Репост из: Thoughts
ቀና ብላ ባየች?!
"ምነው ምን ያህል ሰው እንደሚወዳት አንዴ እንኳን ቀና ባየች?!" አለች ታናሽ እህቷ እንባዋን እያበሰች። "እንኳንም ቀና ብላ ያላየችን" አለ የሰባት አመት ልጇ መኖሩን ራሱ ሳይስተውሉት ቆይተው አሁን የተናገረውን ሲሰሙ ደንግጠው መልስም የሰጠውም አለነበረም
"ለምን መሰለሽ እታቲ" አለ ለአክስቱ ሌሎቹ እየሰሙ ስላልመሰለው "ምክንያቱም አባቷ እንዴት እንዳለቀሰ ብታይ እሷ የበለጠ ታዝን ነበረ ሌላውን ሰው ተይው እትዬ ብርሀኔ እንኳን እንዴት እንዳለቀሱ ብታይ እንደዛ ሲጣሉ እንዳልኖሩ ስትሞት ጊዜ ከልባቸው እንደማይጠሏት አለቃቀሳቸው ያስታውቅ ነበረ ታዲያ ይሄንን ሁሉ ስታይ መሞቷ አይቆጫትም ብለሽ ነው?!"
" ሁሌ ለቅሶ ላይ የሚባል ነገር እንደሆነ እማ ነግራኛለች 'ምነው አንዴ እንኳን ቀና ብለው ለቅሶ እንዴቶ እንዳማረ ቀብር እንዴቶ እንደደመቀ ባየች' ይባላል ለምን? 'ለምን በህይወት እያለሁ ይሄ ሁሉ ሰው አልወደደኝም?! ለምን ስቸገር ሰው አጠገቤ አልነበረም' ብሎ ሟች እንዲቆጭ ነው?! ወይስ ብዙ ሰው አዝኗል ብዙ ወዳጅ ነበረኝ ብዙ መኖር ነበረብኝ ብሎ እንዲቆጭ ነው?! እ አታቲ?!" አላት እጁን አጣምሮ
"ልክ ነህ እንኳንም አላየችን፥ ሞቷ አንሷት ነው ሀዘን የሚጨመርላት?!" ስትል ለቅሶ ጭራሽ አዲስ ሆነ
✍ናኒ
https://t.me/justhoughtsss