በክህደት አትሰበሩ!
➡️➡️➡️➡️🗣️
እምነቱን የበላ ሰው ፍርዱ ከምድር ሳይሆን ከሰማይ ነው፣ አልታየውም ብሎ በድብቅ በወዳጁ ላይ ሸፍጥ የሚሰራ ሰው ቅጣቱ ከሰው ሳይሆን ከፈጣሪ ነው። ከእናንተ የሚጠበቀው ማመን ነው፣ አምናችሁም ሁሉ ነገሩን ለፈጣሪ ስጡት። አምናችሁት፣ ልባችሁን ከፍታችሁለት፣ ራሳችሁን ሰጥታችሁት፣ በራሳችሁ ላይ ሾማችሁት ሳለ እርሱ ግን እምነታችሁን በልቶ፣ የሰጣችሁትን ሀላፊነት ሽሮ፣ የክህደትን ካባ ቢያከናንባችሁ በቅድሚያ ሰውነቱን አስታውሱ፣ በቀጣይነት ምክንያቱን አስተውሉ፣ በመጨረሻም ለራሳችሁ ደህንነትና ውስጣዊ ጤንነት ብላችሁ ለፈጣሪ አሳልፋችሁ ስጡት። ክህደት ትልቅ የልብ ስብራትን ያመጣል፣ ክህደት ያለፈውንም የሚመጣውንም ህይወት ጥላሸት ይቀባዋል፣ ክህደት በቀላሉ ለማይሽር ጠባሳ ይዳርጋል። የሰው ልጅ ለምን የገዛ ወዳጁን፣ ብዙ ክፉና ደግ አብሮ ያሳለፈውን፣ አንድ ሰሞን "የልቤ ነው።" የሚለውን ሰው እንደሚከዳ ቢመረመር ምናልባትም ይሔን ያህል ሚዛን የሚደፋና የሚያሳምን ምክንያት ላይገኝ ይችላል። የክህደት ገፈት ቀማሾች እናንተ ብቻ አይደላችሁም። ክህደት ትናንተ የነበረ፣ ዛሬም ያለ፣ ነገም እንዲሁ የሚኖር ክፉ ተግባር ነው።
አዎ! በክህደት አትሸበሩ፤ አንድ ያመናችሁት ሰው ቃሉን ስላጠፈ ራሳችሁን አትውቀሱ፣ በሌላው ጥፋት ራሳችሁን አትቅጡ። ቢዘገይ እንጂ ማንም ሰው የእጁን ማግኘቱ አይቀርም። ማንም ቃላችሁን በልቶ፣ ልባችሁን አድምቶ፣ ተስፋችሁን አጨልሞ፣ ህይወታችሁን አመሰቃቅሎ አይቀርም። የስራውን የምትሰጡት እናንተ ሳትሆኑ የእናንተንም የእርሱንም ልብ የሚያውቀው ፈጣሪ ነው። እናንተ ምንም ብታደርጉ አንዴ የተሰበረ ልባችሁን ልትጠግኑት አትችሉም። መፍትሔያችሁ አንድና አንድ ነው። እርሱም ራሳችሁን ብርታትና ፅናቱን እንዲሰጣችሁ ለፈጣሪ መስጠት፣ የከዳችሁን ሰውም እንዲሁ ለአምላካችሁ አሳልፎ መስጠት። እናንተ ምን በወጣችሁ በሰው ጥፋት ራሳችሁን ትቀጣላችሁ? እናንተ ምን ለማግኘት ያሳመማችሁን ሰው በልባችሁ አዝላችሁ ትኖራላችሁ? ጥፋት ሳታጠፉ የማንንም በደል አትቀበሉ፣ በሰው መበደላችሁ ሳያንስ ዳግም ራሳችሁን አትበድሉ። በወቅቱ ሁኔታውን መቀቡል ከባድ ቢሆንም ስራው ያውጣው የማለት ብርታት ይኑራችሁ። ያመናትን ሰው የከዳች ነፍስ መቼም ረፍት እንደማታገኝ አስታውሱ።
አዎ! ጀግናዬ..! ሰውን ማመንህ ሞኝነት አይደለም፣ ራስህን አሳልፈህ መስጠትህ ጥፋት አይደለም። ምናልባትም ጥፋት ሊሆን የሚችለው ሁሉም ሰው ልክ እንዳንተው ታማኝና ቃሉን የሚጠብቅ እንደሆነ ማሰብህ ሊሆን ይችላል። አንዳንዴ ያንተ ታማኝ መሆን ከመከዳት ላያድንህ ይችላል፣ ያንተ ጥሩና ሩህሩህ ሰው መሆን ከመገፋት ላያድንህ ይችላል። ህይወት እንዲህ እንደዚህ ነች። አንተ ከልብህ ታማኝ የልቤ የምትለው ሰው ግን ከዳተኛ፣ አንተ መልካም ሰው የእኔ ብቻ የምትለው ሰው ግን አስመሳይ መሰሪ ሊሆን ይችላል። እውነታውን ከመቀበል ውጪ ምንም አማራጭ የለህም። የሰው መጫወቻ መሆንህ ሳያንስ በገዛ ራስህ አትጫወት። አንዴ የፈሰሰ ውሃ አይታፈስም፣ አንዴ የተሰበረ ልብህም እንደቀድሞ ሊሆን አይችልም። እውነታውን ለማድበስበስ አትሞክር፣ የሆነብህን አምነህ ተቀበል። ዓለም ከጥቂት ከሃዲዎች በላይ ልክ እንዳንተ ባሉ ብዙ ታማኞች የተሞላች እንደሆነች እወቅ። ሰው ያቆሰለውን ልብህን ፈጣሪ በሰው ዳግም እንደሚያክመው እመን።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨⭐️
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪