስ🌒
አደግን አፈሯን አቡንነን አደግን ውሃዋን ተራጭተን አደግን ጭቃዋን አቡክተን አደግን......። በመጨረሻም ግን ደከመን ...ወደቅን ሃገርን ጣልን ጎረመስን አልን እሷን ዘነጋን ነጭን አጎላን ደከምን.... መበርታት ነጭ ማምለክ እና መከተል መሠለን ወደቅን.....ሚያነሳን ባህል መናቅ አስመሠልን ግና የወደቅነው ሃገርን ስንጠላ ነበር ይልቅ የደከምነው ባህል ስንጥል ነበር ይልቅስ የሞትነው ነጭ ስንከተል ነበር።

ራሳችሁን ሁኑ
ሃገርን ምሰሉ
ራሳችንን እንሁን
ሃገርን እንምሠል
እንደ ሃገራችን መኖሩ ይበጀናል !!!


እንዴት አመሻችሁ


any recommendation ልደቷን የምናከብርበት ካላችሁ ሹክ በሉን እስኪ


🙆‍♀🙆‍♀እናንተ ዛሬ አይደል እንዴ ትዝ የሚለኝ😅

ለካ ይህቺ ውድ ቻናላችን ሁለተኛ አመቷን የያዘችው ከሳምንት በፊት ነው December 10 ነበረ ልደቷ/anniversaryዋ(ሞት ይርሳኝ በውነቱ)

እና በነዚህ ሁለት አመታት አብራችሁኝ ለቆያችሁ ከመሀልም የተቀላቀላችሁ ሁላችሁም አንባቢዎች ክብረት ይስጥልኝ❤️❤️


እብድ ማነው?

በእብድ እና በጤነኛ መካከል ያለው ልዩነት የልብስ መልበስ ወይ ጎዳና ማደር ወይ ብቻ ማውራት ብቻ አይደለም ከሁሉም የሚልቀው አንድ ነገር ነው:- ችላ የማለት ወይ የመተው ችሎታ

ማህበረሰቡ እንደ ማህበረሰብ ሲያሽቆለቁል እያየ ዝም ማለት የሚችል ሰው በውነቱ ጤነኛ ነው¡

እንዴት ማለት ጥሩ አሁን ተሰብስበው ሳይጠቋቆሙብኝ በፊት እየተማርኩ እያነበብኩ ራሴን በውቀት ካላበቃሁ የምሞት የሚመስለኝ ሸበላ ታዳጊ ነበርኩ።

ከዛ እውቀት ሲያንስ ሳይሆን ሲበዛ እንደሚያጠፋ በራሴ አየሁት አሁንስ እንዴት አላችሁ?!

አስተማሪዎቼም ወላጆቼም ስለሚያበረታቱኝ ከመፅሀፍ ሰፈር አልጠፋም ነበረ። ከሰፈር ሰዎች አንፃር የተሻልኩ እንደሆንኩ ስለሚመስለኝ ዞሮ መግቢያዬ ቃላቶች ነበሩ። ከዛ conspiracy theories ቀልቤን እየገዙት ሲመጡ በስፋት ሰፈርኩባቸው።

ዘመድ ቤት እንግድነት እንኳን ሄጄ የመፅሀፍ መደርደሪያ ስር ነው የምገኘው ታድያ አንድ ቀን ከአስራምናምን አመት በፊት ነው የሆነች መፅሀፍ አየሁ ርዕሷን አሁን በቅጡ የማላስታውሳት ነገር ግን የሀያላን ሀገራት ስብሰባ ነገር እንደሆነ አስታውሳለሁ ያኔ ሁለት አንቀፆች በጉልህ ትኩረቴን ስበውት ደጋግሜ አነበብኩት ምንድነው ጭብጡ አላችሁ?!

"የነቃ ማህበረሰብ ጠር ነው የሚሆንብን። በተለይ ደግሞ እንደኢትዮጵያ ያለች ታላቅ ሀገር ከገባችበት እንቅልፍ ከባነነች አለቀለን ስለዚህ መፍትሄው አንድ ነው ህዝቡን ማደንዘዝ ወጣቱ እና ጎልማሳውን ተዉት ኑሮ ያጦዘዋል፣ ንቃተ ህሊና ምናምን የሚልበት ጊዜ የለውም። ዋናው ህፃናት እና ታዳጊዎች ላይ ነው መሰራት ያለበት። እነሱን መቆጣጠር ደግሞ አይከብድም ስማርት ስልክ እና wifi በየቤታቸው አንኳኩቶ እንዲገባ ማድረግ ብቻ እኮ ነው"

እንግዲህ እኔ ይሄንን ያነበብኩት እኛ ሀገር ስማርት ስልክ ያላቸው በጣት በሚቆጠሩበት ጊዜ ነው በደንብ እንዳስተከዘኝ አስታውሳለሁ። ከዛ ለሆነ ማህበር ተሰብስበን የባጥ የቆጡ ሲነሳ ሲጣል የቴክኖሎጂም ነገር ተነሳና እንዴት እንደጠቀመን ምናምን ሁሉም ደሰኮረ የኔ ambitious አባት ደግሞ "ታያላችሁ አስር አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መረጃ መለዋወጥ እንዴት ቀላል እንደሚሆን ስልክ wifi ምናምን ብርቅ ሆኖብን አይቀርም" ሲል

ከመቀመጫዬ እመር ብዬ ተነስቼ "እና?! ይሄ ጥሩ ነገር ነው?! ሁሉም ቴክኖሎጂ እኮ ዘመናዊነት አይደለም ሁሉም ዘመናዊነትም ጥሩ አይደለም የምትመኙት ነገር በደንብ እወቁ እሺ" ብዬ በሩን አጋጭቼላቸው ወጣሁ

የዛን ለታ "ይሄ ልጅ ለየለት" ብለው ደመደሙ ከዛ ቀስ በቀስ አባቴ ያለው ነገር ሲፈፀም በአይኔ አየሁ ስማርት ስልክ የሌለው መኖር አይችልም የተባለ እስኪመስል ሁሉም እጅ ገባ ከትንሽ እስከትልቅ ከዛ ደግሞ wifi በርካሽ በየሰፈሩ ሲገባ እንደማበድ አደረገኝ።

ቴሌ የሚሰሩትን ሰዎች ላስጠነቅቅ ሞከርኩ "ምን እየተካሄደ እንደሆነ አታውቁም ምን እንደምታከፋፍሉ አታውቁም ትውልድ እየፈጃችሁ ነው" ብዬ ነገርኳቸው በጥበቃ አንጠልጥለው አባረሩኝ

ይሄ ሁሉ አልበቃ ብሎ ብለው ብለው የገዛ ቤተሰቦቼ wifi አስገብተው ጠበቁኝ ከዛ ስልክ ላይ ተጥዶ መዋል የዘመኑ ፋሽን ስለሆነ እኛ ቤት ድረስ አንኳኩቶ ሲገባ ቁጭ ብዬ አየሁ። ዝም ማለት አልቻልኩም

በየመንገዱ ለወጣት ለጎልማሳው በጆሯቸው እየነገርኩ አስጠነቀኳቸው ሁሉም "ያመዋል?! እብድ ነው እንዴ?!" ብለው ከመሸሽ ውጪ እያበዱ እየደነዘዙ ያሉት እነሱ መሆናቸው አልገባቸውም ነበረ

አሁንም ታክሲ ውስጥ tik tok ማየት እርድና እየመሰላቸው ሰላማዊውን ሰው የሚበጠብጡትንም ሰዎች በየተራ አስጠነቀኩ። ማንም አልሰማ ማለቱ እያሳበደኝ ሲመጣ እየታወቀኝ ነበረ

"ብቻህን አታውራ እንጂ" ብላ እናቴ ስትቆጣኝ ነው የእብደት ቅድመ ሁኔታዎችን እያሟላሁ እንደሆነ የገባኝ።

ያሳበደኝ አልሰማ ብሎ በስልክ ሱስ መተብተብ አላቆም ያለው ሰው ወዶ መስሎኝ ነበረ ግን ለማምለጥ እኮ ችግር ውስጥ መሆንን ማወቅ ያስፈልጋል። ቅሉ ያንን ለመረዳት እንኳን ጊዜ ያለው ሰው አልነበረም ምስጋና ለtiktok እና ከተወሰነ ደቂቃ በላይ ትኩረቱን አንድ ነገር ላይ ማድረግ የሚችል ሰው የለም።

አሁንም አልተውኩም እያስጠነቀኩ ነው።

✍ናኒ

https://t.me/justhoughtsss




Репост из: መዲና ዲጂታል መጽሔት/ Medina Digital Magazine
መዲና ቅጽ 1 ቁጥር 9.pdf
15.7Мб
ውድ የመዲና ዲጂታል መጽሔት አንባብያን፥ መዲና ቅጽ 1 ቁጥር 9 እትሟን ይዛ ተመልሳለች።

ሀሳብ አስተያየታችሁን በሶሻል ሚዲያ አካውንቶቻችን ብታጋሩን ደስ ይለናል።

ስለምታነቡን እናመሰግናለን።

https://t.me/Medinamagazine

በተጨማሪም በፌስቡክ እና ኢንስታግራም ቤተሰብ ይሁኑን!

https://www.facebook.com/profile.php?id=61556884335163&mibextid=ZbWKwL

https://www.instagram.com/medinadigitalmegazine?igsh=ejZqbjN3OXF0dHJj

ለአስተያየትዎ

medinadigitalmagazine@gmail.com

ኅዳር 2017 ዓ.ም


✨አቅም አሳጣቺኝ✨

    ገና ከመረፋፈዱ አይኑን እያሻሸ መጥቶ የብፌውን በር በሀይል በርግዶ ራሱ ያጋመሰውን የውስኪ ጠርሙስ አውጥቶ መልሶ ደርግሞ ዘጋው።

    "ተው እንጂ በመከራ የተሰበሰበውን ትኩረቴን የውስኪ ጠርሙስ በማውጣት ሰበብ ባትበታትነው?! ደሞ ሴትዮህ ናት እንጂ ብፌው ምን አደረገህ?!" አልኩ ታላቅ እህትነቴ በሚሰጠኝ ስልጣን

    "ኤልዳና!" በሙሉ ስሜ የሚጠራኝ የእውነት ሲናደድ ስለሆነ ስመሰጥበት የነበረውን መፅሀፍ ዘግቼ "ምንድነው ደግሞ የሆንከው? ደግሞ ምን አደረገች" አልኩት ከተወሰኑ ወራት ጀምሮ ከሙሉ አለም በላይ የእሷ ነገር ብቻ ስለሆነ የሚያቃውሰው ብዬ ነው

    "አዘዘችበት... ጭንቅላቴን አዘዘችበት አቅም አሳጣቺኝ" አለ ውስኪውን በጠርሙሱ እያንቆረቆረው።እንደዚህ ሲል የሜሪ ፈለቀን አዲስን ያስታውሰኛል

    ውስኪው ጉሮሮውን ቅጥል ሲያደርገው ፊቱን ቅጭም እያደረገ ሲያስተናግደው ፈገግ አስባለኝ። 'ሰው ለምን ገንዘብ አውጥቶ ይጠጣል?' እያልኩ ዘወትር የሚደንቀኝን ነገር መልስ አገኘሁለት ግልፅ አይደለ?! ውስጣቸው ልባቸው ከሚቃጠል አካላቸው ጉሮሯቸው ምናምን ቢቃጠል ስለሚመርጡ እኮ ነው

   "ምን አደረገች"

    ሲናደድ እየተንጎራደደ መደስኮር ስለሚወድ የተፈጠረውን ከመስማቴ በፊት ትንሽ ዲስኩር መታገስ አለብኝ

    "የሆነ ሰው ከዚህ በፊት ምን ብሎኝ ነበረ መሰለሽ አለምን የሚመራው control ነው ብሎኝ ነበረ ምን ማለት እንደሆነ ታውቂያለሽ ይሄንን የውስኪ ጠርሙስ ክዳን ባሽከረክረው ይከፈታል ግን ባስቀምጠው አርፎ ይቀመጣል ግን ሳስቀምጠው አርፎ አልቀመጥ ቢል እንዴት ሊያናድድ እንደሚችል አስበሽዋል?"

     "አዎ ልክ ነህ ግን ይሄ ከእሷ ጋር በምን እንደሚገናኝ አልገባኝም"

     "ግልፅ እኮ ነው ሁሉንም ነገር መቆጣጠር ችለሽ እንኳን መቆጣጠር የማትችይው ሰዎችን ነው አርቀሻቸው እንኳን ስሜትሽን ጭንቅላትሽን ሲያዙበት አቅም ያሳጣል አይደል?! ምን ማድረግ ትችያለሽ" አለ ሶፋው ላይ ዘፍ ብሎ ተቀምጦ

    "ዛሬ ምን አድርጋ እንደሆነ እስካሁን አልነገርከኝም እኮ"

    "በህልሜ አየኋት!!"

     ግንባሩን በመዳፉ እየጠፈጠፈ "ወይኔ ሳዶር ወይኔ ወንዱ ናፍቀሽኛል አልኳት እኮ... ምን እንደሚያናድድ ታውቂያለሽ?!"

"ምን" አልኩት ሳቄን ዋጥ አድርጌ

    "በህልም እንኳን... ያውም በራሴ ህልም እንኳን አትስትም እኮ "እኔ ግን አልናፈቅከኝም" አለቺኝ እሺ እኔ የት ልድረስ?! አላገኛትም አላያትም ብዬ ውሎዬን ቀየርኩ እሺ በህልሜም በሰላምም አልተኛ"

   ከዛ በላይ ሳቄን መያዝ አልቻልኩ

"አይይ ሳዲቲ

'ደግሞ እንድነቃ ዳግም ቆሜ
አትመላለሽ መጥተሽ በህልሜ
የቀኑ ማማር ይበቃሻል
ከተኛው ቀልቤ ምን ቀርቶሻል'

የሚለውን የቴዲን ዘፈን ጋብዛት እሺ" እያልኩ ሳቄን አስነካሁት

"የኔን ይስጥሽ ምንም አልልም" ብሎ ውስኪውን ይዞ ሄደ


✍ናኒ


https://t.me/justhoughtsss




Репост из: ቃ ላ ት | Words
ቃ ላ ት - ፩፪ | 12.pdf
22.6Мб
እነሆ

ቃላት 12 | Words | ኪናዊ መጽሔት

ልዩ እትም

https://t.me/Words2014
.
.
ለአስተያየታችሁ :‑
words5102@gmail.com


Репост из: ...ነጠብጣብ ✨💙
✨✨ሴራሚክ የተነጠፈበት ቤት አልወድም....አለችኝ፨

        ለምን ?
ይቀዘቅዘኛል..!! ረገጥ አድርጋ ያወጣቻቸዉ ቃላቶቿ ይባረዳሉ፨
የተለመደዉ የእሁድ ከሰዓት ዉሏችን ነዉ፨እሁድን ከምናፍቅባቸዉ ምክንያቶች ቀዳሚዉ እርሷን ማግኘት ነዉ፨አልፎ አልፎ ብቻ በአጋጣሚዎች ካልሆነ በቀር የማይታጎል የጋራ ጊዜያችን ነዉ እንደመሻታችን የምናሳልፈዉ፨ጓደኛዬ ናት፨
ፊልም ለማየት ፍራፍሬዎችና መጠጦችን ይዘን ፍራሽ ላይ እየተደላደልን ነዉ፨

እየሰማሁሽ ነዉ...አልኳት፨

ልጅ እያለሁ  ከጎረቤታችን በጊዜዉ እና በአካባቢው የደረጃ ስሌት ሀብታም የሚባሉ ጎረቤቶች ነበሩን፨ዘመናዊ እቃዎች ሁሉ ቀድመዉ የሚገኙት እነርሱ ቤት ነዉ፨ቴሌቭዥን ለማየት ተጋድሎ የማያደርግ የሰፈር ልጅ አልነበረም፨ታዲያ ቤታቸዉ ሴራሚክ ነበር ጫማ ተወልቆ የሚገባበት፨ከሁለተኛ ሴት ልጃቸዉ ጋር የአንድ ክፍል ተማሪዎች ነበርን፨ጎበዝ ተማሪም ስለነበርኩ አብረዉ ቢያጠኑስ የምትል የጎረቤታሞች ጥያቄ ቤታችን አንኳኳች፨ለሌሎች በቀላሉ የማይታለፈዉ የግቢያቸዉ በር ለእኔ ክፍት ነበር...የልጅ ነፍሴን የሚወጋጉ ጥቃቅን እሾሆች ቢኖሩትም...

ዝም አለች...አልረበሽኳትም ...ቀጠለችልኝ...

ቤታቸዉ ሥርዓት እንጂ ሕይወትም ሙቀትም የለዉም፨የልጅ ነፍስ አያስቦርቅም፨አብዛኛዉ የልጅነት ዘመኔ እዛ ቀዝቃዛ ቤት ነበር ያለፈዉ:ከእግሮቼ ስር ያስተናገድኩት ቅዝቃዜ እንደሎጥ ሚስት የጨዉ ሃዉልት ስላላደረገኝ እገረም ነበር፨አንዳንዴ በተለይ መወሰን የማትችይባቸዉ ጊዜያቶችሽ ላይ የማታስቆሚያቸዉና የማትናገሪያቸዉ ተደጋጋሚ ክቦችን መዞር ይጠበቅብሻል፨

በእርግጥ የተማርኳቸዉ ብዙ ነገሮችም አሉ ግና አንዳንዴ በጣም የተሰሙሽን ነገሮች አትረሽም፨በአጋጣሚ የተገኘሁበት ቦታ ሸራርፎኛል፨የሆነ እዉነተኛ ዋጋሽን የማታይበት ቦታ የለም...ሰዎች መቼም እንደማያጡት የሚያስቡት:ቢሄድስ ብለዉ የማይፈሩለትን ሰዉ የሚያዩበት የማትታይ ግን የምትሰማ ቁልቁል አተያይ ነገር ...

ታዉቂያለሽ አንዳንድ ትናንት መቼም የማያድግ ህፃን ልጅ ነዉ፨የፈለገ ከእርሱ ርቀሽ ለመሄድ ብትሞክሪ እንኳን ከኋላ ቀሚስሽን እየጎተተ መከተሉ አይቀርም ...በምታየዉ መስኮት በኩል በሃሳብ ሄደች...

ቤቷን እንደአዲስ ቃኘሁት፨እንከን የማይወጣለት ዘመናዊ ቪላ ነዉ፨ገና የመጀመሪያ እርምጃዉን ወደ ቤቷ ያስገባ ሰዉ ነፍሷ ትገባዋለች፨ሕይወትም ድምቀትም አለዉ፨የቤቷ ሙሉዉ ቀለም ነጭ እና ንፁህ ነዉ፨መጋረጃዎቹ ላይ ብዙ የቢራቢሮ ቅርፆች አሉበት፨ግድግዳዎቹ በዉብና ታሪካዊ ስዕሎች ያጌጡ ናቸዉ፨በአንደኛዉ ጥግ ግዙፍ "ምስለ ፍቁር ወልዳ"ምስለ ስዕሏ ስር በገናና ክራር በክብር ተቀምጠዋል፨ቢተኙበት የማይቆረቁረዉ የቱርክ ምንጣፍ ሌላዉ የቤቱ ዉበት ነዉ፨የቤት እቃዎቿ በጥንቃቄ የተመረጡ መሆናቸዉን ቃል ሳያወጡ ይናገራሉ፨የምትፈልገዉ አይነት ቤት ነዉ ያላት...ምናልባትም የዛሬ ህልሞቻችን በልጅነታችን ያጣናቸዉ ነገሮች ይሆኑ እንዴ....?


እርሷ ባለችበት ማንም ሰዉ ዝቅ እንዲደረግ አትፈቅድም፨ሰዉ የምታከብርበት መንገድ የተለየ ነዉ፨ከሰዎች ጋር ተግባብታ የምትኖርበት መንገድ ያስቀናኛል...ዛሬ እንደምትወዳቸዉ ቢራቢሮዎች ክንፎቿን አድሳ የምትበር ሴት ናት፨

ብቻ ግን ያለፉት ነገር ሰብሮ ያላስቀራቸዉ ነፍሶች የሕይወት ዉበቷ ናቸዉ፨ልቤ ታከብራታለች💙

✍️𝓮𝓶𝓾𝔂𝓮𝓮

https://t.me/yeesua_queen


እናንተስ እንዴት ነው የተገናኛችሁት #10

"ይሳኮር እና ቤቲ ናቸው ተረኛ" አለች ሳባ ገና ሳይጀምሩት እየተቁነጠነጠች

ይሳኮር እኔ እነግራችኋለሁ ብሎ ጀመረ "ቤቲ ያኔ Facebook ላይ ትፅፍ ነበረ እኔ ደግሞ እልል ያልኩ አንባቢም ባልሆን ሲያጋጥመኝ አነብ ነበረ ከዛ Facebook ላይ ከሚለቀቁ አገር የፅሁፍ አይነቶች የሷን የምለየው አማርኛ ከእንጊልዘኛ ጋር እየቀላቀለች እንደዘመናዊ ሀበሻ እንጊልዘኛ ጣል ጣል እያደረገች ስለነበረ የምትፅፈው በጣም እበሳጭ ነበረ ይሄንን የተከበረ ቆንጆ ቋንቋ እያለን እያልኩ

ብናደድም ግን የምታነሳቸው ሀሳቦች ስለሚስቡኝ መከታተል ጀመርኩ የሷን ፅሁፎች ደጋግሜ ከማንበቤ የተነሳ የአፃፃፍ ስልቷ ቃላቶቿ በቅርብ እንደማውቀው ሰው እየለመድኩት መጣሁ። ከዛ አንድ ቀን እንዲሁ በሶሻል ሚድያ ላይ ሳውደለድል telegram ላይ የሷን ፅሁፍ ወስደው የራሳቸውን ስም አደርገው post አድርገው ሲሞጋገሱ አየሁ።

ለማላውቃት እሷ ሽንጤን ገትሬ ተከራከርኩ ሌብነት እና ጥበብ ለየቅል ነው ብዬ ያዙኝ ልቀቁኝ አልኩ ይሄኔ Facebook ላይ inbox አደረግኩላት እሷም telegram ላይ ገብታ መብቷን አስከበረች በተከታዮቻቸውም አዋረደቻቸው

በዛውም ስታመሰግነኝ ምንም አይደል ስላት የወሬ ቦዩ ተቀደደ ሌት እና ቀን ያለከልካይ አወራን ከፅሁፎቿ የተረፉኝን የማንነቷን ክፍሎች በደንብ ተዋወቅኳቸው። 'እንገናኝ' ለማለት ሳስብ ሳመነታ 'የመፅሀፍ ምረቃ ስላለ ብትመጣ ደስ ይለኛል' ብላ በጨዋ ደንብ ጋበዘቺኝ።

ከምረቃው ሰዓት በፊት ተነናኘን የዛን ቀን እንደተገናኘ ሳይሆን ለረጅም ጊዜ እንደሚተዋወቅ ሰው አወራን የመፅሐፍ ምረቃው ተጀምሮ በየተራ እየወጡ ደራሲያን ሲያወሩ የእኛን ወሬ በጠበጡት "እንውጣ?!" አለቺኝ በደስታ ብዬ ተያይዘን ወጣን ራት በልተን ወደየቤታችን ተመለስን። ቀልቤንም ሀሳቤንም በዛው ይዛው ሄደች ከዛ በኋላ ምሳ ወይ እራት መገናኘት ግድ ሆነ በፅሁፎቿ የሆነውን ነፍሷን ቀድሜ ማየት ይበልጥ አቀራረበን። ይኸው ነው"ብሎ ብርጭቆውን ከፍ ሲያደርግ

"ዋው!! ቺርስ ለሶሻል ሚድያ ፅሁፎች" አለች ሳባ እየሳቀች

ብዙ ቺርሶች ተከተሉ

https://t.me/justhoughtsss




የጨው ሀውልት መቼ እንደዚህ ይደርቃል
ጅብራ መቼ ይገተራል

ከአመታት በኋላ በቀን ጎዶሎ(እሁድም የቀን ጎዶሎ አለው?!)

ከሌላው ቀን በተለየ ጥድፊያ በሌለበት፥ በሰላም ነበረ እኮ የነቁት አረፋፍደው በተፈጥሯዊ መንገድ ማለት ነው። ፀሀይ በመስኮት ገብታ በሙቀት እና በጨረር ኮርኩራቸው ተንጠራርተንው... (ይሄ ሁሉ ዝብዘባ በስራ ቀኖች ላይ በalarm ጉትጎታ ፀሀይ ሳትነቃ ከቤት ስለሚወጡ ነው)

ከዛማ እየተንጠራሩ ተነስተው ቁርስ አብረው አብስለው እየበሉ "እሺ የዛሬ ውሏችን ምን ይመስላል" አላት አቤል ቀጥሎ የሚጎርሰውን እያስተካከለ "አልረሳሁልህም ያንን ያየሁትን sundress እገዛልሻለሁ ያልከኝን" አለች እንደህፃን እየተቁነጠነጠች

(ቁም ነገሩ እንደህፃን የምንቀብጥበት አጋር ማግኘት ስለሆነ...)

"እሺ ቀለል ያለ ነገር ልበሺ ፀሀይ ስለሆነ አሁን ገዝተን እንመጣለን በዛውም ምሳ ውጪ ነን ዛሬ" አለ የበሉንበትን ሰሀን እያነሳሳ

እንደልጅ ፈነጠዘች ተሯሩጣ ለባብሳ እየተሽከረከረች "እንዴት ነኝ?!" አለችው "አቤት ፍጥነት ለስራ ስትለብሺ እንደዚህ ብትፈጥኚ" አለ እሱም የሚቀይረውን ልብስ እያስተካከለ

"አንተ ደሞ ስራ እና ግብዣ አንድ ነው?! አሁን አምሮብኛል ወይ ነው ያልኩህ"   "ፀዲ የኔ ሚስት እኮ ነሽ እንኳን ዘንጠሽ ተንኳተሽ እንኳን ለኔ ምርጥ አንደኛ መሆንሽን ታውቂያለሽ አይደል" ግንባሯን ሳም አድርጎ የሸሚዙን ኮሌታ ማስተካከል ጀመረ

እሷም ፀጉሯን ስታበጃጅ ሽቶ ስትነሰንስ ቆይታ ተያይዘው ወጡ። ቀሚሱን ያዩበት ሱቅ ገብተው እየለካች እያለ ሌሎች ጥንዶች ገቡ። "ያንን ቀሚስ እኮ ነው ያልኩህ" እያለችው ሲገቡ አለም እሽክርክሪቷን አቆመች...ሁሉም ፀጥ አለ.... የሷም አተነፋፈስ ጭምር... በፊት የምታውቀው ጉሮሮ ስር ውትፍ የሚል የሚያንቅ ስሜት...

የጨው ሀውልት መቼ እንደዚህ ይደርቃል
ጅብራ መቼ ይገተራል

አዲስ አበባ ባህር ናት፣ ከውቅያኖስ ትሰፋለች፣ የተጠፋፋ ሰው አይገናኝም ይሉ አልነበር ታድያ ሲራክ እዚህ ምን ይሰራል?!

አስራ አንድ... አያይ አስራ ሁለት አመት ያለፈው የህፃናት እቃቃ የሚመስል እንደእቃቃ ጨዋታ ግን ጨዋታ ፈረሰ ተብሎ እንደቀልድ ያልተቋጨ ነገር ይሄን ሁሉ አመት ጠብቆ በዚህ አመት ያውም በዚህ ወር በዛሬዋ እሁድ...

...

አቤል ስልኩን እየነካካ ለብሳ እስክትመጣ ሲጠብቅ ቀና ሲል ለብሳ ቆማለች ግን እያየችው አልነበረም የገቡትን ጥንዶች አይታ ሳትንቀሳቀስ ቆማለች

"ፀደይ?!" አለ ሰውየው "ፀደንያ ነው ስሟ ...ኦህ ፀደይ የሚልሽ ሲራክ ማለት እሱ ነው?!" ብሎ አቤል ፀደንያን ሲያያት "አዎ" አለችው በጭንቅላቷ ንቅናቄ

"ሰላም ነው" ብሎ ሲራክንም ሴቷንም ሰላም አላቸው "ሰብለ ትባላለች ባለቤቴ ነች" ብሎ አስተዋወቃቸው ከዛ ሲራክ ራመድ ብሎ ፀደንያን እጇን ያዘውና ከላይ እስከታች አጢኗት ሲያበቃ እንደድሮ አፈፍ አድርጎ አቅፏት "ባልሽ ምርጫ ይችላል" አላት በጆሮዋ ስለቀሚሱ ይሁን ስለሷ ስላልገባት ድብልቅልቅ ያለ ስሜት አስተናገደች።

"ቀሚሱ አምሮብሻል" አለች ሰብለ ፈገግ ብሏ አመሰግናለሁ ብላት ሰላም ተባባሉ። ከሰብለ ጋር የሆነ ነገራቸው ከራሷ ጋር ተመሳሰለባት "ባይወዳት ነው የሚገርመው" ብላ በሆዷ ዞር ስትል የሲራክ እና የአቤል ቁመና መመሳሰል አስገረማት። ከድሮ ጀምሮ ምርጫቸው አለመቀየሩ ፈገግ አስባላት።

"ምሳ ልንበላ እየወጣን ነበረ ተቀላቀሉን እባካችሁ" አለ አቤል ጋባዥነቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ጠላችው መንጋጋውን መንከሱ እያስታወቀበት  "አይ..."ብሎ ሲራክ ሲጀምር "ደስ ይለናል እንደውም እርቦኝ ነበረ" አለች ዞራ እያየችው (የኔ ቢጤ ሆድ አምላኩ ናት ብላ በሆዷ ፈገገች)

የነከሰውን መንጋጋውን ለቀቅ አድርጎ "ለምን ርቦኛል አላልሽኝም ታድያ እሺ ነይ እንሂድ እና እንብላ እባካችሁ ቅደሙ" ብሎ ሲያስቀድማቸው የቀሚሱን ዋጋ ከፍለው ከፊት እነአቤል እነሱ ከኋላ ሆነው ወደ ሬስቶራንቱ ሄዱ

"To be known is to be loved" እንዲል ፈረንጅ አስተናጋጁ መጥቶ ምን ልታዘዝ ሲል "ሩዝ አሁንም ትወጃለሽ አይደል?!" አለ ሲራክ "እህምም" ብላ በንቅናቄ ከመግለፅ ውጪ ምንም አልተናገረችም እንደዚህ የሷ ትዕዛዝ በሲራክ ታዝዞ ሌሎቹ የየራሳቸውን አዘው አስተናጋጁ ሄደ።

"እናት የሆንሽው ነገር አለ እንዴ?!" ብሎ አቤል እጇን ይዞ ጠየቃት "ትንሽ ደክሞኝ ነው" ስትለው የተቀመጠችበትን ወንበር ሳብ አድርጎ ትከሻው ላይ አስደገፈፋት እና ትከሻዋን እንደሚያስተኙት ህፃን እየደባበሰ ቆዩ 'እርግት ያለ እረፍት አቤል ማለት እንደሱ' ነው አለች በልቧ

ሲራክ በሚስቱ ተጠምዷል ፀጉሯ ወደፊት ሲመጣ ሰብስቦ ያስይዝላታል የምታወራውን በጆሮው ብቻ ሳይሆን በአይኑም ነበረ ሲሰማት የነበረው።

እንደዛ ሆነው ቆይተው ምግባቸው ሲመጣ ሲራክ ሰሀኖቹን እያስተካከለ "እማ" ሲል ፀደንያም ሰብለም "ወዬ" አሉ እሱ የጠራው ሚስቱን ነው ፀደንያ የድሮውን አለቅም ማለቷ ክው አደረጋት።

አቤል ምን ብሎ ይሆን ብላ ሳታየው እንኳን ሊናደድ ቀርቶ እርጋታ ያልተለየው ፊቱ ምንም ቅያሜ አይታይበትም። "የልምድ ነገር እኮ ነው አንዳንዴ ያጋጥማል ብሎ ጉንጯን ሳም አደርጎ የመጀመሪያውን ጉርሻ አጎረሳት።

ሲራክ እና ሰብለም እየተጎራረሱ በልተው ጨረሱ።"ትንሽ ስለምንቸኩል ብንሄድ ይሻላል" ብለው ተነስተው ሄዱ። "ፀዲ እቤት እንሂድ አይደል?!" ብሎ አቤልም ይዟት ሄደ።

እቤት እንደደረሱ ሶፋ ላይ ጥቅልል ብላ ማልቀስ ጀመረች "እናቴ የኔ እናት ነይ እስኪ" ብሎ አቅፏት "ስላገኘሽው ነው? ስላገባ ነው? ምንድነው?!" አላት መጨነቁ በድምፁ እያስታወቀ

"ይቅርታ" አለች ሳግ እየተናነቃት "ለምኑ ነው ደግሞ ድንገት መገናኘታችን ያንቺ ጥፋት አይደለም እኮ"

"ትንሽ ላከብርህ ይገባ ነበረ ከአስራምናምን አመት በኋላ ሳገኘው በማግባቱ... የሚሳሳላት ሴት ማግኘቱ ሊያናድደኝ አይገባም ነበረ... አንተን ማግኘቴ በቂ ሊሆን አይገባም ነበር?"እንባዋ መንዠቅዠቁን ቀጥሏል

"እንዴ ፀዲ በእማማ ይዤሻለው በቃ አታልቅሺ እባክሽ እናቴ አታሳዝኚኛ እንዴ ያገኘነው እኮ ተራ ሰው አይደለም ታሪክ የነበረሽን ሰው ነው እና ከዚህ ሁሉ አመት በኋላ ስትገናኙ ምንም የማይሰማሽ መስሎሽ ነበረ?! አንዳንዱን ስሜት እኮ ማስቆም አንችልም መቅናት መናደድ ያለ ነው ያለፉ ነገሮች ላይ አቅም ስለሌለን ሊያናድድ ይችላል ለሱ ደግሞ እኔ አለሁ እሺ"

"እሺ ግን ስማ ሰብለ ቆንጆ ናት አይደል ባይወዳት ነበር የሚገርመው"

"አዎ ቆንጆ ናት ደስ ትላለች ግን ከኔ አስቀያሚ ሚስት አትበልጥም እሷ ስትነፋረቅ የሚያምርባት ይመስልሻል" ሲል የከለከሉትን መጫወቻ እንደሰጡት ህፃን ከለቅሷዋ መሀል ፍልቅልቅ አለች

"በይ ይበቃሻል እሁዳችንን ይሄን ያህል ካበላሸን ይበቃል ቀሚሱን እኮ በጥቁሩ ጫማ አላየሁትም" አላት እሷን ለማስረሳት ምን ማለት እንዳለበት ይውቃል "አዎ... አዎ በቡኒውም አሳይሀለው" ብላ እንባዋን እየጠራረገች ሮጣ መኝታ ቤት ገባች።

✍ናኒ

https://t.me/justhoughtsss

Показано 20 последних публикаций.