MIKRE AIMRO | ምክረ-አዕምሮ™


Гео и язык канала: Весь мир, Амхарский
Категория: Психология


አስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣
አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣
ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው።
@mikreaimro
ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል!
ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ!
🏠Welcome to your Home! 🏘
Personal Contact: @epha_aschalew
Insta: instagra.com/epha_aschalew

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Весь мир, Амхарский
Категория
Психология
Статистика
Фильтр публикаций


ይቅርታን ውደዱ!
፨፨፨/////////፨፨፨
ልብ በአንድም በሌላም፣ ከአንዴም ሁለቴ ሶስቴ ይሰበራል። የሚሰበረው ታምኖ በሚከዳ፣ ተጠብቆ በሚቀር፣ ተከብሮ በሚያስ፣ ትልቅ ቦታ ተሰጥቶት ወርዶ  በሚገኝ ሰው ነው። ይቅርታም ይህን ስብራት የሚጠግን፣ ክፍተትን የሚሞላና ጠባሳን የሚሽር ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠ ፍቱን መድሃኒት ነው። ሰዎች ናችሁ አንድ ቀን ምድር ትከፋለች፣ ፊቷን ታዞርባችኋለች፣ በሰው ሚዛን ይቅርታ የማያሰጥ ጥፋትም ታጠፋላችሁ። በዚህም ወቅት ከእናንተ በላይ ይቅርታን አብዝቶ የሚፈልግ፣ የጥፋቱን መታረም፣ የበደሉን መሻር አብዝቶ የሚመኝ ሰው አይኖርም። በዚህ ሰው ቦታ ሆናችሁ የይቅርታን ልብ ይኖራችሁ ዘንድ ፀልዩ፤ ከፍርጃ የሚያርቅ፣ በደልን ሳይሆን ፅድቅን የሚኖር ማንነት ይሰጣችሁ ዘንድ አምላካችሁን ተማፀኑ።

አዎ! ጀግናዬ..! ይቅርታ ውስጥ ሰላም አለ፣ ይቅርታ ውስጥ ፍቅር፣ አንድነትና መተሳሰብ አለ። ለይቅርታ እጁን የዘረጋን ሰው አንተ ይቅር ባትለው ፈጣሪ ይቅር ይለዋል፤ አንተ መመፀፀቱን ባትቆጥርለት አምላኩ የልቡን ያውቃልና በቸርነቱ ይምረዋል፣ በርህራሔውም በደሉን ይሽርለታል። ማንም ባጠፋው ልክ፣ በበደሉ መጠን መክፈሉ አይቀርም። ነገር ግን ክፍያውን ባንተ መንገድ እንዲያደርግ፣ ጥፋቱም ባንተ በኩል በጥፋት እንዲመለስ አትፈልግ። ሁሉንም ነገር በፍርዱ ለሚያስተምረው፣ በጊዜው ምላሽን ለሚሰጠው፣ እየወደደም ቢሆን ዝም ለማይል፣ መሃሪም ቢሆን ለሚቀጣ አምላክ አሳልፈህ ስጥ። ይቅርባይነትህ ሞኝነት ሳይሆን ብስለት ነው፤ ይቅርባይነትህ ዋጋቢስነት ሳይሆን ለእራስህ የምትሰጠውን ክብርና ቦታ የሚያሳይ ነው። ይቅር ስትል ለእራስህ ውለታ እየዋልክ ነው፤ ሰላም የነሳህን ተጎጂነት ከውስጥህ እያወጣህ ነው፤ እራስህን ከህመምና ከስቃይ እየጠበክ ነው።

አዎ! ይቅርታን ውደዱ! ሰላማችሁን አስቀድሙ፣ የእረፍታችሁ ምክንያት፣ የእርጋታችሁ መንስኤ እራሳችሁ ሁኑ። ማለፍ ያለበት ነገር ልክ እንደ ወራጅ ውሃ እናንተንም ይዟችሁ እንዲያልፍ አትፍቀዱ። ለሚያልፍና ለሚረሳ ጉዳይ የማይገባውን ዋጋ አትክፈሉ። የይቅርታ አምላክ አላችሁ፣ የምህረት ጌታ፣ በደልን የሚተው፣ ኀጢአተኛን የሚፈልግ፣ ፅድቁንም በትዕግስት የሚጠብቅ ፈጣሪ አላችሁ። በምድራዊ ህይወታችን ከሰማያዊ አባታችን ስራ በቀር በገቢር የሚያስተምረን፣ በተግባርም ዋጋችን በተለየ ሁኔታ የሚጨምርልን ነገር የለም። የውድቀታችሁ ምክንያት ሰዎች ቢሆኑ፣ የህመማችሁና የስብራታችሁ መንስኤ ሰዎች ቢሆኑ ዳግም የመነሳት፣ እራሳችሁን የመጠገንና ዋጋችሁን የመጨመር ምክንያታችሁ ደግሞ አንድም ፈጣሪያችሁ ነው፤ ሌላም እራሳችሁ ናችሁ። ስለይቅርታ በምታውቁት ልክ በህይወታችሁ ተግብሩት፣ በእርሱም ሃይል ሰላማችሁን መልሱ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨⭐️
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪




📣💥 ምዝገባው ሊጠናቀቅ 4 ሰዓት ብቻ ቀርቶታል!

❗️ፈጥነው ይመዝገቡ!

የተግባር ሰው መሆን!
BEING PRACTICAL

✍️ ለመመዝገብ በዚህ አድራሻ መልዕክት ያስቀምጡ
@epha_aschalew or
0960411282

ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋


ተነሱና ስሩ!
➡️➡️🗣️
አጭር ነው፣ ግልፅ ነው፣ አሁን መደረግ የሚችል ነው፣ በትንሹ የሚጀመር ነው። አሁን ምንም ስራ ከሌላችሁ፣ ምንምአይነት የገቢ ምንጭ ከሌላችሁ ስራ መናቅ አቁሙና ምንም ይሁን ምን ተነሱና ስሩ፣ ተነሱና ወደ ተግባር ግቡ። ገቢ አስጋስገኘ ድረስ ከባህል ከእሴታችን፣ ከሀይማኖት ከትውፊታችን እስካልወጣ ድረስ ምንም የወረደ ስራ የለም። ስራ እየናቀ ህይወቱን የቀየረ ሰው የለም፣ ስራ እየመረጠ የከበረ ሰው የለም። በቀኝም ዞራችሁ በግራ ስራ የማትሰሩ ከሆነ ማንም የሚሰራው ላይ የመፍረድና ጣት የመቀሰር መብቱ የላችሁም። ቁጭ ብላችሁ ብዙ ገንዘብ ታገኙ ይሆናል፣ ከቤተሰብ ከወዳጅ ከዘመድ የወጪ ታገኙ ይሆናል ነገር ግን ከሰው የሚመጣ ነገር ሁሌም የእናንተ ሊሆን እንደማይችል እወቁ። እድሜያችሁ ለስራ ደርሶ፣ አቅማችሁ ጎልብቶ፣ ገንዘብ አስፈልጓችሁ ቁጭ ብላችሁ ሰውን መለመን ልማዳችሁ ካደረጋችሁ አሁኑኑ ብትነቁ ይሻላችኋል። ምንም ስራ ሳይኖራቸው ስራን የሚንቁ፣ ምንም የሚያስገቡት ገቢ ሳይኖር ትንሽ ገንዘብ የሚንቁ ሰዎች በገዛ እጃቸው ለውድቀት ራሳቸውን የሚያመቻቹ ሰዎች ናቸው። የሚሰራን እየናቃችሁ ህይወታችሁ እንዲቀየር አትፈልጉ።

አዎ! ተነሱና ስሩ! ወስኑና እርምጃ ጀምሩ። ሳይሰሩ፣ አንዳች የወደቀ ነገር ሳያነሱ፣ ምንም እንቅስቃሴ ሳያደርጉ እንዲሁ ራስን ጠብቆ ፅድት ንፅት ብሎ መውጣት እውቀትም ጥበብም አይደለም። መስራት እየቻለ ሳይሰራ የሚበላ፣ ህይወቱን የመቀየር አቅም እያለው ከሰው የሚጠብቅ፣ ራሱን መቻል ሲኖርበት ለዓመታት ሰውን የሚያስቸግር እርሱ የመጨረሻ ሰነፍና የወደቀ ሰው ነው። የማይገባችሁን ቦታ ለራሳችሁ አትስጡ፣ ከአቅማችሁ በላይ ለመኖር አትሞክሩ፣ ሰው እንዲያዝንላችሁ ራሳችሁን አቅመቢስ ደካማ አታድርጉት። ሁሌም ቢሆን ባለው ያምርበታል፣ የሰራ፣ የለፋ፣ የሞከረ ህይወቱን ያሸንፋል። ጥሮ፣ ግሮ፣ ለፍቶ ሞክሮ ያልተሳካለትና እንዲሁ ቁጭ ብሎ የሰው እጅ የሚጠብቅ መሃል ያለው ልዩነት እጅግ ሰፊ ነው። ስለሰራችሁ ብቻ በአንዴ ያልፍላችኋል ማለት አይደለም፣ ምንም ካልሰራችሁ ግን መቼም አያልፍላችሁም። ያ ሞክሮ የተሳሳተው፣ የሚችለውን አድርጎ ያልተሳካለት ሰው የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሙከራውን እስካላቆመና ጥረቱን እስከቀጠለ ድረስ አንድ ቀን የፈለገበት መድረሱ አይቀርም። ነገር ግን ምንም የማይሞክረው፣ ምንም ጥረት የማያደርገው ሰው መቼም ስኬታማ እንደማይሆን እርግጠኛ መሆን ይችላል።

አዎ! ጀግናዬ..! አራዳ ሁን። ባለው አየር ተንቀሳቅሰህ ህይወትህን ወደፊት ፈቀቅ አድርገው፣ ያገኘሀውን እየሰራህ ቀስ ብለህ እደግ። ድህነት ቤት እስኪሰራብህ አትጠብቅ። ትንሽም ብትሆን ሰርተህ የምታገኛት ጥሪት ነፃነትን ትሰጥሃለች፣ በራስመተማመንን ታጎናፅፍሃለች፣ በራስህ እንድትኮራ ታደርጋለች። ስራም ሆነ ገንዘብ፣ ሰራተኛም ሆነ ለፍቶ አዳሪ አትናቅ። የወጣት ተጧሪ ከመሆን ምንም ስራ ሳይመርጡ መስራት እጅጉን ያስከብራል። ዘመኑ እንኳን ሳይሰራ ተሰርቶም ከባድ ሆኗል፣ ጊዜው እንኳን እጅ አጣጥፎ ተቀመጦ ቀን ከሌሊት ተለፍቶም አልሸነፍ ብሏል። በፍፁም ማንም የሚበጅህን እንዲነግርህ አትፈልግ፣ በፍፁም ማንም እስኪጎተጉትህ አትጠብቅ። ራስህን ግፋው፣ ራስህን ስቃይ ውስጥ ክተተው፣ ራስህን ከመቾት ውስጥ አስወጣው። ጥረህ ግረህ፣ ለፍተህ ደክመህ በላብህ የራስህንም በዙሪያህ ያሉ ወዳጆችህንም ህይወት ቀይር። ጊዜው ጥሎህ እየሔደ አንተ ወደኋላ አታፈግፍግ። ከጊዜ እኩል ተራመድ፣ ለነፃነትህ የሚጠበቅብህን መሱዓትነት ሁሉ ክፈል።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪


💗ፍቅር አለ!💗
➡️➡️➡️🗣️🗣️
ትዋደዳላችሁ፣ ትፋቀራላችሁ፣ ትተሳሰባላችሁ፣ አንዳችሁ ያለአንዳችሁ የምትኖሩ አይመስላችሁም፣ ግንኙነታችሁ የጠበቀ፣ ቅርበታችሁ ከፍ ያለ ነው። ነገር ግን በመሃከላችሁ መከባበርና መተማመን የለም፣ ነገር ግን አንዳችሁም ለእራሳችሁ መብት ገደብ አታስቀምጡም፣ አንዳችሁም ለአጋራችሁ ነፃነት ለመስጠት አትሞክሩም፣ ነገሮችን ቀለል አድርጎ ማለፍ አትፈልጉም፣ ታካብዳላችሁ፣ እናንተ ያላችሁት ብቻ እንዲሆን ትፈልጋላችሁ፣ ለግንኙነታችሁ ግብ አላስቀመጣችሁም። ከእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ግማሾቹም ቢሆኑ የእናንተን ግንኙነት የሚመለከቱ ከሆነ የሚጎዳችሁ ግንኙነት (toxic relationship) ውስጥ እንደሆናችሁ አስተውሉ። ፍቅራችሁ ብቻ ለዘላቂውና ለተረጋጋው ግንኙነታችሁ ዋስትና ሊሆናችሁ አይችልም።

አዎ! ጀግናዬ..! ፍቅር አለ፣ ነገር ግን ብቻውን በቂ አይደለም። መዋደድ ይኖራል፣ ነገር ግን ጠንካራ መሰረት ላይ ካልተገነባ የትም አያደርስም። ያላችሁበት ግንኙነት ጤነኛ እንዳልሆነ ከተረዳችሁ በጊዜ ለማስተካከል ሞክሩ። ማንም ለእናንተ ግንኙነት አስደሳችነትና ስኬታማነት ከእናንተ በላይ ሊሰራ እንደማይችል እወቁ። ምናልባት አንዳንድ ግንኙነቶች የተወሳሰቡ ይሆናሉ፣ አንዳንዶችም ምንም የወደፊት አላማ የሌላቸው ይሆናሉ። ነገር ግን ግንኙነት እስከሆኑና በፍቅር ስም እስከተመሰረቱ ድረስ ስሜትን መጉዳታቸው፣ የህይወት ጉዞን ማዛባታቸውና በትርጉም አልባ እስራት ለከፋው ስቃይ መዳረጋቸው አይቀርም። ዋጋ የማትከፍሉለት ግንኙነት የትም እንደማይደርስ እናንተም ታውቁታላችሁ፤ በምትኩ ትዕግስትን የምትኖሩበት፣ ለንግግር ቅድሚያ የምትሰጡበት፣ ግልፅነትን የምትመርጡበት፣ ክብርና እምነት ላይ የምትመሰርቱት ፍቅር ደግሞ ውጤታማ እንደሚሆን ታውቃላችሁ።

አዎ! ላቁመው ብትል የሚይዝህ ነገር አለ፣ ለመለያየት ከወሰንሽ ቦሃላ በውሳኔሽ መፅናት ይከብድሻል። አንዳንዴ እንደማይዘልቅ ታውቃላችሁ ነገር ግን ሁለታችሁም ለጊዜያዊ ስሜታችሁ በመገዛት ተመሳሳይ የሚጎዳችሁ ጉንኙነት ውስጥ ለረጅም ጊዜ ትቆያላችሁ። የማያተርፍላችሁ ግንኙነት ምናችሁ ነው? ሰላም የማይሰጣችሁ፣ ውስጣችሁን የማያረጋጋ፣ ባላችሁ ጥራት ላይ ጥራትን፣ ባላችሁ እውቀት ላይ  እውቀትን የማያክልላችሁ የፍቅር ግንኙነት ምናችሁ ነው? ጥቅሙስ ምንድነው? መቅረፍ ያለባችሁን ጉዳይ በጊዜ ቅረፉ መለያየትን እየፈራችሁ የስቃይ ዘመናችሀን አታርዝሙ፣ በፍቃዳችሁም በፍቅር ስም እራሳችሁን አትቅጡ። በቻላችሁት መጠን ለፍቅራችሁ ታመኑ፣ የሚገባውን ክብርም ከልባችሁ ስጡት።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨⭐️
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪




📣💥 የስልጠናችን ምዝገባ ሊጠናቀቅ ከ 1 ቀን ያነሰ ጊዜ ብቻ ቀርቶታል!

❗️ፈጥነው ይመዝገቡ!

የተግባር ሰው መሆን!
BEING PRACTICAL

✍️ ለመመዝገብ በዚህ አድራሻ መልዕክት ያስቀምጡ
@epha_aschalew or
0960411282

ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋


•// የበታችነት ስሜት አይሰማችሁ •\\

በአንዲት ጠብታ ውስጥ ያለው፣ በውቅያኖስ ውስጥም አለ፡ ዮጋ ይህንን ሱትራ ሁልጊዜም የሚናገር ቢሆንም ሳይንስ የደገፈው ግን በቅርቡ ነው፡፡ አንድ አተም በውስጡ ይህን ሃይል ይይዛል ብሎ ማንም አስቦ አያውቅም፡፡ በዚህ እጅግ በጣም ትንሹ በሆነው የቁስ ክፍል ውስጥ ይህ ሁሉ ሃይል ተደብቆ እንደሚገኝ ማንም አስቦ አያውቅም።

ይህ የዮጋ እይታ ሳይንሳዊ መሆኑ የተረጋገጠው አተምን ወደ ንዑስ አተምነት በመከፋፈል በተደረገው ጥናት ነው፡፡ አንድ አተም በአይን አንኳን ሊታይ አይችልም፤ ይሁን እንጂ በዚህ በአይን በማይታይ አተም ውስጥ ግዙፍ ሃይል አለ፡፡

በሰው ውስጥም የነፍስ አተም በአይን አይታይም። ሆኖም ግን እጅግ በጣም ግዙፍ ሃይል በውስጡ ተደብቆ ይገኛል። ይህ ሃይል፤ ሊገልፅ ሊወጣም ይችላል። ዮጋ እጅግ በጣም በትንሹ ውስጥ እጅግ በጣም ትልቁ እንደሚገኝ ሲናገር በእያንዳንዱ ቅንጣት (particle) ውስጥ የአምላክን መኖር እየገለፀ ነው፡፡

ዮጋ ለዚህ ሱትራ አፅንዖት የሰጠው ለምንድን ነው?

የመጀመሪያው ምክንያት እውነታው እሱ ስለሆነ ነው። ሁለተኛው ምክንያት በትንሹ ውስጥ ትልቁ ተደብቆ እንደሚገኝ ከታወቀ ሰው የራሱን ውስጣዊ አቅም እንዲያስታውስ ስለሚረዳው ነው፡፡ ሰው ትንሽ መሆኑ ሊሰማው የሚችልበት ምክንያት የለም። እጅግ በጣም ትንሹ እንኳ ትንሽነት ሊሰማው የሚችልበት ምክንያት የለም፡፡

ከዚህ በተቃራኒም እጅግ በጣም ሰፊውና ትልቁ እንኳ በኢጐ ስሜት ሊሞላ አይገባውም፤ ምክንያቱም እሱ ውስጥ ያለው እጅግ በጣም ትንሹ ውስጥም አለ፡፡ አንድ ውቅያኖስ በኢጐ ስሜት ከተሞላ እብደት ነው፤ ምክንያቱም እሱ ያለውን ጠብታውም አለው፡፡ ትንሹ የበታችነት፣ ትልቁ ደግሞ የበላይነት ሊሰማቸው የሚችልበት ምክንያት የለም፡፡ የበታችነትም ሆነ የበላይነት ትርጉም የላቸውም፡፡ ሁለቱም ትርጉም አልባ ናቸው ፡፡ ይቀጥላል ........

ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪


ጊዜ ይፈርዳል!
➡️➡️➡️🗣️
ዛሬ ከፍታ ላይ ያላችሁ፣ ዛሬ ዓለምን በመዳፋችሁ የጨበጣችሁ የመሰላችሁ፣ ዛሬ ምቾት ያንገላታችሁ፣ ህይወት የመረጠቻችሁ፣ ኑሮ የፈካላችሁ፣ በላይ በላይ ስኬት የተደረበላችሁ፣ ወዳጅ ዘመድ ፈላጊ አጨብጫቢ የበዛላችሁ አስተውሉ አንድ ቀን ዝቅ ትሉ ይሆናል፣ አስተውሉ የሆነ ጊዜ ያገኛችሁትን ሁሉ ታጡ ይሆናል፣ አስተውሉ የሆነ ሰዓት ብቻችሁን ትቀሩ ይሆናል። ዛሬ ዝቅታ ላይ የተገኛችሁ፣ ዛሬ ዓለም የናቀቻችሁ፣ ዛሬ እድል የጠመመችባችሁ፣ ወዳጅ ዘመድ የራቃችሁ፣ ግፊት ጥላቻን የተቸራችሁ፣ ሳትፈልጉ ብቻችሁን የቀራችሁ፣ ህይወት ፊቷን ያዞረችባችሁ፣ ስኬት እንደ ሰማይ ደስታም እንደ ጨረቃ የራቀቻችሁ አስተውሉ ዝቅታ መጨረሻችሁ አይደለም፣ አስተውሉ በዓለም እንደተናቃችሁ አትቀሩም፣ አስተውሉ ብቸኝነት የዘላለም እጣፋንታችሁ አይደለም። ጊዜ በጊዜው ይፈርዳል፣ ትክክለኛው ሰዓት ሁሉን ነገር ያስተካክላል። ገዢ የነበሩ ተገዢ ይሆናሉ፣ መሪ የነበሩ ተመሪ ይሆናሉ፤ በተቃራኒውም ተገዢ የነበሩ ይገዛሉ፣ ሲመሩ የነበሩ የመሪነትን ዙፋን ይረከባሉ። ስታገኙም ስታጡም፣ ስትሔዱም ስትመለሱም፣ ሲያልፍላችሁም ሲያልፍባችሁም ስሜታችሁን በልክ አድርጉት።

አዎ! ጊዜ ይፈርዳል! ጊዜ ሁሉን በግልፅ ያሳያል፣ ጊዜ ስንዴውን ከእንክርዳዱ፣ ደጉን ከክፉን፣ መልካሙን ከጎጂው ይለያል። አለኝ ብላቹ አትመፃደቁ፣ አጣው ብላችሁም አንገት አትድፉ። ሰጪም ነሺም ፈጣሪ መሆኑን አስታውሱ። ማግኘታችሁ አጥፊያችሁ ከሆነ አይሰጣችሁም፤ ማጣችሁም የሚጎዳችሁ ከሆነ ይሰጣችኋል። ችግር በዝቶባችኋል ማለት እግዚአብሔር ከሰው ሁሉ ለይቶ ይጠላችኋል ማለት አይደለም፤ ምቾት በምቸት ሆናችኋል ማለትም ፈጣሪ ከሰው ሁሉ ለይቶ ይወዳችኋል ማለት አይደለም። እያንዳንዱ ነገር የሚሆነው በምክንያት ነው። ቻዩን ፈጣሪ ያውቃል፣ ደካማውንም እርሱ ያውቃል። እርሱ የሰጣችሁን የሰጠበትን ምክንያት የሚያውቀው እራሱ ብቻ ነው። የእናንተ ድርሻ መቀበልና መቀበል ብቻ ነው። ባለስልጣኑ ባለበት ስልጣን ፈላጊ አትሁኑ፤ ፈላጭ ቆራጩ እያለ በእርሱ ስራ ጣልቃ አትግቡ። ህይወት ምርጫ ነች አንዳንድ ወሳኝ ሁነቶች ግን የፈጣሪ ገፀበረከቶች ናቸው። ሮጣችሁ ማምለጥ ከማትችሉት ነገር ስር አትሩጡ፤ መጨነቅ፣ መጠበብ፣ መዋከብ ለማያስተካክለው ነገር ራሳችሁን አታስጨንቁ፣ ራሳችሁን አታዋክቡ።

አዎ! ጀግናዬ..! ከቀረበልህ የመምረጥ ምርጫ አለህ፣ የተመረጠልህን ግን ከመምረጥ በላይ የመኖር ግዴታ አለብህ።  የትናንት ድካምህ፣ የዛሬ ጥረትህ፣ የአሁን ልፋትህ ፍሬ የሚያፈራበት ጊዜ አለ። የተሻለ ነገን ቁጭ ብለህ አትመኝ፣ ያለስራ መልካም ነገር እንዲገጥመህ አትፈልግ። ጊዜ ሁላችንም ላይ ፈጣሪ የሾመብን ፈራጃችን ነው። ማንም ያልሰራውን ያገኝ ዘንድ አልታዘዘለትም፣ ማንም ያልደከመበት እንዲሰጠው አልተፈረደለትም። ዛሬ የትም ሁን፣ አሁን ምንም ስራ ነገር ግን በስራህ የምታምን፣ ነገህን መቀየር የምትችል፣ ሰው ከሚያስብልህ በላይ ፈጣሪ እንደሚያስብልህ ካመንክ በእርግጥም ምንም ነገር ሊቀየር ይችላል፣ የትኛውንም ከባድ ጊዜ ማለፍ ትችላለህ። ድህነት የህይወት ዘመን እጣፋንታህ አይደለም፣ ማጣት፣ መቸገር፣ መገፋት የተፈረዱብህ ፍርጃዎችህ አይደሉም። ላንተም ቀን እንደሚመጣ፣ ላንተም ፀሃይ እንደሚወጣ፣ ህይወትህ በአምላክ ፀጋና በረከት እንደሚታነፅ ከልብህ እመን። እየተገፋህ፣ እየተጠላህም ቢሆን ጊዜ ከፍ ያደርግሃል፤ ዛሬ ብትረሳም በሞገስ በግርማ አበይት የምትሆንበት ጊዜ ይመጣል። በራስህንም ሆነ በፈጣሪህ መቼም ተስፋ እንዳትቆርጥ።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪


ነፍሳችሁን አትርፉ!
➡️➡️➡️🗣️🗣️
ወጣን ውረድን፣ ስራን አረፍን፣ ሞከርን ሳንሞክር ቀረን፣ ደከምን ሳንደክም ቀረን፣ ዓለምን ዞርን ምድርን አሰስን በስተመጨረሻ አንድ መዳረሻ አለን። እርሱም ወደ አንድ አምላክ ወደ ቅዱስ ፈጣሪ መሔድ ነው። ያኔ እርሱ ፊት የቆምን እለት ምን እናሳየው ይሆን? የትኛው መልካም ስራችን ይመሰክርልን ይሆን? ከየትኛው ትርፋችን ቀድተን እናሳየው ይሆን? ማንም ሆንን ማንም ዳኛችንና ገዢያችን ፈጣሪ ብቻ ነው። በዓለም ሳላችሁ ምን ገዝቷችኋል? በምድር ስትመላለሱ ምን ነፍሳችሁን ወስዷታል? አሁን በዚህች ቅፅበት የሚያሳስባችሁና ቀልባችሁን የሰረቀው ነገር ምንድነው? በውሸት ዓለም እየኖራችሁ ራሳችሁን አትካዱ፣ ነገ ዞር ብሎ ለማያያችሁ ሰው ብላችሁ ራሳችሁን አትጡ፣ በአንድ ጀምበር አመድ በሚሆን ንብረት ፈጣሪያችሁን አትካዱ። የሰው ልጅ ስጋው ብቻ የስጋ ፍቃዱን ስለፈፀመ አይኖርም። ነፍሱም የራሷ ፍቃድ አላትና ፍቃዷ ሊፈፀም ይገባል። ነፍስ እለት እለት የአምላኳን መንፈስ ትጠማለች፣ ነፍስ በየጊዜው ሰማያዊ ሀሴትን ትናፍቃለች።

አዎ! ነፍሳችሁን አትርፉ! የማትሞላዋን ዓለም ለመሙላት አስር ቦታ አትበጣጠሱ፣ የሌለውን ፍፁም ህይወት ለመኖር ብኩን አትሁኑ። ዞሮ ዞሮ ማንም ሰው የሚበላው ያንኑ የዘራውን ነው፤ በስተመጨረሻ ማንም ሰው በእጁ የሚያስገባው ያንኑ የደከመለትን ነገር ነው። ያለ ምንም እረፍት ስጋውን ብቻ ሲመግብ የነበረ ሰው የስጋ ፍቃዱ ሲያይል፣ ለዓለም ብልጭልጭ ሲገዛ፣ ነፍሱ ተጨንቃ ስታስጨንቀው፣ በቁስ ተከቦ ባዶነት ሲያሰቃየው፣ ብዙ ወዳጅ እያለው አንዱም መፍትሔ ሳይሰጠው ሲቀር ራሱን ይመለከታል። ስጋና ዓለም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው። ዓለምን የሚወድ የስጋው ባሪያ ነው፣ መንፈሱን የሚሰማ ግን የነፍሱ ተገዢ ነው። ነፍሳችሁን ጥላችሁ ሁለንተናዊ ብልፅግናን እንዳታስቡ፣ የነፍሳችሁን ፍቃድ ችላ እያላችሁ ደስተኛ እሆናለሁ ብላችሁ እንዳታስቡ። ስጋ የሚበላውን የሚጠጣውን ያህል ነፍስም እንዲሁ የምትበላውና የምትጠጣው ነገር ያስፈልጋታል፣ ስጋ መሳቅ መጫወት እንደሚወድ ሁሉ ነፍስም እንዲሁ የአምላኳን ፍቅር አብዝታ ትናፍቃለች፣ ከእርሱ የሚገኘውን ሀሴት ትጠብቃለች።

አዎ! ጀግናዬ..! በስጋ ፍቃድ ተታለህ ነፍስህን አትበድላት፣ በዓለም ፍቅር ታውረህ የፈጣሪህን በረከት አትጣ። ምንም ያህል ዓምት ምድር ላይ ብትመላለስ፣ ምንም አይነት የተንደላቀቀ ህይወት ብትኖር፣ ከማንም በላይ ትልቅ ስልጣን ቢኖርህ፣ ምንምያህል ታዋቂና ዝነኛ ብትሆን አንድ ቀን እንደ ማንኛውም ሰው ለዓለም ባዳ ለምድርም ወዳጅ መሆንህ አይቀርም። ሁሉን ትተህ ወደ አምላክህ መሔድህ ግልፅ ነው። መሔድህ ካልቀረ ግን ባዶ እጅህን አትሔድ ዘንድ ነፍስህን የሚያስደስት፣ አምላክህንም የሚስመሰግን በጎ ስራን ስራ፤ ከሰው ፊት በላይ ፈጣሪህ ፊት ሞገስን የሚያሰጥህን መልካሙን ምግባር ፈፅም። ጠፍተህ እንደሆነ ራስህን በጥልቀት መርምር፣ ራስህን አጥተህም እንደሆነ ማንነትህን ለመረዳት ሞክር። ፀሃይ በአንዴ አታቃጥልም የዓለም ግለትም እንዲሁ ቀስበቀስ እያሞቀ አለማምዶ በዛው አቅልጦ ያስቀራል። በዓለም እስታ ተቃጥሎ ከመጥፋት ራስህን ጠብቅ፣ በስጋ ፍቃድ ከመገዛት ተቆጠብ፣ ነፍስህን ዋጋ አታሳጣት። መንፈስህን ታደግ፣ ራስህን ግዛ፣ ዓለምንም በፍቃድህ ስር አድርግ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨⭐️
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪




📣💥 ስልጠናችን 2 ቀን ብቻ ቀርቶታል!

❗️ፈጥነው ይመዝገቡ!

የተግባር ሰው መሆን!
BEING PRACTICAL

✍️ ለመመዝገብ በዚህ አድራሻ መልዕክት ያስቀምጡ
@epha_aschalew or
0960411282

ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋


ከፍጥረታት ተማር!
➡️➡️➡️🗣️🗣️
የእድገት ነፃነት አለውና በተቻለው አቅም እስከመጨረሻው ያድጋል። ዛፍን ተመልከት እስክ ጫፍ ያድጋል፤ አንበሳን ተመልከት እስከመጨረሻው ታግሎ አድኖ ይበላል፤ ንስርን ተመልከት ከየትኛውም አዕዋፍ በላይ በከፍታ ላይ ይበራል። እያንዳንዳቸው ፍጥረታት የመጨረሻውን አቅማቸውን ይጠቀማሉ። የሰው ልጅ ግን በምርጫው ይታለላል፤ ድክመቱን ይንከባከባል፤ አለመቻሉን ደጋግሞ ያወራል፤ አደጋን በመፍራት ይታሰራል። ማሰብ መቻሉ ብዙ መስራት እንዲችል እንደሚያደርገው ረስቶታል። አንድ ቦታ ታስሮ ከእፅዋት ባነሰ የእድገት ደረጃ ውስጥ እራሱን ያገኘዋል። ፍጥረታት ምርጫ የላቸውም፤ እድገታቸው ግዴታ ነው፤ አድኖ መብላታቸው ምርጫ ውስጥ አይገባም። ወድቀው ተነስተው፣ ተሰብረው ተጋግጠውም ቢሆን የፈለጉትን ያሳካሉ፤ በእጃቸውም ያስገባሉ። በእንስሳት አለም ሰዶ ማሳደድ፣ ማደን መታደን ህይወታቸው ነውና አንዱ አንዱን አድኖ ለመብላት እስከመጨረሻው መፋለም ይኖርበታል፤ ሌላኛውም ነፍሱን ለማትረፍ ሙሉ አቅሙን ይጠቀማል።

አዎ! ጀግናዬ..! ከፍጥረታት ተማር! ከእድገት፣ ከለውጥና ከስኬት ውጪ ምርጫ እንደሌለህ አስብ። ብዙ አማራጮች ባስቀመጥክ ቁጥር የምትወድቀው አንተ ነህ። አንድ የምትተማመንበት ነገር የለምና ሁሉን ለመያዝ ስትሞክር አንዱንም ሳትይዝ ባዶ እጅህን ትቀራለህ። የያዝከው ብቻ እንደሚያዋጣህ እመን፤ የሚያስከፍልህን ለመክፈል እራስህን አዘጋጅ፤ እንዳታደርገው የሚያደርጉህ ብዙ እንቅፋቶች ቢኖሩም ከማድረግ በቀር ሌላ አማራጭ እንደሌለህ አስተውል። ከውሃ የወጣች አሳ በደቂቃዎች ትሞታለች፤ አንተም ህልምህን መኖር እንዳቆምክ የህይወትን ትርጉም ታጣለህ፤ አላማህ ይጠፋብሃል፤ በመኖርህ ውስጥ ስሜት ታጣለህ፤ የሚገባህን ባለማግኘትህ ስብራት ይሰማሃል። ብዙ ምርጫ ቢኖርህም ምርጫህን እርሳው፤ ብዙ የገቢ ምንጭ ቢኖርህም አንዱን አጥብቀህ ያዝ፤ በብዙ ሰዎች ብትከበብም ጥቂቶቹን ብቻ አቅርብ።

አዎ! የበዛው ምርጫህ እንዳይሸውድህ ተጠንቀቅ፤ የምታገኘው ገቢ እንዳያሰንፍህ፣ የከበቡህ እንቅፋቶች፣ የሚወሩብህ ወሬዎች ከሚገባህ ህይወት እንዳይነጥሉህ እራስህን ጠብቅ። ዛሬን ብቻ ብኖር፣ ህይወቴ ባይስተካከል፣ እራሴን ባላስተምር፣ በሒደት ባላድግ የሚጠብቀኝ ጥፋት ነው ብለህ ማሰብ ጀምር። ምርጫ የሌለው ሰው ተኝቶ አያድርም፤ ቀን ከሌሊት ሲለፋና ሲተጋ ይውላል፤ ያድራል። እድገት ምርጫው ሳይሆን ግዴታው ነው፤ ለውጥ አይቀሬ ቢሆንም በአዎንታዊውና ጠቃሚው ለውጥ ግን አይደራደርም። እድገትን የማይፈልግ፣ ስኬትን የማይመኝ ሰው አይኖርም፤ ፍላጎቱ ግን በሃሳብ ወይም በምኞት ብቻ ስለሆን ምንም ሊያመጣ አይችልም። እድገትን በተግባር፣ ስኬትን በጥረት፣ ደስታን በስራ፣ ህይወትንም በመኖርን ፈልግ። በምንም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ለውጥና እድገት ምርጫ የሌለው አማራጭህ እንደሆነ አስተውል።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨⭐️
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪




ልቤን መልስልኝ!
➡️➡️➡️🗣️🗣️
ፍቅር ነህ፤ አባት ነህ፤ ደግ፣ አዘኛ፣ አሳቢ ንፁህ ጌታ፣ ፍፁም አምላክ ነህ። ለስራህ የሚመጥን ቃል ባይኖርም፣ የሚገልፅህ አገላለፅ ባይገኝም አንተ ግን የአማልክት አምላክ የጌቶች ጌታ ነህ። ትናንት ነበርክ፣ ዛሬም አለህ፣ ነገም ለዘለዓለም ትኖራለህ። ይቅርታህ እጅግ ግሩም ነው፤ ሳትለመን የምትምር፣ ሳትጠየቅ የምትፈውስ፣ ሳይማፀኑህ፣ ሳያለቅሱብህ ይቅር የምትል፣ ትዕግስትህ ገደብ የሌለው፣ ጠብቀህ የማይደክምህ፣ ለቅንነትህ ዳርቻ፣ ለቸርነትህ መጨረሻ የሌለህ አንተ በእርግጥም ፍቅር ነህ፣ አባት ነህ፣ ቸር ጠባቂ ነህ። ስትምር ልኩን ታውቀዋለህ፣ ይቅር ስትል ማሳረፉን ትችላለህ። ቃል አለህ በሰማይ በምድር ልጆችህን ደጋግመህ ለመማር፣ ይቅር ለማለት፣ ለማስተማር። ቃልህንም ስትጠብቅ ኖረሃል፣ ከአባትም በላይ አባት ሆነህ በቃልህ ልክ ተገልጠሃል፤ ምህረትህንም ያለገደብ ሰጥተሃል።

አዎ! ጀግናዬ..! የሚመጥነው ቃል ብታጣ፣ የሚወክለው አገላለፅ ባታገኝ ፍቅር ነህ፣ ደግ ፍፁም አምላክ ነህ በለው። ነገር ግን ፍቅሩ እስኬት ይሆን? ከፈጣሪ ውጪ ምህረትን ማን ያውቃል? ይቅርታን ማን ይወክላል? በንፅህና ማን ይገለፃል? በትዕግስት ማን ይወከላል? ምህረቱ እንጂ ስራችን መቼም ከፊቱ አያቆመንም፤ ቸርነቱ እንጂ ምግባራችን ስሙን ለመጥራት አያበቃንም፤ ርህራሔው እንጂ ማንነታችን ከቤቱ አያቀርበንም። እለት እለት ብንበድልም እለት እለት እየማረ እዚህ አደረሰን፤ በየቀኑ ብናሳዝነው እስከዛሬ ታገሰን፤ ሳናቋርጥ ብናስቀይመው፣ ከትዕዛዙ ብንወጣ፣ ከመንገዱ ብንለየ ጥበቃው ግን ሁሌም አብሮን ነው። ልጅ በአባቱ ይመካል፤ በእናቱም ይፅናናል። አባትነቱ በፈጣሪነት ውስጥ ነውና ክብርን ክብር ላይ እየጨመረ እዚህ አድርሶናል፤ ለዚህም አብቅቶናል።

አዎ! በእርግጥም አምላክን ምን ይገልፀው ይሆን? ፍቅር ነው መባሉ የፍቅርን ዋጋ ከማግዘፉ በላይ እርሱን አይወክለውም፤ ፍፁም መባሉም የፍፁምነትን ዳርቻ ቢያሳይ እንጂ ብቻውን ሊገልፀው አይችልም። መምከር፣ ማስተማር፣ መገሰፅ ሲያውቅበት፣ በምህረቱ ብዛት እያስነባ፣ በማያልቀው ይቅርታው እያስለቀሰ፣ በማይገደበው ቸርነቱ ልብን እየሰረሰረ ዘልዓለማዊ ትምህርትን ያስተምራል፤ እንከን አልባውን ምክር ይለግሳል፤ በቃሉ ብቻ ሰላምን ያድላል፣ ፍቅርን ይሰጣል፤ ፈውስን ይቸራል። አውቀህ የምትጨርሰው ሳይሆን የሚውቅህ አምላክ አለህ። እውቀቱም ፍፁም ነውና ሳትነግረው የሚያስፈልግህን ያውቀል፤ ለዛም ከሌላው የተለየ መንገድን ሰጠህ፣ በሚመጥንህ ልክ አጠነከረህ፣ አስተማረህ፣ ደገፈህ። ምህረቱን እያሰብክ ቀና በል፤ በይቅርታው ዳግም አንሰራራ፤ በቸርነቱ በሚገባ ተማር። "የማያልቀው በደሌን ፍፃሜ በሌለው ምህረትህ ሸፍንልኝ፤ ዳግም እንዳልበድል ልቤንም መልስልኝ" በለው።
የተባረከ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪


ልክህን አስቀድም!
➡️➡️➡️🗣️🗣️
አንተ ማለት ትክክለኛው ማንነትህ ነህ። ዛሬ ታይቶ የሚጠፋ ማንነት የለህም፤ በየጊዜው የሚቀያየርና ለሰዎች እይታ ብቻ የሚኖር ስብዕና የለህም። የምታደርገውን ሁሉ ሰዎች አይተው እንዲያደንቁህ አትፈልግ፤ በሰው ፊት ተወዳጅና ጥሩ ስም ያለው ለመምሰል ከአቅምህ በላይ አትኑር። ሁላችንም ደረጃ አለን፤ እያንዳንዳችን የሚወክለን የገቢ ምንጭ፣ ማንነትና ስብዕና አለን። ለእራሳችን ከመገዛታችን፣ እራሳችንን ከማስደሰታችን፣ በእራሳችን ከመኖራችን በፊት ግን ለታይታና እይታ ውስጥ ለመግባት የምናወጣው ወጪ፣ የምናባክነው ጊዜና ንብረት ሁሉ ዋጋችንን የሚያወርድ እንጂ የሚያሳድግ አይደለም። ሳይኖርህ እንዳለህ ስለታሰብክ፣ ከደረጃህ በላይ ስለተለካህ፣ በማይወክልህ ማንነት ስለታወቅክ ጊዜያዊና የውሸት ኩራት (pride) ሊሰማህ ይችላል፣ ነገር ግን በስተመጨረሻ እራስህን ስታታልል እንደነበር ትገነዘባለህ። መኖራችን ለሰዎች፣ ለስም፣ ለይውንታ፣ ለመወደድና ለክብር አይደለም። መኖራችን ከእራሳችን በላይ ሰዎችን በትክክለኛው መንገድ ለመርዳትና ለማገዝ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ልክህን አስቀድም! እንደ አቅምህ፣ በደረጃህ ተንቀሳቀስ። ሃብታም መስለህ መታየትህ ያለህንም ከማሳጣቱ ውጪ ምንም የሚያተርፍልህ ነገር የለም፤ የቤትህን ክፍተት ሳትሞላ በሔድክበት ሁሉ ካላጋበዝኩ ማለትህ ክፍተትህን አይሞላም፤ ባልሆንከው ሰውነት ለመታወቅ መጣርህ ትክክለኛውን አንተነትህን አይቀይርም። እውነት እውነት ነው፤ ምንም ብትደብቀው፣ ብታስመስልበት፣ በውሸት ብትሸፍነው በጊዜው መታወቁና መገለፁ አይቀርም። ያንቺ ባልሆነው ጌጥ ብታጌጪ አንድም ድጋሜ በእራሱ ጌጥ ለመታየት ትቸገሪያለሽ፣ ሌላም ያለጌጥ ያለውን ማንነት ለማሳወቅ አጣብቂኝ ውስጥ ትገቢያለሽ። ማንም የሚችለውን ያውቃል፤ ወጪውን ገቢውን ጠንቅቆ ይረዳል፤ መጠኑ ለእራሱ ግልፅ ነው።

አዎ! ለጊዜያዊ ከንቱ አድናቆትና ውዳሴ ብለህ እወነተኛ ማንነትህን (identity) አትጣ፤ ከምትችለው በላይ ለመኖር አትሞክር፤ አቅምህን ተረዳው፤ ችሎታህን በሚገባ እወቅ። ማስመሰል ከከፋው ውድቀት በቀር የሚያመጣው ነገር የለም። ሙሉና የተረጋጋ ህይወት የሚገኘው ሰዎች ፊት መስሎ ለመታየት በሚደረገው ጥረት ሳይሆን፣ የእራስን መልክና ገፅ፣ አቅምና ደረጃ በመቀበል በእርሱ ልክ በሚገባ በመኖር ነው። ከሌለህ የለህም፤ እንዳለህ ለማስመሰል የምታስመስልበት ምክንያት የለም። ድህነትህን አይቶ የሚርቅህ ካለ ቢመጣም አንተን ብሎ ሳይሆን ንብረትህን ብሎ እንደሆነ ተረዳ። በየጊዜው እራስህን ከማሻሻል በላይ ለታይታ በመኖርና በማስመሰል እራስህን አታድክም። መኩራት ካለብህ ባለህና እጅህ ላይ ባለው ነገር ኩራ፤ መደሰት ካለብህ ከውጭ በሚመጣ አድናቆትና ውዳሴ ሳይሆን ከገዛ ማንነትህ ከውስጥህ በሚመነጨው ጥልቅ ስሜት ተደሰት።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨⭐️
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪




ከአሉታዊነት ተጠበቅ!
➡️➡️➡️➡️🗣️🗣️
ጥቃቅን ችግሮች አድገው የጭንቀት መንስዔ ይሆናሉ፣ ሰላምን ያሳጣሉ፣ ህመምን ያስከትላሉ። ከስር መሰረታቸው መቀረፍና መወገድ ሲኖርባቸው በቸልተኝነት በመተዋቸው መዘዛቸው ብዙ ሆኖ ይገኛል። አሉታዊ የተባሉት ሃሳቦችም ለእነዚህ ችግሮች ዋንኞቹ መንስኤዎች ናቸው። በትንሹም በትልቁም ሆድ የሚብስህ፣ ለማማረር የቀረብክ፣ ለአሉታዊነት የፈጠንክ፣ ምስጋናን የዘነጋህ ከሆንክ እምቅ አቅምህ እያነሰ፣ ማንነትህ እየወረደ፣ መልካም ስብዕናህ እየተመረዘ፣ በፍቃድህ ነፃነትህን እያጣህ፣ ተናዳጅና ወቃሽ ሆነህ ትቀራለህ። አስተዋይ ልቦና የሚያስብ፣ የሚያመዛዝን አዕምሮ አለህ፣ እርሱም ከአሉታዊነት የፀዱ አዎንታዊነት ላይ የተመረኮዙ ሃሳቦችን ታስተጋባ ዘንድ ይረዳሃል። በአሉታዊነት አለም ድንቅ ተዓምራት አይኖሩም፤ አስደማሚ ክስተቶች አይታሰቡም፤ የተሻሉ አማራጮች መኖራቸውም አይታወሰም። በምሬት ተጀምረው በምሬት የሚያልቁ ቀናቶች ብቻ ይደጋገማሉ፤ የትኛውም ስራ ችግርና ክፍተቱ ብቻ ጎልቶ ይወጣል።

አዎ! ጀግናዬ..! ከአሉታዊነት ተጠበቅ! አሳሪ ሃሳቦችህን ፍታቸው፣ አሰናካይ እይታዎችህን ተፋታ። በግዴታ ሳይሆን ፈልገህና መርጠህ አሉታዊ ሰዎችን ከህይወትህ አስወጣ፤ ራቃቸው፤ ከእነርሱ ጋር ከመመሳሰልህ በፊት ተነጥለሃቸው ሂድ። እነርሱም እንዳንተው ሃሳብ አላቸው፣ ፅኑ አቋም ይኖራቸዋል፤ ይቻላል ስትላቸው በአንቻልም ይመልሱልሃል፤ ልታስረዳቸው ብትሞክር የማይቻልበትን መንገድ በሚገባ ያብራሩልሃል፤ ባለህ ብትኮራም እነርሱ የተሻለ ኖሯቸው ሲያማሩ ትመለከታለህ፤ ችግር ከአፋቸው አይጠፋም፤ ዘወትር ሌላ አካል ለመውቀስ ቆርጠው ተነስተዋል፤ ሃላፊነት መውሰድ የሚባል ነገር አይወዱም፤ የችግሩ ግዝፈት እንጂ መፍትሔው አይታያቸውም። አሉታዊነት ጨለማ ሳይኖር ድቅድቁን ጨለማ፣ ችግር ሳይኖር ግዙፉን ችግር፣ ምንም ጉድለት ሳይኖር የበዛውን እጥረት የመፍጠር አቅም አለው።

አዎ! ሃሳብ ይታሰራል፤ አቅም ይገደባል፤ በምን? በአሉታዊነት፣ በወረደና በዘቀጠ አመለካከት። ለውጥን የሚዘክሩ ሃሳቦች፣ የተሻሉ አማራጮች የማይማርከውና የማያስደስተው ሰው በፍፁም የእድገት ሃሳብህ ደጋፊ ሊሆን አይችልም። ለአመታት ስታቅደው የኖረከው ግዙፍ ተግባር በአንድ አሉታዊ ሃሳብ ብቻ ዋጋ ሲያጣ፣ አፈር ሲሆን፣ ወደ ምንም ሲቀየር ልትመለከት ትችላለህ። ማሰብ የሚከብደው፣ ማቀድ የሚሳነው፣ መመኘት የማይችል ሰው የለም። ነገር ግን ከብዙ አቅጣጫ የሚመጡ አሉታዊና የወረዱ ሃሳቦችን እንዴት መጋፈጥና ማለፍ እንዳለበት የሚያውቀው እጅጉን ጥቂት ነው። ማንም ሰው ያንተን ህልም አይቻልም ቢልህ፣ የማይችለው እርሱ እንጂ አንተ አይደለህም፤ የሚያወራው ከእራሱ እይታ (perspective) እንጂ ካንተ አይደለም፤ ሃሳቡ የእርሱ እንጂ ያንተ አይደለም። በእይታዎችህ ከተሻልክ፣ በሃሳብህ ከበለጥክ፣ በውሳኔዎችህ ካሸነፍክ፣ በእራስህ ከተማመንክ ማንም አያስቆምህም። የምሬት መዓት ሲደረድሩለህ በምስጋና ታከሽፈዋለህ፤ መሰናክሉን ሲዘረዝሩልህ ድልድዩን ትዘረዝርላቸዋለህ፤ ፍረሃታቸውን ሲያስረዱህ ድፍረትህን ታስረዳቸዋለህ። አሉታዊነትን በአዎንታዊነት፤ ምሬትን በምስጋና፣ ቸግርን በመፍትሔ፣ ፍረሃትን በድፍረት ተጋፍጠህ አሸንፋቸው፤ በይቻላል መንፈስም ችለህ ተገኝ።
ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪


ይቅርታ መጠየቅ አቁሚ!
➡️➡️➡️➡️➡️➡️🗣️
ስለ ማንነትሽ ይቅርታ መጠየቅ አቁሚ፤ ስለ አስተሳሰብሽ፣ ስለ እይታዎችሽ፣ ስለ አቋምሽ አንገት መድፋት አቂሚ፤ እራስሽን ስለመሆንሽ፣ የተለየ ምርጫ ስለ መምረጥሽ፣ በተለየ አኳሃን ስለ መራመድሽ፣ ስለ ተለየው የህይወት ትርጉምሽ፣ የህይወት አረዳድሽ ይቅርታ መጠየቅ አቁሚ። ማንም በማንነትሽ፣ በአስተሳሰብሽ፣ በምርጫዎችሽ፣ በእይያዎችሽ የመውቀስ መብት የለውም። ከፍርድ ለማምለጥ፣ ከጥላቻ ለመራቅ፣ ከመኮነን ለመሸሽ ያላመንሽበትን፣ ያልተመቸሽን፣ ያልወደድሽውን ተግባር የመፈፀም ግዴታ የለብሽም። ይቅርታ የምትጠይቂው ለስህተትሽ እንጂ ለማንነትሽ አይደለም፤ ለጥፋትሽ እንጂ ለአንቺነትሽ አይደለም። አምነሽ የተቀበልሽው የገዛ ማንነትሽ የሃፍረት ምልክት፣ ለአንገት መድፋትሽ መንስዔ ሳይሆን የኩራትሽና አንገትሽን ቀና የማድረግሽ ምክንያት ነው። የማንም ያልሆነ፣ የእራስሽ ብቻ የሆነ፣ አንቺነትሽን የሚገልጥ፣ ለተመካችሽና ለአስተዋይሽ መለየ የሆነ የሰውነት አቋም አንዲሁም የፀና የአመለካከትና የእሳቤ አቋም አለሽ። ይህ አቋም የሚያኮራ እንጂ የሚሸማቅቅ አይደለም፤ የሚያስደስት እንጂ የሚያሳዝን አይደለም፤ ቀና የሚያደርግ እንጂ አንገት የሚያስደፋ አይደለም።

አዎ! ጀግኒት..! ይቅርታ መጠየቅ አቁሚ! ስለሆንሽው፣ ስላመንሸበት፣ ስላስደሰተሽ፣ ስለተቀበልሽው ማንነት ይቅርታ መጠየቅ አቁሚ። ሰዎች እንዲቀበሉሽ፣ ሰዎች እንዲወዱሽ፣ እንዲከተሉሽ፤፣ እንዲያደንቁሽ ያልሆንሽውን ከመሆን፣ ያላመንሽበትን ከማድረግ፣ የማይመለከትሽ ቦታ ከመገኘት ተቆጠቢ። ላንቺ ትክክል የሆነ፣ አንቺን ያሳመነ፣ አንቺን የሚገልፅ ተግባር ለሌሎች ስህተትና አሳማኝ ስላልሆነ ብቻ ይቅርታ የመጠየቅ ግዴታ የለብሽም። አቋምሽን የማንፀባረቅ፣ እምነትሽን የመግለፅ፣ ማንነትሽን የማሳየት፣ እራስሽን ሆነሽ የመታየት፣ በሚጠቅምሽ መንገድ የመጓዝ ነፃነት አለሽ። አቋም ስታጪ ብቻ በጥፋተኝነት አጥር ትታጠሪያለሽ፣ በይሉኝታ ትከበቢያለሽ፣ ለተግባርሽ ጥብቅና መቆም ያቅትሻል፤ ሁን ብለሽ ለፈፀምሽውም ጭምር ይቅርታ መጠየቅ ይዳዳሻል። አቋም አልባ ሰው ሲያወላውል፣ ተቀባይነትን ለማግኘት ሲጥር፣ አጉል ትሁት ለመሆን ሲጣጣር፣ ለመወደድ ሲለፋ ጀንበር ትጠልቅበታለች፤ ቀኑም ይጨልምበታል።

አዎ! ጀግናዬ..! ክብርን በፀነው አቋምህ እንጂ በበዛው ይቅርታና ማጎብደድህ አታገኘውም። አንተ አንተ የሚያደርግህ የተለየ አቋም፣ የተለየ አመለካከት፣ የተለየ እይታ፣ ሃሳብና የገዘፈ ህልም መኖርህ ነው። ለአንተነትህ መገለጫና ለማንነትህ መለያ ደግሞ ይቅርታ የመጠየቅም ሆነ የመሸማቀቅ ግዴታ የለብህም። ማንኛውም ሰው እርሱን እርሱ ያደረገው፣ ከሌሎች የነጠለው፣ ለይቶ የሚያሳውቀው የእራሱ ባህሪ፣ አቅም፣ መልክ ወይም ሃሳብ ይኖረዋል። ፈልጎ እንኳን ባያደርጋቸው መታወቂያው ለሆኑ መገለጫዎቹ ይቅርታ የመጠየቅ ግዴታ የለበትም። ትልቅ ህልም ስላለምክ፣ አስደንጋጭ ሃሳብ ስላመነጨህ፣ አይቻልም የተባለውን ለመቻል ስለተነሳህ አትሸማቀቅ፣ አትሳቀቅ፣ ለይቅርታ አትሽቀዳደም። ይቅርታ የሚያስጠይቁና የማያስጠይቁ ነገሮችን ለይተህ እወቅ። ለበደልህ፣ ለጥፋትህ፣ ለጫናህ ይቅርታ መጠየቅ ሊኖርብህ ይችላል። እራስህን ለመሆንህ፣ ፍላጎትህን ለመግለፅህ፣ ስሜትህን ለማስተጋባትህ፣ እውነተኛውን አረዳድህን ለማንፀባረቅህ ግን ይቅርታ የምትጠይቅበት ምክንያት አይኖርም። እራስህን ሆነህ ኑር፤ መገለጫዎችህን በነፃነት ከውን፤ ማንነትህን ግለፅ፤ አምነህ ስለሆነከው ሁሉ ይቅርታ መጠየቅ አቁም።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨⭐️
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪


📣💥 የስልጠናችን ምዝገባ ሊጠናቀቅ 5 ቀን ብቻ ቀረው!

❗️ፈጥነው ይመዝገቡ!

የተግባር ሰው መሆን!
BEING PRACTICAL


✍️ ለመመዝገብ በዚህ አድራሻ መልዕክት ያስቀምጡ
@epha_aschalew or
0960411282

ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

Показано 20 последних публикаций.