💗ፍቅር አለ!💗
➡️➡️➡️🗣️🗣️
ትዋደዳላችሁ፣ ትፋቀራላችሁ፣ ትተሳሰባላችሁ፣ አንዳችሁ ያለአንዳችሁ የምትኖሩ አይመስላችሁም፣ ግንኙነታችሁ የጠበቀ፣ ቅርበታችሁ ከፍ ያለ ነው። ነገር ግን በመሃከላችሁ መከባበርና መተማመን የለም፣ ነገር ግን አንዳችሁም ለእራሳችሁ መብት ገደብ አታስቀምጡም፣ አንዳችሁም ለአጋራችሁ ነፃነት ለመስጠት አትሞክሩም፣ ነገሮችን ቀለል አድርጎ ማለፍ አትፈልጉም፣ ታካብዳላችሁ፣ እናንተ ያላችሁት ብቻ እንዲሆን ትፈልጋላችሁ፣ ለግንኙነታችሁ ግብ አላስቀመጣችሁም። ከእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ግማሾቹም ቢሆኑ የእናንተን ግንኙነት የሚመለከቱ ከሆነ የሚጎዳችሁ ግንኙነት (toxic relationship) ውስጥ እንደሆናችሁ አስተውሉ። ፍቅራችሁ ብቻ ለዘላቂውና ለተረጋጋው ግንኙነታችሁ ዋስትና ሊሆናችሁ አይችልም።
አዎ! ጀግናዬ..! ፍቅር አለ፣ ነገር ግን ብቻውን በቂ አይደለም። መዋደድ ይኖራል፣ ነገር ግን ጠንካራ መሰረት ላይ ካልተገነባ የትም አያደርስም። ያላችሁበት ግንኙነት ጤነኛ እንዳልሆነ ከተረዳችሁ በጊዜ ለማስተካከል ሞክሩ። ማንም ለእናንተ ግንኙነት አስደሳችነትና ስኬታማነት ከእናንተ በላይ ሊሰራ እንደማይችል እወቁ። ምናልባት አንዳንድ ግንኙነቶች የተወሳሰቡ ይሆናሉ፣ አንዳንዶችም ምንም የወደፊት አላማ የሌላቸው ይሆናሉ። ነገር ግን ግንኙነት እስከሆኑና በፍቅር ስም እስከተመሰረቱ ድረስ ስሜትን መጉዳታቸው፣ የህይወት ጉዞን ማዛባታቸውና በትርጉም አልባ እስራት ለከፋው ስቃይ መዳረጋቸው አይቀርም። ዋጋ የማትከፍሉለት ግንኙነት የትም እንደማይደርስ እናንተም ታውቁታላችሁ፤ በምትኩ ትዕግስትን የምትኖሩበት፣ ለንግግር ቅድሚያ የምትሰጡበት፣ ግልፅነትን የምትመርጡበት፣ ክብርና እምነት ላይ የምትመሰርቱት ፍቅር ደግሞ ውጤታማ እንደሚሆን ታውቃላችሁ።
አዎ! ላቁመው ብትል የሚይዝህ ነገር አለ፣ ለመለያየት ከወሰንሽ ቦሃላ በውሳኔሽ መፅናት ይከብድሻል። አንዳንዴ እንደማይዘልቅ ታውቃላችሁ ነገር ግን ሁለታችሁም ለጊዜያዊ ስሜታችሁ በመገዛት ተመሳሳይ የሚጎዳችሁ ጉንኙነት ውስጥ ለረጅም ጊዜ ትቆያላችሁ። የማያተርፍላችሁ ግንኙነት ምናችሁ ነው? ሰላም የማይሰጣችሁ፣ ውስጣችሁን የማያረጋጋ፣ ባላችሁ ጥራት ላይ ጥራትን፣ ባላችሁ እውቀት ላይ እውቀትን የማያክልላችሁ የፍቅር ግንኙነት ምናችሁ ነው? ጥቅሙስ ምንድነው? መቅረፍ ያለባችሁን ጉዳይ በጊዜ ቅረፉ መለያየትን እየፈራችሁ የስቃይ ዘመናችሀን አታርዝሙ፣ በፍቃዳችሁም በፍቅር ስም እራሳችሁን አትቅጡ። በቻላችሁት መጠን ለፍቅራችሁ ታመኑ፣ የሚገባውን ክብርም ከልባችሁ ስጡት።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨⭐️
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪