Репост из: Thoughts
✨ተተክተሻል✨
ደውዬ የልጄ ክርስትና እናት እንድትሆን ጠይቄያት 'እሺ' ስትል ፈገግ አልኩ በቀሉን እንዳገኘ ሰው ውስጤ ደስታ ሲናኝ ተሰማኝ። ለእሷ ብዬ ያስቀመጥኩት ትልቅ ቅርበት ለአዲሷ ጓደኛዬ እንደሰጠሁት ባወቀች ብዬ ተመኘሁ
ከዛ ለሰርጓ የተነሳነውን ፎቶ አገላብጬ አየሁት የመጀመሪያ ሚዜዋ እንደመሆኔ አጠገቧ ነኝ ሁሉም ፎቶ ላይ "የኔ ብቻ ሚዜ ነው የምትሆኚው ያውም የመጀመሪያ" እንዳላልሽኝ ድራሽሽ ሲጠፋ አለመፈለጌን(ይጠብቃል) በይፋ ስታሳዪኝ የመጀመሪያ ሚዜ የሆንኩት ከወር በፊት እንደሆነ በምን አባቴ ላሳይሽ?!
ገና highschool እያለን እንዴት አብረን እንደምናረጅ፣ ልጆቻችንን ጓደኛሞች አድርገን ባህላችንን እንደምናስቀጥል አብረን እንዳላወራን፣ የወንድ ምርጫችን አራምባና ቆቦ ስለሆነ መቼም ባሎቻችን እንደማይግባቡ ገና አስበን እንዳላዘንን፣ የሰርግ ቀሚሶቻችንን እስከ ልጆቻችን ምርቃት እንዳላቀድን..
Telegram ላይ ሳምንት አውርተሽው እንደምትተዪው ልጅ የስድስት አመት ጓደኝነት እንደቀልድ ትውት ስታደርጊው ምን እንደተሰማኝ ታውቂያለሽ?
አለመፈለግን በደማቁ አስተናገድኩት ከዛ ብቸኝነትን ለመልመድ መጣጣር ያንን ለሰፈር ሰው የሚበቃ ሳቄን እንዴት መቆጠብ እንዳለብኝ ራሴን ማስተማር ነበረብኝ
አለማውራት እንደማልችል ታውቂያለሽ፤ ሚስጥር መያዝም እንደዛው ግን ደግሞ ከስህተቴ መማር ስለነበረብኝ አፌን መሰብሰብ፥ ራሴን መቆጣት አስተማርሺኝ ሰው መፈለግ፥ emotionally dependent መሆን ነውር አደረግሽብኝ "ኧረ ቆምጠጥ ማለት ልመጂ አታዋርጂኝ" ብሎ አዕምሮዬ ልቤን እንዲያምባርቅባት አደረግሽ
በዚህ ቢበቃሽ መች አነሰ?! በረባ ባረባው ሆድ ሲብሰኝ ያንቺ መሄድ ነው ጭንቅላቴ ላይ የሚጎላው ከዛ እንደልማዴ ራሴን እወቅሳለሁ "ይሄንን ባልላት ኖሮ... ባላናድዳት ኖሮ" ምናምን እያልኩ አመታት ያለፈውን እያስታወስኩ ራሴን እወቅሳለሁ
ከዛ የመጨረሻ ያጎሳቆልሺኝ ሰዎችን መቅረብ እንድፈራ ስታደርጊ ነው በቃ ያኔ መበሳጨት ጀመርኩ "ማን ስለሆነች ነው ቆይ ይሄ ሁሉ ይገባታል?! ወይስ የኔ መሄዷን አምኖ የሚቀበል ጠንካራ አስተሳሰብ ማጣት ነው?!" እያልኩ ራሴን ደጋግሜ መገሰፅ ጀመርኩ
በዚ መሀል አዲሷ ጓደኛዬን አገኘኋት... መጀመሪያ ፈርቼ ነበር እንዳንቺ ድንገት ተንስታ እልም ብትል ለማን እዬዬ ልል ነው ብዬ እሷ ግን እንዳንቺ የተወሳሰበች አልነበረችም የወሰድሽውን እምነቴን መለሰችው ያልፈጠረብኝን ግልፅነት አስለመደቺኝ ፈጣጣ ሆንኩ ድጋሜ ደውዬ መነፋረቅን normal አደረግኩት እድሜ ለሷ my color ተመልሷል
እናላችሁ ስታገኟት
በናታችሁ ንግሯት
ይብላኝ ላንቺ እንጂ
እሷ ተክታሻለች በሏት
✍ናኒ
https://t.me/justhoughtsss